Thursday, March 10, 2016

በጎጃም ቡሬ ወረዳ ገዳምና ልጃሞር ቀበሌዎች ውስጥ የህዝብ ቁጣ ገነፈለ፡፡


ከደጀን ቤንሻንጉል ለሚገነባው የመንገድ ስራ ፕሮጀክት የገዳምና ልጃሞር ቀበሌዎች ነዋሪዎች ከስድስት መቶ ሺህ ብር በላይ አዋጥተው የቡሬ ወረዳ አስተዳዳሪ ተብዬው ጌታዬ ሽታዬ በተባለ የህወሓት ብአዴን አገልጋይ ገንዘቡ በመበላቱ ነው ህዝቡ የተቆጣው፡፡
በተጨማሪም በጎጃም ፍኖተ ሰላም ከፍተኛ ውጥረት ነግሷል፡፡ ከተማዋ ከፍተኛ ቁጥር ባለው የፌደራል ፖሊስ ጦር ተወራለች፡፡ ከባድ መትረየስ የተጠመደባቸው ፓትሮሎች በዋናው ጎዳና እየተመላለሱ ሽብር በመፍጠር የህዝቡን ስነ-ልቦና ለማወክ በመጣር ላይ እንደሚገኙ ከዛው ከፍኖተ ሰላም ነዋሪዎች ለአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ የተላከው መረጃ ይገልፃል፡፡

No comments:

Post a Comment