Thursday, March 31, 2016

የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ ልዑካን ቡድን የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት እና የመድረክ ሊቀመንበር ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ ጋር በወቅታዊ የኢትዮጵያ ጉዳዮች ላይ ውይይት አደረገ።

ማምሻውን
በአዲስ አበባ በተካሄደው ስብሰባ ላይ ኢ/ር ይልቃል ጌትነት
በሀገሪቷ ውስጥ በየቀኑ ሰዎች በመንግስት ወታደሮች እየተገደሉ
ባሉበት በአሁኑ ወቅት ስለመድብለ ፓርቲ እና ስለነፃ ፕሬስ
ማውራት ቅንጦት ነው በማለት ሀገርቱ ያለችበትን ወቅታዊ ሁኔታ
ለልዑካኑ አብራሪተዋል።ልዑካኑ
በእስካሁኑ ቆይታቸው ከውጭ ጉዳይ ሚንስትር፣ከፈደራል ጉዳይ
ሚንስትር እና ከኢፌድሪ ፓርላማ አፈጉባኤ ጋር ውይይት
አድርገዋል።
ልዑካኑ በጉብኝቱ ማጠናቀቅያ ላይ ለሚዲያዎች መግለጫ
እንደሚሰጡ ይጠበቃል።
መቅዲ የአዴሃን ፍሬ's photo.

Wednesday, March 30, 2016

በዉስጥ አርበኞች የተቀናጀ ስኬታማ የትግል ስልት በተለያዩ ክልሎች በጨካኙ የአጋዚ ጦር ላይ እርምጃ ተወሰደ!


በአማራዉ ክልል ላይ በቋራ ወረዳ በንፋስ ገበያ መጋቢት  ከሱዳን መንግስት ጦር ጋር በመተባበር 24 የኢትዮጵያ ገበሬዎችን የእርሻ ቦታ በማቃጥል 13 የአማራ ተወላጅ ወጣቶችን በመግደል እና 34 ሰላማዊ ነሪዎችን በማገት ግፍ የሰራዉ የአጋዚ ሰራዊት ላይ የዉስጥ አርበኞች ከህዝብ ጋር በመተባበር እርምጃ የወሰዱበት ሲሆን 3 ቀንደኛ የህዝብ ጠላቶች ተወግደዋል።
በተያያዘ መረጃ አድማሱን እያሰፋ የሚገኘዉ የዉስጥ አርበኛ ሐይል ከኦሮሚያ ጀግና አርበኞች ጋር በመቀናጀት በምእራብ ወለጋ ጉደር ከተማ ስምሪት ጥቢያ ካምፕ አድፍጦ በሚገኘዉ የወያኔ አጋዚ ጦር ላይ በተመሳሳይ ጥቃት በመፈጽም ከአርባ በላይ ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ግምቱ ባልታወቀ የወያኔ ንብረት ላይ ጉዳት አድርሰዋል።
በአርሲ ክልል የዉስጥ አርበኞች አካል የሆነ አንድ ጀግና የኦሮሚያ ፖሊስ ክልል አባል 5 የአጋዚ ጦር ወራሪዎች ላይ እርምጃ ከወሰደ በኃላ እራሱን አጥፍቷል።
በትግራይ ክልል በሰሞኑ በተደረገ የመከላከያ ሰራዊት አመራሮች ድብቅ ስብሰባ ላይ
” የትግራይ ህዝብ የወደፊት እጣ ፈንታ ምንድን ነዉ? የወደፊቷ ትግራይ ማለት በፈንጅ የተከበበች ደሴት ናት! የህዝቡን ህልዉና ዛሬ በስልጥን ላይ ያለዉ የትግራይ አማጺ ቡድን ድባቅ መትቶታል ” በማለት የተናገረ አንድ በ10 አለቃ ማእረግ የሚገኝ የትግራይ ተወላጅ ከስብሰባዉ ቦኃላ እራሱን በመግደል ተቃዉሞዉን በአሳዛኝ መልኩ ገልጿል።
በኦጋዴን እና በምስራቅ ኢትዮጵያ ተሰማርቶ የሚገኝዉ የመከላከያ ሰራዊት በአዛዦቹ በመማረሩ ምክንያት እርምጃ እየወሰደባቸዉ፣መልቀቂያ እየጠየቀ እንዲሁም እየተሰወረ በመመናመን ላይ መሆኑን ከዉስጥ የወጡ መረጃዎች እና በሰት ወደተለያየ አፍሪካ ሐገር የተጠለሉ ወገኖቻችን አመላክተዋል።
እራሱን ብሄራዊ መረጃ እያለ የሚጠራዉ አካል በመረጃ ፍሰት ወይም ማፈትለክ ምክንያት በአባላቶቹ ላይ እርምጃ እየተወሰደበት ሲሆን ባጠቃላይ በአጭር ግዜ ዉስጥ ከመረጃ ሰራተኞች ዉስጥ 21 ባለመተማመን ምክንያት ለእስር ተዳርገዉ 18 ያህሉ ከሐገር ለመኮብለል ሲገደዱ ፣ 8 የሚጠጉት ደግሞ በህዝብና በተለያዩ አካላት እርምጃ ተወስዶባቸዋል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ! !
( ጉድሽ ወያኔ )

