Sunday, August 9, 2015

የድረሱልን ጥሪ ያሰሙት የስልጤ-ቂልጦ ቅድስት ማርያም ምእመናን ‹‹ሕዝብን አሸብራችኋል›› በሚል እስከ ዘጠኝ ዓመት ተፈረደባቸው

በኦርቶዶክሳዊ ክርስትናቸው ለሚደርስባቸው በደል መፍትሔ በመሻት የድረሱልን ጥሪ ያሰሙት በምሥራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ የስልጤ ጎሞሮ
ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ሰበካ መንፈሳዊ ጉባ እና ሕንፃ አሠሪ ኮሚቴ አባላት ፣ የሐሰት ወሬዎችን በማሰራጨት ሕዝብን አሸብራችኋል፤ በወረዳው የአስተዳደር
አካላት ላይ ጥርጣሬን በማስፋፋት እና የሕዝብን አስተሳሰብ በማወክ በሕዝብ ዘንድ ጥላቻን አነሣስታችኋዋል በሚል እስከ
ዘጠኝ ዓመት የእስር ቅጣት ተፈረደባቸው፡፡
በደቡብ ክልል ስልጤ ዞን የምሥራቅ አዘርነት በርበሬ ወረ ፍርድ ቤት መደበኛ ችሎት፣ ባለፈው ሳምንት ዓርብ በሦስት ዓመት የእስር ቅጣት ውሳ ያሳለፈባቸው ተከሣሾቹ፣ በሐዲያ እና ስልጤ ሀገረ ስብከት በምትገኘው የቂልጦ ጎሞሮ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን
አመራሮች የኾኑ ስድስት ምእመናን ናቸው፡፡
ተከሣሽ ምእመናኑ ፣ለ ላይ የተመለከቱትን ድንጋጌዎች በመተላለፍ እና የቤተ ክርስቲያኗን ማኅተም በመጠቀም ለተለያዩ መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ላልኾኑ
ተቋማት ባደረሱት እና ሐራ ዘተዋሕዶ በተባለው ድረ ገጽ ላይ ››ብሏል፡፡
በሚል ርእስ በግንቦት ወር መጀመሪያ ላይ የተሰራጨውና የስድስቱም ተከሣሾች ፊርማ ያረፈበት ኢትዮጵያውያን የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በመኾናችን ምክንያት ግፍና በደል
እየደረሰብን ነው፤ የእምነቱ ተከታይ የኾኑ የመንግሥት ሠራተኞች ያለበቂ ምክንያት ከሥራ መባረር፣ የግድያ ዛቻ
እና የተለያዩ በደሎች እየደረሰባቸው ነው፤ በጭንቀት እና በስጋት ላይ ነን፤ መቼ ምን እንደምንኾን አናውቅም፤
በማለት በወረዳው የአስተዳደር አካላት ላይ ጥርጣሬን ያስፋፋና በሕዝብ ዘንድ ጥላቻን ያነሣሣ እንደኾነ በወንጀሉ ዝርዝር ተገልጧል፡፡
ወረዳዋ፣ ፍጹም ሰላም እና የአስተዳደር አካላቱ እና ሕዝቡ፤ የአምልኮ ቦታ አመቻችቶ ከመስጠት አልፎ የቤተ ክርስቲያን
መሠረት ሲጣል ከተለያዩ ቦታዎች የመጡ እንግዶችን በመቀበል እና ለቤተ ክርስቲያኗ ግንባታ ያልተቆጠቡ ድጋፋቸውን እየሰጡ
ያሉበት ነው ያለው ዐቃቤ ሕግ፤ ስለ ወረዳው የማያውቁና በኢንተርኔት የተለቀቀውን ጽሑፍ የተመለከቱ በተለያዩ አካባቢዎች
የሚኖሩ የኅብረተሰብ ክፍሎች በወረዳዋ የሚኖሩ ወዳጅ ዘመዶቻቸው አደጋ ደርሶባቸዋል በሚል በድንጋጤ እና በስጋት በመውደቃቸው በወሬ ሕዝብን
የማሸበር ወንጀል መፈጸሙን ገልጧል፡፡
በወረዳው የተለያዩ ተቋማት የመንግሥት ሠራተኞች የኾኑት ማስረሻ ሰይፈ ቤተ ሥላሴ፣ ሙሉጌታ አራጋው ጥሩነህ፣ ሀብታሙ ተካ ዳግሰው፣ ማሩ ለማ አጋ እና ንጋት ለማ ጁታ እያንዳንዳቸው የአምስት ዓመት ከስድስት ወራት የእስር ውሳኔ ተላልፎባቸዋል፤ በዋና አነሣሽነት የተከሠሡት እና
በሌላ ክሥ የተላለፈባቸውን የአንድ ዓመት ከስምንት ወራት እስር በመፈጸም ላይ የሚገኙት የቤተ ክርስቲያኗ ሰበካ ጉባኤ እና
ር የማርያምወርቅ ተሻገር፣ በስምንት ዓመት ከስምንት ወራት እስር እንዲቀጡ ነው የተወሰነባቸው፡፡
ር የማርያምወርቅ ተሻገርን ጨምሮ ስድስቱም ተከሣሾች ካለፈው ዓርብ ከቀትር
በኋላ ጀምሮ በወራቤ ዞን ማረሚያ ቤት እንደሚገኙ ታውቋል፡፡
፣ በእምነታቸው ምክንያት በአንዳንድ ባለሥልጣናት የደረሰባቸውን አድልዎ እና በደል ለቤተ ክህነት እና ለመንግሥት አካላት
ለማሳወቅና መፍትሔ እንዲሰጣቸው ለመጠየቅ መዘጋጀቱን
በማስታወስ፣ በኢንተርኔት መሰራጨቱ ከሰበካ ጉባኤው እና
ከሕንፃ አሠሪ ኮሚቴው አባላት ዓላማና ፍላጎት ውጭ እንደኾነ
የሰበካ ጉባኤው ጽ/ቤት በቂ/ጉ/ቅ/ማ104/07 በቀን
04/11/07 ‹‹ማስተካከያ›› በሚል ርእስ በጻፈው ደብዳቤ
መግለጫ ሰጥቶበት እንደነበር ተገልጧል፡፡ል፡፡11831814_1706416892915588_4059790612458415956_n

