Monday, August 31, 2015

በትግራይ ወረዳዎች ተመድበው የሚሰሩ አስተዳደሮች ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች እየተገደሉ ነው


በትግራይ ወረዳዎች ተመድበው የሚሰሩ አስተዳደሮች ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች እየተገደሉ እንደሚገኙ ከተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች ያገኘነው መረጃ አመለከተ።በትግራይ ምስራቃዊ ዞን የአዲግራት ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ሃላፊ ሆኖ ሲሰራ የነበረው አፅብሃ ወልደገብርኤል የተባለው ለሆዱ ያደረ የህወሓት ኢህአዴግ ካድሬ ነሃሴ 12 /2007 ዓ/ም ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ቤቱ ውስጥ ተገድሎ እንደተገኘ ምንጮቻችን ከከተማዋ ገለፁ።
ፖሊስ ጉዳዩን ለማጣራት በሚል የተወሰነ እንቅስቃሴ ቢያደርግም ነዋሪው ህዝብ ሊተባበራቸው ባለመቻሉ ምክንያት በግለሰቡ አሟሟት ምክንያት ተሳስሮ ሰዎች ሊጠረጥሩት ሞክረው ህዝቡ ሊቀበላቸው ባለመቻሉ ምክንያት ገዳዩ ሳይታወቅ ዝምታን እንደመረጡ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።
በተመሳሳይ- በሳዕስዕ ፃዕዳ እምባ ሳዕስዕ ቀበሌ የሚኖር ህዝብ ደስታ ጎቢጥ የተባለ የቀድሞ ታጋይ ባልታወቁ ሰዎች ነሃሴ 13 2007ዓ/ም በድንጋይና በዱላ እንደተገደለ ለማወቅ ተችሏል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ- ተገድለዋል እየተባሉ ያሉት ሰዎች ከአካባቢው ካድሬዎች ጋር ስምምነት ያልነበራቸውና ጥቅም ያጣላቸው የኢህአዴግ አባላት ናቸው የሚል ጥርጣሬ በህዝቡ ዘንድ እንዳለ ከአካባቢው ያገኘነው መረጃ አክሎ ገልጿል።

በሑመራ ከተማ የሚገኙ ባለሃብቶች የትጥቅ ትግል በሚያካሂደው አርበኞች ግንቦት 7 የተገደሉትን የኢህአዴግ ሰራዊት አዛዦች ለቤተስባቸው የሚሆን ገንዝብ እንዲያዋጡ እየተገደዱ መሆናቸው ተገለጸ።

በሑመራ ከተማ የሚገኙ ባለሃብቶች የትጥቅ ትግል በሚያካሂደው አርበኞች ግንቦት 7 የተገደሉትን የኢህአዴግ ሰራዊት አዛዦች ለቤተስባቸው የሚሆን ገንዝብ እንዲያዋጡ እየተገደዱ መሆናቸው ተገለጸ።ባለፈው ግዜ በትግራይ ምእራባዊ ዞን አካባቢ የትጥቅ ትግል በሚያካሂደው አርበኞች ግንቦት 7 ለተገደሉት የመከላከያ ሰራዊት አዛዦች ቤተሰቦች የሚሆን ገንዘብ እንዲያዋጡ ሑመራ ከተማ ለሚገኙ ባለሃብቶች እያስገደዷቸው መሆናቸውንና በርካታ ገንዘብ ተዋጥቶ እየተሰበሰበ መሆኑን ምንጮቻችን ከቦታው አስታወቁ።
የአርበኞች ግንቦት 7 ድርጅት በስርዓቱ የመከላከያ ሰራዊት ላይ በወሰደው የማጥቃት እርምጃ ከሞቱት ወታደሮች መካከል ኮለኔል ወልደሚካኤል የተባለ የሚገኝባቸው አዛዦች ለቤተሰቦቻቸው የሚሆን ገንዘብ የዞኑ አስተዳዳሪዎች ከባለሃብቶች በግድ እየሰበሰቡ መሆናቸውን መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።

በገመድ ሾፌሩንና እረዳቱን አንቀው የገደሉ ተያዙ


ነሀሴ 14,12,07ዓ.ም የታክሲ ሾፌሩ ከነመኪናው ወደ ቤቱ አልተመለሰም የመኖርያ ስፍራው ከወይራ ሰፈር ወደ ቤተል ሲኬድ ፓስታቤት አካባቢ በቅ/ጊዮርጊስ ክሊኒክ መግብያ 100ሜ ገባ ብሎ ነው ፡፡ በነጋታውም የለም፡፡ ቤተሰቦቹ ተደናግጠው ለፖሊስ አመለከቱ።
ፖሊስም ከአንድ ሳምንት የአሰሳና የምርመራ ቆይታ በሁዋላ በ20, 12,07 ዓ.ም ይዞት የመጣው ዜና ግን የሾፌሩን ቤተሰቦች ብቻ ሳይሆን የቤተል እና አካባቢውን ነዋሪዎች ያስደነገጠና አንገት ያስደፋ ነበር፡፡
ኤፍሬም ተሾመ ገና የ23 አመት ወጣት ሲሆን የሚኒባስ ታክሲ በማሽከርከር ይተዳደራል፡፡ ስሙ ያልታወቀው የታክሲ ረዳት ደግሞ እድሜው ገና በ አስራዎቹ የሚገመት ታዳጊ ህፃን ነው፡፡
የስራ ሰአት ማብቅያቸው ላይ የመጨረሻ ቢያጆ እንደሄዱ ኮንትራት ይጠየቃሉ። ጠያቂዎቹ አምስት ሲሆኑ “ቤተል ነዳጅ ማደያው ጀርባ ጋር ሰው እንጭናለን “ይላሉ። ኤፍሬምም ባለቀ ሰአት ጥሩ ስራ ተገኝ ብሎ ወደ ተባለው ስፍራ ታክሲውን ይዞ ገባ፡፡
ይሁንና ቢታይ የሚገባ ሰው የለም፡፡ አምስቱ ግለሰቦች በፍጥነት በገመድ ሾፌሩንና እረዳቱን አንቀው ይገድላሉ፡፡ ከዛም አስከሬኑን ይዘው ወደ ገፈርሳ በማምራት ድልድይ ውስጥ ይጥሏቸዋል፡፡
የቤተሰቡ አባላት ይህ መረጃ የተነገራቸው ፓሊስ ከአምስቱ ተጠርጣሪዎች መካከል ሁለቱ የዘረፋትን መኪና ለመሸጥ በማስማማት ላይ እንዳሉ በቁጥጥር ስር በማዋሉ እና ድርጊታቸውንም ስለተናገሩ ነው፡፡
የሚያሳዝነው ይህ መረጃ እስከተጠናከረበት ሰዐት ድረስ የሟች ሰፈር ልጆች የገፈርሳ ነዋሪ እና ፖሊስ አስከሬኑን እየፈለጉ ቢሆንም ማግኘት አልተቻለም፡፡