(አፍሬም ነኝ ከአርበኞች መንደር ) ሚስጢሩ የገባኝ አስመራ ገብቼ ከእንቅልፌ ስነቃና የቀረብኝን ሳዉቀዉ ነዉ።


አባባ . . . አባባ . . . . ስማ አባባ ረሳህ እንዴ አለኝ ያ ባለፈዉ ነኃሴ ወር ስንለያይ ያስለቀሰኝ ልጄ። ምኑን አልኩት። ቅድም ምሳ ላይ የነገርኩህን . . . እንዴ! እሱንማ እንዴት እረሳለሁ። Please don’t አባባ! …… I will not! ሲረጋጋና ደስ ሲለዉ ታየኝና ልቤን ደስ አለው። ልጄ ኮሌጅ የሚገባበት ቀን እኔ ደግሞ ከትግል ጓደኞቼ ጋር የምንገናኝበት ቀን ናፍቆናል። አባባ Good luck አለኝ። እኔም ይቅናህ አልኩት። Good luck እና ይቅናህ የተባባልነው እኔ እሱ የሚመኘዉ ኮሌጅ እንዲገባ እሱ ደግሞ እኔ በድል ኢትዮጵያ እንድገባ ነበር። ሁለታችንም ይቅናን . . . አሜን!!!
አዉሮፕላን ዉስጥ ገብቼ ከተረጋጋሁ በኋላ ኢር ፎኑን ጆሮዬ ውስጥ ሰክቼ አይፎኔ ላይ “Play” የሚለዉን ስጫነዉ ጥላሁን ገሰሰ “አራዊቱ ሁሉ መጥቶ ቢከበኝ” እያለ ጀመረኝ። የምወደው ዘፈን ነበርና ደጋገምኩት። ጥላሁንኮ ድምጻዊ ብቻ አይደለም ነቢይም ነዉ፤ የዛሬ ስንትና ስንት አመት በአራዊቶች እንደምንከበብ ተንብዮ ነበር። የሚቀጥለው ዘፈን ገና ሲጀምር ምን መሆኑ ታወቀኝና. . . . . ኧረ በፍጹም. . . እንዴት ተደርጎ አልኩና አይፎኔን ዘግቼዉ ኪሴ ዉስጥ ከተትኩት። “መለያየት ሞት ነዉ” የሚለዉን የጥላሁን ገሰሰ ሙዚቃ ብወደዉም የጠነከረዉ ሆዴ እንዲባባ በፍጹም አልፈለኩም። አይፓዴን አወጣሁና የአስናቀች ወርቁን ሰዉነት እየሰረሰር ገብቶ አንጀት የሚያርስ ክራር መኮምኮም ጀመርኩ። አስናቀች ኢትዮጵያን ጨምሮ ብዙ ቦታ ወሰደችኝ፤ ደግነቱ ዬትም ትዉሰደኝ ዬት መልሳ መላልሳ እዚያዉ አዉሮፕላኑ ውስጥ ታመጣኝ ነበር . . . አለዚያማ!
አዉሮፕላኑ ወንበር ላይ አንደተኛሁ ከአንድ ጎኔ ወደ ሌላዉ ጎኔ ስገላበጥ ሁለት የተለያዩ ድምጾች ተራ በተራ ጆሮዬ ዉስጥ ገቡ። ከአይፓዴ የሚወጣዉ ድምፅ “እልም አለ ባቡሩ” ይላል፥ የአዉሮፕላኑ ድምጽ ማጉያ ደግሞ “Welcome to Munich” ይላል። እንቅልፋም አይደለሁም፥ እንቅልፌን ሳልጨርስ የሚቀሰቅሰኝ ሰዉም ሆነ ምንም አይነት ድምጽ ግን ጠላቴ ነዉ። ደግሞም የእንቅልፍ ነገር ሆኖብኝ ነዉ እንጂ ሙኒክ መድረሴን ወድጄዋለሁኮ።
እኔንና ሌሎች ከ180 በላይ መንገደኞችን የጫነዉ ዩናይትድ አየር መንገድ በረራ ቁጥር 106 አዉሮፕላን ጎማዎች ከሙኒክ አዉሮፕላን ማረፊያ ወለል ጋር ሲላተሙ ያ ለካሳ ተሰማ ዘፈን አልበገር ያለዉ እንቅልፌ ዳግም አይመጣ ይመስል እልም ብሎ ጠፋ። እኔም የምን እንቅልፍ አልኩና ሙኒክን ለማየት ቸኮልኩ። ሙኒክ ሲባል ከልጅነቴ ጀምሮ እሰማለሁ እንጂ እቺን ዉብ የባቫሪያ ከተማ ሳያት የመጀመሪያዬ ነበር። አይፎኔን አወጣሁና ከአስመራ አሜሪካ ከገባሁ ጀምሮ ስልክ እየደወለ ሙኒክ ካልመጣህ እያለ ለሚጨቀጭቀኝ የአገሬ ሰዉ ስልክ ደወልኩ. . . . ጋሼ ደረስክ እንዴ አለኝ። አዎ እናንተን እየጠበኩ ነዉ አልኩት። ጋሼ እኛ መግባት አንችልም ስትወጣ ታየናለህ አለኝ። ሁለት ተንጠልጣይ ሻንጣዎቼን ግራና ቀኝ ትከሻዬ ላይ አንጠልጥዬ ሻንጣ የጫንኩበትን ጋሪ እየገፋሁ ወደ መዉጫዉ አመራሁ። የሁለቱ ሻንጣዎች ክብደት ትከሻዬን ሲያጎብጠዉ ግዜ ሁለተኛ ለማንም ሰዉ ዕቃ አላደርስም ብዬ ማልኩ። ሁሌም እየማልኩ የምረሳዉ መኃላ ቢኖር ይህ ብቻ ነዉ። ወደ መዉጫዉ ስጠጋ በሩ ወለል ብሎ ተከፈተ። ታክሲዉና አዉቶቡሱ፤ ሸኚዉ፤ እንግዳ ተቀባዩ፤ እኔን መሰሉ ወደ ሙኒክ የሚመጣዉና ሙኒክን የሚለቀዉ መንገደኛ እዚህም እዛም ይተራመሳል። ከዚህ ሁሉ የሰዉና የመኪና ትርምስ ዉስጥ አይኔ ተሽቀዳድሞ ያረፈዉ በዚያ በዉበቱና በድምቀቱ የባንዲራዎች አዉራ በሆነዉ የአገሬ ባንዲራ ላይ ነበር። ሊቀበሉኝ የመጡ ሁለት ኢትዮጵያዉያን ያንን በትንሽነቴ “ደሙን ያፈሰሰ” ብዬ የሰቀልኩትንና ማታ “ተጣማጅ አርበኛ” ብዬ ያወረድኩትን የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ይዘዉ ሲመጡ አየሁና ተጠጋኋቸዉ። ሰንደቅ አላማዉ “አምባሻ” ስለሌለበት አመንኳቸዉ። አለዚያማ ፊቴን አዙሬ ጉዞዬን ወደ አስመራ እቀጥል ነበር እንጂ አምኜ አልጠጋቸዉም ነበር። ወይ ጉድ …… ዘመን አያመጣዉ ነገር የለም. . . . . . የምንተነፍሰዉንም አየር መጠርጠር ጀመርንኮ!
ሙኒክ የገባሁት ሐሙስ ጧት አስር ሰአት ተኩል ላይ ነበር። እሁድ ጧት ለስራ ጉዳይ ሲዊዘርላንድ እስክሄድ ድረስ ከሁለት ቀን ተኩል በላይ ሙኒክ ዉስጥ ቆይቻለሁ። ግን እንኳን ሁለት ቀን ተኩል ግማሽ ቀንም የቆየሁ አልመሰለኝም። ነገሩ ምንድነዉ ብዬ ተገረምኩ። ሚስጢሩ የገባኝ አስመራ ገብቼ ከእንቅልፌ ስነቃና የቀረብኝን ሳዉቀዉ ነዉ። ሙኒኮች በልቼ የምጠግብ፥ ጠጥቼ የምረካ አይመስላቸዉም። ያገኙኝ ሰዎች ሁሉ ብላ፤ጠጣ፤ እንሂድ፤ እንዉጣ፤ ምን እንግዛ፤ ምን እናምጣ፤ ምን ትፈልጋለህ፤ ምን አነሰ ነዉ ጥያቄያቸው። የሙኒክ ወገኖቼ ከኑሯቸዉ በላይ ሲያስቡልኝና ከራሳቸዉ በላይ ሲሳሱልኝ አይቼ እንደ ዐለት የማይነቃነቅ ደጀን አለኝ ብዬ ተመክቼባቸዋለሁ። በተለይ ሙኒክ ውስጥ ያየኋቸዉ ሴቶች እህቶቼ መጥተን እንቀላቀላችሁ እንጂ ከተማ ዉስጥማ ምን እናደርጋለን ነበር ጥያቄያቸዉ። የሙኒክ ሴቶች ደሜ ዉስጥ የቀረዉን የመጨረሻ የፍርሃት ጠብታ ጠራርገዉ ሲወስዱት ታወቀኝና ድፍረቴ ከአናቴ አልፎ ሲያንሳፍፈኝ ተሰማኝ። እቴጌ ተዋበች ለቋራዉ አንበሳ እቴጌ ጣይቱ ደግሞ ለዳግማዊ ምንሊክ ጉልበት፤ ብርታትና ጽናት እንደሆኗቸው ሁሉ ለኔም የሙኒክ ሴቶች ደሜ ዉስጥ ገብተዉ ብርታት፤ ልቤ ዉስጥ ገብተዉ ጽናት ሆኑኝ። አደራ. . . . ሴት የላካዉ ሞት አይፈራም ብላችሁ ለቆራጥ እህቶቼ የምሰጠዉን ምስክርነት እንዳታሳንሱብኝ። የሙኒክ ሴቶች የልብ ልብ የሰጡኝ ዕቃችንን ጠቅልለን ካልተከተልንህ እያሉ ነዉ እንጂ አይዞህ በርታ አለንልህ እያሉ ብቻ አልነበረም።
ቀኑን እንደ ደዋሪ ከወዲህ ማዶ ወዲያ ማዶ ስሽከረከር ዉዬ ስለደከመኝ አርብ ዬካቲት 26 ቀን (Feb 26) አልጋዬ ዉስጥ የገባሁት በግዜ ነዉ። ከሆቴሉ ሰራተኛ ቁልፍ ተቀብዬ መኝታ ክፍሌ ስደርስ አልጋዋ እንኳን ሙሉዉን ኤፍሬም አንድ እግሩንም ተሸክማ የምታድር አልመሰለችኝም። ትንሽዬ አልጋ ናት። ሽንት ቤቱና መታጠቢያ ቤቱም እንደዚሁ። ብቻ ምን አለፋችሁ አዉሮፓ ዉስጥ ትልቅ ነገር ያለም አይመስል። መንገዱ፤ መኪናዉ፤ ሀንጻዉና መኖሪያ ቤቱ ሁሉም ነገር ትንሽ ነው። አዉሮፓዉያን አንድ ነገራቸዉ ግን ትልቅ ከትልቅም ትልቅ ነዉ። ለሀይል ቁጠባና (Energy Conservation) ለአካባቢ ጥበቃ የሚሰጡት ቦታ እጅግ በጣም ትልቅ ነው። አዉሮፓ ስሄድ ሁለት ጉዳዮች ነበሩኝ። አንደኛዉ የሙኒክ ኢሳት ቤተሰቦች ባዘጋጁት የገንዘብ ማሰባሰብ ስብሰባ ላይ ለመገኘት ሲሆን ሁለተኛዉ ደግሞ የትግል ጓደኛዬን የአንዳርጋቸዉ ጽጌን 61ኛ አመት የልደት በዐል ሲዊዘርላንድ ዉስጥ ከሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ወገኖቼ ጋር ለማክበር ነዉ።
አርብ ማታ በግዜ ቆጤ ላይ ስለተሰቀልኩ ቅዳሜ ዬካቲት 27 ቀን ከእንቅልፌ ስነቃ እንደልማዴ እየደጋገመ አላዛጋኝም ወይም ተኛ ተኛ አላሰኘኝም። ፈጣን ሻወር ወስጄ ልብሴን ለባበስኩና ያደርኩበት ሆቴል በነጻ ብላ ያለኝን ቁርስ መቆርጠም ጀመርኩ። ከቁርሱ ይልቅ የጣመኝ ቡናዉ ነበርና አንዴ ደግሜ ሶስተኛዉን ይዤ ጠረቤዛ ቀየርኩና አይፓዴን ከፍቼ ዜና መቃረም ጀመርኩ። ኦሮሚያ ዉስጥ ከሦስት ወራት በፊት የተቀሰቀሰዉ ሀዘባዊ ቁጣ አለመብረዱ፤ የአዲስ አበባዉ ታክሲ ሾፌሮች አድማና ጎንደር ዉስጥ በየቦታዉ የሚፈነዳዉ ህዝባዊ አመጽ ትኩረቴን ከሳቡ ዜናዎች ዉስጥ ዋና ዋናዎቹ ነበሩ። ዜና ማንበቡን ጨርሼ ቀና ስል ጋዜጠኛ ሀይሉ ማሞና ጓደኛዉ መጡና . . . ጋሼ ምሳ እንብላ እንጂ ብለዉኝ ተያይዘን ወጣን።
ፉጨቱ፤ ሆታዉ፤ መዝሙሩና አዳራሹ ዉስጥ በየማዕዘኑ የሚዉለበለበዉ ሰንደቅ አላማችን ገና ስብሰባው አዳራሽ ዉስጥ ሳልገባ በሩቁ የአዳራሹን ስሜት ነገረኝ። አዳራሹ ዉስጥ ያሉት ኢትዮጵያዉያን አላማቸዉ አላማዬ ምኞታቸዉ ምኞቴ እንደሆነ ካውቅኩ ቆይቷል። አዳራሹ ዉስጥ ገብቼ ስሜታቸዉን ሳይ ግን ልባቸዉ ከልቤ ተገናኘና ደሜ ደማቸዉ፤ ሞቴ ሞታቸዉ መሆኑ ዉስጤ ድረስ ዘልቆ ተሰማኝ። ከሰዉነቴና ከሰዉነታቸዉ የአካል ፍላጭ ወጥቶ አዲስ አካል ሲፈጠር ታወቀኝ። አዎ. . . ዜግነት መሰረቱ፤ እኩልነት ማዕዘኑ፤ ነጻነት ጣራዉ፤ ፍትህ ወለሉ፤ አንድነትና ዲሞከራሲ ድርና ማጉ የሆነ ፍጹም አዲስ አካል ሲፈጠር ተሰማኝ። ፍጹም ልዩ ስሜት ነበርና ወደድኩት። አዳራሹ ዉስጥ ገብቼ ብዙም ሳልቀመጥ እኛ በህይወት እንድንኖር የሞት መስዋዕትነት ለከፈሉልን ጀግኖች የሂሊና ጸሎት እናድርስ ሲባል አዳራሹ ዉስጥ ያለዉ ሰዉ በሙሉ ከመቀመጫዉ ተነሳ። አዳራሹ ላንዳፍታ ሰዉ የሌለበት ኦና ቤት መሰለ። ያንን ሰው የሞላበት የስብሰባ አዳራሽ የዝምታ ጽላሎት ዋጠዉ። ሁላችንም በአንድ አፍንጫ እንተነፍስ ይመስል ትንፋሻችን እራሱ አንድ ሆነ።
ሁለቱ የኢሳት ጋዜጠኞች አፈወርቅ አግደዉና ሀይሉ ማሞ ማይክሮፎናቸዉን ጨብጠዉ መድረኩ ላይ ቦታ ቦታቸዉን ይዘዋል። አዳራሹን የሞላዉ ህዝብ እነሱን እነሱ ደግሞ ህዝቡን ያዩታል። ጋዜጠኛ ሀይሉ ማሞ ለእለቱ ጨረታ የቀረበዉን ዉብ የኢሳት አርማ ለተሰበሰበዉ ህዝብ ሲያሳይ ያ የሂሊና ፀሎት ሲደረግ ዝምታ የዋጠዉ አዳራሽ በጭብጨባ ጩኸት የፈረሰ መሰለ። ጨረታዉ በአንድ ሺ ዩሮ ተጀመረ። አፈወርቅ አግደዉ መድረክ ላይ ወጣና በዚያ ጀት ድምጹ ንግግሩን ሲጀምር አዳራሹ ዉስጥ ኢሳት ቴሌቭዥን የተከፈተ መሰለኝ። ከጋዜጠኛ አፈወርቅ አግደዉ አፍ እንደ አብሪ ጥይት እየተወረወሩ የሚወጡት ቃላት አድራሻቸዉ ጆሮ ሳይሆን የተሰበሰበዉ ሰዉ ኪስ ዉስጥ ይመስል ሁሉም እየተነሳ ያለዉን ይለግስ ጀመር። በአንድ ሺ ዩሮ የተጀመረው ጨረታ ብዙም ሳይቆይ አምስት ሺ ዩሮ ደረሰ። አዳራሹ ዉስጥ የነበርኩት ብቸኛ የበረሃ ሰዉ ጨረታዉ አምስት ሺ ዩሮ ላይ የሚቆም መስሎኝ ነበር። ምን ላድርግ እዉነቴን ነዉ። በረሃ ዉስጥ ብቸኛዉ የገንዘብ ቋንቋ ናቅፋ ብቻ ነው። አምስት ሺ ዩሮ ደግሞ እጅግ በጣም ብዙ ናቅፋ ነዉ። ለሁሉም ጨረታዉ እኔ እንዳሰብኩት አልቆመም፤ እንዲያዉም የማሸነፍ እልህ ዉስጥ በገቡ ከተሞችና ግለሰቦች መካከል ፉክክር ፈጠረና 6 ሺ፤ 7 ሺ፤ እና 8 ሺ እያለ ቀጠለ።
የሙኒክ ጨረታ ትዉስታቸዉ በበጋው ፀሐይና በክረምቱ ዝናብ የማይደበዝዝ ሶስት ትዝታዎች ጥሎብኝ አልፏል። ለወትሮዉ እኔ ጨረታ የማዉቀዉ ግለሰቦች በቡድን ወይም በግል ሲጫረቱ ነዉ። የሙኒኩን ጨረታ ለየት ያደረገብኝ አንዱ ነገር የጀርመን ኢትዮጵያዉያን ሙኒክ፥ በርሊን፥ ፍራንክፈርትና ኑረምበርግ. . . ወዘተ እያሉ በከተማ ጭምር ያደረጉት ጨረታ ነዉ። እንግዲህ ይታያችሁ አዉሮፓ ዉስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ጨረታ በተካሄድ ቁጥር የሚጫረቱት በግል፥ በቡድንና በከተማ ጭምር ከሆነ እነዚህ ኢትዮጵያዉያን ለፍትህና ለነጻነት ለሚደረገዉ ትግል የሚያደርጉት አስተዋጽኦ ከሌሎቻችን ይበልጣል ማለት ነው። ሌላዉ የሙኒክ ትዝታዬ የጀርመን ኢትዮጵያዉያን ወያኔን ለማጥፋት በሚደረገዉ ትግል ዉስጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ባደረጉ ጀግኖች ኢትዮጵያዉያን በነ አንዳርጋቸው ጽጌ፤ ርእዮት አለሙ፤ እስክንድር ነጋ፤ ኡስታዝ አቡበከር፤ በቀለ ገርባና አንዱአለም አራጌ . . . ወዘተ ስም መጫረታቸዉ ነዉ። በእነዚህ ጀግኖች ስም የተደረገዉ ጨረታ የጀግኖቹ ስምና ህያዉ ስራቸዉ ከልባችን እንዳይጠፋ ማድረጉ ብቻ ሳይሆን የእነሱን ፈለግ እንድንከተል የሚገፋፋ ነበርና ለሙኒኮች ያለኝ አድናቆት ከፍተኛ ነው። Dank u München!
ሶስተኛዉ ትዝታዬ ሙኒክን ለቅቄ አስመራ ከገባሁ ከሶስት ሳምንታት በኋላ አሁንም ፊቴ ላይ አለ። ካሁን በኋላም ቢሆን እየረሳሁ ብዉልና ባድር ሶስተኛዉን ትዝታዬን የምረሳ አይመስለኝም። ይህ እንደ አፍላ ፍቅር ልቤ ዉስጥ ተተክሎ የቀረዉ ትዝታ የሶስት ሰዎች ትዝታ ነዉ። በአንድ በኩል ፊት ለፊት የመጀመሪያዉ ረድፍ ላይ ተቀምጦ ከተሸነፍኩ ሞቼ እገኛለሁ የሚል ዶክተር አለ። በሌላ በኩል ደግሞ አዳራሹ ኋላ ሆነዉ አንሸነፍም ብለዉ የመሸጉ ባልና ሚስት አሉ። እነዚህ ሶስት ሰዎች ኋላና ፊት ተቀምጠዉ ያካሄዱት ለሰአታት የዘለቀ ፉክክር ተሰብሳቢዉን እንደ ልብ ሰቃይ ድራማ ከፍና ዝቅ ያደረገ ልዩ ትርዕት ነበር።
ዶክተሩ የህክምና ዶክተር ነዉ። ታላቄ ነዉ ሆኖም በቁመት እንጂ በዕድሜ ብዙ አንበላለጥም። የምፈልገዉን ነገር አድርግልኝ ስለዉ ያደርጋል፤ ና ስለዉ ይመጣል። ከሙኒክ ሲዊዘርላንድ እንሂድ ስለዉ ሳያቅማማ ስራዉን ጥሎ ነዉ የተከተለኝ። ቀልዱ፥ጨዋታዉና ቁምነገሩ አይጠገብም፥ በተለይ ከአፈወርቅ አግደዉ ጋር ሲተራረቡ የአራት ሰአቱ የሙኒከ ሲዊዘርላንድ መንገድ እንኳን ያለቀ የተጀመረም አይመስልም ነበር። ብቻ ምን ልበላችሁ ዶ/ሩ ለኔ የነበረዉ አክብሮትና ለእናት አገሩ ለኢትዮጵያ ያለው ፍቅር በኔ ደካማ ብዕር የሚገለጽ አይደለም።
ባልና ሚስት ናቸዉ፥ የተቀመጡት አዳራሹ የመጨረሻ ረድፍ ላይ ነዉ። አይቸኩሉም ደግሞም አይዘገዩም። ፈጣሪ ያደላቸዉ ስጦታ ነዉ መሰለኝ ትክክለኛዉን ግዜ ያዉቁታል። ሲማከሩ ጆሮና አፍ ገጥመው ያንሾካሽካሉ። ሲስማሙ ስምምነታቸዉን የሚናገረዉ ባልየዉ ነዉ። የእነዚህ ባልና ሚስት ፍላጎት ጨረታዉን ማሸነፍ ሳይሆን ኢሳትን መርዳት መሆኑን የሁለቱም ፊት በግልጽ ይናገራል። ከላይ ባስተዋወቅኳችሁ ዶክተርና በእነዚህ ባልና ሚስት መካከል የተደረገዉ የጨረታ ፉክክር አዳራሹ ዉስጥ የተሰበሰበዉን ኢትዮጵያዊ ልብ ሰቅዞ የያዘ ፍጹም ልዩ ድራማ ነበር። ፉክክሩ ማሸነፍ ብቻ ሳይሆን የአገር ፍቅርና እኛነት የታየበት እንዲሁም የማይቀረዉን ብሩህ የአገራችንን ተስፋ ከወዲሁ በናሙና መልክ ፈንጥቆ ያሳየ ዉብ መድረክ ነበር። በገንዘብ አስተዋጽኦ መልኩም ቢታይ ባልና ሚስትና ዶክተሩ ያደረጉት ፉክክር የጨረታዉን ጣሪያ ከሃያ ሺ ዩሮ በላይ አድርሶታል። በነገራችን ላይ እዚህ መጣጥፍ ዉስጥ ስማቸዉን ጠቅሼ ብጽፍ ደስ የሚለኝ ብዙ ኢትዮጵያዉያን አሉ። የማላደርገዉ ክፉ ብቻ ሳይሆን ጭራሽ ደንቆሮ የሆነ ጠላት ስላለን ነዉ። ይህ ጠላት የደደብነቱ ብዛት የሥልጣን ክልል ያለዉም አይመስለዉም፤ አዉሮፓና አሜሪካ ዉስጥ የጻፈ፥ የተናገረና ሀሳቡን የገለፀ ኢትዮጰያዊ ላይ እድሜ ልክ እስራት ይፈርዳል። ደሞስ ጭንቅላታቸዉ በንፍጥ ብቻ የተሞላና ሰዉነታቸዉ በተዘረፈ ሀብት የደለበ ሰዎች ከዚህ የተለየ ምን ሊያደርጉ ይችላሉ?
ከሙኒክ የሲዊዟ መናገሻ ቤርን ድረስ የአራት ሰአት መንገድ ነዉ። በረጂም በረራና በቅዳሜዉ የአዳራሽ ዉስጥ ቆይታ የተዝለፈለፈዉ ሰዉነቴ እየከዳኝ ቢሆንም የግድ ሲዊዘርላንድ መሄድ ነበረብኝና ተንገዳግጄ መኪናዉ ዉስጥ ገብቼ የአራት ሰአቱን መንገድ ተያያዝኩት። የሙኒከ ሲዊዘርላንድ መንገድ የሚያልፈዉ በኦስትሪያ በኩል ነዉ። ከጀርመን ወጥቼ ኦስትሪያ መግባቴን ያውቅኩት ሁለቱ አገሮች ድንበር ላይ የቆሙትን ፖሊሶች ስመለከት ነዉ፤ ለዚያዉም ባይነገረኝ ኖሮ አላዉቅም ነበር። መኪናዉ ዉስጥ እንቅልፍ ብጤ ሞካክሮኝ ነበር ግን የጋዜጠኛ አፈወርቅ አግደዉና የዚያ ደግ ዶክተር ጨዋታ እንኳን እንቅልፍ ሌላም ነገር የሚያስረሳ ነበርና ጨዋታቸዉ እንቅልፌን አባረረዉ። የመኪናዉ ዉስጥ ቀልድ፥ ተረብና ጆክ ከአካባቢዉ የተፈጥሮ ዉበት ጋር ሆነዉ መንፈሴን እያደሱት ድካሜን አስረሱኝ። አፈወርቅን የምትወዱት በቴሌቭዥን መስኮት ዉስጥ ብቻ አይታችሁት ከሆነ ብዙ ገና ብዙ ይቀራችኋል . . . ምኑን አያችሁና። አፈወርቅ ሲቀርቡት ጨዋታዉ፤ ቀልዱና ቁም ነገሩ አይጠገበም። ስለምንም ነገር ሲናገር የራሱ የሆነ ልዩ ዜማና ቃና አለዉ። ታሪክ ሲናገር በታሪኩ ዉስጥ ይዟችሁ ያልፋል። የታሪኩን መቸትና የተዋንያኑን ስም ከአባት ስም ጋር ሲናገር መጽሐፍ የሚያነብ እንጂ በቃሉ የሚናገር አይመስልም። የአማርኛ ቋንቋ በተለይ የቅኔ ችሎታዉ ይኸ ሰዉ ዋልድባ ነዉ ጋሙጎፋ ተወልዶ ያደገዉ ያሰኛል።
ከሙኒክ ተወጥቶ ኦስትሪያ እስኪገባ ድረስ ከመንገዱ ግራና ቀኝ የሚታየዉ ዘመናዊ እርሻ ከሳንሆዜ ሳንታክላራ ሲኬድ የሚታየዉን ሜካናይዝድ እርሻ አስታወሰኝ። የአዉሮፓና የአሜሪካ መመሳሰል ገረመኝ። በሃሳቤ ረጂም ርቀት ወደኋላ ተጓዝኩና አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስማር ከአዋሳ አዲስ አበባ በአዉቶቡስ ስጓዝ አዉቶቡሱ ቆቃን እንዳለፈ አርሲ ነጌሌ እስኪደርስ ድረስ አልፎ አልፎ የማያቸዉ ትናንሽ እርሻዎች ፊቴ ላይ መጡ። አስናቀች ወርቁ “እንደ መቀነቴ ዞሬ ዞሬ እዚያዉ” ብላ የተጫወተችዉ ዘፈን ትዝ አለኝና ሆዴ በቁጭት ተሞላ። አዎ የኛ ነገር ዞሮ ዞሮ እዚያዉ ነዉ። እርሻው እዚያዉ፤ ገበሬዉ እዚያዉ፤ ፋብሪካዉ እዚያዉ ባጠቃላይ የኑሮ ደረጃዉ እዚያዉ ነዉ። እዚያዉ ድሮ የነበረበት ቦታ። ወደፊት እናያለን እንጂ ወደፊት አንሄድም። ይህንን ሳስብ ተቆጨሁ . . . ተናደድኩ። ለምን አልናደድ ለምንስ አልቆጭ . . . እኛና ድህነት፤ እኛና ኋላቀርነት፤ እኛና እየረገጡ ከሚገዙን ጋር መሞዳሞድ ሞት ካልለየን በቀር ላንለያይ የቆረብን ይመስላልኮ!
እኛ ኢትዮጵያውያን ከአዉሮፓና ከአሜሪካ ለምንድነዉ ይህን ያህል የምናንሰው ብዬ እራሴን ጠየኩና መልሳ ሳጣ የአዉሮፓን ዉበት ማድነቄን ቀጠልኩ። እዉነቱን ለመናገር የኋላ ቀርነታችን ምክንያት ጠፍቶኝ አይደለም። ለምን መናጢ ደሃዎች እንደሆንም ጠፍቶኝ አይደለም። ችግሩ. . . የኋላ ቀርነታቸንን ምክንያት ባሰብኩ ቁጥር ከዚህ አሳፋሪ ኋላ ቀርነት ለመላቀቅ የምናደርገዉ ጥረት እምብዛም መሆኑን ስለማዉቅ ማሰቤን አቆምና ንዴትና ቁጭት ዉስጥ እገባለሁ። የኔ ነገር ደግሞ ጉድ ከጉድም ጉድ ነው፤ አራሴን ስጠይቅ የማገኘዉ መልስ ቁጭትና ንዴት ነዉ። ቁጭትና ንዴት ደግሞ እንደገና ጥያቄ ያጭሩብኛል። ይገርማል .… አገሬ ከድህነት ኡደት እኔ ከጥያቄ ኡደት ላንላቀቅ የተማማልን ይመስላል። የራሱ ፊደል፥ ስነጽሁፍና የራሱ የሆነ የዘመን መቁጠሪያ ቀመር ያለዉ ሀዝብ እንዴት ያልሰለጠነ ህዝብ ተበሎ ይጠራል? አባይን፤ አዋሽን፤ ሸበሌን፤ዴዴሳን . . . ወዘተ ይዞ አገር እንዴት ይራባል? አክሱምን፤ ላሊበላንና ፈሲለደስን የገነባ ህዝብ ለምን ከኋላ ቀሮች ተርታ ስሙ ይጻፋል? ለምን? ለምን? ለምን?
ኦስትሪያ ስደርስ እርሻዉ፤ መኪናዉ፤ ከተማዉ፤ የሰዉ መልክና ቋንቋዉ ምንም አልተለየብኝም። ልዩነት አለ ቢባል ጀርመንን ለቅቄ ኦስትሪያ የሚባል አገር መድረሴ ብቻ ነዉ። ኦስትሪያን ለቅቄ ሲዊዘርላንድ ስገባም ፊት ለፊቴ ላይ ጉብ ጉብ ብለዉ ከሩቁ ከሚታዩኝ ተራራዎች ዉጭ ከተማዉ የጀርመንን ከተሞች ይመስላል፤ ብዙዎቹ መኪናዎች ጀርመን ዉስጥ የተሰሩ መኪናዎች ናቸው፤ ቋንቋዉም ጀርመንኛ ነዉ። ከአሜሪካ ተነስቼ ሲዊዘርላንድ እስክደርስ ድረስ በአራት አገሮች ዉስጥ አልፍያለሁ (አሜሪካ፥ ጀርመን፥ ኦስትሪያና ሲዊዘርላንድ) – ማነህ ተብዬ ፓስፖርት የተጠየኩት አሜሪካንን ስለቅና ሙኒክ ስገባ ብቻ ነው።
ሽፍታዉ ልቤ መሸፈት አይታክተዉ ነገር አሁንም ሸፈተ። ደግሞስ ይሸፍት አንጂ. . . . ለምን አይሸፍት? የተወለድኩት ኢትዮጵያ ዉስጥ ነዉኮ! እኛ ሰዎች እግዚአብሄር በአምሳያዉ እኩል አድርጎ ፈጥሮን አንዱ መሪዉን መርጦ ሲሾም ሌላዉ በገዛ መሪዉ ሲጎሸም፤ አንዱ በልቶ ጠግቦ ሲያምርበት ሌላዉ የሚበላዉ አጥቶ ህይወት ሲከዳዉ፤ አንዱ ሁሌም አሳሪ ሌላዉ ሁሌ ታሳሪ፤ አንዱ የበላይ አንዱ የበታች ሲሆን እንኳን የሰዉ ልብ ከሳር ዉጭ ሌላ የማያዉቀዉ በሬም ይሸፍታል። ጀርመንን፤ ኦስትሪያንና ሲዊዘርላንድን ሳይ በገዛ አገራቸዉ ማናችሁ እየተባሉ በየኬላዉ የሚጉላሉት ምስኪን ወገኖቼ ትዝ አሉኝ። ቤንች ማጂ ዉስጥ ወደ ክልልህ ተመለስ ተብሎ የተገፋዉ ወገኔ በርቀት ታየኝ። ቤኒሻንጉል ዉስጥ አለክልልህ ምን ታደርጋለህ ተብሎ ንብረቱን ተቀምቶ እየተረገጠ የተባረረዉ ኢትዮጵያዊ ወገኔ ትዝ አለኝና ሆዴን አመመኝ። ጋምቤላ ዉስጥ የአያት ቅድም አያቶቹ መሬት ጠመንጃ ባነገቱ ጉልበተኞች ተቀምቶ ሲታርስ እሱ ተመልካች የሆነው አኝዋክ ወገኔ ትዝ አለኝ።
ከጀርመን ሲዊዘርላንድ ስንጓዝ መኪናዉ ዉስጥ የነበርነዉ አምስት ሰዎች ሁላችንም ኢትዮጵያዉያን ነን። አዉሮፓ ዉስጥ አገሮችን በሚያሳስብ ደረጃ ከፍተኛ የስደተኛ ቀዉስ አለ። ሆኖም ከጀርመን ወጥተን በኦስትሪያ በኩል ሲዊዘርላንድ እስክንደርስ ድረስ አንድም ግዜ ማናችሁ የሚል ጥያቄ አልቀረበልንም። ተመልሰን ጀርመን ስንገባም እንደዚሁ። እትብቴ በተቀበረባትና የዚህ አለም ጉዞዬን ስጨርስ የመጨረሻ ማረፊያዬ እንድትሆን በምፈልግባት ምድር እንደ ቆሻሻ ነገር የሚረገጠዉ መብቴ በባዕድ አገር ሲከበር አየሁና “ኢትዮጵያዊነት” ምን ያደርጋል ብዬ አማረርኩ። ችግሩ ኢትዮጵያዊነት ላይ ሳይሆን ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት ቆርጠዉ በተነሱ ከሃዲዎች ላይ መሆኑ ገባኝኛ እነዚህን ከሃዲዎች ማጥፋት አለብኝ አለኩ። አዎ! እነዚህን ከሃዲዎች ማጥፋት አለብኝ ። “ማጥፋት” አለብኝ ሲባል አባባሉ በተግባር ካልተተረጎመ የባዶ ቃላት ጫጫታ ወይም የሞተ ሰዉ ዛቻ ነዉ። አንተ/አንቺ አንባቢ አስተዉል/አስተዉይ። ነፃነትና ፍትህ የሌሉበት አገር ሁሉ የአጥፊዎችና የጠፊዎች መድረክ ነዉ። ጠፊና አጥፊ ባሉበት ቦታ ደግሞ ሁለቱም ያጠፋሉ። አጥፊ ስራዉ ማጥፋት ነዉና ያጠፋል። ጠፊ ደግሞ ላለመጥፋት የሚያደርገዉ ምንም ነገር ስለሌለ እራሱን በማጥፋት ከአጥፊዉ ጋር ይተባበራል። የኛ የኢትዮጵያዉያን ችግርም ይኼዉ ነዉ. . . ጠፊዉም አጥፊዉም እኛዉ እራሳችን ነን። ከዛሬ በኋላ ግን እኛ አጥፊዎች ጠላታችን ጠፊ መሆን አለበት። ተፈላሲፌባችሁ ከሆነ ይቅርታ . . . እንደዚህ የሚያንበለብለኝ ዉስጤ ያለዉ ላለመጥፋት የማጥፋት ፍላጎት ነዉ። ሲዊዘርላንድ መናገሻ ቤርን መድረሴን ያወቅኩት መኪናዋ ቆማ . . . ጋሼ እንዉረድ ስባል ነው።
የኢትዮጵያን የቁርጥ ቀን ልጅ የአንዳርጋቸዉ ጽጌን 61ኛ አመት የልደት በዐል ለማክበር ሲዊዘርላንድ ዉስጥ የሚኖረዉ ኢትዮጰያዊ ከያለበት ተሰባስቧል። አዳራሹ ከመሙላቱ የተነሳ መቀመጫ ያጣዉ ሰዉ ያዳራሹን ዳር ዳር አጨናንቆታል። በየማዕዘኑ የሚወዛወዘዉ የኢትዮጰያ ሰንደቅ አላማ ለአዳራሹ ልዩ ዉበት ሰጥቶታል። የእንኳን ደህና መጣህ ጩኸቱ፥ ጭብጨባዉና ፉጨቱ አዳራሹ የእግር ኳስ ስታድዩም እስኪመስል ድረስ ቀለጠ። አጠገቤ የቆመው ጋዜጠኛ አፈወርቅ አግደዉ ጭብጨባዉ ለኔ ነዉ ላንተ ብሎ ጠየቀኝ . . . ለኛ ነዉ አልኩት። ሳቅ አለና ሁለት እጆቹን ዘርግቶ ተሰብሳቢዉ እንዲቀመጥ ተማፀነ። እኔም እጆቼን ዘርግቼ አብሬዉ ተማፀንኩ። ከእግራቸዉ ጣት እስከ ጸጉራቸዉ ጫፍ ድረስ ፍቅር በፍቅር የሆኑት የሲዊዝ ኢትዮጵያዉያን የምን መቀመጥ አሉና ሆታዉና ጭብጨባዉ ቀጠለ። ጧት ሙኒከን ስለቅ ድካም በድካም የነበረዉ ሰዉነቴ ዉስጥ አዲስ ሀይል እየገባ ሲያጠነክረኝ ተሰማኝ። ለካስ እኛ ሰዎች ምናብ ለምናብ ስንናበብ ዉጤቱ ፍቅር፥ ሀይልና ብርታት ነዉ። ብቻ ምን አለፋችሁ የሲዊዘርላንድ ኢትዮጵያዉያን እንደ ሲዊዝ ቸኮለት የሚጣፍጥ የአገር ልጅነት ፍቅር አቀመሱኝና በወገን ፍቅር ሰከርኩ። ሲዊዞች፥ ቸኮለታቸዉና ፍቅራቸዉ በጣም ተመቸኝ…….. ግን ብዙ ስራ ስላለብኝ የአንዲን ልደት ሻማ አብርተንና ኬኩን ቆርሰን “መልካንም ልደት” አንዲ ብለን ከዘመርን በኋላ ተለያየን። ጉዞ እነሱ ወደ ቤታቸዉ እኔ ወደ ሙኒክ ሆነ።
ረቡዕ መጋቢት 2 (March 2) ቀን በጧት ተነስቼ ቁርስ ከበላሁ በኋላ ከአዲሶቹ የሙኒክ ጓደኞቼ ጋር ተያይዘን ጉዞ ወደ ኦሎምፒክ መንደር ሆነ። ሙኒክ ኦሎምፒክ ልጅነቴን ይዞ የሚመጣ ብዙ ትዝታ አለዉ። የሜክሲኮዉ ኦሎምፒክ ጀግና ሻምበል ማሞ ወልዴ የመጨረሻዉን የኦሎምፒክ ማራቶን፤ ሻምበል ምሩፅ ይፍጠር ደግሞ የመጀመሪያዉን የኦሎምፒክ ሩጫ የሮጡት ሙኒክ ኦሎምፒክ ላይ ነዉ። ምሩዕ ይፍጠር ሙኒክ የሄደዉ ለ10ሺና ለ5ሺ ሜትር ዉድድሮች ሲሆን በ10ሺ ሜትር ሦስተኛ ከወጣ በኋላ የ5ሺ ሜትር የመጨረሻዉ ዉድድር ከተጀመረ በኋላ በመድረሱ ያሸንፋል ተብሎ በጉጉት ይጠበቅ በነበረዉ ዉድድር ላይ ሳይሳተፍ ቀርቷል። ሙኒክ ኦሎምፒክ አሳዛኝ ታሪክም አለዉ። ጨለማዉ መስከረም (Black September) በመባል የሚታወቀዉ የፍልስጥኤማዉያን አክራሪ ቡድን ኦሎምፒክ መንደር ዉስጥ አሸምቆ ገብቶ በእስራኤል አትሌቶች ላይ አደጋ ያደረሰዉ በዚሁ እንደ ኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር በ1964 ዓም በተካሄደዉ ሙኒክ ኦሎምፒክ ላይ ነበር። በነገራችን ላይ ሙኒክ ኦሎምፒክ የተካሄደዉ ጥቁር አሜሪካዊዉ ጆዜ ኦዉንስ በርሊን ኦሎምፒክ ላይ የወርቅ ሜዳሊያዎች አሸንፎ የናዚ ሂትለር መሪዎች ጥቁር ስለሆንክ ከኛ እጅ ሜዳሊያ አትቀበልም ካሉት ከ36 አመታት በኋላ ነበር።
ሙኒክ ዉስጥ በመጨረሻ የጎበኘሁት ከከተማዋ 19 ኪሎ ሜትር ወጣ ብሎ የሚገኘዉንና በ1944 ዓም የተሰራዉን የዳሁ ናዚ ማጎሪያ (Concentration Camp) ነበር። ዳሁን ጎብኝቶ ለመጨረስ ወደ ሦስት ሰአት አካባቢ ፈጅቶብኛል። እነዚህ ሦስት ሰአቶች ወደፊትም ወደኋላም እየወሰዱኝ ዳሁ የጭካኔና የእልቂት ቦታ የመሆኗን ያክል የይቅርታና የመማማሪያ ቦታም እንደሆነ አሳይተዉኛል። ዳሁ ለሰዉ ልጅ ቁስሉም መድኃኒቱም ሰዉ መሆኑ የታየበትና የሰዉ ልጆች ጭካኔ መድረስ የሚችልበት የመጨረሻዉ ከፍታ ላይ የደረሰበት ቦታ ነዉ። ዳሁ አሁንም ድረስ ሲያዩት ጣረ ሞትን የሚጣራ የጨለማና የብርህን፤ የሞትና የህይወት፤ የጭካኔና የምህረት ቦታ ነዉ። ዳሁ የናዚ ግፍና ጭካኔ እማኝ ነዉ። ዳሁ የዘግናኝ ታሪክ ቅርፊት፡ የብሩህ ዘመን ትዉፊት፥ ቂምና ጥላቻን አብናኝ ይቅር ብሎ ይቅርታ ለማኝ ቦታ ነዉ። ዳሁ አይዋሽም . . . እንኳን ሊዋሽ ጭራሽ ዉሸት የሚባል አያዉቅም። ዳሁ ከአንዱ ክፍል ወጥተን ወደ ሌላዉ ክፍል በገባን ቁጥር የሚነግረን እዉነት ግን እግዚኦ መሀረነ ክርስቶስ ያሰኛል። ያቆስላል፤ ያደማል፤ ልብ ይሰብራል፤ ሆድ ይቆርጣል። እስረኞች ከመኝታ ቤታቸዉ እየተነዱ ገላችሁን ስለምትታጠቡ ልብሳችሁን አዉልቁ ተብለዉ ወደ ሌላ ክፍል ይወሰዳሉ። የሚቀጥለዉ ክፍል ዉስጥ የሚጠብቃቸዉ የመታጠቢያ ገንዳ ሳይሆን የመርዝ ጋዝ ገንዳ ነዉ። እስረኞቹ በመርዝ ጋዝ ከተገደሉ በኋላ እሬሳቸዉ ወደሚቀጥለዉ ክፍል ይወሰድና አገር የሚያክል ምድጃ ዉስጥ እየተጣለ ይቃጠላል። ይህ ግፍና ጭካኔ የተፈፀመዉ በሰዉ ልጆች ላይ ነዉ፤ ይህንን ግፍና ጭካኔ የፈፀሙትም የሰዉ ልጆች ናቸዉ። ጀርመንና ፖላንድ ዉስጥ ስላሉ የናዚ ጀርመን ማጎሪያ ካምፖች ከሰማሁ ቆይቷል። ይህንን በተለያዩ መጽሐፍት ላይ ያነበብኩትን ታሪክ ታሪኩ የተፈጸመበት ቦታ ላይ ቆሜ ስመለከት ግን አእምሮዬ ማሰብ አቆመና በድን ሆኜ ቀረሁ። ሁለት እጆቼን ዘርግቼ አማተብኩና . . . . . እንዲህ አይነት ክፉ ጭካኔ ዬትም ቦታ መደገም የለበትም ብዬ የዳሁ ጉብኝቴን ጨረስኩ።
ጀርመን፥ ኦስትሪያ፥ ሲዊዘርላንድና ዳሁ ስለ አሁኗና ስለወደፊቷ ኢትዮጵያ በየራሳቸዉ መንገድ የሚነግሩን ብዙ ነገር አለ። ዳሁ በሚባለዉ የናዚ ሂትለር ማጎሪያ ካምፕ ዉስጥ የተፈጸመዉን ግፍና ጭካኔ የፈጸሙት እኛን የመሰሉ የሰዉ ልጆች ናቸዉ እንጂ ከጥልቅ ባህር ዉስጥ የወጣ ዲያብሎስ አይደለም። ጀርመን፥ ኦስትሪያና አራት የተለያዩ ቋንቋዎች የሚነገሩባት ሲዊዘርላንድ ድንበር፤ ቋንቋ፤ባህልና ሐይማኖት ሳያግዳቸዉ ከአንዱ አገር ወደ ሌላዉ እንዳሰኛቸዉ እየተዘዋወሩ በኤኮኖሚ ተሳስረዉ በሰላም የሚኖሩት አርቆ አስተዋይ መሪዎቻቸዉ በወሰዱት መልካም እርምጃ ነዉ እንጂ እግዚአብሄር ከሰማይ ወርዶ የልዩነት ግድግዳቸዉን አፍርሶላቸዉ አይደለም። ክፉዉም ስራ የሰዉ ልጆች ስራ ነዉ፥ መልካሙም ስራ የሰዉ ልጆች ስራ ነዉ።እኛ ኢትዮጵያዉያን ምርጫችን ምንድነው? አዉሮፓ ዉስጥ ሰዉ ከአባቱ ገዳይ ጋር ተስማምቶ ሲኖር እያየን እኛ ከወንድሞቻችንና ከእህቶቻችን ጋር በሠላም ጎን ለጎን መኖር ለምን አቃተን? አዉሮፓዉያን በየአገሮቻቸዉ መካክል ያለዉን ድንበር አፍርሰዉ በአንድ ገንዘብ ሲገበያዩ እኛ በአንድ አገር ዉስጥ ለዘመናት አብሮ በኖረ ህዝብ መካከል አጥር የምንሰራዉ ለምንድነዉ?
ሙኒክ ከመሄዴ በፊት አሜሪካ ሜሪላንድ ዉስጥ አንድ ትልቅ ህዝባዊ ስብሰባ ላይ ተገኝቼ ነበር። እዚህ ስብሰባ ላይ የእምነት አባቶች፤ የሲቪክና የፖለቲካ ድርጅቶች መሪዎች፤ አባቶች፤ እናቶችና ወጣቶች ተገኝተዉ ነበር። የሁሉም ፍላጎት አንድ፤ አንድና አንድ ብቻ ነበር። እሱም ፍትህ፤ እኩልነትና ነጻነት የሰፈነባት ኢትዮጵያ እዉን ሆና ማየት ነዉ። አዉሮፓ መጥቼ ጀርመንና ሲዊዘርላንድ ዉስጥ ከሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ወገኖቼ ጋር ስገናኝ የተሰማኝ ስሜት አሜሪካ ዉስጥ ከተሰማኝ ስሜት ጋር ፍጹም ተመሳሳይ ነበር። እርግጠኛ ነኝ ኢትዮጵያዉያን በሚኖሩበት የአለም አካባቢ ሁሉ ፍላጎታቸዉ ፍትህ፥ ነጻነትና ዲሞክራሲ ነዉ። ግን ፍትህና ነጻነትን ስለፈለግናቸዉ ብቻ አናገኛቸዉም። የተናጠል ትግል ደግሞ ተራ በተራ የወያኔ ምሳና ቁርስ ያደርገናል እንጂ ነጻነታችንን አያስገኝልንም። በእርግጥ ነጻነት ስንደሰትበት ደስታዉ በግለሰብ ደረጃ ነዉ፤ ሆኖም ነጻነታችንን ጠላት እንዳይቀማን የምንጠብቀዉና ከተቀማንም ታግለን የምናስመልሰዉ በጋራ ነዉ። ስለዚህ ጽኑ የሆነዉ የፍትህና የነጻነት ፍላጎታችን ጽናት ባለዉ የጋራ ትግል ካልተደገፈ ያለን አማራጭ እየተረገጥን መኖር ብቻ ነዉ።
ወያኔ የበላይ በሆነባት በዛሬዋ ኢትዮጵያ ዉስጥ እንደዳሁ አይነት በሰዉ ዘር ላይ የተፈጸመ ወንጀል ሊፈጸም አይችልም የምንል ሰዎች ካለን ወደ ኋላ ዞር ብለን አኝዋክንና ኦጋዴንን ልንመለከት ይገባል። ዛሬ ወያኔ ኦሮሚያ ዉስጥ መብቴ ይከበር ብሎ በጮኸ ኢትዮጵያዊ ላይ የሚወስደዉ ፍጹም አረመኔያዊ የሆነ እርምጃም የሚያሳየን ወያኔ የስልጣን ገመዱ ባጠረ ቁጥር የማያደርገዉ ምንም ነገር እንደሌለ ነዉ። የወደፊቷ መልካም ኢትዮጵያ የምትናፍቀን ኢትዮጵያዉያን ከጀርመን፥ ከኦስትሪያ፥ ከሲዊዘርላንድና ከዳሁ የምንማረዉ ጠቃሚ ትምህርት አለ። ዛሬ በማድረግ ወይም ባለማድረግ የምንፈጽማቸዉ ብዙ ስህተቶች አሉ። እነዚህ ስህተቶች የጠላታችንን የወያኔን የሥልጣን ዘመን ማራዘማቸዉ ብቻ ሳይሆን ወያኔ ከተወገደ በኋላም ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ለመገንባት በምናደርገዉ ጥረት ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ያደርጋል። ለምሳሌ ኦሮሚያ ዉስጥ ለወራት የዘለቀዉ ህዝባዊ ቁጣና እምቢተኝነት በሌላ አገር የሚካሄድ ይመስል ብዙዎቻችን ከጎን ቆመን ተመልክተናል። ይህ አጉልና የማያዋጣ ቸልተኝነት ነገ በአማራ፤ በሲዳማ፤ በሃዲያና በኮንሶ … ወዘተ አካባቢዎች የሚነሱ ህዝባዊ እንቅስቃሴዎችን ኦሮሞዉ በቸልተኝነት እንዲመለከት ያደርገዋል። ኢትዮጵያ ዉስጥ አማራዉ ለኦሮሞ ካልጮኸና ኦሮሞዉ ከአማራዉ ጋር አብሮ ካልታገለ አማራዉ፤ ኦሮሞዉ ባጠቃላይ የኢትዮጵያ ህዝብ ከወያኔ ባርነት ነፃ አይወጣም። ወደድንም ጠላን ታሪክ ኢትዮጵያ ዉስጥ ሲዳማን በወላይታ፤ ጉጂን በጌዲኦ፤ ትግሬን በአማራ፤ አማራን በኦሮሞ . . ወዘተ አዉድ ዉስጥ ጠቅልሎ አስቀምጦናል። ከዚህ ጥቅልል ዉስጥ በተናጠል አንዱ ብቻዉን ነፃ መሆን አይችልም። ወያኔ ጨፍልቆ የሚረግጠን አንድ ላይ ነዉ፤ ነፃ የምንወጣዉም አንድ ላይ ነዉ። ኢትዮጵያና አንድነቷ አደጋ ላይ ወድቀዋል። ኢትዮጵያዊነት የምንለዉ ክቡር ማንነትም ከፍተኛ አደጋ ላይ ነዉ። እነዚህን ጣምራ አደጋዎች ማቆም የዚህ ትዉልድ ሃላፊነት ብቻ ሳይሆን ግዴታም ነዉ። የወደፊቷ ኢትዮጵያ ዉስጥ ዳሁን የመሰለ የመታሰቢያ ቦታ እንዲኖራት በፍጹም መፍቀድ የለብንም። ይህ እዉን የሚሆነዉ ግን እኛ ኢትዮጵያዉያን እጅ ለእጅ ተያይዘንና ትከሻ ለትከሻ ተደጋግፈን የዛሬዋን ኢትዮጵያ ከእልቂት አድነን የነገዋን ኢትዮጵያ በፍትህ፤ በነጻትና በዲሞክራሲ መሰረት ላይ መገንባት ከቻልን ብቻ ነዉ። ሌላ ምንም መንገድ የለመልኩም። ቸር ይግጠመን።
Abel Shiferaw's photo.


