Friday, March 4, 2016

የወያኔ መከላከያ ሰራዊት ፓትሮል ና አንድ የህዝብ ማመላለሻ ሚኒባስ ተጋጭተው አራት ወታደሮች ሞቱ


ነገሩ እንዲህ ለአስቸኮይ ጉዳይ ታዘው በአዘዞ ከተማ የሚገኘው 24 ኛ ክፍለ ጦር ካምፕ ተነስቶ ወደ መተማ ከተማ ለመድረስ ከስምንት በላይ የመከላከያ ሰራዊት ወታደሮችን ጭኖ ከተገቢው በላይ በፍጥነት ይጎዝ የነበር አንድ የመከላከያ ፓትሮል መኪና ከአንድ የህዝብ ማመላለሻ ሚኒባስ ሙሉ ተሳፋሪ ጭኖ ከጭልጋ ከተማ ተነስቶ ወደ ጎንደር ከተማ ይጎዝ በነበረበት ወቅት አዘዞ ከተማ መግቢያው ላይ የተጋጩ ሲሆን አራት የመከላከያ ወታደሮች ሲሞቱ ከሚኒባሱ ደግሞ አንድ ሰው የሞተ ሲሆን ወደ አምስት ሰዎች ቀላል እና ከባድ ቁስለኞች በጎንደር ሆስፒታል የህክምና እረዳታ እየተደረገላቸው ይገኛሉ ።ፓትሮሉ ሚኒባሱን ገጭቶ የወደቀ ሲሆን ሚኒባሱ ግን ከጋቢናው አንስቶ ግማሽ ጎኑ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል።
በዚህ አጋጣሚ ገበሬዎች የወታደሮችን መሳሪያ በመያዝ ከአካባቢው ተሰውረዋል ።

No comments:

Post a Comment