Monday, August 3, 2015

Breaking News የወያኔው ካንጋሮ ፍርድቤት በእነ አቡበክር አህመድ የክስ መዝገብ የተጠቀሱ 18 ተከሳሾች ከ22 እስ ከ 7 አመት ፈረደባቸው


22 አመት የተቀጡት ፍርድ ቤቱ በሽብር ወንጀሉከፍተኛ ሚና ነበራቸው ያላቸው አቡበክር አህመድ፣
አህመዲን ጀበል፣ ያሲን ኑሩ እና ከሚል ሸምሱ ናቸው ።
ችሎቱ በመዝገቡ የተጠቀሱ 5ኛ፣ 7ኛ፣ 8ኛ፣ 11ኛ እና 15ኛ ተከሳሾችን፥ በድሩ ሁሴን፣ ሳቢር ይርጉ፣ መሃመድ አባተ፣ አቡበክር አለሙ እና
ሙኒር ሁሴንን እያንዳንዳቸውን በ18 አመት ጽኑ
እስራት ቀጥቷቸዋል ።
ሼህ መከተ ሙሄ፣ አህመድ ሙስጠፋ፣ ሼህ ሰኢድ አሊ፣ ሙባረክ አደም እና ካሊድ ኢብራሂም የ15 አመት ጽኑ እስራት ተወስኖባቸዋል ።
እንዲሁም ሙራድ ሽኩር፣ ኑሩ ቱርኪ፣ ሼህ ባህሩ ዑመር እና የሱፍ ጌታቸውን በ7 አመት ጽኑ እስራት ቀጥቷቸዋል ።
ተከሳሾችም ይሁን ከሳሽ አቃቤ ህግ የቅጣት አስተያየት እንዲያቀርቡ የ10 ቀን ጊዜ በችሎቱ ተሰጥቷቸው የነበረ ሲሆን ፥ አቃቤ ህግ ቀድሞ
ማቅረቡን ችሎቱ አትቷል ።
ተከሳሾች የአቃቤ ህግን የቅጣት አስተያየት ካላየን አናቀርብም ማለታቸውን ተከትሎ ችሎቱ የአቃቤ
ህግ የቅጣት አስተያየት እንዲደርሳቸው ትዕዛዝ አስተላልፎ ነበር ።
ይሁን እንጂ ከተሰጣቸው የመጀመሪያው 10 ቀን ሌላ ተጨማሪ ቀን ቢሰጣቸውም የቅጣት ማቅለያ ሊያቀርቡ አልቻሉም ።
ፍርድ ቤቱ ቅጣቱን ያስተላለፈው አቃቤ ህግ ተከሳሾች ወንጀሉን የፈጸሙት በስምምነትና በአንድነት ነው የሚለውን የቅጣት ማክበጃ ተቀብሎ
ነው ።
ችሎቱ ከእስራት ቅጣት በተጨማሪ ተከሳሾች ይህ ውሳኔ ከፀናበት እለት ጀምሮ ለአምስት አመታት እንዳይመርጡ ፣ እናዳይመረጡ ፣ በየትኛውም ቦታ ዋስም ምስክርም እንዳይሆኑ በአጠቃላይ ከማህበራዊ መብታቸው አግዷል ።

No comments:

Post a Comment