የተቃዋሚ ድርጅቶች ብዛት ከወያኔ ስልጣን መራዘም ጋር ያለው ግንኙነት

የአገሪቷ ህዝብ ከዳር እሰከ ዳር ባለው አገዛዝ ተገፍግፎ እንዴት ከዚህ አገዛዝ ነፃ እንደሚወጣ ሌት ከቀን በሚማስንበት በዚህ ጊዜ ወያኔ እንዴት የስልጣን ዘመኑ ሊረዝም ቻለ ?
ዋነኛው ምክንያት አንድና ግልፅ የሆነ ነገር ነው የህዝቡን እሮሮ በመተራስ ተገን በማድረግ ስልጣን ላይ በአቋራጭ ቁጭ ሊሉ ያሰቡ ራሳቸውን ግን የተቃዋሚ ድርጅት ነን የሚሉ ቁጥር ስፍር የሌላቸው በጣም ብዙ ጎራዎች በመፈጠራቸው ዋነኛው ምክንያት ሆኖ መቅረብ ይችላል
በሰላማዊ መንገድም ሆነ ትጥቅ አንስተው በረሃ የወረዱት የፖለቲካ ድርጅቶች እውነት ከወያኔ የተሻለ አጀንዳ ያላቸው አይመስሉም ወያኔ ያደረገውን እሱም እየደገሙት ነው እንጂ ስለ አንድ አገር የሚታገሉ አይመሰሉም
እነዚህ ቁጥራቸው እንደ ከዋክብት የበዛ ድርጅቶች ለምን መታረቅንና በአንድ እቅፍ ስር ሆነው መታገሉን ጠሉ ?
ይህም ምክንያቱ ግልፅ ነው ዋናው አላማቸው የስልጣን ጥማትእና የወንበር ጉጉት ሰለሆነ ብቻ ነው
በዚህም የተነሳ የአማራው ነገድ ትንሽ ከተሰባሰበና ከጠነከረ ወደ ስልጣን ወንበሩ አያስደርሰንም በሚል እሳቤ የአማራ መደራጀት በሁሉማ አቅጣጫ ለማክሸፍ ይጥራሉ
መልዕክቱ ለሁሉም የተቃዋሚ ( የወያኔ እድሜ ማራዘሚያዎች) ለሚሉት ጠቅላላ ነው
ምክንያቱም ማንኛውም ለአንድ አገር እየታገልኩ ነው የሚል ድርጅት ሌሎችን እንኳ ጨፍልቆ በስር ማድረግ ቢያቅተው እሱ ተጨፍልቆ አንድ አካል መሆን የማይችልበት ምንም ምክንያት ሊኖረው ባልተገባ ይህ እኮ ነው ለአገር የሚከፈል መስዋዕትነት

እነዚህን ከስር የምትመለከቷቸውን ፎቶዎች ወዳጆቼ ከባህር ዳር ዛሬ ሌሊት ላኩልኝ።( ሄኖክ የሺጥላ )


ስለ ፎቶዎቹ ምንነት ባጭሩ ላስቀምጥ
ተደብዳቢው አማራ
ደብዳቢው ወያኔ ትግሬ
የድብደባው ምክንያት አማራ መሆን
ተጠያቂ የለም
ይህንን ለማስቆም የሚቆም አማራ የለም
ይህንን ኣይቶ ቁጭት ውስጥ ሊገባ የሚችል አማራ የለም
ድብደባው ይቀጥላል ወይ ኣዋ!
ይህንን ፎቶ ለብዙ ደቂቃ ተመለከትኩት ። ኣይኖቼ እንባ ተሞልተው ጥርሴን እያፋጨሁ ደግሜ ደጋግሜ ኣየሁት። ወዳጄ በውስጥ መስመር የፃፈልኝን ኣሳዛኝ ታሪክም ኣነበብኩ ። ማልቀስ ኣልችልም ፥ ኣሁንም ያለቀስኩ ኣይመስለኝም ፥ ግን ፊቴ ላይ እንባ የሚመስል ነገር እንደነበር ኣስታውሳለሁ ። መናደድም ኣልፈልግም ፥ ምክንያቱም ከመናደድ የሚመጣው ሽንፈት እንደሆነም ኣውቃለሁ ። ግን ማሰብ እፈልጋለሁ ፥ ድጋሚ ወደ ራሴ ተመልሼ እውነታውን በጥሞና ማየት እና መረዳት እፈልጋለሁ ።
በቃላችን መሰረት የወዳጄን ምንነትም ሆነ ማንነት ለመናገር ኣሁን ጊዜው ኣይደለም ። ግን ይህ ድብደባ ምን ማለት እንደሆነ ላስረዳ።
ብዙ ለአማራ የሚጮህ ፥ እቆጫለሁ ባይ እኔ ባለሁበት ኣማሪካ ይኖራል ። እጅግ ብዙ ነገር ማድረግ የሚችል ኣቅም ያለው አማራ በየ ሃገሩ እንደሚኖር ኣውቃለሁ ። ትንታግ የሆኑ ፥ በሳል እና ብልህ አማሮች። ግን ደሞ ኣቅማቸውን የማያውቁ ፥ ከስብሰባ እና ጥናታዊ ፅሁፍ ከማቅረብ ውጪ እኔ እስከማውቀው ድረስ ኣንድ እርምጃ ወደፊት መራመድ ያልቻሉ መሆናቸውን ሳስብ ይገርመኛል። ነፃነት እና የኣማሪካ ህግ የተቀላቀለባቸው ተቆጪዎች በመሆናቸው ፥ ይቆጡና ግን መራመድ ይፈራሉ ፥ ይናደዱና ግን መተግበርን ይሰጋሉ ፥ ይበሳጩና ግን መሆንን ይሸሻሉ ። በመሆን እና ባለመሆን መሃከል የቆሙ ተቆርቋሪዎች ስለሆኑ ፥ ወገኖቻቸው ዛሬም ይደበደባሉ ፥ ይታሰራሉ ፥ ይታረዛሉ ፥ ይገደላሉ ። በመራመድ እና በመቆም መሃል ስላሉ ፥ ወገኖቻቸው እያለቁ ነው ። ይህም ፎቶ የነዚህ የኣማራ ልሂቃን ውሳኔ መዘግየት ውጤት ነው ። ሃያ ኣምስት ኣመት ለመራመድ የከበደን ፥ ሃያ ኣምስት ኣመት ቀና ለማለት የከበደን በውሳኔና በፈረንጅ ሃገር ህግ መሃል ስለቆምን ይመስለኛል ።
ኣማሪካንን ሳስብ የህግ ሃገር ነች ። የነፃነት ሃገር ነች ። የሰዎች መብት የሚከበርባት ሃገር ነች ። ይህ ሁሉ እውነት የሚሆነው ግን በመጀመሪያ ከማንም በላይ ለኣማሪካኖች እና ኣማሪካ ውስጥ ለሚኖሩ ህዝቦች ነው ። ኣማሪካ ከኣማሪካ ውጭ ሁል ጊዜ ልክ ነች ብዬ የማስብ እብድ ግን ኣይደለሁም ። ለምሳሌ ፕሬዝዳንት ኦባማ ኢትዮጵያ በሄደ ጊዜ የኢትዮጵያ ምርጫ ዲሞክራሲያዊ ነበር ሲል ተሰምቷል ። ምርጫው ፍትሃዊ ስለነበረ ነው ? ኣይደለም ! ኦባማ መረጃ ስለሌለው ነው ? ኣይደለም ! ዋነኛ ምክንያቱ ለኣማሪካ ልክ የሚሆነው ኣባባል ምርጫው ፍትሃዊ ነው የሚለው ኣባባል ብቻ ስለነበረ ነው ። ኣማሪካ ውስጥ ስኖር የኣማሪካን ህግ ኣክብሬ መኖር እሻለሁ ማለት የኣማሪካ መሪ የኢትዮጵያዊያኖች ስቃይ ቸል ብሎ ሲያልፈው እቀበላለሁ ማለት ኣይደለም ። ኣማሪካን ሃገር መስረቅ ያሳስራል ። ኦባማን መተቸት ግን ኣያሳስርም ። ለነፃነት መታገል ግን ኣያሳስርም ። ቢያሳስርም ታግዬ እታሰራለሁ እንጂ ፈርቼ ዝም ኣልልም ። ከዚ በባሰ እና በተወሳሰበ ደረጃ ባንድ ጎን ለኣማሪካ ህግ ተገዥ ለመሆን ኣስበን ፥ በልላ ጎን ደሞ የህዝባችን ስቃይ ኣስቆጭቶን ፥ ፍርሃት እና ውሳኔ ተጋጭቶብን ስለመቆማችን መካዳችን ይመስለኛል ለውጥ እንዳናመጣ ያደረገን ። የኣማሪካ ህግ ንፁሃን ዜጎች ይገደሉ የሚል ኣይመስለኝም ፥ የሚል ከሆነ ግን ኣላከብረውም ፥ የኣማሪካ ህግ የኣማሪካ መንግስት የተሳሳተ መረጃ እንዲናገር ፍቃድ ኣይሰጠውም፥ የሚሰጠው ከሆነ ግን በእንደዚህ ኣይነቱ ህግ ኣልገዛም ፥ የኣማሪካ ህግ ሰዎች በዘራቸው ተቆጥረው እና ተጠርተው ሲገደሉ በማየታችንን ይህንን ለማስቆም ማንኛውም ኣይነት ትግል ውስጥ ብንገባ እና ጉዳዩን እንደ ኣንድ መንግስት ለመፍታት ከመሞከር ይልቅ ገዳዮቹን እያወደሰ « ምንም የተፈጠረ ነገር የለም !» ቢለኝ ፥ ኣሁንም እንዲህ ኣይነቱን ህግ ኣላከብርም ። እኔ በግሌ ህግ ከማይከበርበት ገነት ፥ በህግ የሚተዳደር ገሃነምን እመርጣለሁና።
ምን ለማለት ነው ፥ ኣማሮች የቱን ትመርጣላችሁ ? እንዲህ ብናደርግ ኣማሪካ እንዲህ ብታደርገንስ የሚለውን ፍርሃት ወይስ የማደርገው ነገር ህጋዊ ነው ፥ ለሰው ልጆች መብት የመቆም ትግል ነው ፥ የነፃነት ጥያቄ ነው በሚለው ላይ ኣምኖ ከፓናል ዲስኩር እና ከረባት ኣስተካክሎ ለማውራት ፥ ከመጨቃጨቅ እና ከመጠቋቆም ይልቅ ህዝባችሁን በቁርጠኝነት ከመከራ ለመታደግ ትግል መታገል ? ህዝቡ ትግል ይፈልጋል ፥ ህዝቡ እናንተን ያያል ፥ የህዝቡ በትረ ሙሴ ለመሆን ግን ፥ በማንነት እና በፍርሃት መሃል ከመቆም ነፃ መውጣት ያስፈልጋል ።
የኣማራ ደም በከንቱ ፈሶ ኣይቀርም !
ሄኖክ የሺጥላ
መቅዲ የአዴሃን ፍሬ's photo.መቅዲ የአዴሃን ፍሬ's photo.
መቅዲ የአዴሃን ፍሬ's photo.መቅዲ የአዴሃን ፍሬ's photo.