የሙስና ተጠርጣሪዎች በዱባይና በደቡብ ሱዳን የገዟቸው ስድስት ቤቶች ታገዱ


በሕገወጥ መንገድ ተይዞ የነበረ 500 ካሬ ሜትር ቦታ ለመንግሥት ተመለሰ
የፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በ2008 በጀት ዓመት ከሐምሌ 1 ቀን 2007 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ነሐሴ 15 ቀን 2007 ዓ.ም. ድረስ በሙስና ተጠርጥረው በክስ ሒደት ላይ ከሚገኙ ሰዎች፣ 28 ቤቶችን በፍርድ ቤት
ማሳገዱንና ስድስቱ ቤቶች በዱባይና በደቡብ ሱዳን ጁባ ከተማ የሚገኙ መሆናቸውን ገለጸ፡፡
ኮሚሽኑ ለሪፖርተር በላከው መግለጫ እንደገለጸው አራት ቤቶችን በዱባይ፣ ሁለት ቤቶችን ደግሞ በደቡብ ሱዳን ጁባ ከተማ ውስጥ አሳግዷል፡፡ ቀሪዎቹ 22 ቤቶች በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች የሚገኙ መሆኑንም ኮሚሽኑ አክሏል፡፡
በዱባይና በጁባ ከተማ የታገዱት ቤቶች፣ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጁባ ቅርንጫፍ ላይ ተፈጽሟል በተባለ የሙስና ወንጀል ከተጠረጠሩ የባንኩ ሠራተኞችና ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ “ወርቅ ነው” በማለት ባሌስትራ በማቅረብ በአጭበረበሩ ግለሰቦች የተገዙ መሆናቸውን፣ ቀሪዎቹ ቤቶች ደግሞ በሌላ የሙስና ወንጀል ድርጊት የተጠረጠሩ ግለሰቦች መሆናቸውን ኮሚሽኑ አብራርቷል፡፡
ኮሚሽኑ በአዲሱ በጀት ዓመት አንድ ወር ተኩል ጊዜ ውስጥ ከ3.2 ሚሊዮን ብር የሚበልጥ ገንዘብና በየካ ክፍለ ከተማ በአንድ ግለሰብ በሕገወጥ መንገድ ተይዞ የነበረ 500 ካሬ ሜትር ቦታ ለመንግሥት ማስመለሱን ገልጿል፡፡ በተለያዩ የሙስና ወንጀል ድርጊቶች ጋር በተያያዘ 21 የግንባታና 35 የቤት አውቶሞቢሎች፣ 56 የተለያዩ ዓይነት ተሽከርካሪዎች፣ የአክሲዮን ገንዘብን ጨምሮ ከ53 ሚሊዮን ብር በላይና አንድ የግል ድርጅት በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ማሳገዱን ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡
የግንባታ ማሽነሪዎች፣ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችና ገንዘብ ያሳገደው በሙስና ወንጀል ተጠርጥሮ ክስ ከተመሠረተበት የእስራኤሉ ኮንስትራክሽን ኩባንያ ትድሃር ሲሆን፣ አብዛኛው ገንዘብ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የደቡብ ሱዳን ጁባ ቅርንጫፍ ሠራተኞች ከነበሩት ተጠርጣሪዎች መሆኑን ኮሚሽኑ ገልጿል፡፡

Sunday, August 30, 2015

ከወደ ጎንደር! አስደንጋጭ ተሰምታል



ጎንደር መተማ መስመር 11 የሰሊጥ ከባድ መኪና ሹፌሮች በወያኔ ደህንነት ደላሎች አማካኝነት ሱዳን ዉስጥ የተሻለ ክፍያ ያለዉ ስራ እናገናኛችሁ በማለት ከወሰዱ በሁዋላ 11ዱም በሱዳን ወታደሮች አራጅነት በወያኔ ደህንነት ደላሎች አሳራጅነት ካረዷቸዉ በሁዋላ በእሳት አቃጥለዋቸዋል::
የተገደሉበት ምክንያት ለጊዜዉ ባይታወቅም ወያኔ የነፃነት ታጋዮችን በየቀኑ በየትም የሚቀላቀሉ ወጣቶችን ለመቆጣጠርና በማስፈራራት ”መንገዱ ሰላም አደለም:: ወደሱዳን መስመር አትሂዱ…”
የሚልና ከተቻለም ጉዳዩን ከነፃነት ሀይሎች በተለይም ከአርበኞች ግንቦት ሰባት እና ደምሂት ጋር በማያያዝ ሰፊ ተቀባይነት ያገኙበትን ስም ለማጠልሸትና ተጠያቂ ሊያደርግ እንዳሰበ ዉስጥ አዋቂወች ጠቁመዋል::
ሙዋቾቹ የአማራ ተወላጅ መሆናቸዉ ተገልጿል:: የሟች ቤተሰቦች እንዳሉት የሟቾችን አስከሬን ቢጠይቁም እንደተቃጠለ ተነግሯቸዋል!!

