Monday, August 24, 2015

እነ ማቲያስ መኩሪያ ለነሃሴ 27 ተቀጠረባቸው


አይ ኤስ አይ ኤስ በኢትዮጵያውያን ላይ የፈፀመውን አሰቃቂ ግድያ ለመቃወም መንግስት በጠራው ሰልፍ ሰበብ የታሰሩት እነ ማቲያስ መኩሪያ ለነሃሴ 27/2007 ዓ.ም ተቀጠረባቸው፡፡ ፖሊስ በጊዜ ቀጠሮ ወቅት ‹‹የቪዲዮ ማስረጃም አለን›› በማለቱ ተከሳሾቹ ‹‹ቪዲዮው ይቅረብልን፡፡ የቪዲዮ ማስረጃው ለእኛም የመከላከያ ምስክርነት ይጠቅመናል›› ብለው ጠይቀው የነበር በመሆኑ፤ ፍርድ ቤቱ የቪዲዮ ማስረጃው መቅረብ እንዳለበትና እንደሌለበት ብይን ለመስጠት ለነሃሴ 5/2007 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቶ ነበር፡፡ ይሁንና በዚህ ቀን የመናገሻ ፍርድ ቤት የማይሰራ በመሆኑ ችሎቱ በአራዳ ፍርድ ቤት በተረኛ ዳኛ ታይቶ ‹‹ጉዳዩ አልተመረመረም፡፡›› በሚል ብይን ለመስጠት ለነሃሴ 18/2007 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቶ ነበር፡፡ በዛሬው ቀጠሮም ተረኛ ዳኛው ‹‹የምንሰራው በተራ ስለሆነ አላየሁትም፡፡ አልተመረመረም›› በሚል ለብይን ለሃሴ 27/2007 ዓ.ም ሌላ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
ተከሳሾቹ 4 ወር ሙሉ በመጉላላት ላይ መሆናቸውን በመግለፅ በቶሎ ፍርድ እንዲሰጣቸው ገልጸዋል፡፡ አንደኛ ተከሳሽ ማቲያስ መኩሪያ ‹‹4 ወር ሙሉ ያለ ፍርድ እየተጉላላን ነው፡፡ በቶሎ ፍርድ ሊሰጠን ይገባል›› ሲል ቅሬታውን አቅርቧል፡፡ ፍርድ ቤቱ ቪዲዮው ላይ ብይን ለመስጠት ቀጠሮ ሲሰጥ የዛሬው ለአራተኛ ጊዜ ነው፡፡ ተከሳሾቹ ባለፈው ችሎትም የፍርድ ሂደቱ መጓተቱን አስመልክተው ቅሬታ ማቅረባቸው ይታወሳል፡፡
በማቲያስ መኩሪያ መዝገብ የተከሰሱት 1ኛ ማቲያስ መኩሪያ፣ 2ኛ መሳይ ደጉሰው፣ 3ኛ ብሌን መስፍን፣ 4ኛ ተዋቸው ዳምጤ ሲሆኑ ከመሳይ ደጉሰው ውጭ ያሉት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ናቸው፡፡
Ethio Hagere's photo.

No comments:

Post a Comment