ኢትዮጵያ ወደ 30 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ እዳ አለባት ተባለ


ኢሳት ዜና :-ጋዜጠኛ አንዱአለም ሲሳይ ታዋቂውን የኢኮኖሚክ ፕሮፌሰር ዶ/ር አለማየሁ ገዳን ያቀረቡትን ጥናታዊ ጥሁፍ በመጥቀስ እንደዘገበው የኢትዮጵያ መንግስት በውጭ ብድር ላይ ያለው ፍላጎት እየጨመረ መምጣት ፣ በአገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ አደጋ ደቅኑዋል፡፡
ፕ/ር አለማየሁ ጥናታቸውን ያቀረቡት የማህበራዊ ጥናት መድረክ ባዘጋጀው ውይይት ላይ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ከቻይና 17 ቢሊዮን ዶላር፣ ከቱርክ 3 ቢሊዮን ዶላር፣ ከህንድ 1 ቢሊዮን ዶላር፣ ከአለም ባንክ 6 ቢሊዮን ዶላር እንዲሁም በቅርቡ ከአውሮፓ ዩሮ ቦንድ 1 ቢሊዮን 500 ሚሊዮን ዶላር መበደሩዋን የተናገሩት ፕ/ር አለማየሁ፣ በወጪ ንግዱና በገቢ ንግዱ መካከል ያለውን 10 ቢሊዮን ዶላር ክፍተት የሚሞሉት እነ ቻይና ናቸው ብለዋል፡፡
ቻይና ድጋፉዋን በድንገት ነገ ብታቁዋርጥ ምን ይፈጠራል፣ ቻይና ኢትዮ ቴልኮምን ወይም አየር መንገድን ካልሸጣችሁ ወይም የአክሲዮን ድርሻ ካልሰጣችሁኝ ድጋፌን አቆማለሁ ብትል ምን ይፈጠራል; አገሪቱ ሙሉ በሙሉ ሙሉ በሙሉ እንደምትንኮታኮት አረጋግጥላችዋለሁ ይላሉ ፕሮፌሰሩ፡፡
የቻይና የህንድ ወይም የቱርክ ኢንቨስትመንት ስራ በመፍጠር፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር በማምጣት እንዲሁም ምርትን ወደ ውጭ በመላክ የሚገኝን ገቢ በመጨመር በኩል ያለው ጠቀሜታ እጅግ አነስተኛ ነው ያሉት ፐ/ር አለማየሁ፣ በፈረንጆች አቆጣጠር ከ2003 እስከ 2012 93 የቻይና ኩባንያዎች 600 ሚሊዮን ዶላር ኢንቨስት አድርገው፣ ለ69 ሺ ሰዎች በቁዋሚነት እና ለ79 ሺ ሰዎች ጊዚያዊ ስራ ቢፈጥሩም ፣ ቴክኖሎጂን በማሸጋገርና የውጭ ምንዛሬ በማስገኘት በኩል ድርሻቸው እዚህ ግባ የሚባል አይደለም ብለዋል፡፡
ፕ/ር አለማየሁ፣ ከደቡብ ኮሪያውያን በመማር በጊዜ ከዳ መውጣት እንደሚገባ መክረዋል፡፡
ዘገባው የኢትዮጵያን እድገት በተመለከተ የኢህአዴግ ባለስልጣናት የሚሰጡት መግለጫ እርስ በርስ የሚጣረስ መሆኑንም አመልክቱዋል፡፡ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ኢኮኖሚው በ7 በመቶ ሊያድግ ይችላል ሲሉ፣ አማካሪያቸው አቶ አርከበ እቁባይ ደግሞ በ11 በመቶ ያድጋል ብለዋል፡

Sunday, March 27, 2016

ሰበር ዜና በአቡነ ማትያስ ትህዛዝ መምህር ግርማ እዳያስተምሩ ተከለከለ


ብፁህ አቡነ ሳይሮስ ለመንጋው እና ሉተቸገሩት በማሰብ አባታችንን ወንጌልን እና የፈውስ አገልግሎት እንዲሰጡ በሀገረ ስብከታቸው በቅጥር እንዲያገለግሉ ካደረግዋቸው በዋላ በመልካም ፈቃዳቸው እያገለገሉን ሳለ የብፁህ አቡነ ሳይሮስን መልካም ፍቃድን በመሻር የህዝቡ ድህነት አይመለከተኝም በማለት በአባ ማትያስ ቀጥተኛ ትእዛዝ አገልግሎቱ ተቋርጧል ይህንንም አሳፋሪ ዜና ሲስማ የነበረው ህዝብ ለምን ድህነታችንን ጠሉት አባታችንንም ለምን ያንገላቱብናል በማለት በለቅሶና በጩህት እሮሮዋቸውን አሰሙ እንዲሁም ለሚመለከተው አካል ሁሉ ችግራችንን አይቶ ባፋጣኝ መልስ እንዲስጠን በልኡል እግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን በማለት ተናግረዋል።
አስገራሜ የአባቶች እይታዎች ቅዱስ ሲኖዶስ ሳያውቀው ምላተ ጉባዬ ሳያቀው ( ሳይወሰን ) ለመንጋው አለማስብ ለታመመው ለተቸገረው በዊልቸር ለመጣው ለአቅመ ደካማው ባለማስብ በጭካኔ ጠቅላይ ቤተክህነት ምጳፍ ሲገባው አሰራርን ያላማከለ ደብዳቤ ወጥትዋል መምህር ግርማም በአባ ማትያስ የትም እንዳያገለግሉ ተወስኖባቸዋል የህዝብ መዳን ያላስደሰታቸው የህዝቡን ችግር ያልተረዱ እግዚአብሔር ፍርዱን ይስጥ! ህዝቡም በዛሬው እለት ቤተክርስቲያናችን የጋራ እንጂ የአባ ምትያስ ብቻ አይደለችም በማለት እንዲሁም የህዝብ ችግር ያላስደስታቸው የህዝብ መዳን ያላስደስታቸው አባት እያሉ አምፀዋል ለአባታችን በረከት ነው ክርስቶስም በቤተ ክህነት ያሉ ሊቃውንት አባቶች ነው ሲፍተን የኖረው በማለት ተናግረዋል
Memhir Girma Wondimu - መልአከ መንክራት መምህር ግርማ ወንድሙ's photo.
Memhir Girma Wondimu - መልአከ መንክራት መምህር ግርማ ወንድሙ's photo.

የታክሲዎች የስራ ማቆም አድማ በአዲስ አበባ ሊደረግ ነው !


ከወር በፊት አዲሱን የአሽከርካሪዎች ህግ በመቃወም የታክሲ ሹፌሮች ለተከታታይ ሁለት የሥራ ቀናት አገልግሎት በማቆም አድማ መምታታቸውና መንግስትም ከአድማው 12 ሰዓታት ቀደም ብሎ አዲሱን የአሽከርካሪዎች ደንብ ለሶስት ወራት በስራ ላይ ከማዋል እንደሚቆጠብ መግለጹ አይዘነጋም፡፡
በመንገድና ትራንስፖርት ባለሥልጣን መሥሪያ ቤት በኩል ለሶስት ወራት ስራ ላይ እንደማይውልና ውይይት እንደሚደረግበት የተነገረለት ደንብ አሁን ያለምንም ውይይትና ማሻሻያ በተጠናከረ ሁኔታ በሥራ ላይ እየዋለ በመሆኑ አሽከርካሪዎቹ ያቋረጡትን የስራ ማቆም አድማ ለመቀጠል መወሰናቸውን መረጃዎች ጠቁመዋል።
የተወሰኑ ሹፌሮች በአዲሱ ደንብ መሰረት መንጃ ፍቃዳቸውን ተቀምተው ሥራቸውን ለማቆም መገደዳቸውን የተመለከቱ አጋሮቻው ለመጋቢት 19 እና 20 (ነገና ከነገበስቲያ) በድጋሚ የሥራ ማቆም አድማ እንደሚያደርጉ ውስጥ ለውስጥ ተነጋግረው መወሰናቸው ታውቋል።

Saturday, March 26, 2016

የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ስልጣናቸውን ለቀቁ።


ኢሳት ዜና :-በገዛ ፍዳቸው ስልጣናቸውን የለቀቁት አቶ ሀብቴ ፊቻላ በሁለት ወራት ልዩነት ውስጥ የፌዴራል ፍ/ቤቶችን ከለቀቁ ከፍተኛ ባለስልጣናት መካከል አራተኛው ሆነዋል።
ባለፈው የካቲት ወር የመጀመሪያ ሳምንት የጤና እክል ገጥሞኛል በሚል በገዛ ፈቃዳቸው ከሀላፊነታቸው የለቀቁት የፌዴራል ጠ/ ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት እና የህገመንግስት አጣሪ ጉባኤ ቁልፍ ሰው የነበሩት አቶ ተገኔ ጌታነህ ነበሩ።
አቶ ተገኔን ተከትሎ የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ ውብሸት ሽፈራው እንዲሁም የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ፕሬዚደንት የነበሩት አቶ ደሳለኝ በርሄ ስራቸውን ለቀዋል።
አፈጉባኤ አቶ አባዱላ ገመዳ አቶ ሀብቴ ፊቻላ ከመጋቢት 15 ቀን 2003 ዓም ጀምሮ በሀላፊነት ሲያገለግሉ ቆይተው በገዛ ፈቃዳቸው ስራ ለመልቀቅ ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት፣ ከየካቲት 1 ቀን 2008 ዓም ጀምሮ እንዲሰናበቱ የዳኞች አስተዳደር ጉባኤ መወሰኑን ለፓርላማ አባላት አሳውቀዋል። አባ ዱላ ም/ፕሬዚደንቱ የለቀቁበትን ምክንያት ከመግለጽ ተቆጥበዋል።
የአስፈጻሚ አካላት በቀጥታና በተዘዋዋሪ መንገዶች በፍ/ቤቶች ስራ ውስጥ ጣልቃ መግባቱ እየተጠናከረ መምጣቱ ከፍተኛ የኢህዴግ ደጋፊ ናቸው የሚባሉ ዳኞችንና የፍ/ቤት መሪዎችን ሳይቀር ከስራቸው ራሳቸውን እንዲያገሉ ትልቅ ምክንያት ሳይሆን እንደማይቀር ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ወገኖች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

ደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ተቃዋሚዎች የወያኔን ኢንባሲ አስጠነቀቁ ! !


ደቡብ አፍሪካ በተለይም በጆሃንስበርግ የሚኖሩ የወያኔ ተቃዋሚዎች ላይ የትግራዩ ነጻ አዉጭ ቡድን ፕሪቶሪያ በሚገኘዉ ተወካዩ ኢንባሲ አማካኝነት ወንጀል ለመፈጸም ማሴሩን ከዉስጥ የወጣ መረጃ አመላክቷል።
በኢትዮጵያ ዉስጥ ሰባዊ መብታቸዉ ተገፎ በግፍ የሚወዷትን ሐገራቸዉን ጥለዉ በደቡብ አፍሪካ የፖለቲካ ጥገኝነት ተሰጥቷቸዉ የሚኖሩት ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን በተለያየ ወቅትና ግዜ ህወሃት ወያኔ በሐገራችን ዉስጥ የሚፈጽመዉን ኢሰባዊ ድርጊት በመቃወም አደባባይ እየወጡ ድምጻቸዉን የሚያሰሙና የተለያዩ ተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ ደጋፊዎች የሆኑ ስደተኞች ላይ በሙሰኛ ፖሊሶችና በዘራፊዎች የተደገፈ ዉንብድና ለመፈጸም እየተሞከረ መሆኑን ያነጋገርናቸዉ ስደተኞች አረጋግጥዋል፡፤
ለጊዜዉ ስማቸዉን መጥቀስ ያልፈለጉ ነገር ግን ተደጋጋሚ የጥቃት ሙከራ የተደረገባቸዉ አንድ ግለስብ ”
መኪና ሳሽከረክር በተደጋጋሚ ማንነታቸዉን የማላዉቃቸዉ ሰዎች ይከታተሉኛል አንዳንዴ ፖሊሶች ነን ብለዉ ያስቆሙኝና ዛቻና ማስፈራሪያም ይደርሰብኛል ለሚመለከተዉ አካል ሁሉ አመልክቼ እራሴን በመጠበቅ ላይ እገኛለዉ ”
ሲሉ ሌላኛዉ ደግም
” በመኪና ክትትሉ ተጠናክሮ ቀጥሏል የት እንደምንገባ የት እንደምንሄድ የት እንደምንዉል ሁሉ ለማወቅ የሚደረግ አይነት ነገር ነዉ እኛ አንፈራም ሐገራችንን ወስደዉብናል እዚህ ደቡብ አፍሪካ በኛ በተቃዋሚዎች ወገን በሚገኝ አንድ ግለሰብ ላይ አንዳች ነገር ቢከሰት ማን እንደሚጎዳ ያዉቁታል እያንዳንዳቸዉ የወያኔ ሰላዮች እንዲሁም ደጋፊዎች የኢንባሲዉ ሰራተኞች አምባሳደር ሙሉጌታን ጨምሮ ከሰኒ ሳይድ እስከ ሜለን የት እንደሚኖሩና የት እንደሚዉሉ እናዉቃለን መድረስ ያለብን ቦታ ሁሉ ደርሰናል እንደርስማለን አሁንም በስደት ተጠልለን በምንኖርበት ሐገር ላይ እንዲህ ያለ ተልካሻ ዉንብድናቸዉን በመላዉ አለም ላይ የምትገኙ ወገኖቻችን በሙሉ ተገንዝባችሁ በማንኛዉም መልኩ ለሚደርስብን አደጋ ቀጥታ ተጠያቂዉ የትግራይ ነጻ አዉጭ ቡድን ፕሪቶሪያ የሚገኘዉ የኢትዮጵያ ኢንባሲ መሆኑን እያስገነዘብን እራሳችንን ለመከላከል ማንኛዉን አይነት ዝግጅት ያደረግን ምሆኑን እናሳዉቃለን።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ! !
( ጉድሽ ወያኔ )
Gudish Weyane's photo.

ሠማያዊ ፓርቲን ለማፍረስ ዝግጅቶች ተጠናቀዋል።


ሠማያዊ ፓርቲ በሃገራችን ሠላማዊ የፖለቲካ ትግል ውስጥ ተስፋ ከተጣለባቸው ፓርቲዎች ውስጥ በእድሜ አጭር ቢሆንም በውስጡ በያዛቸው ጠንካራ አባላቱ የተነሳ ለአመታት ተኝቶ የነበረውን የሰላማዊ ትግል ከሞተበት አንስቶ መልካም የሚባል በወሬ ሣይሆን በተግባር የተደገፈ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ እያካሄደ ያለ ፓርቲ ነው በዚህ እንቅስቃሴ የተነሳ የፓርቲው አባል የሆነው ሳሙኤል አወቀ ተግድሏል፤ የኢንጂነር ይልቃል እጅ ተሰብሯል፤ የሺዋስ፣ ዮናታን፣ ማቲያስ እና በርካቶች አሁንም በእስር ላይ ይገኛሉ፤ ወረታው ከስራው ተባሯል፤ ወይንሸት ጭንቅላቷ ላይ የመሰንጠቅ አደጋ አጋጥሟታል፤ በርካቶች በድብደባ ምክንያት ሕመምተኛ ሆነዋል፤ ጌታቸው ሽፈራው የሰማያዊ ፓርቲ ጋዜጣ ላይ ትፅፋለህ ተብሎ ታስሯል ይህ ሁሉ ምንም ማለት አይደለም አንድ ታጋይ ትግል ውስጥ ሲገባ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት የደረሰባቸው ጉዳቶች ሊያጋጥሙት እንደሚችሉ እሙን ነው ሆኖም አምነሀቸው አብረህ ትግል ውስጥ ያሉ ጓዶችህ ለኢህአዴግ አድረው ፓርቲህን ሲያፈርሱት ስታይ ያማል።
ነገሩ እንዲህ ነው ኢህአዴግ ሠማያዊ ፓርቲን ለማፍረስ የፓርቲው አባላትን መጠቀሚያ ለማድረግ ሲሯሯጥ መቆየቱ አይዘነጋም ታድያ ነገሮች ተመቻችተው ከሰሞኑ የሰማያዊ ፓርቲ ኦዲተሮች የፓርቲውን ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃልን ጨምሮ ወረታው፣ ወይንሸትን እና ስለሺን በገንዘብ ማጭበርበር በመክሰስ ከፓርቲው ለማገድ ውስጥ ለውስጥ ተስማምተው የጨረሱ ሲሆን የኢዲተሮቹን ውሣኔ እሁድ ይፋ የሚያወጡት ሲሆን ከዚሁ ጋር ተያይዞ ጠቅላላ ጉባኤው የተጠቀሱትን አመራሮች ለማባረር ውስጥ ለውስጥ እየተሠራ ይገኛል የሚገርመው ኦዲተሮቹ ያሳለፍነው እሁድ ከሁለት የገዢው ፓርቲዎች የደህንነት ሐይሎች ጋር በመሆን እነይልቃልን እንዴት ማባረር እንዳለባቸው ተስማምተው ጨርሰዋል። እነዚህ ሰዎች ከዚህ ቀደም ጠንካሮቹን ዮናታን፣ እያስፔድንና ዮናስን ከፓርቲው ማባረራቸው አይረሳም። እኔ በግሌ ሠማያዊ ፓርቲን የማውቀው አሁን ይባረራሉ በተባሉት ሀገር ወዳድ ግለሰቦች እና በተባረሩት ወጣቶች ምክንያት ነው። እነዚህ ድንቅ ወጣቶች ሰማያዊ ውስጥ ባይኖሩ ሰማያዊ ፓርቲ በሕይወት መኖሩንም እኔንጃ ስለሆነም ሁላችንም በሰላማዊ ትግል ኢህአዴግን በማስወገድ ዴሞክራሲያዊ ስርአት መገንባት እንችላለን ብለን የምናስብ ኢትዮጵያውያን በሙሉ ከእነኢንጂነር ይልቃል ጎን በመቆም ሰማያዊ ፓርቲን ከመፍረስ እናድነው።
በቀጣይ ሰማያዊ ፓርቲን ለማፍረስ እየሰሩ ያሉ ግለሰቦችን ማንነት ከመረጃ ጋር የማቀርብ መሆኔን ከወዲሁ እገልፃለሁ።

Wednesday, March 23, 2016

በማኅበረ ቅዱሳን የተዘጋጀው ዐውደ ርእይ ታገደ


ገና ከማለዳ እናት ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ለማገልገል ዓላማ ሰንቆ ወገቡን ታጥቆ የተቋቋመው ማኅበረ ቅዱሳን ከጥቂት ዓመታት ወዲህ የተቀናጀ በሚመስል ጥቃት እየተገፋ ይገኛል፡፡ ሰሞኑን እንደ ሽውታ ሰምተናት ግን አልፋ የሄደች የምትመስል ዜና ነበረች፡፡ የእርሷ ዜና አንዱ ግልባጭ ይኸው ዛሬ በድራማ መልክ ብቅ ብሎ ከዐውደ ርእዩ ይልቅ ገዝፎ ይታያል፡፡
ዛሬ በቁጥር ኤማ/1089-520-21/08 በቀን 14 መጋቢት 2008 ከኤግዚቢሽን ማዕከልና የገበያ ልማት ድርጅት የወጣው ደብዳቤ እንዲህ ይነበባል፡፡
በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ለማኅበረ ቅዱሳን ጽ/ቤት
ጉዳዩ፣ በነገው ዕለት የሚከፈተው ኤግዚቢሽን መሠረዙን ስለማሳወቅ
በኢግዚቢሽን ማዕከልና በማኅበረ ቅዱሳን ጽ/ቤት መካከል በተፈጸመው ውለታ መሠረት የጽ/ቤቱ ኤግዚቢሽን በነገው ዕለት እንደሚከፈት ይታወቅ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ከፈቃድ ጋር በተያያዘ ያልተሟላ በመኾኑ በታሰበው መልኩ ዝግጅቱን ለማካሄድ አስቸጋሪ ኾኖ ተገኝቷል፡፡ ለተፈጠረው ክፍተትም ኤግዚቢሽን ማዕከሉ አዘጋጆቹንና ተሳታፊዎችን ከፍተኛ ይቅርታ ይጠይቃል፡፡
በቀጣይ አስፈላጊ የኾኑ ፈቃዶች ሁሉ ሲሟሉ ተለዋጭ ፕሮግራም በማዘጋጀት አስፈላጊውን አገልግሎት ሁሉ እንደምንሰጥም በታላቅ አክብሮት እንገልጻለን፡፡
ከሰላምታ ጋር
(የማይነበብ ፊርማ)
ታምራት አድማስ
ዋና ሥራ አስኪያጅ
ማናኛውም አካል ውለታ ከመፈጸሙ አስቀድሞ የተዋዋዩን አካል ሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጥ ግዴታው ነው፡፡ በዚህ ደረጃ በርካታ ውለታ በመፈጸም የሚታወቀው የዐውደ ርእይ ማዕከል ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር ውል ሲዋዋል ማረጋገጥ የሚገባውን ሁሉ ሳያረጋግጥ ነበረ ለማለት አይቻልም፡፡ አሁን ዛሬ በአሥራ አንደኛው ሰዓት በሕዝብ ላይ በደልና ግፍ የሚፈጽም ማስታወቂያ ማውጣት ምን ያኸል አሳዛኝ እንደኾነ መገመት አይከብድም፡፡
ከበርካታ አውራኅ ልፋት እና ድካም በኋላ፣ የስንት ወንድሞች እና እኅቶች እንቅልፍ ለምኔ ተጋድሎ በኋላ፣ ስንት እና ስንት ወጪ ከወጣ በኋላ፣ በርካታ የመግቢያ ትኬቶች ለተመልካቾች እንዲሠራጩ ከተደረገ በኋላ ሊከፈት ሰዓታት ብቻ የቀሩትን ዐውደ ርእይ በአስራ አንደኛው ሰዓት ሠርዣለሁ ማለት ከአጥንት ሥር ዘልቆ የሚሰማ ሕማም ነው፡፡ ይኽንን ታላቅ ዐውደ ርእይ ለማካሄድ ማኅበረ ቅዱሳንን እና የቤተ ክርስቲያን አለኝታ የኾኑ ምእመናን የከፈሉት መሥዋዕትነት እንዲህ በአንድ ብጣሽ ወረቀት ይቅርታ እንጠይቃለን በማለት ብቻ እንደዋዛ የሚሸኝ አይደለም፡፡
ከውሣኔው በስተጀርባ እነማን እንዳሉ እርግጠኛ ለመኾን ብዙ ልፋትን አይጠይቅ ይኾናል፡፡ የዚህ ውሣኔ መራራ ገጽታ ግን ከተባዳዮቹ ልቡና በምንም ላጲስ እንደማይጠፋ ሊታወቅ ይገባዋል፡፡ ብዙ የማባበያ ቃላት ሊሠነዘሩም ይችሉ ይኾናል፡፡ ዓላማን በማባበያ ማሰናከል ግን ፈጽሞ ተቀባይነት የለውም፡፡ ትናንት በኢቤኤስ ይተላለፍ የነበረውን መንፈሳዊ መርሐግብር እንዲታገድ ተደረገ፡፡ ዛሬ ደግሞ አደባባይ ላይ የወጣው ዐውደ ርእይ ታገደ፡፡ ዝቅ ብሎ ከባት የተጀመረው ወደ አናት እያደገ መምጣቱ የመጨረሻ ግቡን ያመላክታል፡፡ እናስ መጨረሻው ወዴት ነው?
ዐውደ ርእዩ የቤተ ክርስቲያን ልጆች ድርሻቸውን ዐውቀው በተሰጣቸው ጸጋ ቤተ ክርስቲያንን እንዲያገለግሉ የማነቃቃት ዓላማ ነበረው፡፡ ይኽም አንዱ የቤተ ክርስቲያንን ሥራ ለማገዝ እንጂ ሌላ ቅንጣት ታክል ጉዳይ የለበትም፡፡ የቴሌቪዥን መርሐ ግብሩም ቃለ ወንጌልን ለማሠራጨት እንጂ ሌላ አጀንዳ አልነበረውም፡፡
የማይታሠረውን ቃለ እግዚአብሔር ለማሠር መሞከር አዲስ ምንፍቅና ይኾናል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንደነገረን “የእግዚአብሔር ቃል ግን አይታሠርም” ፪ጢሞ ፪፥፱። ለዚህ ደግሞ ምንም ዓይነት ቦታ የለንም፡፡ በዚህ ቢታገድ እግዚአብሔር በወጀብ እና በዐውሎ ነፋስ ውስጥ መንገድ አለው እና በሚከፍትበት ይከፍተዋል፡፡ ቅስማችንን ለመስበር ታስቦ ከኾነ ያበረታናል እንጂ አንገታችንን እንደማንደፋ እልፍ ጊዜ እልፍ ልንነግራችሁ እንወዳለን፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ “ስደክም ያን ጊዜ ኃይለኛ ነኝ” ያለውን እያሰብን ከድካም ወደብርታት ከምንሸጋገር በቀር ከዓላማችን ዝንፍ አንልም፡፡ ፪ቆሮ ፲፪፥፲።
የሚኾነውን ባናውቅም የታሰበውን እናውቃለንና አንደነግጥም፡፡ አሁንም ግን ሥራችንን በቅንነት እንቀጥላለን፡፡ በዚህ ጉዳይ ሀዘን የሚሰማችሁ ወንድሞች እና እኅቶች በማዘን ሰይጣንን እና ተልእኮ አስፈጻሚውን ከማስደሰት ይልቅ በተሻለ ሥራ እና መንፈሳዊ ቆራጥነት ወደፊት እንጋደል፡፡ ከዚህም የሚበልጥ መከራ ቢመጣ ወደ ኋላ አንመለስምና፡፡ እንባችንን የሚያብሰውን እግዚአብሔርን ተስፋ በማድረግ እንደበረታን እንቁም፡፡

