Wednesday, August 19, 2015

ከ100 በላይ ኢትዮጵያዊያን በኬንያ ፖሊስ ተያዙ


በኬንያ ፖሊሶች በቁጥጥር ስር የዋሉት 100 ኢትዮጵያዊያን ትናንት አመሻሽ ላይ ነው፡፡በወጣትነት የእድሜ ክልል የሚገኙት ታሳሪዎቹ በተፋፈነ ሁኔታ በአንድ ትልቅ መኪና ተሳፍረው ወደ ናይሮቢ በመገስገስ ላይ እንዳሉ በፖሊሶች በተደረገ ፍተሻ መያዛቸው ታውቋል፡፡ታሳሪዎቹ ወደ ደቡብ አፍሪካ ለማቅናት አቅደው የነበሩ መሆናቸውም ተነግሯል፡፡ እንደ ዴይሊ ኔሽን ዘገባ ከሆነም ስደተኞቹ በሞያሌ በኩል በድብቅ በማለፍ ወደ መሩ ካውንቲ ማምራታቸውን መረጃ የነበራቸው የኬንያ ፖሊሶች በቀላሉ በቁጥጥር ስር ሊያውሏቸው ችለዋል፡፡ ኢትዮጵያዊያኑ የሚገኙበት የካንጌታ ፖሊስ ጣቢያ ኃላፊዎች ምርመራ በማከናወን ላይ እንደሚገኙ መናገራቸው ተወስቷል፡፡
በሚያዘያ ወር ከሁለት የተለያዩ ቤቶች ከኢስሊና ኪማኢኮ 40 ኢትዮጵያዊያን በፖሊሶች በተደረገ አሰሳ መታሰራቸው ይታወቃል፡፡
እስረኞቹ ወደ ደቡብ አፍሪካ ለማምራት ወደ ኬንያ መግባታቸውን ከመናገር ውጪ ምንም አይነት የጉዞ ዶክመንት አለመያዛቸው ተስተውሏል፡፡ ስደተኞቹ በሁለት ቡድን ተከፋፍለው ወደ ሁለት ቤቶች እንዲያመሩ ከመደረጋቸው አስቀድሞ ወደ ኬንያ በአንድነት መግባባቸውን የተናገሩት ፖሊስ ኦፊሰሩ በርናርድ ኒያክዋካ ‹‹ምቹ ባልሆነ ሁኔታ ውስጥ እንዲኖሩ ተደርገው ነበር፡፡
በዚህ ውስጥ ተሳትፎ ሲያደርጉ የነበሩ ሰዎች ላይ ክስ ለመመስረት ወኪሎቻቸውን በማፈላለግ ላይ እንገኛለን››ብለዋል፡፡

No comments:

Post a Comment