የኦሮሞ ሕዝብ ያነሳውን ጥያቄ ተከትሎ በሕወሓት መንግስት የኦሮሞን ህዝብ እንዲያረጋጉ ተልከው በየሚዲያው እየወጡ ሲያስተባብሉ የከረሙት የኦህዴድ ማዕከላዊ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ኦቦ ዳባ ደበሌ ከስልጣናቸው ተነስተው ወደ ኦሮሚያ የትምህርት ቢሮ ተዘዋውረዋል:: በርሳቸው ቦታ ላይም በሕወሓት መንግስት ተላላኪነታቸው “ኦቦ ገብረመድህን” የሚል ስም የተሰጠው አቶ በከር ሻሌ ይህን ቁልፍ ስልጣን መረከቡን ምንጮች ገልጸዋል::
አቶ በከር ሻሌ ከዚህ ቀደም የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ከመሆኑ በፊት በሚኒስትር ዴኤታነት የገቢዎችና ጉምሩክ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሆኖ ለወራት የሰራ ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተርነት ተነስቶ ወደ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ተዛውሮ እንዲሰራ ተደርጎ የነበረው አቶ በከር፣ በጽሕፈት ቤቱ ለተወሰኑ ወራት በሚኒስትር ዴኤታነት ካገለገለ በኋላ የአዳማ ከተማ ከንቲባ ሆኖ መሾሙ ይታወሳል::
ከግንቦት 21 ቀን 2005 ዓ.ም. ጀምሮ ደግሞ በሙስና ወንጀል በሕወሐት ተከሰው የታሰሩትን አቶ መላኩ ፈንታን ተክቶ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዳይሬክተር የተደረገ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በተመሣሣይ ሁኔታ የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት ባላወቀበት ሁኔታ የኦህዴድ ማዕከላዊ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሆኖ በቀጭን ደብዳቤ ተሹሟል::
በቀጣይም ልክ እንደ ዳባ ደበሌ ሁሉ የኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናት ከየስልጣናቸው እየተነሱ ወደ ሌላ ቦታ እንደሚዘዋወሩ ምንጮቻችን ገልጸው ተረኞች ተራቸውን እየጠበቁ ሕወሓት ማድባቱን ተያይዞታል ብለውናል::
No comments:
Post a Comment