በፍንዳታው የሟቾች ቁጥር ከዚህም ከፍ እንደሚል የተገመተ ሲሆን 500 ሰዎችም ጉዳት ደርሶባቸዋል።
የቻይና ዜና አገልግሎትን ጠቅሶ ቢቢሲ እንደዘገበው፥ ፍንዳታዎቹ የተከሰቱት ሩሃይ ሎጂስቲክስ በተባለ አደገኛ የሆኑ ኬሚካሎችን በያዘ መጋዘን ላይ ነው።

ፍንዳታው የፈጠረው የእሳት አደጋ በርካታ ህንጻዎችንና ተሽከርካሪዎችን ከጥቅም ውጪ አድርጓል።
ሁለተኛው ፍንዳታ ከመጀመሪያው የበለጠ ከባድ እንደነበር የተነገረ ሲሆን፥ በሬክተር ስኬል 2 ነጥብ 9 የተመዘገበው የመሬት ንዝረት በርካታ ኪሎሜትሮች ድረስ እንደተሰማም ተጠቁሟል።
የቻይና የመሬት መንቀጥቀጥ ኔትዎርክ ማዕከል እንዳስታወቀው የመጀመሪያው ፍንዳታ የሶስት ፈንጂዎችን፤ የሁለተኛው ፍንዳታ ደግሞ የ21 ፈንጂዎችን ያህል ድምጽ አሰምተዋል።
ፕሬዚዳንት ዢ ጂንፒንግ በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች ነብስ የማዳንና ፍንዳታው የፈጠረውን እሳት የመቆጣጠሩ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።
ፍንዳታው የተከሰተበትን መጋዘን የሚያስተዳድሩት ግለሰብም በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው መሆኑ ተጠቅሷል።
ፍንዳታው ያስከተለውን አደጋ ለመቆጣጠር የሚደረገው ጥረት አሁንም የቀጠለ ሲሆን፥ ከሟቾቹ መካከል 12ቱ የእሳት አደጋ ሰራተኞች መሆናቸውንም ቢቢሲ በዘገባው አመልክቷል።
የአደጋውን ምክንያት ግን እስካሁን በውል አልታወቀም።
No comments:
Post a Comment