
ተቃውሞ ቀዝቅዟል በሚል ኦሕዴዶችን ግምገባ አስገብቶ እየጠበጠበ በማባረር ላይ የሚገኘው ሕወሓት መራሹ ቃገዛዝ በኦሮሚያ ክልል ያለው ተቃውሞ ዳግም ያገረሻልተቃውሞ የሚል ሪፖርት በደህንነት ቡድኑ በኩል ከቀረበ ጀምሮ በኦሮሚያ ክልል ውጥረት መንገሱ ታውቋል:: በሪፖርቱ ይፈነዳባቸውል የተባሉት በሃረርጌ አርሲ እና ወለጋ አከባቢዎች እንዲሁም ከፊል ሸዋ የተለያዩ ወታደራዊ ታጣቂዎች የደህነት ሃይሎች ከመላኩም በላይ የአየር ላይ ክትትል በሄሊኮፕተር መጀመሩም ታውቋል::ድንገት መንገድ ቢዘጋ የጦር ሃይሉን በሂሊኮፕተር ለማራገፍም መታቀዱን የደህነት ምንጮቹ ተናግረዋል::በድሬዳዋ ካምፓስ ቀን ላይ አርግዞ የነበረው ተቃውሞ ማምሻው ፈንድቷል::
በጋምቤላ አከባቢ ዳግም ግጭቶችን ለመቀስቀስ ያቀደው የሕወሓት አመራር በየክልሉ ወንጀል እየፈጸመ የሚገኘው በአከባቢ ተወላጅ በሆኑ አስተዳደሮች እና ካድሬዎች መሆኑ የተደረሰበት ሲሆን ከባላይ ሆነው የሕወሓት አመራሮች ትእዛዝ በመስጠት የአከባቢ ተወላጆች በገዛ ወገኖቻቸው ላይ እርምጃ እንዲወስዱ እና እንዲያስወስዱ በማድረግ ነገን ራሱን ከተጠያቂነት በመሸሽ የሾማቸውን የአከባቢ ተወላጆች ፍርድ ቤት ገትሮ በወንጀለኛነት ለመጠየቅ እንዲያመቸው መሆኑ ታውቋል::
በአማራ ክልል እና በትግራይ እንዲሁ የሕዝብ እንቅስቃሴዎች ይኖራሉ የሚለው ሪፖርቱ ሳይቀጣጠሉ ለማዳፈን እንቅስቃሴ መጀመሩ ታውቋል::የተቃዋሚ ሃይሎች የኢሕኣዴግን የካድሬ መዋቅሮች ተቆጣጥሮታል የሚለው መረጃቸውን በመያዝ የላይኛው አካል ምንም ጥፋት እንደሌለው የሚሸፋፍን ግምገማ ማካሄዳቸው የዚሁ የደህንነት ሪፖርት አንዱ አካል እንደሆነ ታውቋል::ስርኣቱ በውጥረት አጣብቂኝ ውስጥ መሆኑ ስጋት የገባቸው አሜሪካኖቹ የሃገሪቱ ጽጥታ አደጋ ውስጥ ስለሆነ ረሃቡን አሳበው ለቴክሊካል ድጋፍ ሃገር ቤት እንደከተሙ መገናኛ ብዙሃን አረጋግጠዋል:
No comments:
Post a Comment