አዲስ አበባ በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ፊት በኦሮሚያ የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ አስመልክቶ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ የሞከሩ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ታሰሩ። ዛሬ ጠዋት ወደ አራት ሰዓት ገደማ ከአሜሪካ ኤምባሲ ፊት የተገኙት ተማሪዎች ቁጥራቸው ወደ 20 እንደሚጠጋ የዓይን እማኞች ይናገራሉ።
ወትሮውንም በከፍተኛ ጥበቃ ስር ያለው ኤምባሲ ከተማሪዎቹ ሰላማዊ ሰልፍ ሙከራ በኋላ በኢትዮጵያ የፀጥታ ኃይሎች ተጨማሪ ጥበቃ ሲደረግለት ተስተውሏል። በስድስት ፒክ አፕ መኪና በተጫኑ የአዲስ አበባ እና የፌደራል ፖሊስ ኃይሎች አካባቢው ሲጠበቅ እንዳስተዋሉ የዓይን እማኞች ይገልፃሉ።
በአሜሪካ ኤምባሲ ይታይ የነበረው አይነት ያልተለመደ የፖሊስ ክምችት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ስድስት ኪሎ ዋናው በር እና አምስተኛ በር ረፋዱ ላይ እና ከሰዓት ታይቷል።
ከዚህ ሁኔታ ጋር በቀጥታ ይገናኝ አይገናኝ ባይታወቅም ወደ አምስት ሰዓት ግድም በኤምባሲው “እሳት ተነሳ” በሚል ጉዳያቸውን ለማስፈፀም በቦታው የተገኙ ባለጉዳዮች ከየቢሮዎቹ ለግማሽ ሰዓት ያህል እንዲወጡ መደረጋቸውን በቦታው የነበሩ ምንጮች ያስረዳሉ።
No comments:
Post a Comment