Sunday, March 27, 2016

የታክሲዎች የስራ ማቆም አድማ በአዲስ አበባ ሊደረግ ነው !


ከወር በፊት አዲሱን የአሽከርካሪዎች ህግ በመቃወም የታክሲ ሹፌሮች ለተከታታይ ሁለት የሥራ ቀናት አገልግሎት በማቆም አድማ መምታታቸውና መንግስትም ከአድማው 12 ሰዓታት ቀደም ብሎ አዲሱን የአሽከርካሪዎች ደንብ ለሶስት ወራት በስራ ላይ ከማዋል እንደሚቆጠብ መግለጹ አይዘነጋም፡፡
በመንገድና ትራንስፖርት ባለሥልጣን መሥሪያ ቤት በኩል ለሶስት ወራት ስራ ላይ እንደማይውልና ውይይት እንደሚደረግበት የተነገረለት ደንብ አሁን ያለምንም ውይይትና ማሻሻያ በተጠናከረ ሁኔታ በሥራ ላይ እየዋለ በመሆኑ አሽከርካሪዎቹ ያቋረጡትን የስራ ማቆም አድማ ለመቀጠል መወሰናቸውን መረጃዎች ጠቁመዋል።
የተወሰኑ ሹፌሮች በአዲሱ ደንብ መሰረት መንጃ ፍቃዳቸውን ተቀምተው ሥራቸውን ለማቆም መገደዳቸውን የተመለከቱ አጋሮቻው ለመጋቢት 19 እና 20 (ነገና ከነገበስቲያ) በድጋሚ የሥራ ማቆም አድማ እንደሚያደርጉ ውስጥ ለውስጥ ተነጋግረው መወሰናቸው ታውቋል።

No comments:

Post a Comment