Saturday, March 12, 2016

“በኢህአዴግ ልክ የተሰፋ ጥብቆ ዴሞክራሲ አብቅቶለታል፡፡” ዶ/ር መራራ ጉዲና


በኦሮሚያ ክልል የተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ በአራት ወር ውስጥ በመንግስት ታጣቂ ከ270 በላይ ሰው እንደተገደለ ዶ/ር መራራ ጉዲና ገለጹ፡፡ የህውሓት መንግስት ወደህዝብ መውረድ አለበት፡፡ ለሀገሪቱ ችግር ዋነኛ ተጠያቂው ኢህአዴግ ነው፡፡ ከጥብቆ ዲሞክራሲ ወደ እውነተኛ ዴሞክራሲ መሸጋገር ካልተቻለ ሀገሪቷ ወደ ቀውስ እንደምትገባ አስጠነቀቁ፡፡ በሌላ በኩል በቤች ማጂ የሱርማ ብሄረሰብ የታየው እጅና አንገት እንደከብት ማሰር በኢትዮጵያ መንግስት የተፈጸመ ወንጀል እንደሆነ የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሸነር አቶ/ሲሳይ ጋረደው አረጋገጡ፡፡ ድርጊቱን የፈጸሙት ወታደሮች እያጣራን እንገኛለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡ በሱርማ ህዝብ የሚፈጸመው ግፍ ቀደም ሲል ጀምሮ የቆየ እንደሆነ አንድ ተወላጅ ለVOA ተናግረዋል፡፡

No comments:

Post a Comment