Thursday, August 20, 2015

በኢትዮጵያ አስቸኳይ የምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ዜጎች ቁጥር 4.5ሚልዮን መድረሱ ተገለጠ

በተባበሩት መንግሰታት የሰብአዊ ድጋፍ ቢሮ ይፋ ባደረገው አዲስ ሪፖርት በኢትዮጵያ የምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ዜጎች ቁጥር በያዝነው ወር 4.5ሚልዮን መድረሱን ይፋ አድርጓል፡፡
የ2015 ግማሽ አመት የሰብአዊ ድጋፍ ተፈላጊነት ከተገመገመ በኋላ ሪፖርቱ ይፋ ሲደረግ ለጋሽ አገራትና የኢትዮጵያ መንግስት ተወካዩች በስፍራው መገኘታቸውን መረጃው ጨምሮ ጠቁሟል፡፡
ሪፖርቱ በተጨማሪ ለምግብና ምግብ ነክ ላልሆኑ ነገሮች የሚያስፈልገው የእርዳታ መጠን በጃንዋሪ(ጥር)ወር ተተንብዮ ከነበረው 386 ሚልዩን ዶላር የ10.6 በመቶ ለውጥ ማሳየቱን በመጥቀስ ከዚህ ውስጥ 158ሚልዩን ዶላሩ በግማሽ አመቱ የሚፈለግ መሆኑን አስታውቋል፡፡
በ2015 ሁለተኛ ግማሽ አመት የሰብአዊ ድጋፍ አስፈላጊነት የናረው በዝናብ መጥፋት፣የእርዳታ እህልና በመጀመሪያው የአመቱ አጋማሸ በእቅድ ተይዞ የነበረው ተጨማሪ የምግብ ድጋፍ በመዘግየቱ የተነሳ ነው ብሏል፡፡

No comments:

Post a Comment