ነዳጅ የያዘው መኪና ተቃጥሎ የሁለት ሰዎች ህይወት አለፈ



zeway eth




በኢትዮጵያ ከ እለት ወደ እለት እየደረሰ ያለው የመኪና አደጋ አስፈሪና በተለይም በመኪና ረዥም መንገድ መሄድን የማያስመኝ እየሆነ መጥቷል:: ዛሬ ጠዋት ላይ በዝዋይ ከተማ አካባቢ በደረሰ የመኪና አደጋ ወደ እሳትነት ተቀይሯል::
ከአካባቢው ለዘ-ሐበሻ የደረሱ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ነዳጅ የያዘው የጭነት መኪና ከሕዝብ ንብረት ማመላለሻ አይሱዙ መኪና ጋር የተጋጩ ሲሆን ነዳጅ የያዘው መኪና እሳት ተነስቶበት ለሁለቱም መኪኖች መቃጠል ምክንያት ሆኗል:: እስካሁን የዘ-ሐበሻ ምንጮች እንደሚሉት የመኪናዎቹ አስከርካሪዎች የሁኑ 2 ሰዎች ተቃጥለው ሕይወታቸው አልፏል:: ሆኖም ግን ፖሊስ ሰፋ ያለ ማብራሪያ የሰጠው ነገር የለም::

በእነ አበባው መሃሪ መንደር ፍርሃትና ድንጋጤ መፈጠሩ ተሠማ


ጥቅምት 28_ 30 /2007 ዓም የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ )ጠቅላላ ጉባኤ ሲደረግ አበባወ መሃሪ በተራ አባልነት እቀጥላለሁ በማለት ለጉባኤው በደብዳቤ አሳውቆ ከወጣ በኋላ
በመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ላይ ምርጫ ቦርዱ ፕሬዝደንት አድርጎ ሾመው አበባው መሃሪ በጠቅላላ ጎባኤ ፕሬዝደንት ሆኖ የተመረጠው እውነተኛው የመኢአድ ፕሬዝደንት አቶ ማሙሸት አማረን ፍርድ ቤት ነፃ እንዳለ ሲሰሙ ከፍተኛ ድንጋጤ መፈጠሩን የውስጥ መረጃዎቻችን አረጋግጠዋል ምን ማድረግ እንዳለባቸው ጀሌዎዘቹን ሰብስቦ ውይይት አድርገዋል በተነሳው ሀሳብ መግባባት ሳይችሉ ቀርተዋል 
ቀደም ሲል በኛ በኩል ይፋ የተደረገውን በእስር ላይ የሚገኙትን አባላት ስም ዝርዝር በመውሰድ ከኛ ጋር ያብራሉ ብለው ያሰቧቸውን ስም ዝርዝር በመውሰድ ታስረውብናል ማለታቸው ይታወቃል ማሙሸት አማረን ጨምሮ የበርካታ አባላት ስም ዝርዝር እንዳላሳወቁ ማንም የሚያውቀው ነው ስም ዝርዝሩ የደረሳቸው ሠዎች ማሙሸት አማረ የናንተ አባል አይደለም ወይ ተብለው ሲጠየቁ ማሙሸት የኛ አባል አይደለም ብለዋል
በአሁኑ ሰአት ማሙሸት ነጻ በመባሉ ትልቅ ድንጋጤ አንደፈጠረባቸው የታወቀ ሲሆን ምን አባልባት የወያኔን ደህንነት ደጅ ሊጠኑ እንደሚችሉ ይጠበቃል ለአብዛኞቹ አባላት መታሰር የነ አበባው መሃሪ እጅ እንዳለበት በተደጋጋሚ ተገልጿል ማረጋገጥ የሚፈልግ ካለ ቅሊንጦ ጎራ በማለት በእስር ላይ የሚገኙትን አባሎች በመጠየቅ እውነቱን ማረጋገጥ ይቻላል ፡፡

Saturday, August 29, 2015

ሱዳን ከአማራ ክልል ጋር በምትዋሰንበት በኩል የሚገኘውንና ሶስት ወንዞች የሚያቋርጡትን የ250ካሬ ኪ.ሜ የቆዳስፋት መሬት እንደገና ይካለል ዘንድ ለኢትዮጵያ መንግስት ጥሪ አደረገች፡፡/አዋዜ/


የሱዳን ገዳሪፍ ግዛት ሀገረ ገዢ ሜርጋኔ ሳሌህ በኢትዮጵያና በሰዳን መካከል አለ ብለው የሚያምኑት የረጅም ግዜ የድንበር ውዝግብ ይፈታ ዘንድ ድንበሩ እንዲካለል መጠየቃቸው ተሰማ፡፡ ሄራል ትርቢውን የተሰኘው ጋዜጣ ትላንት እንደዘገበው ሱዳን በምስራቃዊ ግዛቴ ገዳሪፍ ደቡብ ምስራቅ አል-ፍልሻጋ በተባለው አከባቢ ይገኛል የምትለውና የኢትዮጵያ አርሶ አደሮች መሬታችው መሆኑን ሚናገሩለትን ይህን ምሬት ጉዳይ ከቀ/ጠ/ሚ/ አቶ/መለሰ ዜናዊ ግዜ ተጀምሮ እሳቸው ድንገት በመሞታቸው መቋረጡን ያስታውሳል ጋዜጣው፡፡ እናም አሁን ‹‹የኢትዮጵያና ሱዳን መንግስታት ድንበሩን እንደገና ለማካለል በተስማሙት መሰረት ይፈጸምና ድንበር ውዝግቡ ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ ይፈታ››› ብለዋል ገዳሪፍ ሀገረ ገዢ፡፡
የሱዳኑ ሄራልድ ትርቢውን የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች ‹‹ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ የኢትዮጵያን ምድር ለሱዳን አሳልፎ ትቶለታል በማላት ይከሳሉ›› ሲል ጋዜጣው ጽፏል፡፡ በባለፈው የፈረንጆች አመት ህዳር ወር የሱዳኑ አል-በሽርና የኢትዮጵያው ጠ/ሚ ሀይለማሪያም ደሳለኝ በቀ/ጠ/ሚ/ አቶ/መለሰ ዜናዊ ሞት የተነሳ የተቋረጠውን ድንበሩን እንደገና የማካለል ስራ የሚጀመርበትን አዲስ ቀን እንዲወስኑ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሮቻቸው መመሪያ ማስተላለፍቸውን ጋዜጣው ጠቅሷል፡፡
አዲስ ይደረጋል በተባለው ማካለል ጉዳይ ይሆናል ተብሎ የሚጠበቀው መሬት 250 የ250 ካሬ ኪ.ሜ ነው ምናልባት የአዲስ አበባን ጠቅላላ ስፋት ከግማሽ በላይ የሚሆን መሬት ማለት ነው፡፡ በውስጡ ደግሞ ለእርሻ እጅግ ተስማሚ መሬት የሆነ 6 መቶ ሺ ሄክታር 6 መቶ ሺ የእግር ኳስ ሜዳ የሚያክል ለም መሬት አለው፡፡
የሱዳኑ ሄራልድ ትርቢውን እንደተነተነው ይህን ለም መሬት ደግሞ አጥባር ሲቲት ባዝላን የሰተሠኙ ወንዞች አቋርጠውት የሚያልፉ በመስኖ ሊለማና በአመት ሁለት ግዜ ሊመግብ የሚችል በጠራ ቋንቋ ጮማ መሬት ነው የሱዳን ገዳሪፍና ብሉ ናይል ግዛቶች ከአማራ ክልል ጋር የሚዋሰኑ ናቸው፡፡
ምንጭ ፤- አዋዜ

