Thursday, March 17, 2016

አልሸባብ የፑትላንድ ወደብን መልሶ ተቆጣጠረ::


ሶማሊያ ዉስጥ የሚንቀሳቀሰዉ ታጣቂ ቡድን የአልሸባብ ተዋጊዎች በከፊል ራስ ገዝዋ ፑንትላንድ የሚገኝ ትንሽ ወደብ መያዛቸዉን ሮይተርስ ዘገበ። ባሳለፍነው የፈረንጆች አመት የአፍሪቃ ኅብረት የሶማሊያ ሰላም አስከባሪ « AMISOM» እና የሶማሊያ ብሔራዊ ጦር አል ሸባብን በስፋት ከተቆጣጠረዉ ደቡባዊ የሶማሊያ ግዛት ማስለቀቃቸዉ ይታወሳል።
እንደ ባለስልጣናት ገለፃ በዚያን ጊዜ የአሸባብ ተዋጊዎች የአፍሪቃ ኅብረት የሰላም አስከባሪዉ የጦር ኃይል «AMISOM» ከሚቆጣጠረዉ ክልል ዉጭ ማለት ወደ ሰሜናዊ ፑንትላንድ ግዛት ሄደዋል። በዚሁ ሳምንት ዉስጥ አሸባብ ትናንሽ ከተሞችን መልሶ ተቆጣጥሮአል፤ በደቡባዊዉ ክፍልም ጥቃት አድርሶ ሰዎች ተገድለዋል።
የፑንትላንድ ጉዱግ አካባቢ ገዢ ሀሰን ሞሐመድ ለሮይተርስ እንደገለፁት የአሸባብ ተዋጊዎች በበርካታ ጀልባዎች ላይ ሆነዉ ጋራድ ከተማን ተቆጣጥረዋል። ቡድኑ ጥቃቱን የሰነዘረዉ ትናንት መሆኑንም አመልክተዋል። የተጠቀሰዉን ወደብ ስለመያዝ አለመያዙ እስካሁን ከኧሸባብ የተገለፀ ነገር ግን የለም። የፑንትላንድ የባህር ዳርቻ ግጭት ለሚበዛበትና አልቃይዳ ለሚንቀሳቀስበት ለየመን በቅርበት ላይ ይገኛል።
 

No comments:

Post a Comment