Monday, March 7, 2016

ቻግኒ -ጎጃም የምርጥ ዘር ማዳቃያው ማዕከል በእሳት ወደመ

ከቻግኒ ከተማ በቅርብ እርቀት ላይ የሚገኘው የኢትዩጲያ ምርጥ ዘር ኢ ተርፕራይዝ ማዕከል የበቆሎ ማዳቀያ ማሳ እና የተከመረ የወንዴ በቆሎ ክምር በአካባቢው በተነሳ እሳት ሙሉ በሙሉ ወድሟል ።የእሳት አደጋው የተከሰተው በቻግኒ ዙሪያ ገባው ካሉት ተራሮች የተነሳ እንደሆነ የአይን እማኞች ተናግረዋል።እሳቱን የለኮሰው ማን እንደሆነ እስካሁን አልታወቀም።
የማዕከሉ ሰራተኞች ከቀኑ በ6፡30 ለምሳ ሲወጡ የተከሰተው የእሳት አደጋው በሰርቢስ ወደ ከተማ ሲሄዱ መንገድ ላይ ጢሱን አይተው ቢመለሱ ሙሉ በሙሉ ወድሞ ወደ ቢሮወች እያመራ በደረሱበት ወቅት ቢሮውን ተረባርበው ከእሳቱ አትርፈውታል ። ቻግኒ ከተማ አንድ ወጣት በስልክ እንዳናገርኩት ብናኙ ከተማው ድረስ በነፍስ ሃይል እንደተበተነ ገልፀውልኛል።

No comments:

Post a Comment