ዓለም ሥጋት የሆኑት ሴት አጥፍቶ ጠፊዎች


ሴቶች በአጥፍቶ መጥፋት ሲሳተፉ ማየት እምብዛም የተለመደ አልነበረም፡፡ ሆኖም በናይጄሪያ መንግሥት አክራሪ ተብሎ የተፈረጀው ቦኮ ሐራም ሴቶችንና ታዳጊ ሕፃናትን በአጥፍቶ መጥፋት እያሳተፈ ይገኛል፡፡ ለድርጊቱ ይረዳው ዘንድም የቦኮ ሐራም የሴቶች ክንፍ ካዋቀረ ሰንብቷል፡፡
የቡድኑ የሴት ክንፍ አብዛኞቹ አባላት ደግሞ በቡድኑ ታጣቂዎች ከየትምህርት ቤቱና ከየመንደሩ የሚጠለፉ ሴቶች ናቸው፡፡ እነዚህ ሴቶች በሚስትነትና በሠራተኝነት ከማገልገላቸው ባለፈም፣ በአጥፍቶ መጥፋት መሳተፍ ከጀመሩ ሰነባብተዋል፡፡ የአጥፍቶ መጥፋቱን የሚፈጽሙትም በናይጄሪያ ብቻ ሳይሆን በቻድ፣ በካሜሩንና በኒጀር ነው፡፡ ቦኮ ሐራም የታገቱ ሴቶችን ለአጥፍቶ መጥፋት መጠቀሙም በናይጄሪያም ሆነ በአካባቢው አገሮች ሥጋት ፈጥሯል፡፡
ማክሰኞ ነሐሴ 19 ቀን 2007 ዓ.ም. ሁለት የቦኮ ሐራም አጥፍቶ ጠፊዎች በሰሜን ምሥራቅ ናይጄሪያ በምትገኘው ደማቱሩ በፈጸሙት ጥቃት አምስት ሲሞቱ 41 ያህል መጎዳታቸውን አሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡
በተለያየ ሥፍራ ከደረሱ ሁለት ፍንዳታዎች አንዱ የተፈጸመው 14 ዓመት በሚሆናት ታዳጊ መሆኑም ታውቋል፡፡ ሁለተኛውን አጥፍቶ መጥፋት ለመፈጸም የተመለመለው ታዳጊ ወንድ ግን ከታለመለት ሥፍራ ሳይደርስ የታጠቀው ቦምብ በመፈንዳቱ ሌሎች ላይ ጉዳት ሳይደርስ ራሱ ሞቷል፡፡
ቦኮ ሐራም ማክሰኞ ምሽት ማተሚያ ቤት እስከገባንበት ጊዜ ድረስ ለጥቃቱ ኃላፊነቱን ባይወስድም፣ ከጥቃቱ ጀርባ ያለው ቦኮ ሐራም ሊሆን እንደሚችል ዘገባው ያሳያል፡፡ የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት ሙሐማዱ ቦሃሪ ሥልጣን ላይ ከወጡ ካለፈው መጋቢት 2015 ወዲህ፣ ማክሰኞ ዕለት የተመዘገበውን ጨምሮ ከአንድ ሺሕ በላይ ንፁሐን በቦኮ ሐራም ተገድለዋል፡፡ ቦኮ ሐራምን አሽመደምዳለሁ ብለው የፕሬዚዳንትነቱን ሥልጣን ከጉድላክ ጆናታን የረከቡት ቦሃሪ፣ ሥልጣን ከያዙ ጥቂት ጊዜያት ቢሆንም ቦኮ ሐራምን መቆጣጠር ተስኗቸዋል፡፡ ባለፉት አምስት ወራት ብቻ ቡድኑ ከአንድ ሺሕ በላይ ሲገድል ቁጥራቸው ያልታወቁ ሴቶችና ሕፃናትን ጠልፏል፡፡ ቡድኑ ከተመሠረተ ካለፉት ስድስት ዓመታት ወዲህ ብቻ 20 ሺሕ ዜጎችን ሲገድል፣ ከሁለት ሚሊዮን በላይ ከቀያቸው እንዲሰደዱ ምክንያት ሆኗል፡፡
እ.ኤ.አ. በ2015 መጀመርያ ላይ የቻድና የናይጄሪያ ጥምር ጦር ቦኮ ሐራም የራሱን አስተዳደር ከመሠረተባቸው 25 ሥፍራዎች እንዲለቅ ያደረጉት ቢሆንም፣ የጥቃት ሥልቱን ቀይሮ በአጥፍቶ ጠፊዎች መጠቀም ጀምሯል፡፡ ለዚህም ታዳጊ ወጣቶች በተለይም ሴቶችን ጥቅም ላይ እያዋለ ነው፡፡ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዓለም አቀፍ ትምህርት ልዩ መልዕክተኛ ጎርደን ብራውን፣ በናይጄሪያ ቺቦክ በአዳሪ ትምህርት ቤት ይማሩ የነበሩ ሴቶች በቦኮ ሐራም የመጠለፋቸውን ዓመታዊ ፕሮግራም አስመልክተው፣ ቦኮ ሐራም ሴቶችን ለአጥፍቶ መጥፋት መጠቀሙን አውግዘው ነበር፡፡
ከአምስት ወራት በፊት በሰጡት መግለጫም ቦኮ ሐራምን ማስቆም ካልተቻለ ታዳጊ ሴቶችና ወንዶች ለቦኮ ሐራም አጀንዳ ማስፈጸሚያነት ሊውሉ እንደሚችሉም ጠቁመው ነበር፡፡
