Wednesday, August 5, 2015

ምናልባት ጫካ መግባት ነበራባቸው

እነዚህ ውድ የኢትዮጵያ ልጆች እንዳማንም ኢትዮጵያዊ በአከባቢያቸው ከሚቀርቧቸው አብሯቸው ከሚማሩ ከሚሰሩ ጓደኞቻቸው ማናችንም እንደምንዝናናው በገሃድ የምናያቸው ድንቅ ውብ ኢትዮጵያውያን አሻባሪ ያላቸው አካል ጫካ መግባት የአሻባሪነት ተቃራኒ መስሎት ይመሥለኛል። ግን ይህ በሰላም ባደጉበት በኖሩበት ሀገር አሸባሪ የተባሉት ወጣቶች ብዙ ወዳጅና ጓደኛ አብሮ አደግ ጀግና እንዳላቸው የተዘነጋ ይመስላል ። ምክነያቱም እነሱ በገሃድ እኔ ኢትዮጵያዊ እንደኢትዮጵያዊነቴ ለመብቴ ለነፃናቴ ለእምነቴ ብለው በግልፅ ጫካ ሳይገቡ ህዝብ መድረክ ላይ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው እኩልነን ብለው አምነው ማንንም ሳይፈሩ ሰብኣዊነት ባለው መንገድ ህዝባዊ ጥያቄ የህዝብን ድምፅ ይሰማል ላሉት አካል በማቅረባቸው አሸባሪ ተባሉ 22 አመታትም ፅኑ እስራት ተፈረዳባቸው። ይህ ውሳኔ ምናልባት ሀገራዊ ወይም ህዝባዊ ሳይሆን ወገንተኛዊ ስሜታዊ ቡድናዊ እንጂ ህሊናን መሰረት ያደረገ ህገ ደንብን የተከተለ እንዳልሆና መላው የሀገራቸው ህዝብ ጠንቅቆ ያቃዋል።
ሀሳቤ ግን ጫካ መግባትን ነው : ጫካ መግባት እኛ ሀገር ቀላል ነው እንደ ድሮ ጫካዎች ባይኖሩንም ምክንያቱም ጥቅም ስላላቸው ተመንጥረው አልቀዋልና ። ሆኖም ግን ጫካን ተገን አድርጎ ራስን ለማሸሽ ሌላን ለመጉዳት አምባገነንነትን ለማስፈን አሊያም አምባገነን ለመሆን ጫካ መግባት ትክክለኛ አሻባሪዎችን ለመፍጠር ወይንም ለማጥፋት ጥሩ መንገድ ነው ። ማለት እንደ እኛ ሀገር ህግ ባይሆንም እንደ እኛ ሀገር ላለው ስርዓት: ትላንት የተጨቆኑ የታሰሩ የተሰቃዩ የተፈተኑ የታቃዋሚ ቡድን ዛሬ ምናልባት ጫካ በይገቡም በራሃ ወርደው ይሆናል ወርደዋልም። ነገ ግን በግልፅ ይህ የኔ መብት ነው ይከበርልኝ ብለው ህጋዊ እውቅና አግኝተው ሲጠይቁ የነበሩ አካላት ነገ በራሃውን ይወዱት ወይም ጫካውን ይጠብቁት ማን ነው ዋስትና ወስዶ ሚያግዳቸው ። ዛሬ መሪ ሆኖ ሀገርን ወይንም አንድን ቡድን የሚመራ አባል አመጣጡን ቢረሳውም ከኃላ ግን እንዴት ከምን ብለው የሚያጠኑ ወጣቶች ይኑሩ አይኑ የሚያቅስ የትኛው FBI ይሁን.የሚቆጣጠረው በየትኛው ክልል ነው እውነት ይህ አምባገናናዊ ስ�ርዓት እንደዚህ ያሉ ጀግኖችን አሻባሪ ብሎ ነገ በስጋት መንፈስ የነሱን ሰላማዊ መንገድ ንቆ የሱን አውሬያዊ የጫካን ስልት መምረጥ እንደሚኖር ማነው እውነት እርግጠኛው ይህ እውነት ለሀገር አመራር እበቃለው ብሎ የሚል አካል ካለ አማራር ወይም ህዝብን ሀገርን መሪ ምን እንደሚመራ ሊረዳ ይገባዋልና ማስታወል ሊሳናው አይገባም።
ምክንያቱም የራሱን ታሪክ እየረሳ የተነሳበትን ሰበብ ነው ሚዘራው እንዴት እንደተነሳና እንዴት እንደመጣ ራሱን በሽምግልና በእርጅናም ይሁን በማሀይምነት የመጣበት የተፈጠረበትን ታሪክ ረስቷልና ። አሁንም ማስታወል ተስኖታልና አስታዋይ ይምከራው ባይ ነኝ
Fitihn Batigist's photo.
Fitihn Batigist's photo.

No comments:

Post a Comment