Monday, August 17, 2015

በጠቅላይ ሚኒስተራችን የትውልድ ቦታ በሆነችው በቦሎሶ ሶሬ በከተማ ማስፋፊያ ፕሮጀክት ምክንያት ነዋሪዎች ከፖሊስ ጋር ተጋጩ


በጠቅላይ ሚኒስተራችን የትውልድ ቦታ በሆነችው በቦሎሶ ሶሬ በከተማ ማስፋፊያ ፕሮጀክት ምክንያት ነዋሪዎች ከፖሊስ ጋር ተጋጩ
በደቡብ ክልል ወላይታ ዞን ሥር በምትገኘው የቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ከከተማ ማስፋፊያ ፕሮጀክት ጋር በተያያዘ, ሕገወጥ ግንባታዎችን ለማፍረስ የአረካ ከተማ ማዘጋጃ ቤት በመሞከሩ ነዋሪዎች ከፖሊስ ጋር መጋጨታቸው ታወቀ
የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የትውልድ ቦታ በሆነው የቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ዋና ከተማ አረካ ዙሪያ የሚገኙ ስድስት ቀበሌዎችን በከተማው ሥር ለማካለል, በሕገወጥ መንገድ ተገንብተዋል በተባሉ ከ 940 በላይ ቤቶች ላይ ማዘጋጃ ቤት እንዲፈርሱ ሐሙስ ነሐሴ 6 ቀን 20 07 ዓ.ም. ቀለም መቀባት ጀምሮ ነበር
ነገር ግን ባለይዞታዎች የተገነቡትን ቤቶች በቀጥታ በከተማ ማካለሉ ውስጥ ማስገባት እየተቻለ ሊፈርስብን አይገባም በማለት በመቃወማቸው, በተጠቀሰው ዕለት ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት አካባቢ ግጭት መነሳቱን ምንጮች ለሪፖርተር ገልጸዋል

No comments:

Post a Comment