የቺቦክ ሴት ተማሪዎች በተጠለፉበት አንደኛ ዓመት ዋዜማ በሦስት ሴት አጥፍቶ ጠፊዎች የተጀመረው የቦኮ ሐራም ጥቃት ዛሬ ተስፋፍቷል፡፡ ከዓለም አቀፍ ሕጎችና ስምምነቶች በተቃራኒ፣ ቦኮ ሐራም ሕፃናትን በዕድሜና በፆታ ሳይለይ ለአጥፍቶ መጥፋት እያዋለም ነው፡፡ ‹‹ዓለም ቦኮ ሐራም የሚፈጽመውን ርኩስ ተግባር የሚቃወምበትና የሚያወግዝበት ጊዜ አሁን ነው፡፡ ታዳጊ ሴቶች እየተበዘበዙና ያላግባብ ጥቅም ላይ እየዋሉ ነው፡፡ ብዙ ታዳጊ ሕፃናት አስደንጋጭ ወደሆነ ግዳጅ ከመሰማራታቸው በፊት ዓለም አቅሙን ተጠቅሞ ቦኮ ሐራምን ሊያቆመው ይገባል፤›› ብለውም ነበር ብራውን፡፡
ይህ ግን የተሳካ አይመስልም፡፡ በመሆኑም ናይጄሪያውያን በቦኮ ሐራም ሚሊሻዎች ከሚደርስባቸው ግድያ ባለፈ ለሴት አጥፍቶ ጠፊዎች ተጋላጭ ሆነዋል፡፡ ቦኮ ሐራምም የጠለፋቸውን ታዳጊ ሴቶች አመለካከት በመቀየርና በአጥፍቶ መጥፋት እንዲሳተፉ ማድረጉን ገፍቶበታል፡፡ ታዳጊዎቹ ለግዳጅ ተልዕኮም እየዋሉ ናቸው፡፡
በናይጄሪያ የመጀመርያው የሴት አጥፍቶ መጥፋት ጥቃት የተፈጸመው እ.ኤ.አ. በ2014 ሰኔ ወር በምሥራቅ ናይጄሪያ ጐምቢ ነበር፡፡ በወቅቱ ጥቃቱን የፈጸመችው በመካከለኛ ዕድሜ ላይ የምትገኝ ሴት ብትሆንም፣ ከዚህ በኋላ የተከሰቱ ጥቃቶች በታዳጊ ሕፃናት የተፈጸሙ ናቸው፡፡ ሁለተኛው ጥቃት የተፈጸመው የመጀመርያው በተፈጸመ በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ በሌጐስ ደቡባዊ አቅጣጫ በምትገኘው አፖፖ ነበር፡፡ ከዚህ በማስቀጠል በዚሁ ዓመት ነሐሴ ወር በሰሜን ናይጄሪያ እንቅስቃሴ በሚበዛባት ካኖ ከተማ አራት የአጥፍቶ መጥፋት ጥቃቶች የተፈፀሙ ሲሆን፣ ሁሉም በታዳጊ ሴቶች የተፈጸሙ ናቸው፡፡ በዚሁ ወር የአሥር ዓመት ታዳጊ ሴት በ18 ዓመት እህቷና በአንድ ግለሰብ እየተመራች ጥቃት ልትፈጽም ስትል ሁሉም በቁጥጥር ሥር ውለዋል፡፡
የአጥፍቶ ጠፊዎችን በቁጥጥር ሥር መዋል ተከትሎ የአገሪቱ ሚዲያዎች ምንጭ ሳይጠቅሱ፣ ቦኮ ሐራም ከ15 ዓመት በታች ያሉ 177 ሴቶችን ለአጥፍቶ መጥፋት ወንጀል እያሠለጠነ መሆኑንና ከእነዚህ ውስጥ 75 ያህሉ በናይጄሪያ ጥቃቱን ለማድረስ ዝግጁ መሆናቸውን ዘግበው ነበር፡፡ በለንደን ኪንግስ ኮሌጅ ዲፌንስ ዲፓርትመንት የዶክትሬት ተማሪ የሆነችው ኤልዛቤት ፒርሰን እንደምትለው፣ ሴቶችን ለአጥፍቶ መጥፋት መጠቀም የአንድ ሸማቂ ቡድን መዳከምን የሚያሳይ መሆኑን ነው፡፡ በጦር ግንባር ያሉ ወንዶች ሲመናመኑ ሴቶችን ለሽብር መጠቀም በአልቃይዳ ውስጥም የተለመደ ነበር ብላለች፡፡
እ.ኤ.አ. በ2009 የተመሠረተው ቦኮ ሐራም 270 የሚሆኑ ሴት ተማሪዎችን ከጠለፈ በኋላ እየተስፋፋ የመጣው የሴት አጥፍቶ ጠፊዎች፣ የሚዲያ ቀልብ ለመሳብ የተደረገ ነው የሚሉ ወገኖችም አሉ፡፡ ምክንያቱም ቦኮ ሐራም በተለይ በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲታወቅና ሰፊ የዜና ሽፋን እንዲያገኝ የረዳው በቺቦክ የሚማሩ ሴት ተማሪዎችን ከጠለፈ በኋላ መሆኑ ነው፡፡ ሆኖም ቦኮ ሐራም ከተቆጣጠራቸው አካባቢዎች አዛውንቶችን ብቻ አስቀርቶ ወንዶችንና ሴቶችን እየጠለፈ መውሰድ መጀመሩና ለጦርነት ማሳተፉ የቀድሞ ሚሊሻዎቹ እየተመናመኑ መምጣታቸውን የሚያመላክት ነው፡፡ ይህ ባይሆን ኖሮ ቦኮ ሐራም ‹‹ሴቶች በቤት መቀመጥ እንጂ ወጥተው መሥራትም ሆነ መዋጋት አይችሉም፤›› ከሚለው ፍልስፍናው ጋር የሚጣረስ ተግባር አያራምድም ነበር፡፡