የፌዴራል ፖሊስ ተጠሪነቱ ለጠ/ሚኒስትሩ እንዲሆን የሚደነግግ አዋጅ በዛሬው ዕለት ለፓርላማ ቀረበ፡፡


ኢሳት ዜና :- በአሁኑ ወቅት ፌዴራል ፖሊስ ተጠሪነቱ ለፌዴራልና አርብቶአደር ልማት ሚ/ር ሲሆን አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ፖሊስን ለአንድ አስፈጻሚ መ/ቤት ብቻ ተጠሪ አድርጎ መቀጠል የአሰራር ክፍተት ይፈጥራል ተብሎ በመታሰቡ ወደፊት በጥናት ላይ ተመስርቶ እስኪወሰን የፌዴራል ፖሊስ ተጠሪነት ለጠ/ሚኒስትሩ እንዲሆን በረቂቅ አዋጁ ተደንግጎአል፡፡ በመሆኑም አሁን በስራ ላይ ያለው የፌዴራል ፖሊስ ኮምሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 720/2004 ተጠሪነት የሚመለከተው ድንጋጌ ለጠ/ሚኒስትሩ በሚል እንዲሻሻል ቀርቦአል፡፡ የብአዴኑ ነባር ታጋይ አቶ ካሳ ተክለብርሃን የፌደራልና አርብቶ አደር ልማት ሚኒስትር ሆነው በተሾሙ በአጭር ጊዜ ውስጥ የፌደራል ፖሊስ ተጠሪነት እንዲለወጥ መደረጉ፣ የህወሃት እጅ አለበት የሚሉና በህወሃትና ብአዴን መካከል ያለው ልዩነት እየሰፋ መምጣቱን አመላካች ነው በማለት አስተያየቶች እየቀረቡ ነው።በኦሮሚያና በአንዳንድ የሀገሪቱ አካባቢዎች በተደጋጋሚ እየተነሱ ያሉትን ሕዝባዊ ተቃውሞዎች ለመቆጣጠር አመቺ ሁኔታን ከመፍጠር ጋር የተያያዘ የፖለቲካ ውሳኔ ሊሆን ይችላል የሚሉ አስተያየቶች መሰንዘራቸውን ዘጋቢያችን ገልጿል። የፌደራል ፖሊስ መስሪያ ቤት በአብዛኛው በህወሃት ታጋዮች የተሞላ ነው። በሌላ በኩል በፌዴራል የስነምግባርና የጸረ ሙስና ኮምሽን ፣በገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ፣በሸማቶችና በፍትሕ ሚ/ር ስር ተበታትኖ ስራውን ያከናውን የነበረውን የአቃቤ ህግ መ/ቤት በአንድ ሚኒስቴር መ/ቤት በማደራጀት ሁሉንም ወጥነት ባለው መልኩ ለማገልገል ያሰችላል የተባለ ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማው ቀርቦአል፡፡ አዲሱ ሚኒስቴር መ/ቤት የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ በመባል የሚታወቅ ሲሆን የቀረበው የማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ በጸረ ሙስና ኮምሽን፣ በገቢዎችና ጉምሩክ፣ በሸማቶችና በፍትህ ሚኒስቴር ይቀርቡ የነበሩ ክስችን እንዲሁም በፍትሀብሔር ጉዳይ መንግስት በመወከል በሀገር ውስጥ በዓለም አቀፍ የፍትህ መድረኮች ለመንቀሳቀስ ያሰችለዋል ተብሎአል፡፡የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ተጠሪነቱ ለጠ/ሚኒስትሩ እና ለሚኒስትሮች ም/ቤት በጣምራ መሆኑንም ረቂቅ አዋጁ ያሳያል፡፡ የፌዴራል ማረሚያ ቤትም ከፌዴራልና አርብቶአደር ልማት ጉዳዮች ሚ/ር ስር ወጥቶ በፌዴራል ጠ/አቃቤ ህግ ስር እንዲሆንም በዚህ ረቂቅ አዋጅ ተደንግጎአል፡፡ ይህንንም ተከትሎ የአስፈጻሚ አካላትን ለመደንገግ የወጣው አዋጅ ማሻሻያ ቀርቦበታል፡፡ አዋጆቹ ለዝርዝር እይታ ለሚመለከታቸው ቋሚ ኮምቴዎች ተመርተዋል፡፡

ሰበር መረጃ የኮንሶ ህዝብ ለነፃነቱ የሚያደርገው ትግል ከፍተኛ ፍርሃት ውስት የከተታቸው የህወሓት ቅጥረኞች አስቸኳይ ስብሰባ ጠሩ


የኮንሶ ህዝብ ለነፃነቱና ለዲሞክራሲ የሚያደርገው ትግል ከፍተኛ ፍርሃት ውስት የከተታቸው የህወሓት ቅጥረኞች የሆኑት የደህዴን ካድሬዎች በዛሬው ዕለት አስቸኳይ ስብሰባ ጠርተው ነበር። የኮንሶ ህዝብ አስራ ሁለት የጎሳ መሪዎችን ጨምሮ ከ’60000 በላይ (በግምት ከበፊቱ የበለጠ) ህዝብ የተሳተፈበት የዛሬው ህዝባዊ ስብሰባ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለኮሚሽነር ለማ ገዙማ ማንሳቱን ከኮንሶ ያገነኛቸው መረጃዎች ያመላክታሉ። ከ’#KonsoProtests ጋር በተያያዘ :
➤ የታሰሩ ግለሰቦች በአስቸኳይ እንዲፈቱ
➤ የቆሰሉትና የተደበደቡትን በአስቸኳይ እንዲታከሙ
➤ ለሞቱት ግለሰቦች ተገቢው ካሳ እንዲከፈላቸው
➤ ልዩ ሀይል የተባለው ሰው በላ ሰራዊት ከኮንሶ በአስቸኳይ እንዲወጣ
➤ ፍስሀ ጋረደው ፡ ዳዊት ኩሰያ፡ ኩሴ ፒሴ፡ ጋሻው፤ ኩስያ እና ተባባርዎቻቸው ለፍርድ እንዲቀርቡ
➤ የኮንሶ ህዝብ ዋናና መሰረታዊ የዲሞክራሲ ጥያቄ ፤ ልዩ ወረዳ ሳይሆን በዞን ደረጃ ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ ሙሉ በሙሉ እንዲመለስ
የኮንሶ ህዝብ ከላይ የተጠቀሱት የነፃነት ፣ የፍትህ ፣ የእኩልነትና የዲሞክራሲ ጥያቄዎች እስካተመለሱት ድረስ በማንናቸውም ማማለያዎች እንደማይታለልና የአንባገነን አገዛዙን ጥቃቶችን ፈርቶ ከትግሉ ወደ ኋላ እንደማያፈገፍግ በስብሰባው ላይ አሳውቋል።
ድል ለኮንሶ ህዝብ ! ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!

በኦሮሚያ 300 የሚሆኑ ባለሥልጣናት ከሥራ ተባረሩ


በኦሮሚያ ክልል ከሚካሄደዉ ሕዝባዊ ተቃዉሞ ጋር በተያያዘ ከሃላፊነታቸዉ የተነሱ በተለያየ ደረጃ ላይ የሚገኙ ባለስልጣናት ቁጥር 300 መድረሱን ምክትል ርእስ መስተዳደሩ አስታወቁ።
በክልሉ ከተካሄደዉ ሕዝባዊ ተቃዉሞ ጋር በተያያዘ ሃላፊነታቸዉን በአግባቡ አልተወጡም በተባሉ አመራሮች ላይ የሚወሰደዉ እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ርእሰ መስተዳደሩ አቶ እሼቱ ደሴ ተናግረዋል።
እስክንድር ፍሬዉ ከመንግስት መገናኛ ብዙሃን ያገኘዉን አድርሶናል፥ የድምጽ ፋይሉን በመጫና ያድምጡ።

Tuesday, March 22, 2016

ሰበር መረጃ . . . ከዉስጥ አርበኞች የተሰጠ ማስጠንቀቂያ…


የትግራይ ነጻ አዉጪ ቡድን መጠቀሚያና መሳሪያ በመሆን እያገለገሉ የሚገኙት አንዳንድ የእምነት ተቋማትንና መሪዎችን እንዲሁም ሽማግሌዎችን መሰረት ባደረገ መልኩ በዳንሻ ህዝብ ላይ እርቅ በሚል ሰበብ ግፍ እየተሰራ መሆኑን ደርሰንበታል!
ግፍም እየተፈጸመባቸዉ የሚገኙ አማራ ኢትዮጵያዊያንን ጎብኝተናል!
ይህ እንዲሆን ምክንያታዊ መጠቀሚያ የሆናችሁ ግለሰቦች እራሳችሁን እንድትፈትሹ እያስጠነቀቅን!! 
ከእንግዲህ የወልቃይት ጠገዴን አማራ የማንነት ጉዳይ እና ተዛማጅ የመብት ጥያቄዎችን ያነሱ ወገኖቻችንን በእርቅም ሆነ በማንኛዉም ሰበብ በማታለል ለጎጠኛዉ የትግራይ ሽፍታ አሳልፋችሁ የምትሰጡ የሐይማኖት ተቋማት አባቶች የሐገር ሽማግሌ ተብዬዎች ከእኩይ ተግባራችሁ እንድትታቀቡ እያሳሰብን።
በታገቱና በተገደሉብን ወገኖቻችን እጥፍ ምላሽ ከመስጠት አንጻር እንዲሁም ሆን ብለዉ የዳንሻ ህዝብ ላይ አፈናዉ እና ግድያዉ እንዲጠናከር ባደረጉ እና በተዛማጅ ከወያኔ ጋር ንክኪ ባላቸው ግለሰቦች ላይ እርምጃ መዉሰድ ጀምረናል ይህም ተጠናክሮ ይቀጥላል !!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ! !
( ጉድሽ ወያኔ )

በአሁኑ ስአት የጠገዴ ህዝብ ሰላማዊ ሰልፍ እያደረገ ነዉ


ህገወጦች ከድርጊታቸዉ ይታቀቡ የአማራ ብሄር ጥያቀየችንና ደንበራችን ይከበር እያሉ ነዉ
ድል ለወልቃይት ጠገዴ አማራወች ዉርደት ለጨቆኙ የትግራይ ወራሪ ሃይል !!
በተመሳሳይ ዜና የትግራ መስተዳደር ከባድ መሳሪያወች ወደዳንሻ እያስገባ ስለሆነ
ህዝቡ ስልታዊ መከላከል እንዲያደረግ መንግስት ድርጂቱን ተከታትሎ
እርምጃ በትግራይ አስተዳደር ሰላማዊ ዜጎችን ማሰርና ማፈናቀል እንዲያቆም
መአቀብ ይደረግበት !!
ሞላ ህዝባችን ከትግራይ የሚያስገቡትን መንገዶች በጥንቃቄ ክትትል እንዲያደረውግ
ድል ለወልቃይት ጠገዴ ህዝብ !!

የዩናይትድ ስቴትስ አራት የሕዝብ እንደራሴዎች ለሃገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጃን ኬሪ ኦሮምያ ክልል ውስጥ ስለተፈጠረው ሁኔታ ማብራራያ እንዲሰጧቸው ጠየቁ።


የሕግ መወሰኛ ምክር ቤቱ አባላት ጄፍሬ መርክሌ እና ራን ዋይደን፤ እንዲሁም የሕግ መምሪያው አባላት ኧርል ብላሚኖር እና ሱዛን ባናሚቺ፤ ዓርብ፣ march 17/2016 ዓ.ም ፈርመው ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በላኩት ደብዳቤ ላይ ኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ ጠቃሚ አጋርና ከውጭ እርዳታዋም ግንባር ቀደም ተቀባዮች አንዷ መሆኗን አመልክተዋል።
የዩናይትድ ስቴትስ የሕዝብ እንደራሴዎች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጃን ኬሪ ስለኦሮምያ ሪፖርት እንዲያቀርቡላቸው የጠየቁበት ደብዳቤየዩናይትድ ስቴትስ የሕዝብ እንደራሴዎች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጃን ኬሪ ስለኦሮምያ ሪፖርት እንዲያቀርቡላቸው የጠየቁበት ደብዳቤ
ይሁን እንጂ መንግሥታቸው የሚሰጠው ገንዘብ የዩናይትድ ስቴትስን ዘላቂ ጥቅሞችና እሴቶቿን የሚጎዱ አለመሆናቸውን ማረጋገጥ እንደሚገባ እንደራሴዎቹ አሳስበዋል።
በመሆኑም በመጭዎቹ ዘጠና ቀናት ውስጥ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ኦሮምያ ክልል ውስጥ ለተነሣው ተቃውሞ የሃገሪቱ የፀጥታ ኃይሎች በሰጡት ምላሽ በሰው ላይ የደረሱ ጉዳቶችን፣ የዘፈቀደ እሥራቶችን፣ የሰብዓዊ መብቶች ረገጣዎችን ዝርዝር እንዲያቀርቡላቸው እንደራሴዎቹ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩን ጠይቀዋል።
ከተቻለም ለተፈፀሙት የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች ተጠያቂ ነው የሚባል ሰው ወይም ሰዎችን ማንነት እንዲለዩና በሰላማዊ ተቃዋሚዎች ላይ ወንጀሎችን የፈፀሙ ሰዎችን ሕግ ፊት ለማቅረብ መንግሥቱ የወሰዳቸው እርምጃዎች ካሉም እንዲያሳውቋቸው እንደራሴዎቹ አክለው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩን አሳስበዋል።

የብሪታኒያ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማት ለኢትዮጵያ የሚሰጠው የጸጥታና የደህንነት ድጋፍ እንዲቆም ጠየቁ


የብሪታኒያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሩን በቅርቡ በኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ጉብኝት ተከትሎ የሃገሪቱ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማት በብሪታኒያ ለኢትዮጵያ የምትሰጠው የጸጥታና የደህንነት ድጋፍ እንዲቆም አሳሰቡ።
ሃገሪቱ ዜጋዋ የሆኑት አቶ አንዳርጋቸው በእስር ላይ እያሉ በየአመቱ ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ ለጸጥታና ደህንነት ስልጠናዎች ድጋፍ በማድረግ ላይ መሆኗን ጋዜጣው የተለያዩ መረጃዎችን ዋቢ በማድረግ ባቀረበው ዘገባ አስፍሯል።
ብሪታኒያ ለኢትዮጵያ የምትሰጠው ይኸው ድጋፍ በሃገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩልና በኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስቴር ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኝ ሲሆን፣ አዲሱን ፕሮግራም ባለፈው አመት መጀመሩም ታውቋል።

የብሪታኒያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ቢያረጋግጥም ዝርዝር መረጃን ከመስጠት መቆጠቡን ኢንዲፔንደንት ጋዜጣ በዘገባው አመልክቷል።
ይሁንና፣ የብሪታኒያ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶችና የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ቤተሰቦች እንዲሁም ሌሎች ታዋቂ ግለሰቦች ብሪታኒያ የምትሰጠውን ድጋፍ እንድታቋርጥ የሚጠይቅ ዘመቻ መክፈታቸውን ከጋዜጣው ሪፖርት ለመረዳት ተችሏል።
ሪፕሪቭ የተሰኘው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ብሪታኒያ ቀጥላ ያለው ድጋፍ አሳሳቢ የሆነ ጥያቄ አስነስቶ እንደሚገኝ ገልጿል።
የስቃይ ሰለባ በሆኑ ሰዎች ዙሪያ የሚሰራው የሬድሬስ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት የህግ አማካሪ የሆኑት ኬቪን ላኡ በበኩላቸው ብሪታኒያ የአቶ አንዳርጋቸው መፈታትን ከማሳሰቧ ይልቅ ለኢትዮጵያ የጸጥታ አገልግሎት ድጋፍ መቀጠሏ ፍትሃዊ አለመሆኑን ለኢንዲፔንደንት ጋዜጣ አስታውቀዋል።
የፓርላማ አባላትም በቅርቡ በኢትዮጵያ ጉብኝት ለሚያደርጉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሩን ደብዳቤን በመጻፍ አቶ አንዳርጋቸው ያለምንም ቅደመ-ሁኔታ እንዲፈቱ ግፊትን እንዲያደርጉ ጥያቄ ማቅረባቸውም ታውቋል።
ከአንድ ሳምንት በኋላ ወደ አዲስ አበባ የሚጓዙት ካሜሮን በሁለቱ ሃገራት መካከል ያሉ የጸጥታና የደህንነት ትብብሮችን በማንሳት ሰፊ ውይይትን እንደሚያካሄዱ የሚጠበቅ ሲሆን፣ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጉዳይም በሁለቱ ወገኖች መካከል አጀንዳ ሆኖ እንደሚነሳም ይጠበቃል።

Monday, March 21, 2016

የህወሃት ወታደራዊ ሰላዮች ወደ ኤርትራ ዘልቀው ሊገቡ ሲሞክሩ መረሸናቸው ተነገረ


በኤርትራ እና በዙሪያዋ ለስለላ ስራ እንዲሁም ለቃኘዉ የዉጊያ ስምሪት እንዲጠቅሙ ተብለዉ የተሰማሩ የህወሃት ወታደራዊ መረጃ ሰራተኞች እየታደኑ መታፈናቸዉን የሚያረጋግጡ መረጃዎች አፈትልከዉ ወጥተዋል።
በተልይም ሞላ አስገዶም ከኤርትራ ወደ ህዉሃት ከፈረጠጠ ወዲህ በኤርትራ እና በነጻነት ሐይሎች የደህንነት ክትትል ምክንያት በህወሃት መረጃ ሰንሰለቱ ስር የነበሩ ሰላዮች በሙሉ መረሸናቸዉን የወያኔ ወታደራዊ ደህንነት በማረጋገጥ ለመከላከያ ሚኒስቴሩ እና ለሚመለከታቸዉ የደህንነት ክንፎች አሳዉቋል።
ወታደራዊ ደህንነቱ ሌሎች በተለያየ ምክንያት ወደ ኤርትራ ሰርገዉ እንዲገቡ የተደረጉ የስለላ ሰዎች በተለይም የአርበኞች ግንቦት ሰባትን አጠቃላይ ፖለቲካዊና መሰረታዊ የአደረጃጀት እርከን፣ እንዲሁም ወታደራዊ ኮርሶችና ዲስፕሊኖችን፣ ስልታዊ መዋቅርንና አቀማመጥን ለመሰለል እንዲረዱ ከተሰማሩ ግለሰቦች ዉስጥ አንዳቸዉም የት እንደገቡ ለማወቅ ያለመቻሉን ምንጮቻችን ጠቅስዋል።
ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ወደ ዉጊያዉ አምድ ከተቀላቀሉ ወዲህ ከኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ በፍጥነት እየአሰገሰ በመምጣት ላይ የሚገኘዉን የለወጥ ነዉጥ መቛቋም የተሳነዉ የትግራይ ነጻ አዉጭዉ ቡድን ወታደራዊ ደህንነት የአርበኞች ግንቦት 7ን እና የጥምር ሐይሎችን እንቅስቃሴ ማወቅ እንኳ እንደተሳነዉ የደህንነት ስልቱም መበለጡን በተለይም የተሳሳቱ መረጃዎች እየደረሱት ላም ባልዋለበት!! ሲቅበዘበዝ የነጻነት ሐይሎቹ ሽምቅ ዉጊያ ሰለባ እየሆነ መምጣቱን ለተደራቢ አዛዡ ሉተናንት ጄኔራል ዮሃንስ ገብረመስቀል በማቅረብ የተወያየ ሲሆን።
ስርአቱ አሁን ባጋጠመዉ የመረጃ መዳፈን ምክንያት ስጋት ላይ ስለወደቀ ድንገተኛና የተጠናከረ ተመላላሽ ጥቃት እንዲሰነዘር እንዲሁም በጎንደር ዙሪያ የሚገኘዉ የመከላከያ ሰራዊት በእጅጉ እንዲጠናከር ለማድረግ ከሸዋሮቢት የመጡ አዲስ ወታደሮች ወደ ክፍለ ጦሮች እንዲካተቱ እና አጥቂዉ የግንባር ሐይል ለመመሪያ ዝግጁ እንዲሆን በአመራሮች ቢወሰንም ከተራ ወታደር አንስቶ እስከ ከፍተኛ አመራሮች መመሪያ ለመቀበል ስጋት ላይ ናቸዉ።
ይህን መረጃ አያይዘዉ የላኩልን ምንጮች በኤርትራ የሚገኙ የነጻነት ሐይሎች ከምንዜዉም በበለጠ በንቃትና በመጠናከር እየወደቀ የሚገኘዉን ባለ ሁለት እግር ዝሆን ለመጣል እንዲዘጋጁ መዘናጋትን ፈጽመዉ እንዳያስቡት አስጠንቅቀዋል።
ከአራት እግሮቹ ሁለት የፊት እግሮቹን የቆሰለ ዝሆን ለመጣል ዝሆን መሆን አያስፈልግም።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ! !
( ጉድሽ ወያኔ )

የወልቃይት ታጣቂ ኃይሎች በጠብመንጃ አጥሮ በመዝጋት ተከዜን ተሻግሮ ከትግራይ ወደ ወልቃይት የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን በመግታት ላይ ነው፡፡


ትግራይና ወልቃይትን የሚያገናኙ ጎዳናዎች መዘጋታቸው ተነገረ፤ ፌደራል ፖሊስና የትግራይ ልዩ ኃይል የወልቃይትን ምድር ወሮታል፡፡
የወልቃይት ህዝብ ያነሳውን የአማራ ማንነት ጥያቄ ለመቀልበስ ህወሓት አጠናክሮ የጀመረውን በህብረተሰቡ ዘንድ ተቅባይነት ያላቸውን ግለሰቦች አፍኖ ድብዛቸውን የማጥፋት ተግባር
በመቃወም የወልቃይት ህዝብ እርምጃ መውሰድ ጀምሯል፡፡ በመሆኑም ዋና፣ ዋና መንገዶችን በጠብመንጃ አጥሮ በመዝጋት ተከዜን ተሻግሮ ከትግራይ ወደ ወልቃይት የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን በመግታት ላይ ነው፡፡
የወልቃይት ታጣቂ ኃይሎች ከወለቃይትና ትግራይ ወሰን ላይ በመመሸግ በእግርም ወደ ወልቃይት የሚጓዙ ሰዎችን መታወቂያ መጠየቅ ጀምረዋል፡፡
በአዲ ጎሹ በኩል ከትግራይ ወደ ወልቃይት የሚያስገባው አውራ ጎዳና እና እንዲሁም በተጨማሪ ከሁመራ ወደ ጎንደር የሚሄደው መንገድ በወልቃይት ታጣቂ ኃይሎች ቁጥጥር ስር ውለው
ተዘግተዋል፡፡
ትናንትና ጠዋት ከወደ ትግራይ የተነሳች መኪና “ካዛ” ላይ መሽገው በነበሩት የወልቃይት ታጣቂዎች ተኩስ ተከፍቶባታል፡፡ ህወሓት ከትናንት ወዲያ አፍኖ የወሰዳቸውየወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ አስተባባሪ ኮሚቴ አባል የሆኑት “አቶ ሊላይ ብርሃነ” ደብዛ መጥፋትና “ሩዋልሚ” ከተባለ ወንዝ ዳር አንድ ማንነቱ
ሊለይ ያልቻለ አስከሬን መገኘቱ የህዝቡን ቁጣ እንዳባባሰው ተገልጿል፡፡ እናም ህወሓት ከፍተኛ ቁጥር ያለው ፌደራል ፖሊስና የትግራይ ክልል ልዩ
ኃይል ጦር በወልቃይት ምድር አሰራጭቶ በተለይም ደግሞ ዳንሻ በሰራዊት ተከባ ትገኛለች፡፡ የወልቃይት ህዝብና ልዩ ኃይሎች በመዋጋት ላይ ናቸው፡፡

