Thursday, August 6, 2015

ሰበር ዜና … በሳውዲ አሲር በአጥፍቶ ጠፊ 15 ተገደሉ፣ 7 ቆሰሉ !


በሳውዲ ምዕራባዊ የሀሪቱ ክፍል የአሲር ግዛት 15 ያህም ሲገደሉ 7 ያህል መቁሰላቸውን የሳወዲ የሀገር ውስጥ ሚኒስትር አስታውቋል ። ከሞቱት 15 ነዋሪዎች መካከል 12 ያህሉ ልዩ ኮማንዶ የጸጥታ ኋላፊዎች ሲሆኑ 3 ያህሉ ደግሞ የጸጥታ ክፍሉ ሲቪል ሰራተኞች መሆናቸው የጠቆመው የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ መግለጫ ከቆሰሉት ሰባቱ አንዱ መትረፋቸው አጠራጣሪ መሆኑንም በቃል አቀባዩ በሜጀር ጀኔራል መንሱር አልቱርኪ በኩል የተላለፈው መግለጫ ጠቁሟል !
ቃል አቀባይ ሜጀር ጀኔራል መንሱር አልቱርኪ በዚሁ መግለጫ ጥቃቱ ዛሬ በእኩለ ቀን ሀሙስ ዝሁር ጸሎት ላይ ወደ ጸጥታ አስከባሪዎች መስጊድ ሰርጎ በገባ አጥፍቶ ጠፊ የተፈጸመ መሆኑ ባይረጋገጥም ጥርጣሬው እንደዳለ ጠቁሟል !
ይህ በእንዲህ እንዳለ የሳውዲ የሀይማኖት አባቶች ጥቃቱን በጽኑ ማውገዛቸው ሲገለጽ የአሲር ሀገረ ገዥ ልዑል ፈይሰል ቢን ካልድ ጥቃቱ የተፈጸመበትን ቦታና በጥቃቱ ጉዳት የደረሰባቸውን ህክምና ወደሚያገኙበት የከሚስ ምሸት ሆስፒታል ሄደው መጎብኘታቸው ተጠቁሟል !
ቸር ያሰማን !
ነቢዩ ሲራክ
ሀምሌ 30 ቀን 2007 ዓም

No comments:

Post a Comment