በቦኮ ሐራም ውስጥ ሴቶች ያለፍላጎታቸው በግዳጅ የወንጀልና የአጥፍቶ መጥፋት ተሳታፊ ሲሆኑ በሌላ በኩል በፍላጎት የሚቀላቀሉም አሉ፡፡ ምክንያቱም ቡድኑ የሴቶች ክንፍ የመሠረተ ሲሆን፣ ይህንን በመሠረተ በጥቂት ቀናት ውስጥ ተከታታይ የአጥፍቶ መጥፋት ጥቃቶች በሴቶች ተፈጽመዋል፡፡ ከዚህ በኋላም ሦስት ሴቶች ቦኮ ሐራምን የሚቀላቀሉ ወጣት ሴቶችን፣ እንዲሁም ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ደግሞ በሰላይነት ሲመለምሉ በቁጥጥር ሥር ውለዋል፡፡ ቦኮ ሐራም በናይጄሪያና በቻድ ጥምር የጦር ኃይል ጥቃት እየደረሰበት ቢሆንም፣ ሴቶችን ለአጥፍቶ መጥፋት እየተጠቀመ ነው፡፡ የናይጄሪያ መንግሥትና ዓለም አቀፍ ተቋማት ደግሞ የቦኮ ሐራምን አካሄድ እያወገዙ ነው፡፡
የሴት አጥፍቶ ጠፊዎች በናይጄሪያ ብቻ ሳይሆን ግጭት ባሉባቸው አገሮች ሁሉ የሚገኙ መሆኑን እ.ኤ.አ. በ2011 የተሠራው የአሜሪካ የደኅንነት መረጃ ትንታኔ ያሳያል፡፡ እንደ መረጃው ከሆነ፣ ሴቶች ካላቸው የእናትነት ባህሪ አንፃር በአጥፍቶ መጥፋት ይሳተፋሉ ተብለው አይጠረጠሩም፡፡ ሆኖም ከወንድ የበለጠ ትልቅ ጥፋት የሚያደርሱት፣ እርጉዝ በመምሰልና ሰፊ የሰዎች እንቅስቃሴ በሚኖሩባቸው ሥፍራዎች በመገኘት ነው፡፡ አብዛኞቹ ሴት አጥፍቶ ጠፊዎች በ20ዎቹ መጨረሻ የዕድሜ ክልል የሚገኙ ሲሆን፣ ይህም በአብዛኛው ወንድ አጥፍቶ ጠፊዎች ከሚገኙበት ዕድሜ ከፍ ያለ ነው፡፡
የመጀመሪያው በሴት አጥፍቶ መጥፋት የተፈጸመባት አገር ሊባኖስ ናት፡፡ እ.ኤ.አ. በ1985 የሶሪያ ሶሻል ናሽናሊስት ፓርቲ አባል የሆነች ሴት ቦምብ የተጠመደበት መኪና በማሽከርከር፣ ሁለት የእስራኤል ወታደሮችን ገድላ ሁለት አቁስላለች፡፡ እ.ኤ.አ. በ1991 የቀድሞው የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ራጂቭ ጋንዲ የተገደሉትም በሴት አጥፍቶ ጠፊ ነው፡፡ በቺቺኒያ የሚገኙ የሩሲያ ወታደሮችና ሲቪሎች፣ በኩርድ የሚገኙ የቱርክ ወታደሮችም በሴት አጥፍቶ ጠፊዎች ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል፡፡
ዋፋ ኢድሪስ የመጀመርያዋ የፍልስጤም አጥፍቶ ጠፊ ብትሆንም፣ እ.ኤ.አ. በ2002 በኢየሩሳሌም በፈጸመችው አጥፍቶ መጥፋት ራሷን ብቻ ገድላለች፡፡ በዚሁ ዓመት የ18 ዓመቷ አያት ኣል አክራስ ሁለት የእስራኤል ሲቪሎችን መግደል ችላለች፡፡ ሐማስ እ.ኤ.አ. በ2004 ለቡድኑ የመጀመርያ የሆነችውን ሪም ሪያሺ በአጥፍቶ መጥፋት በማሳተፍ ሰባት ሰዎችን ማስገደል ችሏል፡፡ እ.ኤ.አ. በ2003 የኢራቅ ሁለት ሴት አጥፍቶ ጠፊዎችም በኢራቅ የአሜሪካ ወታደሮች ላይ ጥቃት አድርሰው ሞተዋል፡፡
እ.ኤ.አ. በ2010 ደግሞ ሁለት የቺቺኒያ አጥፍቶ ጠፊዎች በሞስኮ ባቡር ጣቢያ በፈጸሙት ጥቃት 38 ሰዎች ሲገድሉ፣ ከ60 በላይ አቁስለዋል፡፡ በዚሁ ዓመት በፓኪስታን የዕርዳታ ማዕከል ውስጥ በሴት አጥፍቶ ጠፊ በተፈጸመ ጥቃት 43 ሰዎች ተገድለዋል፡፡ የሴት አጥፍቶ ጠፊዎች እየበራከቱ መምጣት ለዓለም ሌላው ሥጋት ሆኗል፡፡ ተግባሩ ከ20 ዓመታት በፊት የተጀመረ ቢሆንም ጎልቶ መውጣት የጀመረው በቅርቡ ነው፡፡ በተለይ የናይጄሪያው ቦኮ ሐራም ከ18 ዓመት በታች ያሉ ሴቶችን ለአጥፍቶ መጥፋት መጠቀሙ ለየት ያደርገዋል፡፡