Saturday, March 19, 2016

በኦሮሚያ በየቦታው የአጋዚ ጦር አባላት እየተገደሉ እየተገኙ ነው


በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የአጋዚ ጦር አባላት እየተገደሉ እየተገኙ እንደሚገኙ ከተለያዩ ሥፍራዎች ለዘ-ሐበሻ የሚደርሱ መረጃዎች አመለከቱ:: ታክስ ሰብሳቢዎችም እንዲሁ በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ቦታዎች ተዘዋውረው ግብር ለመሰብሰብ ሲሞክሩ በሚደርስባቸው ጥቃት የተነሳ ሥራ መስራት እንደተቸገሩም ለማወቅ ተቻለ::
የዘ-ሐበሻ የመረጃ ምንጮች እንዳመለከቱት በ አርሲ በባሌ በምስራቅ እና ም ዕራብ ሐረርጌ, በምስራቅ ሸዋ; በ ም ዕራብ ሸዋ የተለያዩ ቦታዎች በየቀኑ የአጋዚ ጦር አባላት ባልታወቁ ሰዎች እየተገደሉ በየጫካው ሥር እንደሚገኙ ታውቋል””
በም ዕራብ ሸዋ አምቦ; አመያና ግንደበረት ባለፉት 3 ሳምንታት ብቻ ከ6 በላይ የአጋዚ ጦር አባላትተገድለው ተገኝተዋል:: እንደ አይን እማኞች ገለጻ በግንደበረት ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን አካባቢ የአጋዚ ጦር አባላት ላይ ህዝቡ እርምጃ እንደወሰደም ታውቋል::
ከግንደበረት አካባቢ የተገኙ መረጃዎች እንደሚያመለከቱትም ህዝቡ ተፈትሮዋዊ ያልሆኑ ገደሎችን በመሥራት የአጋዚ ጦር መኪኖች ሲሄዱ እንዲገለበጡ በማድረግ ላይ እንዳለም ታውቋል::
በአሪሲ ሮቤ; መርቲ; ገደብ; እና ኮፈሌም እንዲሁ የአጋዚ ጦር አባላት እየሞቱ እየተገኙ ሲሆን መንግስት ግን ይህን ደብቆ እንደሚገኝ ታውቋል::
ይህ በ እንዲህ እንዳለ በኦሮሚያ የተለያዩ ቦታዎች ግብር ለመሰብሰብ የሚንቀሳቀሱ የመንግስት አካላት ላይ ሕዝቡ ጥቃት በማድረሱ የተነሳ ግብር ሰብሳቢዎች “ህዝቡን ፈራነው ስለዚህ ሄደን ግብር ክፈሉ ማለት አንችልም” በማለት ሥራ እንዳቆሙ ለመረዳት ተችሏል:: ግብር ክፍሉ እያሉ በም ዕራብ ሸዋና በምስራቅ ወለጋ የተንቀሳቀሱ የመንግስት አካላትን ሕዝቡ በቆመጥ ቀጥቅጦ እንዳባረረም ለዘ-ሐበሻ የደረሱ መረጃዎች አመልክተዋል::
ከም ዕራብ ወለጋ የደረሱን መረጃዎች እንደሚያመለከቱትም በተለይም በነጆ; በጃርሶና ጊምቢ አካባቢም ህዝቡ አድብቶ በመጠበቅ በአጋዚ ወታደሮች ላይ ጥቃቶችን እየፈጸመ ይገኛል:

በኢትዮጵያ አንድ ነጋዴ እስር ቤት እንዳለው ጠ/ሚ/ር ሃ/ማርያም ተናገሩ


በኢትዮጵያ አንድ ነጋዴ እስር ቤት እንዳለው ጠ/ሚ/ር ሃ/ማርያም በግልፅ ተናግረዋል። ቱጃሩ ዛሬ ጡንቻው እንዲፈረጥም ጥርጊያ መንገድ ያመቻቹት በስልጣንና እስር ቤት ይገኛሉ። የደህንነት ሹም ወ/ስላሴና የጉምሩክ ሃላፊ ገ/ዋህድ እንዲሁም በረከት ስሞኦንና አዜብ መስፍን ይጠቀሳሉ። 200 ነጋዴዎች በቱጃሩ ትእዛዝ በጉምሩክ ግቢ በኮንቴነር ውስጥ እንዲታሰሩ ያደረገው ገ/ዋህድ (የተጠቀሱት ባለስልጣናት ተባብረዋል) ድብደባ ይፈፅምባቸው ነበር። ፍ/ቤት ፍታ ሲለው አንፈታም ብሎ በአደባባይ ተናገረ። ከታሳሪዎቹ በድብደባ ጆሯቸው ይመግልና ይሰቃዩ እንደነበር ቢገልፁም ሰሚ አልተገኘም፤ የፍ/ቤት ውሳኔ አልተከበረም። 2 ነጋዴዎች የገዛ ህይወታቸውን እንዲያጠፉ ተደርጓል። የሪፖርተር ጋዜጣ አዘጋጅ በመፃፉ ብቻ በጠራራ ፀሀይ የግድያ ሙከራ ተፈፀመበት። ድርጊቱን የፈፀሙ በቦሌ የሸኙት በረከትና ወ/ስላሴ ነበሩ። በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ከባንክ ቱጃሩ እንዲበደሩ ፍቃድ ሲሰጡ የቆዩት በረከት ናቸው። ..ብዙ ማስረጃና መረጃ ማቅረብ ይቻላል። ቢዘገይም ጠ/ሚ/ሩ ሀቁን አፍርጠዋል፤ እርምጃ ባይወሰድም! በአንፃሩ በቀለ ገርባ፣ እስክንድር ነጋ፣ ተመስገን ደሳለኝ፣ አብርሀ ደስታና ሌሎች ንፁሀን “ህግ ይከበር! መናገርና መፃፍ መብት ይጠበቅ! ግድያና እስር ይቁም!” ብለው በሰላማዊ መንገድ በመጠየቃቸው ከነወ/ስላሴ ጋር እስር ቤት እንዲማቅቁ ተደርገዋል። ሃ/ማርያም ዛሬ ያመኑትን ጉዳይ እነዚህ ወገኖች ለአመታት ሲጮሁበት ከርመዋል። ..ነጋዴው የእግር ኳስ ክለብ ከማፍረስ እስከ እስር ቤት ማቆም ደረሰ።ነገ ደግሞ መንግስት ላለማቆሙ ማረጋገጫ የለም። ለነገሩ እስር ቤት አስቀድሞ ማቆሙ ..

ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገንዘቡን ከወሰዱ በኋላ ገንዘቡን ወደ hard currency ለውጠው እዚ ሃገር USA Colorado ላይ ቤት የገዙ ሰዎች አሉ በስም የሚታወቁ ! ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና

ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከልማት ባንክ ያለምንም ሚያዣ ይሄነው የሚባል ንብረት የሌላቸው ሰዎች ናቸው ብሩ ሚሰጣቸው ብሩን ከወሰዱ በኋላ በተወሰነ ደረጃ መሬት ላይ ያውላሉ የቀረውን በውጪ ምንዛሪ ለውጠውት ገንዘብ ያሸሻሉ። በስምና በዝርዝር አንድንድ የመጡ ዳታዎችም አሉ በተጨማሪ ለማጣራትና የተሟላ ነገር ይዞ ለመቅረብ ግዜ ስለወሰደ ነው።
ሃገር ቤት ያሉ ሰዎች ብቻ ሳይሆኑ ለምሳሌ Denver Colorado አካባቢ ያሉ ሰዎች ኢትዮጵያ ውስጥ ሄደው ኢንቬስተር ተብለው መሬት ይሰጣቸዋል በመሬቱ ስም ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገንዘቡን ከወሰዱ በኋላ ገንዘቡን ወደ hard currency ለውጠው እዚ ሃገር USA Colorado ላይ ቤት የገዙ ሰዎች አሉ በስም የሚታወቁ ሰለዚህ በከፍተኛ ደረጃ አሁን የመሬቱ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክና ከኢትዮዽያ ልማት ባንክ የሚወጣው ገንዘብ በተዘዋዋሪ መንገድ ወደ ውጪ እየሸሸ ነው። ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና
 

አለማቀፍ ተቋማት ያለመንግስት ፈቃድም ቢሆን የረሀብ አደጋውን አስከፊነት ለአለም ይፋ ሊያደርጉ ነው

  • በኢትዮዽያ የርሀብ አደጋው እየከፋ መምጣቱን ተከትሎ አለማቀፉ ማህበረሰብ የኢትዮዽያ መንግስትን ፈቃድ ሳይጠብቅ አዲስ የእርዳታ ጥሪ ለማቅረብ እየተዘጋጀ ነው። የአሜሪካ አለማቀፍ የልማት ተቋም (USAID) ዛሬቅዳሜ March 19 በጉዳዩ ላይ በአዲስ አበባ መግለጫ ይሰጣል።
    የሚከተለው የግብርና ስትራቴጂ ስኬትማ እንደሆነ በተደጋጋሚ የሚያውጀው የኢትዮጵያ መንግስት በአየር ፀባይ ለውጥና በብልሹ አስተዳደር ምክንያት በተከሰተው ድርቅ አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል። እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ዜጎች ከጊዜ ወደ ጊዜ የማሻቀቡ ነገር የማይፈልገውን ነገር ግን ግድ የሆነበትን የተረጂዎችን ቁጥር እና የእርዳታ መጠን እንደገና እንዲከልስ አስገድዶታል።
    የድርቁ ጉዳት በፀናባቸው አንዳንድ አካባቢዎች ለአመት ከመንፈቅ ያህል ጠብ አልል ያለው ዝናብ ነገሮችን እያወሳሰበ እና መጪውን ጊዜም አስፈሪ እያደረገው ይገኛል። የኢትዮጵያ መንግስት ከእርዳታ ለጋሾች ጋር ተጨቃጭቆ እና ተሟግቶ በየጊዜው ይፋ የሚያደርገው የሰብዓዊ እርዳታ ዶሴ በጉዳዩ ዙሪያ ለሚሰሩ ድርጅቶችና ኤምባሲዎች ወሳኝ ሰነድ ነው። በዚህ ሰነድ ላይ ተመስርተው ነው የእርዳታ እጃችሁን ዘርጉልን ኦፌሴሊያዊ ጥያቄ የሚያቀርቡት።
    የዓለም አቀፍ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ቁጥር አንድ ራስ ምታት ከሆነችው ሶሪያ እና ጦርነት አላባራ ካለባት የመን እኩል የኢትዮጵያ ጉዳይ አፅንኦት እንዲሰጠው ለጋሾችን የማሳመን ከፍተኛ የቤት ስራ አለባቸው።
    “የሶሪያ ጉዳይ ገንዘቡን እየመጠጠ ነው” ይላሉ በህፃናት ዙሪያ የሚሰራ የግብረ ሰናይ ድርጅት ኃላፊ።
    “አንድ ተራ ሶሪያዊ በኢትዮጵያ ከሚገኘው ተረጂ አስር እጥፍ የላቀ እርዳታ ይደርሰዋል። ” የኃላፊውን መከራከሪያ ቁጥሮችም ይደግፉታል። ለሶሪያ ሰብዓዊ ቀውስ ለጋሾች 10 ቢሊዮን ዶላር ሲሰጡ ለኢትዮጵያ ግን እስካሁን የለገሱት 700 ሚሊዮን ዶላር ነው። ይህ ማለት ኢትዮጵያ ያስፈልገኛል ብላ በህዳር 2008 ዓ.ም ከጠየቀችው 1. 4 ቢሊዮን ዶላር ያገኘችው እኩሌታውን ብቻ ነው።
    ግብረ ሰናይ ድርጅቶችን አሁን እያሳሰባቸው ያለው ገንዘቡ እንኳ አሁን ቢመጣ ለተረጂዎች የሚከፋፈለው እህልና ምግብ ከግዢው እስከ ማጓጓዙ ድረስ የሚፈጀው ጊዜ ነው። ይህ ጊዜ ከአራት እስከ ስድስት ወር ድረስ የሚወስድ መሆኑ ደግሞ መጪውን ጊዜ በስጋት እንዲመለከቱት አድርጓቸዋል።
    ጉዳዩ ያሳሰባቸው አንዳንድ ምዕራባውያን ሀገራት የኢትዮጵያ መንግስት የሚያወጣውን ሰነድ እንኳ መጠበቅ አልፈለጉም። የኢትዮጵያ መንግስትን እንደማያስደስተው ቢያውቁም የሚፈለገውን እርዳታ በአፋጣኝ ለማግኘት እና ህይወት ለማትረፍ ሲሉ ለየመንግስቶቻቸው በሚልኳቸው ሪፖርቶች የሰብዓዊ ችግሩን ደረጃ ወደ “L3″ ከፍ አድርገውታል።
    ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ እርዳታ ድርጅቶች በሚከተሉት የአስቸኳይ ችግሮች ምደባ መሰረት “L3″ ከጫፍ የሚቀመጥ
    ነው። ድርጅቶቹ ይህን ምደባ የሚጠቀሙት ጉዳቱ ከፍ ላለ እና ለግዙፍ ሰብዓዊ ቀውስ ነው። እንደተባበሩት
    መንግስታት የእርዳታ ማስተባበሪያ ቢሮ (OCHA) ገለጻ መሰረት ተመድ እና አጋሮቹ በአሁን ወቅት በአራት ሀገራት
    ያሉ ችግሮችን በዚህ ምደባ ፈርጀዋቸዋል። ሀገራቱ — ጎረቤታችን ደቡብ ሱዳን፣ በአቅራቢያችን የምትገኘው የመን
    እና በመካከለኛው ምስራቅ ያሉት ኢራቅ እና ሶሪያ ናቸው።
    “ፊት ለፊት L3 ብለን አንጠራውም። ነገር ግን እየሰራን ያለነው በዚያ ደረጃ ነው” ይላሉ አንዲት ምዕራባዊት ዲፕሎማት። የአሜሪካው ዩ.ኤስ.አይድ ከሳምንት በፊት ወደ ኢትዮጵያ የላከውን ቡድን ምንነት መመልከት የድርቁ ሁኔታ በለጋሽ ሀገራት እንዴት እየታየ እንደሆነ ተጨማሪ ማገናዘቢያ ይሰጣል።  የድንገተኛ አደጋ ተከላካይ  ኤክስፐርቶችን ያካተተው የመጀመሪያው የዩ.ኤስ.ኤይድ ቡድን Disaster Assistance Response Team
    (DART) ይባላል። የሎጀስቲክ ጉዳዮችን የሚከታተል ሌላ ቡድንም በቅርብ ቀን ቀዳሚዎቹን እንደሚቀላቀልም
    ተነግሯል።
    በዓመት ወደ 65 ለሚጠጉ አደጋዎች ምላሽ የሚሰጠው ዩ. ኤስ.ኤይድ እንዲህ አይነት ባለሙያዎቹን
    የሚልከው እንደ መሬት መንቀጥቀጥ ና ጎርፍ ላሉ አፋጣኝ እና ጉዳታቸው ላቅ ላሉ አደጋዎች ነው ይላሉ የዋዜማ
    ምንጮች።
    ለጋሾች አለማቀፍ የመገናኛ ብዙሀን ወደ ኢትዮዽያ እንዲገቡ አፋጣኝ ፈቃድ እንዲስጥ መንግስትን ማግባባት ይዘዋል። መንግስት ግን ለአብዛኞቹ ጋዜጠኞች ፈቃድ መከልከሉና በሀገር ቤት ያሉትን ችግሩን እንዳያጋልጡ በመፍራት ማሰሩ አሳዛኝ መሆኑን ለጋሾች ያሰምሩበታል።ምዕራባዊቷ ዲፕሎማት የኢትዮጵያን ድርቅ እና ያስከተለውን ቀውስ መጠን ትልቅነት ለማመላከት በችግሩ ምክንያት ከቀዬው የተፈናቀለውን ሰው ቁጥር በምሳሌነት ያነሳሉ። “በሀገር ውስጥ ያለው ስደት ትልቅ ነው። እስካሁን ከ250,000— 500,000 ሰው በችግሩ ምክንያት የነበረበትን ቦታ ለመልቀቅ ተገዷል።”
    “ዕርዳታ ፈልገህ ችግርህን ደሞ ደብቀህ ውጤታማ መሆን አይቻልም፣ አሁን መንግስት ፈቀደም አልፈቀደም አለማቀፉ ማህበረስብ ህይወት የማትረፍ ግዴታ አለበት” ይላሉ በቅርቡ ኢትዮዽያን የጎበኙ የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤት ባልደረባ።
    እየጨመረ የመጣው በምግብ እጥረት የተጎዱ ህጻናት እና እናቶች ቁጥርም የጉዳዩን አሳሳቢነት የሚመሰክር ነው።
    በሳምንቱ መግቢያ የወጣው የተባበሩት መንግስታት የእርዳታ ማስተባበሪያ ቢሮ ሪፖርት እንደሚያመለክተው 2.2
    ሚሊዮን የሚሆኑ ህጻናት፣ ነፍሰ ጡር እና በማጥባት ላይ ያሉ እናቶች በመጠነኛ የምግብ እጥረት ተጠቅተዋል።
    450,00 ህጻናት ደግሞ በፅኑ የምግብ እጥረት ተጎድተዋል። 2.2 ሚሊዮን የነበረው አስቸኳይ የዘር እርዳታ
    የሚያስፈልጋቸው ገበሬዎች ቁጥር ወደ 3.3 ሚሊዮን ከፍ ብሏል።
    የሚፈለገው እርዳታ ማሻቀቡን ከተለያዩ ሪፖርቶች እና ከረጂዎች የማያቋርጥ ውትወታ የተገነዘበ የሚመስለው
    የኢትዮጵያ መንግስት በየዘርፉ ያለውን ቁጥር ለመከለስ መስማማቱ ግብረ ሰናይ ድርጅቶችን አስደስቷል። የበልግ እና
    መኸር ወቅቶችን ተከትሎ በዓመት ሁለቴ ይወጣ የነበረው የሰብዓዊ እርዳታ ሰነድ በአጭር ጊዜያቶች ውስጥ ሲከለስ
    ለሶስተኛ ጊዜ ነው። በነሐሴና ህዳር ከወጡት ሰነዶች ተከታይ የሆነው እና የድርቅ ተጎጂዎችን ቁጥር ከ10
    ሚሊዮን በላይ ከፍ እንደሚያደርገው የሚጠበቀው ሰነድ ዝግጅት ከሶስት ሳምንት እስከ ወር ሊወስድ እንደሚችል
    በተባበሩት መንግስታት ያሉ የዋዜማ ምንጮች ያስረዳሉ።
    የችግሩን አንገብጋቢነት ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ የሚጠቁሙት ዲፕሎማቷም ሆኑ የግብረ ሰናይ ድርጅቱ ኃላፊ
    የሚያስፈራቸው አንድ ነገር አለ። ፍርሃታቸው አጥንታቸው ያገጠጠ እና ፊታቸው የጎደጎደ ህጻናት ምስል የዓለም
    አቀፍ ብዙሃን መገናኛዎችን የፊት ገጽ እና የቴሌቪዥን ስክሪን እንዳያጣብብ ነው። ይህ ከመሆኑ በፊት ፈጣን
    እርዳታ የድርቅ ተጎጂዎች ዘንድ እንዲደርስ እየተመኙ መጪውን በስጋት አሻግረው ይመለከታሉ

Friday, March 18, 2016

በደቡብ ኢትዮጵያ ኮንሶ ልዩ ወረዳ ውጥረቱ እንደነገሠ ነው።


በህወሓት(ደኢህዴን) እና የእነሱ ቅጥረኛ በሆኑት የአካባቢው ሆድ አደር ተሿሚዎች ምክንያት የማንነት እና ዘር የማጥፋት አደጋዎች ከፊታችን ተደቅኖብናል፤ ከዚህ በፊትም በስውር ሲፈፀምብን ነበር ይላል አንድ የኮንሶ ወጣት በውስጥ መስመር በላከልኝ መልዕክት።
የኮንሶ ልዩ ወረዳ በደቡብ ኢትዩጵያ ውስጥ ከሚገኙት 8 ልዩ ወረዳዎች አንዷ ናት ። በማዕከላዊ እስታቲስቲክስ ዳታ መሰረት ወደ 305,000(ሶስት መቶ አምስት ሺ) የሚያክል ህዝብ ብዛት አላት። ይህንን የሚያክል ህዝብ ይዛ ቀድሞንም ኢ-ፍትሃዊ በሆነ መንገድ በወረዳ ደረጃ በመዋቀሯ ምክንያት የአካባቢው ህዝብ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በአቅራቢያው ባለማግኘት ምክንያት ምን ያክል በከፋ ስቃይ ውስጥ እንደነበር መገመት አያዳግትም። በነገራችን ላይ እንደ አጠቃላይ ከተመለከትን የደቡብ ኢትዩጵያ ህዝቦች በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት ሁሉም ክልሎች ሲነጻጸር በመሰረተ ልማት ዝርጋታና በእድገት የመጨረሻ ደረጃ ላይ እንደሆነ ወርልድ ባንክን ጨምሮ ሌሎች የአለም አቀፍ ድርጅቶች ከአንድ አመት በፊት ሪፖርት ማውጣታቸውን አስተውሳለሁ ። ከዚህ አንፃር ስንመለከት በኮንሶም ይሁን ሌሎች የደቡባዊ ኢትዩጵያ ወረዳዎች እና ዞኖች አንድ ገበሬ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ለማግኘት በአማካይ የ5 ወይንም የ6 ሰዓት መንገድ በባዶ እግሩ መጓዝ ይጠበቅበታል። ደርሶ መልስ ባላጋንን የ11 ሰዓት መንገድ። ለዛውም በየአካባቢው በወያኔ መስፈርት የተሾሙት ትንንሽ መሳፍንቶችን ግልምጫ እና ስድብ ለማስተናገድ። ወደ ኮንሶ ጉዳይ ስንመጣ የኮንሶ ህዝብ የፍትሕ ያለህ የሚል ጩሄት ለክልልና ፌደራል መንግስታት ማስተጋባት የጀመሩት ከዛሬ 8 ወር በፊት ነው። እርግጠኛ ነኝ የልማት እና ተያያዥነት ያላቸውን ጥያቄዎች ማቅረብ የጀመሩት በዚህች ስምንት ወር ብቻ ሳይሆን ከዛ በፊትም በነበሩበት ተከታታይ ጊዜያት ይሆናል የሚል እምነት አለኝ። አሁን በዚህ 8 ወራት ውስጥ እያየለ የመጣው የኮንሶ ህዝብ ጥያቄዎች በአይነቱም በይዘቱም ጠንከር ያሉ ናቸዉ ። ሁለት መሰረታዊ ጉዳዩች ጋር የተገናኘ ነው ይላል ከአካባቢው መረጃ የሰጠኝ ግለሰብ። አንደኛው ወቅቱን በትክክል ባያስታውስም ከቅርብ ጊዜ በፊት በአንድ የአለም አቀፍ ድርጅት አማካኝነት በኮንሶ አከባቢ በተደረገው ጥናት መሰረት በአካባቢው ከፍተኛ የማዕድን ክምችት እንደተገኘና እስከ አሁን ጉዳዩ በምስጢር ተይዞ ተቀምጧል ይላል ወጣቱ። ከዚህው ጋር በተያያዘ ለቁፋሮ ቅድመ ሁኔታዎችን ለማመቻቸት የክልሉ መንግሥት እና የአካባቢው ተሿሚ መሳፍንቶች በርካታ የኮንሶ ነዋሪዎችን በማስገደድ ከነበሩት ቦታ ከታላመዱበት የአኗኗር ዘይቤና ባህል በማፈናቀል ወደ ባስኬቶ ልዩ ወረዳ እና ወደ ደቡብ ኦሞ ዞን በሰፈራ ፕሮግራም በግዳጅ ማንነታቸዉ በማስካድ እየወሰዷቸው ነው። ከዚህ በፊትም በግዳጅ ብዙ ሰው ተፈናቅሎ በሰፈራ ፕሮግራም ሄዷል ይላል ወጣቱ ።ሌላው በቅርቡ የተመሰረተ አንድ ሰገን ዞን የሚባል የኮንሶ ልዩ ወረዳ አጎራባች አለ ። ደቡብ ክልል ውስጥ 13 ነባር ዞኖች እና 8 ልዩ ወረዳዎች አሉ። ይህኛው 14ኛ መሆኑ ነው። የሰገን ዞን ሲመሰረት ከዚህ ቀደም በኮንሶ ወረዳ ክልል ውስጥ የነበሩ በርካታ ቀበሌዎች በግዳጅ ወደ ሰገን ዞን እንዲካለሉ ተደርጓል ይላል። በዚህም ምክንያት የኮንሶ ማንነት በኃይል በማስካድ ያልታወቀ በቅርቡ በመጣ ሰገናዊ ማንነት በኃይል የማጥመቅ ስራ እየተሰራ ይገኛል። ሌላኛውና ሁለተኛው አንኳር ጥያቄዎቸው 305,000 ህዝብ ሆነን ሳለ በአንድ ወረዳ መስተዳድር ስር መዋቀራችን ተገቢ አይደለም ቀድሞንም በዞን ደረጃ መሆን ነበረበት ሰለዚህ መንግሥት ያለውን የህዝብ ቁጥር ታሳቢ በማድረግ የዞን ማዋቅር ሊሰጠን ይገባል የሚል ጥያቄ ነው። በተጨማሪም ኋላ ቀር ነን መንገድ እና የመሳሰሉ የልማት ስራዎች እንዲሰራልን የሚሉ ጥያቄዎችም አሉበት ። እነዚህንና የመሳሰሉትን ጥያቄዎች አንግበው የኮንሶ ህዝብ ሰላማዊት ህዝባዊ ትግል ከጀመሩ ይህ 8ኛው ወራቸው ነው ። ከ4 ጊዜ በላይ የአካባቢው ተወካዮች ወደ ክልልና ፌደራል መንግሥት ተንቀሳቅሰዋል። የተሰጣቸው ምላሽ ግን ያልጠበቁት ሆኖ ነው ያገኙት። የክልሉን ልዩ ኃይል፣ የፌደራል ፖሊስ ፣በደቡብ ክልል የፀጥታ ኃይል ዩኒፎርም ጭንብል አጋኣዚ እና የመሳሰሉትን ታጣቂዎች በአካባቢው ማራገፍ ነው የሆነው። እስከ አሁን ድረስ ብዙ ሰዎች በጥይት ተደብድበው ተግድለዋል ብዙ ሰውም ታስሯል። የአካባቢው ባህላዊ ንጉስ ሳይቀር በአሁኑ ሰዓት እስር ላይ ናቸዉ ።በዛሬው እለትም አንድ ታወቂ ነጋዴ ታፍኖ እንደተወሰደ ከስፍራው መረጃ ወጥቷል። ትግሉ ግን አልቆመም የሚቆምም አይነት አይደለም። እጅግ በጣም የሚያሳዝነው ነገር ይላል ወጣቱ በአሁኑ ሰዓት የኮንሶን ህዝብ መንገድ በመምራት እና ልዩ ልዩ እርዳታ በማድረግ እያሰጨፈጨፉና እያሰቃዩ የሚገኙት ከኮንሶ አብራክ የወጡ የአካባቢው ተሿሚዎች መሆናቸው ነው በማለት ቋጭቷል። በኔ እይታ ከኮንሶ አብራክ የተውጣጡ ተሿሚዎች በመተግበር ላይ የሚገኙት ጭካኔ የተሞላበት ድርጊት በአሁን ሰዓት ለአካባቢዬና ለህዝቤ ነፃነት እታገላለሁ ለሚሉት እና ለተከታዮቻቸው በተጨማሪም ከእርሱም ፍጹም ነፃነት በመሻት ላይ ላሉ ሁሉ ትልቅ መልእክት እያስተላለፈ ይገኛል።ነፃነት ማለት በየቦታው ትናንሽ መንግስታትን በአንድም በሌላ መልኩ እየተደራጁ በመፍጠር መካከለኛውንና የበታችኛውን የህብረተሰብ ክፍል ወደ ታች ደፍጥጦ በመያዝ መዝረፍ እና ደም ዕምባ ማስለቀስ እንዳልሆነ ያመላክታል።

የአቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ስብሰባ (p. መስፍን ወልደ ማርያም)

(ይህ ጽሑፍ ሪፖርተር ጋዜጣ በጻፈው ግምገማ ላይ የተመሠረተ ነው፤ የምጠቅሰው ሁሉ ከዚያው ነው፤ ብዙ ቪድዮዎችን ለማየት ሞክሬ አፈናው ከባድ ስለሆነ አልቻልሁም፡፡)
አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ከሥልጣን ውጭ ያሉ ሰዎችን ሰብስቦ ለማነጋገር የመወሰኑን ሀሳብ መንፈስ ቅዱስ ሹክ ያለው ይመስላል፤ ነገር ግን በመንፈስ ቅዱስና በኃይለ ማርያም ደሳለኝ መሀከል ጣልቃ የገባና መልእክቱን የለወጠው ኃይል አለ፤ ‹‹በብሔራዊ ጉዳዮች ላይ መግባባት — ስለኢትዮጵያ ሕዳሴ›› መነጋገር የሚለው ሀሳብ በመሠረቱ ጠቃሚና ተገቢ ነው ብዬ አምናለሁ፤ ሆኖም ይህ ጉዳይ የሚመለከታቸውና የሚያገባቸው ‹‹ምሁራን›› ብቻ ናቸው የሚል ቅዠት የለኝም፤ በተለይ ምሁራን ማለት ‹‹እኛው … ነን›› እንዳለው ከሆነ!
በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ችግር ሁሉ እያለቀሱ የሚኖሩት ምሁራን አይደሉም፤ ችግሩን በትክክል ሳይረዱ ስለመፍትሔ ማሰብ የጉልበተኞች መንገድ መሆኑን ጠንቅቀን እናውቃለን፤ መፍትሔ የሚፈልግ ሰው ሰብስቦ ማነጋገር የሚያስፈልገው ችግሩ በየዕለቱ የሚገርፋቸውን የሚወክሉ ሰዎችን ነው፤ የተወሰኑ ምሁራን ለመፍትሔው ስለሚያስፈልጉ በታዛቢነት ቢኖሩ ጥሩ ነው፤ እንደዚያም ሆኖ ችግሩን የሚናገሩ ሰዎች ከፍርሃት ነጻ የሚሆኑበት መድረክ መኖሩን ማረጋገጥ ያሻል፡፡
አሁን አቶ ኃይለ ማርያም ያደረገው ስብሰባ ከጥቂት ዓመታት በፊት መለስ ዜናዊ ካደረገው እምብዛም የተለየ አይደለም፤ የመለስም ሆነ የኃይለ ማርያም ዓላማ ከሥልጣን ውጭ ከሆኑ ዜጎች ጋር በአገር ጉዳይ ላይ ለመመካከር፣ ለመከራከር፣ ለመወያየትና ወደስምምነት ላይ ለመድረስ አይደለም፤ በእንደዚህ ዓይነቱ ሥርዓት ውስጥ ይህ ሊሆን አይችልም፤ ጉልበተኞቹ እንደተለመደው የሚፈልጉት ሀሳባቸውን በጉልበት ለማጽደቅ ነው፤ ከተጋበዙት መሀከል አንድ ሰው ተነሥቶ ጋዜጠኞችን ሁሉ አስራችሁ፣ ጋዜጦቹን ሁሉ አግዳችሁ፣ የተለያዩ ድርጅቶች ሕዝቡን እየሰበሰቡ እንዳያወያዩ እየከለከላችሁ፣ የሃይማኖት መሪዎች እንኳን በነጻነት እንዳይሠሩ እያደረጋችሁ እኛን የመረጣችሁን እንድትነግሩን ነው? ወይስ እንድንነግራችሁና ነገ ቃሊቲ እንድንገባ ነው? ብሎ ቢጠይቅ መጋረጃው ይቀደድ ነበር፤ ይህ ጥያቄ ወይም አስተያየት ከተሰብሳቢው ቢሰነዘር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ‹‹ፖሊቲከኛው ጥግ ጥጉን ይዞ ከመታኮስ ባለፈ … ዴሞክራሲያዊ ባህል ማዳበር እንዳቃተው …›› ብሎ መናገር አይደፍርም ነበር፤ ‹‹ፖሊቲከኛ›› የተባለውን መተኮስ ያስተማረው ማነው? ተብሎ ቢጠየቅ ምን ይመልሳል፤ መለስ ዜናዊን ጠይቄው ነበር፤ ‹‹መንገዱን ጨርቅ ያድርግላቸው›› ነው ያለው!
እዚያ ለተሰበሰቡት ‹‹ምሁራን›› ፖሊቲከኛው ‹ዴሞክራሲያዊ ባህልን ማዳበር› አቅቶታል ሲል መልስ ተሰጥቶት እንደሆነ አላውቅም፤ ካልተሰጠው ግን የያዘው ሰይፍ ግለቱ ‹ምሁራኑን› እንዳቀለጣቸው ሌላ ማስረጃ አያስፈልግም፤ ሀሳብን የመግለጽን ነጻነት፣ የመደራጀትን፣ የመሰብሰብን፣ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግን በማይቻልበት፣ በፖሊቲካው ቀርቶ በሃይማኖትም በኩል ሰዎች በነጻነት መወያየትና መሪዎቻቸውን የመምረጥ መብት ተነጥቀው ባለበት አገር ጩኸቴን ቀሙኝ እንደሚባለው ምንም ሥልጣን የሌላቸውን የተቀናቃኝ ክፍል ፖሊቲከኞች የዴሞክራሲ ባህል አላዳበሩም ብሎ ለመውቀስ የሚችልበት መድረክ በእርግጥ ‹የምሁራን› ሊሆን አይችልም፤ አቶ ኃይለ ማርያም የበዳይ ወቃሽ በመሆኑ ላይ ይገፋበታል፤ ‹‹ዓመጽ የማይቀሰቅስ የሀሳብ ብዝኃነት እንዴት ነው እዚህ አገር መፍጠር የሚቻለው?›› ብሎ ይጠይቃል፤ በአዳራሹ ውስጥ የተሰበሰቡት ሁሉ በአንድ ላይ ‹‹በነጻነት!›› ብለው ቢጮሁ ያስተምሩት ነበር፡፡
አቶ ኃይለ ማርያም አያይዞም ‹‹የሀሳብ ልዩነት ብዙ አያስፈራንም፤ የሚገለጹበት መንገድ ነው የሚያስፈራው››፣ ‹‹ከኋላ ጦር አሰልፎ ከፊት በሀሳብ ልፋለም .. የሚለው ነው ያስቸገረን፤›› ተቀናቃኞቹ ጦር እንዳላቸው አግአዚ ይመስክር!
አቶ ኃይለ ማርያም ‹‹በአንድ ትውልድ የተጣመመ የፖሊቲካ ባህል ተሸክመን ቁርሾን ለዚህ ትውልድ እያስተላለፍን ነው፤›› ያለው እውነት አለበት፤ እሱ በዚያ ‹‹የተጣመመ የፖሊቲካ ባህል›› ባመጣው ትውልድ ውስጥ ነበረ? ነበረም አልነበረም ዛሬ እሱ የሚያገለግለው ያንን ትውልድ እንደሆነ የተገነዘበ አይመስለኝም፡፡
በአቶ ኃይለ ማርያም ንግግር ውስጥ የሚያስገርመውና ግራ የሚያጋባው ጣል አድርጎ ያለፋት አንዲት ዓረፍተ ነገር ነች፡– ‹‹አንድ ትልቅ ነጋዴ የራሱ እስር ቤት አለው ቢባል ታምናላችሁ?›› ማመን የሚያስቸግረኝ አንድ የትልቅ አገር ጠቅላይ ሚኒስትር ይህንን መናገሩ እንጂ በጉልበተኞች አገር አንድ ጉልበተኛ የራሱ እስር ቤት ቢኖረው ምን ያስደንቃል!
የሪፖርተር አንባቢዎች በሰጡት አስተያየት፡—
6 ከመቶ የሚሆኑት ተደስተዋል፤
4 ከመቶ አልተደሰቱም፤
71 ከመቶ የተሻለ የሚፈልግ፤
በሪፖርተር መረጃ መሠረት የአቶ ኃይለ ማርያም ስብሰባ የራሱን ተከታዮች እንኳን በከፊልም ያላስደሰተ ይመስላል፤ ምናልባት የመንፈስ ቅዱስን ሹክታ አክብሮ እንደገና እንዲያስብበት ይርዳው፡፡

የብሪታኒያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሩን በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጉዳይ ያላቸውን ስጋት ለኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ ለኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ ሁለት ጊዜ ደብዳቤ መጻፋቸው ተነገረ


)
በቅርቡ በኢትዮጵያ ጉብኝትን ያደርጋሉ ተብለው የሚጠበቁት የብሪታኒያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሩን በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጉዳይ ያላቸውን ስጋት በመግለጽ ለኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ ሁለት ጊዜ ደብዳቤ መጻፋቸውን የሃገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ሃሙስ ዘገቡ። የሃገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሲያደርግ የቆየው ጥረት ውጤት አለማምጣቱን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ደብዳቤውን እንደጻፉ በዝ ፊድ ኒውስ የተሰኘ ጋዜጣ አስነብቧል። የብሪታኒያ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ወደሃገራቸው የሚመለሱበትን ሁኔታ ለማመቻቸት በርካታ ጥረቶችን ሲያደርግ ቢቆይም የተፈለገው ውጤት ሊገኝ አለመቻሉን ሬፕሪቭ የተሰኘ የብሪታኒያ ድርጅት በድረ-ገጹ አስፍሯል። የጥረቱን አለመሳካት ተከትሎች ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሩን በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጉዳይ ያላቸውን ስጋት በመግለጽ ለጠቅላይ ሚኒስቴር ሃይለማሪያም ደሳለን ሁለት ጊዜ ደብዳቤ መጻፋቸውን ጋዜጣው የሃገሪቱን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዋቢ በማድረግ ዘግቧል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በኢምባሲ ተወካዮች በቋሚነት እንደሚጎበኙ በተደጋጋሚ ማረጋገጫን ቢሰጡም የተገኘ ውጤት አለመኖሩን ጋዜጣው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘን መረጃ ዋቢ በማድረግ በዘገባው አስነብቧል። የብሪታኒያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም ያደረገው ጥረት ውጤት አለማስገኘቱን አስመልክቶ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ዴቪድ ካሜሩን ሪፖርት ሲያቀርብ መቆየቱም ታውቋል። በቅርቡ በኢትዮጵያ ጉብኝትን የሚያደርጉት ዲቪድ ካሜሩን የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ጉዳይ በማንሳት ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር ውይይትን ያካሄዳሉ ተብሎ ይጠበቃል። ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት አስቀድሞ የሃገሪቱ ከፍተኛ የኢሚግሬሽንና የደህንነት ሃላፊዎች ከሁለት ሳምንት በፊት በኢትዮጵያ ጉብኝት ማድረጋቸውን መዘገባችን ይታወሳል። የብሪታኒያው ጠቅላይ ሚኒስትር ለአቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ በጻፉት ደብዳቤም ሁለቱ ሃገራት ካላቸው የጠበቀ ግንኙነት አንጻር በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጉዳይ ዙሪያ ሲደረገ የቆየው ውይይት ፍሬ አለማፍራቱ ቅሬታን እንደፈጠረባቸው በደብዳቤያቸው አስፍረዋል። ዴቪድ ካሜሩን ይህንን ጉዳይ ከአቶ አንዳጋቸው ጽጌ ቤተሰቦች ሲለዋወጡ መቆየታቸውንም ለመረዳት ተችሏል።

Thursday, March 17, 2016

የኢትዮጵያ ህዝብ ማንንም ሳይጠብቅ ለነፃነቱ እንዲነሳ ጄኔራል ከማል ገልቹ ጥሪ አቀረቡ


ኢሳት ዜና:- ህብር ራዲዮ ከላስቬጋስ እንደዘገበው፤ የመገንጠል ሀሳቡን ከፕሮግራሙ ያወጣው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ሊቀመንበር ጄኔራል ከማል ገልቹ፤ በአሁኑ ወቅት የግንባሩ ዋነኛ ዓላማ በተባበረ የኢትዮጵያ ህዝብ ክንድ ወያኔን በማንበርከክ ለህዝቡ ጥያቄ እንዲገዛ ማድረግ መሆኑን በድጋሚ በማረጋገጥ፤ ህዝቡ ሳይከፋፈልና ማንንም ሳይጠብቅ ለነፃነቱ እንዲታገል ጥሪ አቅርበዋል።
.
እንደ ህብር ዘገባ፤ ጄኔራል ከማል ይህን ጥሪ ያቀረቡት፤ እሳቸው የሚመሩት የኦሮሞ ነፃነት ግንባር በቅርቡ የመገንጠል ፕሮግራሙን በመተውና የኢትዮጵያ ህልውናን በመቀበል ከሌሎች ድርጅቶች ጋር ተባብሮ ለመታገል መነሳቱን አስመልክቶ ለተሰነዘሩባቸው ጥያቄዎች ምላሽ በሰጡበት ወቅት ነው።
.
ጀነራል ከማል በዚሁ ምላሻቸው፤ የነፃነት ትግሉን ወደፊት ለመግፋት ያስችላል ያሉትን የኦነግ ዓላማን አብራርተዋል። ኦነግ ፤ለትግል እንቅፋት ይሆናሉ ያላቸውን ነገሮች ማስተካከሉን የገለፁት ጄኔራል ከማል ህዝቡ ይህን መንገድ ተከትሎ ማንንም ሳይጠብቅ ራሱን ነፃ እንዲያወጣም በአጽንኦት አሣስበዋል።
.
የኢትዮጵያ ህዝብ ተባብሮ በስልጣን ላይ ያለውን የግፍ ስርዓት እንዲያስወግድ ከተፈለገ ፤የተቃውሞ ትግሉን የሚመሩ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ ያሉ ወገኖች መተባበር እንዳለባቸውም ጀነራሉ ሳይጠቁሙ አላለፉም።
.
«ወያኔ በኢትዮጵያ ህዝብ ክንድ ከተንበረከከ በኋላስ- ምን አይነት መንግስት ይመሰረታል?» በሚለው አብይ ጥያቄ ዙሪያ የድርጅታቸውን አቋም ሲገልጹም፦ ኦነግ ከሌሎች ጋር በመሆን ምን አይነት አገር መመስረት እንዳለበት እንደሚነጋገርና ግንባሩ ለህዝቡ የሚያቀርበውን አማራጭ እንደሌሎቹ ድርጅቶች ሁሉ ለህዝቡ አቅርቦ በህዝቡ ውሳኔ የወደፊት እጣውን እንደሚወሰን አመልክተዋል።
.
ጄኔራል ከማል ገልቹ፤ የአቶ መለስ አስተዳደርን አውግዘው ከመከላከያ ሰራዊቱ የተለዩት ምርጫ 97ን ተከትሎ ወያነ ሰራዊቱን ሽፋን በማድረግ በህዝቡ ላይ የወሰደውን ህገ-ወጥ ግድያ በመቃወም ቢሆንም፤ እ.ኤ.አ ከ2001 ጀምሮ በህቡዕ በኦነግ አመራር ውስጥ ተሳትፎ እንደነበራቸው ገልፀዋል።

ሕወሓት እንደጥርስ መፋቂያ አንድ ጊዜ ተጠቅሞ የጣላቸውን የቀድሞ ወታደሮቹን እየሰበሰበ ነው


(አቶ አሰገደ ገብረሥላሴ እንደዘገቡት) የህወሓት ነበር ታጋዮች ለመጭው ቅዳሜ መጋቢት10/07/08 ዓ ም በህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ ሥብሠባ ተጠርተዋል የዚህ ሥብሠባ ኣለማ ኣልታወቀም::
የታጋይ ነበር ሥብሠባ የሕወሓት መሪዎች በውሥጣቸው ቀውሥ ወይ መከፋፈል ሢፈጠር ሢጨንቃቸው የሚጠሩት ሥብሠባ ነው:: ያጋጠማቸው ችግር እሥከሚፈቱ ወይ እሥከሚረጋጉ ጡሮታ እንሠጣሃለን; መቋቋምያ እንሠጣሀለን; ሥራ እንፈጥርላሀለን በማለት እንደሚሠብኩትም ታውቀዋልLL በተጨማሪም ህወሓት የበላይነቱ እና ማንነቱ ተነጥቋል የሚል ሠበካ እንዳለም ከወዲሁ ይናፈሣሣል ::
ይህ ሥብሠባ በመላው ትግራይ ኣዲሥ ኣበባ ይደረጋል ተብሏል::
ሕወሓት ደርግን ካሥወገዱ በኋላ ከ60 000 በላይ ወታደሮች ውስጥ 32 ሺህው ዲሞክራሢያዊ ጥያቄ በማንሣታቸው የህወሓት ኣማራርን ተግባራት በመቃወማቸው የተባረሩት ከዛ በኋላም በኣድልዎ በጎጠኝነት የተባረሩና በትውልድ ቀያቸው እንዳይኖሩም ከህዝብ ከወላጆቻቸው እንዲነጠሉ በማድረግ የተሣቃዩ ናቸው::
በተጨማሪ በጦርነት ኣካላቸው የጎደሉ 126 000 ወታደሮች ውሥጥ ከ4500 የማይበልጡ ጡሮታ ወይ በርድ የሚያገኙ ሌሎች ግን የተካዱ ነበሩ:: በድህነት ተሠቃዩ ሴት ታጋዮች ኣማራጭ ኣጥተው ወደ ዝሙት ሥራ ተሣማሩ:: የሕወሓት መሪዎች እና ተላላኪ ካድሬዎቻቸው ልዩ ዘር የሆኑባት አገር ሆነች::
እንግዲ የጅግኖች ካሣ ይህ ሆነ እና: የሕወሓት መሪዎች ግን ይህን ታጋይ የበረን ወታደር እንደ የጥርሥ መፋቅያ ተጥቀመው ይጥሉታል:: አንድ ጊዜ ደግሞ ሲጨንቃቸው የማያደርጉትን ተሥፋ በመሥጠት ይሰበስቡታል : ተጠቅመውም ይጡሉታል:: የኣሁኑ ሥብሠባም ላላቸው መከፋፈል ችግር ወደ ኣንዱ እንዳይወግኑ ሠብከው ወደ ጠባብነት ጎራ በማሠለፍ ሊጠቀሙባቸው ወይም ማሃል ሠፋሪ ለማድረግ ነው::
ይህን ለማሣካትም ጡሮታ እናደርግላችሁአለን ወይ ድጎማ እንሠጣችሁ ኣለን እያሉ ይሠብካሉ : በተግባር ግን ኣይውልም::

መረጃ……. ሐይለማያም ደሳለኝ በጥቂቱ አሻፈረኝ እያሉ ነዉ!!


በትናንትናዉ እለት በቤተ መንግስት ዉስጥ በተጠራ ሚስጥራዊ ስብሰባ ላይ እጃቸዉን በመክተት የጸጥታ ሐላፊዎችን አስደንግጠዋል።
በቤተ መንግስቱ የጸጥታ ጉዳዬች ዙሪያ ለመነጋገር በሚል ሰበብ ተደጋጋሚ ሚስጥራዊ ስብሰባዎችን ታግሼያለዉ! አሁን ግን ከተለያዩ ክልሎች በተለይም አዲስ አበባ ላይ የሚገኙ ከፍተኛ የክቡር ዘበኛና የደህንነት የበላይ አካሎች ከመከላከያ የበላይ ሹማምንቶች ጋር የሚካሄደዉ ዉይይት በምን ጉዳይ ላይ እንደሆነ ማወቅ ያሻናል በማለት ስብሰባዉ በሓይለማርያም ደሳለኝ ትእዛዝ የተሰረዘ ሲሆን በጉዳዩ ላይ ሪፖርት እንዲያደርጉ የተጠየቁ የክቡር ዘበኛ የበላይ ሐላፊዎች ግቢዉን ለቀዉ ወጥተዋል።
ጉድሽ ወያኔ
Gudish Weyane's photo.

