
ነሀሴ 14,12,07ዓ.ም የታክሲ ሾፌሩ ከነመኪናው ወደ ቤቱ አልተመለሰም የመኖርያ ስፍራው ከወይራ ሰፈር ወደ ቤተል ሲኬድ ፓስታቤት አካባቢ በቅ/ጊዮርጊስ ክሊኒክ መግብያ 100ሜ ገባ ብሎ ነው ፡፡ በነጋታውም የለም፡፡ ቤተሰቦቹ ተደናግጠው ለፖሊስ አመለከቱ።
ፖሊስም ከአንድ ሳምንት የአሰሳና የምርመራ ቆይታ በሁዋላ በ20, 12,07 ዓ.ም ይዞት የመጣው ዜና ግን የሾፌሩን ቤተሰቦች ብቻ ሳይሆን የቤተል እና አካባቢውን ነዋሪዎች ያስደነገጠና አንገት ያስደፋ ነበር፡፡
ኤፍሬም ተሾመ ገና የ23 አመት ወጣት ሲሆን የሚኒባስ ታክሲ በማሽከርከር ይተዳደራል፡፡ ስሙ ያልታወቀው የታክሲ ረዳት ደግሞ እድሜው ገና በ አስራዎቹ የሚገመት ታዳጊ ህፃን ነው፡፡
የስራ ሰአት ማብቅያቸው ላይ የመጨረሻ ቢያጆ እንደሄዱ ኮንትራት ይጠየቃሉ። ጠያቂዎቹ አምስት ሲሆኑ “ቤተል ነዳጅ ማደያው ጀርባ ጋር ሰው እንጭናለን “ይላሉ። ኤፍሬምም ባለቀ ሰአት ጥሩ ስራ ተገኝ ብሎ ወደ ተባለው ስፍራ ታክሲውን ይዞ ገባ፡፡
ይሁንና ቢታይ የሚገባ ሰው የለም፡፡ አምስቱ ግለሰቦች በፍጥነት በገመድ ሾፌሩንና እረዳቱን አንቀው ይገድላሉ፡፡ ከዛም አስከሬኑን ይዘው ወደ ገፈርሳ በማምራት ድልድይ ውስጥ ይጥሏቸዋል፡፡
የቤተሰቡ አባላት ይህ መረጃ የተነገራቸው ፓሊስ ከአምስቱ ተጠርጣሪዎች መካከል ሁለቱ የዘረፋትን መኪና ለመሸጥ በማስማማት ላይ እንዳሉ በቁጥጥር ስር በማዋሉ እና ድርጊታቸውንም ስለተናገሩ ነው፡፡
የሚያሳዝነው ይህ መረጃ እስከተጠናከረበት ሰዐት ድረስ የሟች ሰፈር ልጆች የገፈርሳ ነዋሪ እና ፖሊስ አስከሬኑን እየፈለጉ ቢሆንም ማግኘት አልተቻለም፡፡
No comments:
Post a Comment