Friday, August 28, 2015

ህውሓት/ኢህአዴግ አሁንም እድሜው አጭር ነው !


ህውሓት ባካሄደችው ጠቅላላ ጉባሄ ከመረጠቻቸው 9 ከፍተኛ አመራሮች መካከል ወ/ሮ አዜብ መስፍን ይገኙበታል፡፡ የወ/ሮ አዜብ መስፍን በከፍተኛ አመራር ደረጃ መመራጣቸው ፣በቀጣይ በድርጅቱ ውስጥ የአቶ መለስ ዜናዊ “ዕራይ” ከሚዲያ ሽፋን እና ከንግግር ድምቀት ባለፈ የባለቤታቸውን “ራእይ” በተግባር ለመፈፀም እና ለማስፈፀም ከፍተኛ የሆነ ትጋት እንደሚያደርጉ የሚጠበቅ ነው፡፡
ከውሓት ጀርባ ድርጅቱን የሚመሩት አቦይ ስብሓት ነጋ እና የእሳቸውን ቡራኬ የሚቀበሉ ድግሞ ፤ የአቶ መልስ ዜናዊ “ራእይ” ከግለሰብ ፍላጎት አልፎ የድርጅት መገለጫ እና ማስፈፀሚያ መሆን የለበትም የሚል ፍልስፍና ይከተላሉ፡፡ በዚህም ምክንያት ከወ/ሮ አዜብ እና የእሳቸው ታማኝነት ከሚያረጋግጡ ጋር አንገት ለአንገት ተያይዘው መፋጠጣቸው የማይቀር ሃቅ ነው፡፡
ይህ ደግሞ በህውሓት እና በኢህአዲግ ድርጅት በቀጣይ አለመረጋጋት የበዛበት የስልጣን ውጣ ውረድ መብዛቱ ከወዲኹ የሚጠበቅ ነው፡፡ ለማስታውስ ያልህ አቶ መለስ ሞቱ ሚስጥር በሆነበት ወቅት አቦይ ስብሓት ነጋ “‪‎መለስ_ኖረ_አልኖረ‬ ፣በቀለ ኖረ አልኖረ፣ ፋጢማ ኖረች አልኖረች ……….”ማለታቸው የሚታወስ ነው፡፡
የህውሓት የትኛውም ቡድን የሚፈልገውን ዓላማ ለማስፈፀም እና ለመፈፀም የሚችለው ኢህአዴግ እንደ ድርጅት መቀጥል ሲችል ብቻ ነው፡፡አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ በህውሓት ፊት አውራሪነት የሚመራው የኢህአዴግ ገዥው መንግሰት ውጫዊ እና ውስጣዊ በሆኑ ምክንያቶች እድሜው አጭር እንደሚሆን የብዙ ሰው ግምት ነው፡፡
ይድነካቸው

የቀድሞ አንድነት ፓርቲ ማህበራዊ ጉዳዮች ኃላፊ አቶ አለነ ማህፀንቱ ውሳኔ ሳያገኙ ቀሩ


‹‹ስብስባን በማወክ›› ወንጀል የተከሰሱት የቀድሞ አንድነት ፓርቲ ማህበራዊ ጉዳዮች ኃላፊ አቶ አለነ ማህፀንቱ ውሳኔ ሳያገኙ ተለዋጭ ቀጠሮ እንደተሰጣቸው፤ የተከሳሹ ጠበቃ አቶ ገበየሁ ይርዳው ገለፁ፡፡
አቶ አለነ ዛሬ ነሐሴ 21 ቀን 2007 ዓ.ም አራዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቀርበው የነበረ ሲሆን፤ መዝገባቸውን እየተከታተለ የሚገኘው ተረኛ ችሎትም መዝገቡን እየተመለከተ እንዳለና ብይኑ እንዳልደረሰ ገልፆ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ አቶ ገበየሁ፣ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ እንደተቃወሙና ደምበኛቸው ብይን ለማግኘት ይህን ያህል ጊዜ መንገላታት እንደሌለባቸው እንዲሁም ዋስትናቸውን መከልከላቸው አግባብ እንዳልሆነ ለተረኛው ችሎት አስረድተዋል፡፡ ተረኛ ችሎቱ ብይኑ ስላልደረሰ ውሳኔ ላይ እንዳልደረሱ በመግለፅ ውሳኔውን ለማስተላለፍ ማለትም አቶ አለነ ‹‹ክሳቸውን ሊከላከሉ ይገባል ወይስ መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነፃ ተሰናብተዋል›› በሚለው ላይ ብይኑን ለማስተላለፍ ተለዋጭ ቀጠሮ ለመስከረም 5 ቀን 2008 ዓ.ም ሰጥቷል፡፡
አቃቤ ህግ በአቶ አለነ ማህፀንቱ ላይ ሁለት ምስክሮችን አሰምቶ ተከሳሹ ብይን ሳያገኙ፤ መዝገባቸው ከመደበኛ ችሎት ወደ ተረኛ ችሎት እንደተላለፈ ይታወቃል፡፡ አቶ አለነ መንግስት አይኤስን ለማውገዝ በጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ‹‹ስብሰባን አውከዋል›› የሚል ክስ ቀርቦባቸው፤ ክሳቸውን ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በመሆን ከግንቦት ወር 2007 ዓ.ም ጀምሮ እየተከታተሉ እንዳለ አይዘነጋም፡፡

