Wednesday, August 12, 2015

መጽሐፍ ቅዱስን ለወንጀል መፈጸሚያነት የሞከረች ወጣት ለእስራት ተዳረገች


ሞኒካ ራየንስ በአሜሪካ የደቡብ ካሮሊና ነዋሪ ስትሆን ባለፈው አርብ አንድ በህግ ጥላ ስር የሚገኝ ወዳጇን ለመጠይቅ ወደ ዩኒየን እስር ቤት መጽሐፍ ቅዱስን ይዛ ጎራ ትላልች ። የ24 አመቷ ሞኒካ የእግዜአብሔር ቃላት ያለበት ፣ በሃዘን እና በመከራ ወቅት አጽናኝ የሆነው መጽሐፍ ቅዱስን ይዛ እስረኛው ዘመዷን መጠየቋ የተባረከ ሐሳብ ነበር ።
በተጠቀለለ ወረቀት ሽፋን ላይ “መጽሐፍ ቅዱስ “ የሚል ማስታወሻ ያሰፈረቸው እና ለእስር ቤቱ ፖሊሶች ለዘመዷ አሳልፈው እንዲሰጡላት ከአደራ ጭምር የጠየቀችው ሞኒካ ያ “ መጽሓፍ ቅዱስ “የተባለው ስጦታዋ ይዘቱ ግርምታ እና ጥርጣሬ የፈጠረባቸው የእስር ቤቱ ሐላፊዎች “መጽሐፍ ቅዱሱን” በልዮ የ መመርመሪያ መሳሪያ (X-Ray Scan) ሲመለከቱት “መጽሓፍ ቅዱሱ “ መጽሓፍ ቅዱስ ብቻ ሳይሆን በውስጡ (በመጋጠሚያው )ላይ በሲጋራ መልክ የተጠቀለሉ ሶስት አደንዛዥ እጾች (ማሪዮና) እና የሲጋራ ዱቂቶች ተደብቀው ያገኛሉ ። ፖሊሶቹ መጽሐፍ ቅዱሱን ሲያገለባብጡ “ ወ/ት ራየንስ” የሚል ስም ተጽፎ ያገኛሉ። ወንጀሉን ማን ፈጸመው ?የመጽሐፍ ቅዱሱ ባለቤትስ ማን ነው? ለሚለው መጠየቅ ብዙም ያልደከሙት ፖሊሶቹ ባለፈው እሁድ በአቅራቢያቸው ከሚገኝ አንድ የመኪና ማቆሚያ አካባቢ ቅኝት ሲያደርጉ ተጠርጣሪዋ ሞኒካን ያገኟታል ።
ያ የእግዜአብሔር ቃላት ያዘለው የቅዱስ መጽሐፍ መንፈሳዊ ዋጋውን ዝቅ በማድረግ እና በውስጡ አደንዛዥ እጽን በመደበቅ ወደ እስር ቤቱ ለማስገባት የሞከረችው ሞኒካ ለጊዜው ፈጣሪን ብታስከፋም፣ አማኞችን ብታሳዝንም ፣ የፈጣሪ ስሬቶች ከሆኑት ከምድራዊ ገዢዎች(ከፖሊሶች) ለማምለጥ ግን አልቻለችም፣ ዘመዷን ለመጠየቅ እና እግረ መንገዷንም አደንዛዥ እጽን ለማሰረግ ወደ ጣቢያ ጎራ ያለችው ሞኒካ እርሷም ሕግን በመተላለፍ ወንጀል ተጠርጥራ፣ ከፖሊስ ጣቢያ ተወርውራ በእስር ላይ የሚገኘው ወዳጇን ተቀላቅላ “አሳ ጎርጓሪ ዘንዶ ያወጣል”እንዲሉ እርሷም ፍርዷን በመጠባበቅ ላይ ትገኛለች። እዚህ ላይ ሞኒካ የየትኛው ሐይማኖት ተከታይ እንደሆነች እና ባልጠፋ እቃ ለምን ቅዱስ መጽሐፍን ለወንጀል መፈጸሚያዋ መሳሪያነት እንደመረጠችው ለጊዜው ባይገለጽም ክብር ለሚገባው ሁሉ ክብር አለመሰጠቱ በነፍስም ሆነ በሰጋ ዋጋ እንደሚያሰከፍል ከሞኒካ ገጠመኝ በቀላሉ መማር ይቻላል።
Tamiru Geda's photo.Tamiru Geda's photo.

No comments:

Post a Comment