አልሸባብ የፑትላንድ ወደብን መልሶ ተቆጣጠረ::


ሶማሊያ ዉስጥ የሚንቀሳቀሰዉ ታጣቂ ቡድን የአልሸባብ ተዋጊዎች በከፊል ራስ ገዝዋ ፑንትላንድ የሚገኝ ትንሽ ወደብ መያዛቸዉን ሮይተርስ ዘገበ። ባሳለፍነው የፈረንጆች አመት የአፍሪቃ ኅብረት የሶማሊያ ሰላም አስከባሪ « AMISOM» እና የሶማሊያ ብሔራዊ ጦር አል ሸባብን በስፋት ከተቆጣጠረዉ ደቡባዊ የሶማሊያ ግዛት ማስለቀቃቸዉ ይታወሳል።
እንደ ባለስልጣናት ገለፃ በዚያን ጊዜ የአሸባብ ተዋጊዎች የአፍሪቃ ኅብረት የሰላም አስከባሪዉ የጦር ኃይል «AMISOM» ከሚቆጣጠረዉ ክልል ዉጭ ማለት ወደ ሰሜናዊ ፑንትላንድ ግዛት ሄደዋል። በዚሁ ሳምንት ዉስጥ አሸባብ ትናንሽ ከተሞችን መልሶ ተቆጣጥሮአል፤ በደቡባዊዉ ክፍልም ጥቃት አድርሶ ሰዎች ተገድለዋል።
የፑንትላንድ ጉዱግ አካባቢ ገዢ ሀሰን ሞሐመድ ለሮይተርስ እንደገለፁት የአሸባብ ተዋጊዎች በበርካታ ጀልባዎች ላይ ሆነዉ ጋራድ ከተማን ተቆጣጥረዋል። ቡድኑ ጥቃቱን የሰነዘረዉ ትናንት መሆኑንም አመልክተዋል። የተጠቀሰዉን ወደብ ስለመያዝ አለመያዙ እስካሁን ከኧሸባብ የተገለፀ ነገር ግን የለም። የፑንትላንድ የባህር ዳርቻ ግጭት ለሚበዛበትና አልቃይዳ ለሚንቀሳቀስበት ለየመን በቅርበት ላይ ይገኛል።
 

ኢትዮጵያውያን በኩዌት እየታደኑ ነው


 ስለኩዌት መረጃውን ያገኘሁት ግሩፕ ውስጥ ስገባ ነው። ኤልዳና ፖስታዋለች አነበብኩት። ይጠቅማል እሰራለሁ ትንሽ ለውጥ አገኛለሁ ብሎ ለሚያስብ ጥንቃቄ ይሻል። ወደው ከኮንትራት ቤት አልጠፉ..
ኩዌት ውስጥ የምትገኙው ኢትዮጵያውያን እንዲሁም ኤርትራውያን ራሳችሁን ጠብቁ የኩዌት መንግሥት የተለያዩ ሀገር ዜጋዎችን መንገድ ላይ በማስቆም ፍተሻ እያረገ ነው። ፓስፖርታቸው ያልታደሰ በህገ-ወጥ መንገድ የገቡ እንዲሁም ከዚይ በፊት በተለያየ ነገር የተጠረጠሩ… እንዲሁም ህጋዊ ያልሆኑትን በማሰር ወደ ሀገራቸው እንመልሳለን ብለው ፍተሻውን አጡፈውታል
የመኖሪያ ወረቀት ያላችሁም ስትንቀሳቀሱም ፓስፖርታችሁን መያዝ አትርሱ። በተለይ ግን ተገፍታችሁ እና መከራ ሆኖባችሁ ከኮንትራት ቤት ወጥታችሁ ፓስፖርት እጃችሁ ላይ የሌለ ፓስፖርት ኖሯችሁ መኖሪያ ፍቃድ የሌላችሁ አብዝታችሁ ጥንቃቄ አድርጉ።
ኢትዮጵያውያን ሰንት እንደተያዘ ባይታወቅም ፎቶው ላይ እንደምትመለከቱት ስደተኞች ናቸው። ክፉውን ያርቅልን።
አሜን!!!!!

በጅማ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ካምፓስ የተማሪዎች መኝታ ክፍል ተኩስ ተከፈተ

በጅማ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ካምፓስ ተማሪዎች ተቃውሞ ማሰማታቸውን ተከትሎ በሕወሓት ወታደሮች በቅጥር ጊቢውና በተማሪዎች መኝታ ክፍል ተክስ መክፈታቸው ተሰማ::
ከአካባቢው  የደረሱ መረጃዎች እንዳመለከቱት ኦሮሚያን በ8 ዞኖች ከፋፈለው ከሚመሩት የሕወሓት የመከላከያ ሰዎች መካከል የሆኑት ወታደሮች በጅማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን በመቀጥቀጥ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሳቸው የደረሰን መረጃ አመልክቷል::
እንደ ዓይን እማኞች ገለጻ የጅማ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ካምፓስ በከፍተኛ ውጥረት ውስጥ ይገኛል:: በርካታ ተማሪዎች በጥይት እና በደረሰባቸው ቅጥቀጣ ተጎድተዋል::
Haregeweyn Abeje's photo.

‹‹ብሔርን ከብሔር ከማናቆር ያለፈ ፋይዳ የሌለው ሐውልት እስከ መሥራት ተደርሷል፤›› ፕሮፌሰር ባህሩ


ፕሮፌሰር ባህሩ ይህን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ ከምሁራን ጋር ባደረጉት ውይይት ላይ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ይለማርያም ውይይቱን ሲከፍቱ ባሰሙት ንግግር፦”መንግሥት ኅብረተሰቡን ለማንቀሳቀስ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን፣ እንዲሁም ሌሎች ፕሮጀክቶችን አገራዊ መግባባት ለመፍጠር በሚያስችል አኳኋን ቀርፆ ተግባራዊ ለማድረግ እየጣረ ቢሆንም፣ ፖለቲከኛው ጥግ ጥጉን ይዞ ከመታኮስ ባለፈ የመቻቻልና የመወያያት ዴሞክራሲያዊ ባህልን ማዳበር አቅቶታል” ብለዋል። አቶ ሀይለማርያም አክለውም፦ ‹‹በአንድ ትውልድ የተጣመመ የፖለቲካ ባህል ተሸክመን ቁርሾን ለዚህ ትውልድ እያስተላለፍን ነው፤›› ሲሉ ይተደመጡ ሲሆን፤ “አመፅ የማይቀሰቀስ የሐሳብ ብዝኃነት እንዴት ነው እዚህ አገር መፍጠር የሚቻለው?” ሲሉም ጠይቀዋል፡፡ ያቶ ሀይለማርያምን ማብራሪያ ተከትሎ ሀሳብ ለመሰንዘር እድል ያገኙት የኢትዮጵያ ታሪክ ተመራማሪ ፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴ ፦‹‹የኢትዮጵያ ህዳሴ ከታሪክ ጋር የተሳሰረ ነው፡፡ ህዳሴውን ዕውን ለማድረግ የኢትዮጵያን ታሪክ ማወቅ ያስፈልጋል፤ አሁን ላይ በኢትዮጵያ ታሪክ ዙሪያ ከፍተኛ ብዥታ ይታያል፤›› ብለዋል፡፡ “የብሔር ብሔረሰብን ታሪክና አገራዊ ታሪክን ለማጣጣም ችግር እየተፈጠረ እንደሆነ ያወሱት ፕሮፌሰር ባህሩ፣ ‹‹ብዙ ጊዜ ከሚያቀራርቡን ይልቅ የሚያለያዩንን ማጋነን እየተለመደ መጥቷል፤›› ብለዋል፡፡ ‹‹ብሔርን ከብሔር ከማናቆር ያለፈ ፋይዳ የሌለው ሐውልት እስከ መሥራት ተደርሷል፤›› ያሉት ፕሮፌሰር ባህሩ፤‹‹እነዚህን ችግሮች አስወግዶ አገራዊ መግባባት በመፍጠር ረገድ መንግሥት ምን ያህል ተዘጋጅቷል?›› ሲሉ ጠይቀዋል፡፡ አንድ ምሁር በበኩላቸው “የኢትዮጵያ ህዳሴ”የተባለበት ምክንያት ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ለማንቀሳቀስ ታስቦ መሆኑ እንደሚያስደስት በመጠቆም፣ በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ ያለው ሁኔታ ግን ሕዝቡን ለህዳሴ ከማነሳሳት ይልቅ ቀዝቃዛ ውኃ እየቸለሰበት መሆኑን ተናግረዋል፡፡ አሁን ባለው ፖለቲካዊ ሥርዓት የተለየ አመለካከት ማስተናገድ የማይችል፣ ይልቁንም የሚያሸማቅቅ መሆኑንም ምሁሩ ጠቁመዋል። ‹‹አንዳንድ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች የፖለቲካ ምኅዳሩ ጠቧል ይላሉ፡፡ ነገር ግን የጠበበው ሁሉም ነገር ነው፡፡ የጋዜጠኝት ምኅዳሩ፣ የሲቪል ሶሳይቲ ምኅዳሩ፣ የነጋዴነት ምኅዳሩ፣ ሁሉ ጠቧል››ያሉት ምሁሩ፤ ይኼ የሆነው የወጡትን የፀረ ሽብር፣ የፀረ ሙስና፣ የግብር፣ የበጎ አድራጎት አዋጆች በመቀጠም መሆኑንም ገልጸዋል፡፡ ‹‹ኢሕአዴግ መስከረም ላይ ባካሄደው ጉባዔ በአገሪቱ ያለውን የመልካም አስተዳደር ችግር ጠቅሶ በዋናነት ከፍተኛውን አመራር ተጠያቂ ማድረጉን እንደገለጸ ያስታወሱት ምሁሩ፤ “እርስዎ በጥቅምት ወር ካቢኔዎን ሲያሾሙ ግን ፓርላማ ይዘዋቸው የመጡት እኒያኑ የድሮ ካቢኔ አባላትን ነው፡፡ በካቢኔው ያላካተቷቸውን ደግሞ አማካሪ ብለው አጠገብዎ አድርገዋቸዋል፤ይኸው በመጋቢት ወርም ምንም ለውጥ የለም” ሲሉ ተችተዋል፡፡ የኢትዮጵያ ታሪክን በተመለከተ ስላለው ብዥታ ፕሮፌሰር ባህሩ ያነሱትን ሀሳብ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያምም እንደሚጋሩት ገልጸዋል። አቶ ሀይለማርያም አያይዘውም፦‹‹‹‹በመጀመርያዎቹ ምዕተ ዓመታት አካባቢ የነበረው የኢትዮጵያ ታሪክ የእያንዳንዱ ብሔር ብሔረሰብ ታሪክ ነው፣ በዚህ ላይም መግባባት አለብን፤›› ብለዋል፡፡ በተነሱት ሌሎች ጥያቄዎችና አስተያየቶች ዙሪያ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

Wednesday, March 16, 2016

ገንዘባችሁን ከሕወሓት ባንኮች ከወጋገንና አንበሳ ባንኮች አውጡ”!! – አርበኞች ግንቦት 7


የኢትዮጵያ ሕዝብ በአለፉት 23 ዓመታት በህወሓት ዘረኛ አገዛዝ የደረሰበት ስቃይ እንዲቀንስ፤ ገዢዎቹ ከጫንቃው እንዲወዱ፤ ህወሓትን አውርዶ የሚፈልጋቸው መሪዎችን በነፃነት እንዲመርጥ ሲጠይቅና አቤቱታ ሲያሰማ ቆይቷል። በ1997 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ሕዝብ ምኞት የሚሳካ መስሎ የታየ የነበረ ቢሆንም በአገዛዙ አረመኔዓዊ እርምጃ ተሰናክሏል። ከጥቂት ዓመታት ወዲህ “ድምፃችን ይሰማ” የሚሉ አቤታዎች ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች መምጣት ጀምሯል – “ድምፃችን ይሰማ ሙስሊሞች”፣ “ድምፃችን ይሰማ ኦርቶዶክሶች”፣ “ድምፃችን ይሰማ መምህራን”፣ “ድምፃችን ይሰማ ተማሪዎች”፣ … ወዘተ። በተለይ ሙስሊም ወገኖቻችን በተደራጀ መንገድ “ድምፃችን ይሰማ” እያሉ ሲወተውቱ ሦስት ተከታታይ ዓመታት አልፈዋል። ወገኖቻችን “ድምፃችን ይሰማ” በማለታቸው ተደብድበዋል፣ ታስረዋል፣ ተገድለዋል።
wegagen bank
አቤቱታ የሚሰማ ጆሮ የሌለው አገዛዝ ሲገጥም ምን ይደረጋል? ለአቤቱታ አቅራቢው ያለው ምርጫ ከሁለት አንድ ነው። ወይ አቤቱታን እርግፍ አድርጎ ጥሎ በደልን ተቀብሎ “እህህ !” እያሉ መኖር፤ አሊያም “በቃኝ፣ እንቢ አልገዛም” ማለት፤ ሦስተኛ ምርጫ የለም።
አቤቱታ ሰሚ ሲያጣ እና ሕዝብ መሮት “እንቢኝ፣ አልገዛም” ሲል ነው ሕዝባዊ እምቢተኝነት ተቀሰቀሰ የሚባለው። ሕዝባዊ እምቢተኝነት ብዙ መልኮችና ቅርጾች ቢኖሩትም ዋነኛዎቹ መገለጫዎች ሁለት ናቸው። አገዛዙ ሕዝብ እንዲያደርግ የሚፈልገውን አለማድረግ እና/ወይም አገዛዙ ሕዝብ እንዲያደርግ የማይፈልገውን ማድረግ።
ለምሳሌ፣ አገዛዙ ሹማምንቱ እንዲከበሩ፣ ሕዝብ እንዲታዘዝላቸው ይፈልጋል፤ እንቢ ያለ ሕዝብ ግን የአገዛዙን ሹማምንት ይንቃል፣ በየደረሱት ያዋርዳቸዋል፣ “አልታዘዛችሁም” ይላቸዋል። ማንኛውም መንግስት የዳኝነት ሥርዓቱ እንዲከበርለት ይፈልጋል፤ በደል የመረረው ሕዝብ ግን የአምባገነኖች ችሎት ውሳኔ አይቀበልም፤ ዳኞችንም ዳኝነትንም አያከብርም። ሕዝብ የመንግሥትን ግብር በወቅቱ እንዲከፍል የማንኛውም መንግሥት ፍላጎት ነው። በመንግሥት ያመረረ ሕዝብ ግን ግብር አይከፍልም፤ መክፈል ግድ ከሆነበትም አዘግይቶ፣ አስለፍቶ ነው። የመረረው ሕዝብ ምሬቱን መፃፍ በሌለበት ቦታ ይጽፋል። በደል የበዛበት ሕዝብ “ዝም በል” ሲሉት ይናገራል፤ “ተናገር” ሲሉት ዝም ይላል።
አገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ የሕዝባዊ እምቢተኝተኝነት እርምጃዎች ጅምሮች እየታዩ ነው። በአማራ ክልል፣ ሕዝብ በሹማምንት ላይ የራሱን እርምጃ መውሰድ ጀምሯል። ሕዝብ ራሱ የፓሊስንም የፍርድ ቤትንም ሥራ ተክቶ እየሠራ ነው። ይህ መበረታታት ያለበት ትልቅ እርምጃ ነው። እንደዚሁም ሁሉ በተለይ ወጣቶች ብሶቶቻቸውን በብር ኖቶች ላይ ጽፈው ገበያው እንዲያዘዋውራቸው እያደረጉ ነው። ይህም “የወረቀት ገንዘብን ለተሠራበት ዓላማ ብቻ ተጠቀሙ” የሚለውን ህግ በመጣስ ለቅስቀሳ ሥራ መጠቀም በመሆኑ የሕዝባዊ እምቢተኝነት አካል ነው። በሚቀጥሉት ጥቂት ወራት ውስጥ በርካታ የወረቀት ገንዘቦች በምሬት መግለጫነት ይውላሉ ተብሎ ይገመታል።
በተጓዳኝ በርካታ አማራጭ ስልቶች ሥራ ላይ መዋል ይኖርባቸዋል። ለምሳሌ፣ ተቀማጭ ገንዘብን ከህወሓት ባንኮች ማውጣት በቀላሉ ተግባራዊ ሊደረግ የሚችል ስልት ነው። በውጋጋን ባንክ ተጀምሮ ወደ አንበሳ ኢንተርናሽናል ከዚያም ወደ ንግድ ባንክ ማሸጋገር ይቻላል።
በወገኖቻችን ላይ የግፍ ፍርድ የሚያስፈርዱ አቃቢያነ ህግ እና የግፍ ብይኖችን የሚሰጡ ዳኞች በቸልታ ሊታለፉ አይገባም። በእስር ቤቶችም በወገኖቻችን ላይ ሰቆቃ እየፈፀሙ ያሉ ጨካኞች ከሰላማዊ ሕዝብ ጋር ተደባልቀው ሰላማዊ ሕይወት እንዲመሩ ሊፈቀድላቸው አይገባም። እነዚህ ሁሉ ሊወገዙ፣ ሊገለሉ፣ በየደረሱበት ሊዋረዱ ይገባል።
በአገዛዙ መንግሥታዊ መዋቅር ውስጥ የሚገኙ ወገኖቻችን በሥራቸው ላይ መለገም ተቀባይነት ያለው በጎ ተግባር እንደሆነ ሰፊ ግንዛቤ ሊያገኝ ይገባል። ከአምባገነን ሥርዓት ጋር መተባበር እኩይ ተግባር ሲሆን አምባገነን ሥርዓትን ከውስጥ መቦርቦር ደግሞ የሚበረታታ ሰናይ ሥራ ነው።
ለወያኔ አገዛዝ ግብር መክፈል የምናቆምበት ሰዓትም ተቃርቧል። በራሳችን ገንዘብ ገዳዮቻችን እንዲሰለጥኑብን መፍቀድ የለብንም። ስለሆነም “ግብር አንከፍልም”፤ “መዋጮዎቻችሁ አይመለከቱንም” የምንልበት ቀን ቀርቧል።
በፋይዳ የለሽ ምርጫ የሀገር ሀብት ሲመዘበር ማየት አንሻም። በአግባቡ ለማይቆጠር ድምፃችን አንድም ደቂቃ የምናባክንበት ምክንያት የለምና ሁላችንም የምርጫ ካርዶቻችንን ቀዳደን ቁርጭራጮቹን በየመንገዱ ልንበትናቸው ይገባል።
እነዚህን እነዚህን የመሳሰሉ ናቸው የሕዝባዊ እምቢተኝነት የመጀመሪያ ደረጃዎች። እነዚህን እያደረግን በምስጢር መደራጀታችንን እንቀጥል። ከጥቂት በኋላ አምባገነኑን ሥርዓት የሚያንበረክክ ኃይል እንፈጥራለን። ጥቃት ቢደርስ የሚመክት ኃይል የተደራጀ በመሆኑም ሕዝባዊ እምቢተኝነትና ሕዝባዊ አመጽ ተቀናጅተው እንዲሄዱ ይደረጋል።
አርበኞች ግንቦት 7:የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ሕዝባዊ እምቢተኝነትንና ሕዝባዊ አመጽን አቀናጅቶ ለመምራት የተዘጋጀ፤ ለዚህ የሚያበቃው ድርጅታዊ አቅም እየገነባ ያለ ድርጅት ነው። አርበኞች ግንቦት 7 “እንሰባሰብ በወያኔ ላይ የምናቀርባቸው ተቃውሞዎች በሙሉ ወደ እምቢተኝነት ከፍ እናድርጋቸው” ይላል

ለኢሕአዴግ ጥፋት መነሻው፣ ሕዝብ ያሰማው ቅሬታ አይደለም ተባለ


የአረና ትግራይ ፓርቲና የመድረክ የአመራር አባል አቶ ገብሩ አሥራት ከሌሎች ሁለት የፖለቲካ ተንታኞች ጋር፣ በጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ሪፖርት ላይ በመጽሔቱ ክፍል ትንታኔ ይሰጣሉ
የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ባለፈው ሐሙስ ለፓርልማቸው ባቀረቡት ሪፖርት፣”በኦሮሚያና በሌሎችም አካባቢዎች ለተፈጠረው የሕዝብ ቅሬታ ፓርቲዬና መንግሥቴ ኃላፊ ናቸው” ብለዋል። ምን ማለትነው? “ኃላፊነት መውሰድ” ሲባልስ እስከምን ድረስ ይሄዳል?በዚህና በሌሎችም የጠቅላይ ሚኒስትሩ ሪፖርት ላይ ሦስት እንግዶችን ለትንታኔ ጋብዘናል።
ሁለቱ ከኢትዮጵያ ናቸው፤ አቶ ገብሩ አሥራት፣ የአረና ትግራይ ፓርቲና የመድረክ አመራር አባል፣ አቶ አበባው አያሌው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የታሪክና የሥነ-ጥበብ መምህር፣ ከዚህ ከዩናይትድ ስቴትስ ፕሮፌሰር ዓለማየጉሁ ገብረማራም በካሊፎርንያ ስቴት ዩኒቨርስቲ (California State University) የፖለቲካ ሳይንስና የህገ-መንግሥት መምህር።
ያወያያቸው አዲሱ አበበ፣ ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ሪፖርት አንድ ዘለላ ነቅሶ በማውጣት ይጀምራል። ውይይቱን ለማዳመጥ ከዚህ በታች ያለውን የድምጽ ፋይል ይጫኑ።

Tuesday, March 15, 2016

የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት መቀመጫቸውን በአዲስ አበባ ላደረጉ 21 የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት ተወካዮች በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ገለጻ ማድረጋቸውን ገለጹ፡፡


ሊቀመንበሩ ዛሬ መጋቢት 6/2008 ዓ.ም በአዲስ አበባ የአውሮፓ ህብረት ጋባዥነት በተለያዩ የሀገሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን፣ በተለይ በኦሮሚያ፣ ጋንቤላ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ኮንሶ እና ወልቃይት አካባቢዎች ስለተከሰቱ ህዝባዊ የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች ለተወካዮቹ ገለጻ ማድረጋቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ተናግረዋል፡፡
በኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት ምክትል ኃላፊ ተርሂ ሌተነን በመሩት ገለጻ ላይ ሊቀመንበሩ ኢ/ር ይልቃል በኢትዮጵያ ስላለው የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና ማህበራዊ ቀውሶች ላይ ማብራሪያ መስጠታቸውን ገልጸዋል፡፡ በዚህም በሀገሪቱ በአሁኑ ወቅት 18 ሚሊዮን ዜጎች ለርሃብ መዳረጋቸውን፣ የኑሮ ውድነት መጨመሩን፣ ሙስና መንሰራፋቱን፣ የገቢ አለመመጣጠን መጉላቱን እና የስራ አጥነት ችግር እየከፋ መሄዱን ለተወካዮች መግለጻቸውን ተናግረዋል፡፡
በፖለቲካው መስክም ኢትዮጵያ ውስጥ መድብለ ፓርቲ ፖለቲካ ጨርሶ መዘጋቱን፣ ፓርቲዎች በጸረ-ሰላምነት ተፈርጀው በመንግስት እየተሰለሉ መሆናቸውን በፍርድ ቤት የቀረበ ማስራጃ ማረጋገጡን፣ የሰማያዊ እና መድረክ ፓርቲዎች አባላት በግፍ እስር ላይ መሆናቸውን እንዳብራሩ ለነገረ ኢትዮጵያ አስረድተዋል፡፡
በኦሮሚያ ክልል ህዝቡ መብቱን ለመጠየቅ ለተቃውሞ መውጣቱን ተከትሎ በአራት ወራት ጊዜ ብቻ በመንግስት ከ260 ሰዎች በላይ መገደላቸውን በዝርዝር እንዳስረዱ ሊቀመንበሩ ገልጸዋል፡፡ በወልቃይት የማንነት ጥያቄ አለን በሚል ለትግራይ ክልል እና ለፌደሬሽን ም/ቤት ህጉን ተከትለው ጥያቄ ያነሱ ዜጎች መታሰራቸውንና በመንግስት ሚዲያዎች ግጭት ቀስቃሽ ዘገባ እየቀረበ እንደሆነ መታዘባቸውን፣ ይሄም እንደሚያሳስባቸው ለተወካዮች ማብራራታውን ተናግረዋል፡፡
በመሆኑም ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ችግሮች ከኢህአዴግ በላይ በመሆናቸው መንግስት ሁሉም ፓርቲዎች፣ የማህበራት ተወካዮች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ሌሎች የሚሳተፉበት አካታች ውይይት እንዲደረግ እንዲፈቅድ ጥሪ ማቅረባቸውንና የህብረቱ ሀገራትም ይህ እንዲሆን አስፈላጊውን ግፊት እንዲያደርጉ ማሳሰባቸውን አስረድተዋል፡፡