Monday, August 31, 2015

በትግራይ ወረዳዎች ተመድበው የሚሰሩ አስተዳደሮች ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች እየተገደሉ ነው


በትግራይ ወረዳዎች ተመድበው የሚሰሩ አስተዳደሮች ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች እየተገደሉ እንደሚገኙ ከተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች ያገኘነው መረጃ አመለከተ።በትግራይ ምስራቃዊ ዞን የአዲግራት ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ሃላፊ ሆኖ ሲሰራ የነበረው አፅብሃ ወልደገብርኤል የተባለው ለሆዱ ያደረ የህወሓት ኢህአዴግ ካድሬ ነሃሴ 12 /2007 ዓ/ም ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ቤቱ ውስጥ ተገድሎ እንደተገኘ ምንጮቻችን ከከተማዋ ገለፁ።
ፖሊስ ጉዳዩን ለማጣራት በሚል የተወሰነ እንቅስቃሴ ቢያደርግም ነዋሪው ህዝብ ሊተባበራቸው ባለመቻሉ ምክንያት በግለሰቡ አሟሟት ምክንያት ተሳስሮ ሰዎች ሊጠረጥሩት ሞክረው ህዝቡ ሊቀበላቸው ባለመቻሉ ምክንያት ገዳዩ ሳይታወቅ ዝምታን እንደመረጡ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።
በተመሳሳይ- በሳዕስዕ ፃዕዳ እምባ ሳዕስዕ ቀበሌ የሚኖር ህዝብ ደስታ ጎቢጥ የተባለ የቀድሞ ታጋይ ባልታወቁ ሰዎች ነሃሴ 13 2007ዓ/ም በድንጋይና በዱላ እንደተገደለ ለማወቅ ተችሏል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ- ተገድለዋል እየተባሉ ያሉት ሰዎች ከአካባቢው ካድሬዎች ጋር ስምምነት ያልነበራቸውና ጥቅም ያጣላቸው የኢህአዴግ አባላት ናቸው የሚል ጥርጣሬ በህዝቡ ዘንድ እንዳለ ከአካባቢው ያገኘነው መረጃ አክሎ ገልጿል።

No comments:

Post a Comment