ይኹንና የሐዲያ እና ስልጤ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅን
ጨምሮ የወረዳ እና የዞን ከፍተኛ አመራሮች፣ የሃይማኖት
አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎች በተገናኙበት መድረክ
የተፈጠረውን ችግር በመግባባት ለመፍታት እና ከሥሩ
ለማድረቅ በተስፋ እየተጠበቀ ባለበት ኹኔታ፣ የቤተ ክርስቲያኗ
ምእመናንና አመራሮች ከሥራ መፈናቀላቸው ሳያንስ ለእስር
መዳረጋቸው በእጅጉ እንዳሳዘናቸው ኢትዮ-ምኅዳር
ያነጋገራቸው የወረዳዋ ምእመናን ገልጸዋል፡፡ የፍትሕ ሒደቱም
ተከሣሾቹ በዘፈቀዳዊ እስር፣ በሽምግልና ሰበብ እና
በቀጠሮ የሕግ አማካሪ የማግኘት፣ የማማከር እና
የመከላከል መብታቸው የተጣበበበት እና ከፍተኛ ተጽዕኖ
የተደረገበት እንደነበር አስረድተዋል፡፡
ከውሳኔው በኋላም በየምሽቱ በወረዳው አስተዳደር ቢሮ ድረስ
እየተጠሩ፣ ‹‹ከዚኽ በኋላ በማንኛውም ነገር አንዳች ስታደርጉ
ብናያችኹ አስፈላጊውን ርምጃ እንወስድባችኋለን የሚል ዛቻ
እና ማስፈራሪያ እየተፈጸመብን ነው፤›› ብለዋል፡፡ የሥራ ልምድ
እና የድጋፍ ደብዳቤ በሚጠይቁበት ወቅትም ሰብአዊ እና
የዜግነት መብታቸውን የሚጥስ በደል እየደረሰባቸው እንደኾነና
በአገልግሎታቸው ጉልሕ አስተዋፅኦ ያላቸው ጠንካራ ምእመናን
በየምክንያቱ ከአካባቢው መራቅን እንደመረጡ አስረድተዋል –
‹‹በሥራ ልምዳችን ላይ አስነዋሪ ቃላት እየጻፉ፣ ይኼም
ሲበዛባችኹ ነው፤ ይህንንም እኛ ስለኾን ነው
የሰጠናችኹ ይሉናል፡፡››
ቅዳሴ ቤቱን የሚጠብቀው ቤተ ክርስቲያኑ፣ የዕንጨት እና የሽቦ
አጥሩ እየተነቃቀለ እና ከብት እየተነዳበት ሣሩም በከብት
እንዲበላ እየተደረገ እንዳለ ተጠቁሟል፡፡
‹‹መታሰር በክርስትና ያለ ነው፤ መገፋታችን ጥሩ ነው፤›› ያሉት
የሐዲያ እና ስልጤ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ አባ
ቢንያም ከበደ በበኩላቸው፣ የፍርድ ቤቱ የውሳኔ ግልባጭ
ባይደርሳቸውም ጉዳዩን ለክልሉ አስተዳደር እና ለፍትሕ ቢሮ
ማሳወቃቸውን ተናግረዋል፡፡ ጠበቃ በማቆም ይግባኝ ለመጠየቅ
ማሰባቸውንና ክልሉም ‹‹ነገሩ ላይ ጣልቃ እንዲገባ ጥሩ
አቅጣጫ ተይዟል›› ብለዋል፡፡
የወረዳው አስተዳደር በሰጠው ቦታ ላይ ጥቅምት 24 ቀን
2007 ዓ.ም. በአህጉረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ
ቀሌምንጦስ መሠረቷ የተጣለውና ሥራዋ የተጠናቀቀው የቂልጦ
ጎሞሮ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ቤት(ምረቃ) ሰኔ
21 ቀን ለማከናወን ታስቦ የነበረ ቢኾንም ላልተወሰነ ጊዜ
መተላለፉንና ገና እንዳልተሰወነም ዋና ሥራ አስኪያጁ
ተናግረዋል፡፡
በስልጤ ዞን ምሥራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ቂልጦ ከተማ
በየዕለቱ ከሚደርስባቸው ማሸማቀቅ የተነሣ በጭንቀት ውስጥ
የሚገኙትን ኦርቶዶክሳውያን ለማጽናናት፣ ከሐዋሳ እና ከአዳማ
የምእመናን ጉዞዎች እየተደረጉ ሲኾን ሰላማቸው እስኪጠበቅ
ድረስም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተገልጧል፡፡

No comments:

Post a Comment