Friday, March 4, 2016

በሀገሪቱ የተጀመረው የስራ ማቆም አድማ የህወሓት መንግስት ተረብሿል፡


በመርካቶ የሚገኙ አስመጪና ሊኪ ነጋዴዎች የምንጠየቀው ግብር ካቅማችን በላይ ሆኖብናል በማለት ሁሉም በሕብረት ወደ ሀገር ውስጥ
የሚያስገቡትን ዕቃ የማቆም አድማ ሊመቱ መሆኑ እየተነገረ ይገኛል፡፡ የአሽከርካሪዎች የስራ ማቆም አድማ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ በሰሜን ወሎ ከትላንት
በስቲያ የጀመረው የአሽከርካሪዎች የስራ ማቆም አድማ በደቡብ ወሎ በተለይ በኮምቦልቻ ተጠናክሮ እየተካሄደ ሲሆን ደሴ: ከሚሴ: ባቲ: ሸዋ ሮቢት የሚጓዙ
መደበኛ የትራንስፖርት አውቶቡሶች: ሚኒባሶች: አባዱላ የተሰኙ መኪናዎች አድማውን በመምታት ላይ ናቸው። ደብረ ብርሃን ሊቀላቀሉ መሆኑ እየተነገረ ነው፡፡ የተጀመረው
እንቅስቃሴ ሁሉንም ክፍል እያነቃቃው መሆኑ የህወሓት መንግስትን አስጨንቆታል፡
በዛሬው ዕለት በነቃምት ምስራቅ ወለጋ የሾፌሮች ስራ ማቆም አድማ እንደቀጠለ ነው።

No comments:

Post a Comment