Thursday, August 27, 2015

በሆቴል ባለቤቶች ቸልተኝነት የተነሳ የደረሰ እጅግ አሳዛኝ አደጋ ።


ለልጆችህ ቃል ገብተሀል ፣ ት/ት ከመከፈቱ በፊት ከአዲስ አበባ ወጣ አርገህ ልታዝናናቸው እናም በቃልህ መሰረት 3 ልጆችህን ይዘህ አሪፍ አድርጎ ሊያዝናችሁ እንደሚችል ወዳሰብከው ወደ ወሊሶ ትነዳና ነጋሽ ሎጅ ትገባለህ ትንሽ አረፍ ብለህም ወደ መዋኛው ቦታ ከደቂቃዎች በፊት ከሄዱት ሁለት ወንድሞቿ ጋር ለመቀላቀል የፈለገችውን ሴቷን ልጅህን ይዘህ መዋኛው ገንዳ ጋር ስትደርስ የሁለት ልጆችህን ሬሳ በመዋኛ ገንዳው ላይ እየተንሳፈፈ ትደርሳለህ ። ምን ይውጥሀል ከደቂቃ በፊት ይስቁ ይቦርቁ የነበሩ ልጆች አሁን ሬሳ ሆነው ስታይ ምን ታደርጋለህ ? ለማን ነው አቤት የምትለው ? ትናንት የሆነው ይሄ ነው ። ይሄ አሳዛኝ ነገር ነበር የተከሰተው ። አባት ላዝናና ብሎ ሳቂታ በ 13 እና በ 12 አመት አመት የሚገመቱ ቆንጅዬ ልጆች ከቤት ይዞ ወጣ ፣ በደቂቃዎች ውስጥ በጨካኝ ሞት ሁለት ልጆቹን አጣ ምን ይዞ ይመለስ ?
በሆቴሉ ውስጥ ላይፍ ሴቨር ባለመኖሩ ምክንያት ብቻ ታዳጊ ህፃን ነብዩ ዳንኤልና ፣ ታዳጊ ህፃን ቅዱስ ዳንኤል ሊዝናኑ በወጡበት ቦታ ቀሩ ፣ ገንዘባቸውን እንጂ የደንበኛ ህይወት ግድ በማይሰጣቸው ንዝህላል የ ነጋሽ ሎጅ አስተዳደሮች በፈፀሙት መቼም የማይካስ ስህተት በደቂቃ ሁለት ልጆቹን ያጣውን አባትና ሀዘኗን መቋቋም ያልቻለችውን እናት ማየት ምንኛ ልብ ይነካል ? ለመሆኑ ይህን ፈቃድ የሚሰጠው ቢሮ አንድ መዋኛ ገንዳ በውስጡ ያካተተ መዝናኛ ሲሰራ ላይፍ ሴቨር እንዲቀጠር የሚያስገድድ ህግ የለም እንዴ ? መንግስት ይህን በሆቴሉ አስተዳዳሪዎች ንዝህላልነትየተፈፀመን ከግድያ የማይተናነስ ወንጀል እንዴት ያየው ይሆን ? ይህን አሳዛኝ ነገር ከሰማን በሁዋላ ስለ ጉዳዩ ተጨማሪ ማብራሪያ ለመጠየቅ በ 011 3410002 ወሊሶ ወደሚገኘው ነጋሽ ሎጅ ደውለን ፣ ስልካችንን የተቀበለው ሰው ጉዳዩ ከሚመለከተው ሰው ጋር እንደሚያገናኘን ቃል ገብቶ ፣ መልሰን ስንደውል ስልካቸውን አጥፍተዋል ። በርግጥ እንዳሰቡት ከኛ መሸሽ ችለዋል ። ከህሊና ፍርድስ ኸረ ከህግስ ማምለጥ ይችሉ ይሆን ?
እንደወጣችሁት ለቀራችሁት ታዳጊዎች እግዚያብሄር ነብሳችሁን በአፀደ ገነት ያኑረው ።
.
note ፥ ይሄን አሳዛኝ ሁኔታ ለሌላው ት/ት ይሆን ዘንድ ሼር ማድረግ ብንችል መልካም ነው ። ነገም ሌላ እናት ፣ ነገም ሌላ አባት ልጆቹን ሊያዝናና ይዞ ወጥቶ ባዶ እጁን እንዳይመለስ ሊረዳ ይችላል
(ዋሲሁን ተስፋየ )

No comments:

Post a Comment