ከኦባማው ጉብኝት በኋላ አሜሪካ ኢትዮጵያ ተጨማሪ እግረኛ ጦር ወደ ሶማሊያ እንድታስገባ ያዘዘቻት ሲሆን እግረኛ ጦሩም የሚዘምተው በዚህ ሳምንት መጨረሻ ወይም በሚቀጥለው ሳምንት መጀመሪያ መሆኑ ታውቋል። ለአልሸባብ ማገዶነት የተመረጠው ክፍለጦር ደግሞ በሜጄር ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ (ዋናው መሪ ስዩም ሃጎስ ቢሆንም) የሚመራው የምዕራብ ክፍለ ጦር ሲሆን ለዚህ ዘመቻ የተመለመሉ ወታደሮች በአሁኑ ሰዓት ጋምቤላ ውስጥ በዝግጅት ላይ እንደሚገኙ ተረጋግጧል።
እግረኛው ጦር ሊዘምትበት የታቀደው የደቡቡ ሶማሊያ አካባቢ ሲሆን ይህን አካባቢ አልሸባብ ለረጅም ጊዜ ጠንቅቆ የሚያውቀው እንደሆነና ቦታውም በእግር ጦር “የማይሞከር” የሚባል አይነት እንደሆነ መረዳት ተችሏል። የዘመቻውን ምንነትና አይነት የተረዱ አንዳንድ ወታደሮች በከፍተኛ ጭንቀትና የተስፋ መቁረጥ ስሜት ውስጥ እንደሚገኙ፤ «መሞታችን ካልቀረ እዚሁ አገራችን ላይ ስናመልጥ እንሙት» ብለው ከሰራዊቱ ሊያመልጡ የተዘጋጁም እንዳሉ መረጃው አመላክቷል።
ከሁለት ወራት በፊት መንገድ ላይ በተጠመደ ፈንጂ ከ፴(ሰላሳ) በላይ የኢትዮጵያ ወታደሮች ተገድለው መንግስት ጉዳዩን ሸፋፍኖ ማለፉ ይታወሳል።
እስከመቼ ነው ወንድሞቻችን ለባለስልጣኖች ሆድ ሲባል ለማገዶነት የሚቀርቡት???

No comments:
Post a Comment