

በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለከተማ ወረዳ 10 በተለምዶው ሰሚት በሚባለው አካባቢ በደረሰ አሰቃቂ የመኪና አደጋ የ6 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተሰማ::
የአካባቢው ነዋሪዎች በፎቶ ግራፍ አስደግፈው በላኩት መረጃ እንደገለጹት አደጋው የደረሰው ሰሚት የለስላሳ መጠጦች ፋብሪካ አካባቢ በሚገኝ መስቀለኛ መንገድ ላይ ሲኖ ትራክ መንገድ ስቶ ከመንገድ ጋር ሲጋጭ ግንብ በመፍረሱ በአቅራቢያው ሰው አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ ባጃጅ መኪና ላይ በመውደቁ አሽከርካሪውን ጨምሮ ተሳፋሪዎች ሕይወታቸው አልፏል:: ከሟቾች መካከል ሁለቱ ሴቶች መሆናቸውም ታውቋል::: ፖሊስ የአደጋውን ሁኔታ እያጣራ ይገኛል:: በዚህ አደጋም በርካታ ሰዎች መቁሰላቸው ተሰምቷል::
No comments:
Post a Comment