
ህውሓት ባካሄደችው ጠቅላላ ጉባሄ ከመረጠቻቸው 9 ከፍተኛ አመራሮች መካከል ወ/ሮ አዜብ መስፍን ይገኙበታል፡፡ የወ/ሮ አዜብ መስፍን በከፍተኛ አመራር ደረጃ መመራጣቸው ፣በቀጣይ በድርጅቱ ውስጥ የአቶ መለስ …ዜናዊ “ዕራይ” ከሚዲያ ሽፋን እና ከንግግር ድምቀት ባለፈ የባለቤታቸውን “ራእይ” በተግባር ለመፈፀም እና ለማስፈፀም ከፍተኛ የሆነ ትጋት እንደሚያደርጉ የሚጠበቅ ነው፡፡
ከውሓት ጀርባ ድርጅቱን የሚመሩት አቦይ ስብሓት ነጋ እና የእሳቸውን ቡራኬ የሚቀበሉ ድግሞ ፤ የአቶ መልስ ዜናዊ “ራእይ” ከግለሰብ ፍላጎት አልፎ የድርጅት መገለጫ እና ማስፈፀሚያ መሆን የለበትም የሚል ፍልስፍና ይከተላሉ፡፡ በዚህም ምክንያት ከወ/ሮ አዜብ እና የእሳቸው ታማኝነት ከሚያረጋግጡ ጋር አንገት ለአንገት ተያይዘው መፋጠጣቸው የማይቀር ሃቅ ነው፡፡
ይህ ደግሞ በህውሓት እና በኢህአዲግ ድርጅት በቀጣይ አለመረጋጋት የበዛበት የስልጣን ውጣ ውረድ መብዛቱ ከወዲኹ የሚጠበቅ ነው፡፡ ለማስታውስ ያልህ አቶ መለስ ሞቱ ሚስጥር በሆነበት ወቅት አቦይ ስብሓት ነጋ “መለስ_ኖረ_አልኖረ ፣በቀለ ኖረ አልኖረ፣ ፋጢማ ኖረች አልኖረች ……….”ማለታቸው የሚታወስ ነው፡፡
የህውሓት የትኛውም ቡድን የሚፈልገውን ዓላማ ለማስፈፀም እና ለመፈፀም የሚችለው ኢህአዴግ እንደ ድርጅት መቀጥል ሲችል ብቻ ነው፡፡አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ በህውሓት ፊት አውራሪነት የሚመራው የኢህአዴግ ገዥው መንግሰት ውጫዊ እና ውስጣዊ በሆኑ ምክንያቶች እድሜው አጭር እንደሚሆን የብዙ ሰው ግምት ነው፡፡
ይድነካቸው
No comments:
Post a Comment