ፍርድ ቤቱ አቶ ማሙሸት አማረ በነፃ እንዲቀለቀቅ ወሰነ

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተርየአራዳ ፍርድ ቤት አራተኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ ነሃሴ 22/2007 ዓ.ም በዋለው ችሎት አይ ኤስ አይ ኤስን ለመቃወም መንግስት ከጠራው ሰልፍ አንድ ቀን ቀድሞ ከለቅሶ ቤት ወደ ቤተ መንግስት የተደረገውን ሰልፍ አደራጅቶ መርቷል እንዲሁም ለዋናው (ለሚያዝያ 14/2007 ዓ.ም) ሰልፍ አነሳስቷል በሚል ክስ የተመሰረተበት አቶ ማሙሸት አማረ በነፃ እንዲለቀቅ ወስኗል፡፡
አቃቤ ህግ ነሃሴ 20/2007 ዓ.ም አቶ ማሙሸት ገንዘብ ከፍሎ ወጣቶችን ሰልፍ እንዳስወጣቸው፣ ወጣቶችን እንዳደራጀ፣ በሰላማዊ ሰልፉ ወቅትም መንግስትን የሚተቹ መፈክሮችን በመሪነት ሲያሰማ እንደነበርና ለሚያዝያ 14 ሰልፍም ሲያደራጅ እንደነበር ያስረዱልኛል ያላቸውን ሶስት የሰው ምስክሮችን ማሰማቱ ይታወሳል፡፡
ይሁንና ፍርድ ቤቱ የአቃቤ ህግ ምስክሮች የግል ሰራተኛ እንደሆነ በምስክርነት ቃላቸው ቢሰጡም በመስቀለኛ ጥያቄ አንደኛው የመንግስት ሰራተኛ፣ ሁለተኛው የወጣቶች ሊግ ከዚህም አለፍ ሲል የኢህአዴግ አባል፣ ሶስተኛው ደግሞ የጥቃቅንና አነስተኛ ባልደረባ መሆናቸውን በማመናቸው የሰጡት ምስክርነት ትክክል አለመሆኑን ያስረዳል ብሏል፡፡ በተጨማሪም ምስክሮቹ ገዥው ፓርቲን የሚደግፉና የወጣት ሊግ አባል ሆነው ገዥው ፓርቲን የሚቃወም ግለሰብ ላይ የሰጡት ምስክርነት ገለልተኛ ነው ብሎ ለማመን ያስቸግራል ብሏል፡፡
ከዚህም ባሻገር ምስክሮቹ የገዥው ፓርቲ ደጋፊ ሆነው እያለ አቶ ማሙሸት አማረ በተደጋጋሚ ይደውልላቸው እና ይገናኙም እንደነበር የመሰከሩ ሲሆን አቶ ማሙሸት ቀንደኛ የገዥው ፓርቲ ተቃዋሚ ሆኖ እያለ ከመንግስት (ከገዥው ፓርቲ) ቀንደኛ ደጋፊዎች እንዲህ አይነት ግንኙነት ይኖረዋል ብሎ ለማመን እንደማይቻል አስረድቷል፡፡ በሌላ በኩል ከ4 አመት ጀምሮ እስከ 7 አመት አዲስ አበባ ውስጥ የኖሩት ምስክሮች ስለ ሰልፉ ባስረዱበት ወቅት ቤተ መንግስትን ጨምሮ ሰልፉ ያለፈባቸውን ቦታዎች አናውቃቸውም ማለታቸው ራሳቸውን ከመስቀለኛ ጥያቄ ለማዳን ያደረጉት እንደሆነ ፍርድ ቤቱ ገልጾአል፡፡ በመሆኑም የምስክሮቹ ቃል ታማኒነት ስለሌለው አቶ ማሙሸት አማረ መከላከል ሳያስፈልገው በዛሬው ዕለት በነፃ እንዲለቀቅ ሲል ፍርድ ቤቱ ወስኗል፡፡
አቶ ማሙሸት አማረ ሚያዝያ 14/2007 ዓ.ም በተካሄደው ሰልፍ ላይ ሁከትና ብጥብጥ ፈጥሯል በሚል ተከሶ የነበር ቢሆንም በወቅቱ ከምርጫ ቦርድ ጋር በነበረው ክርክር ሰልፉ ላይ አለመገኘቱን የሚያጋግጥ መረጃ በማምጣቱ በነፃ እንዲለቀቅ ተወስኖ ነበር፡፡ ነገር ግን ክሱ ወደማነሳሳት ተቀይሮ እስከዛሬ እስር ቤት እንዲቆይ ተደርጓል፡፡

ግንቦት ሰባት ሊቀላቀሉ ሲሄዱ ተይዘዋል በሚል የሽብር ክስ የተመሰረተባቸው እነ ብርሃኑ ተ/ያሬድ ላይ የአቃቤ ህግ ምስክር ተሰማ፡፡


ዛሬ ነሀሴ 22/2007 ዓ.ም በፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 14ኛ ወንጀል ችሎት የቀረቡት አንደኛ ተከሳሽ ብርሃኑ ተ/ያሬድ፣
ሁለተኛ ተከሳሽ እየሩሳሌም ተስፋው፣ ሦስተኛ ተከሳሽ ፍቅረማርያም አስማማው እንዲሁም አራተኛ ተከሳሽ ደሴ ካህሳይ ‹‹አቃቤ ህግ በጻፈውና ለተከሳሽ በደረሰው የክስ ማመልከቻ ላይ አቃቤ ህግ የሰው ማስረጃ (ምስክር) አልጠቀሰም፤ እኛም መቃወሚያ ስናስገባም ሆነ እምነት ክህደት ቃል ስንሰጥ ይህን ግምት ውስጥ በማስገባት ነው፤ በመሆኑም የአቃቤ ህግ ምስክር ሊሰማብን አይገባም›› በሚል ተቃውሞ
ቢያቀርቡም አቃቤ ህግ ለፍርድ ቤቱ ባስገባው ክስ ላይ ምስክሩን መጥቀሱን በማስረዳት ምስክሩ እንዲሰሙለት ጠይቋል፡፡
ፍርድ ቤቱ የደረሰው የክስ ማመልከቻ ላይ ምስክር እንደተመዘገበ በማረጋገጥም ብቸኛ ሆነው የቀረቡትን አንድ የአቃቤ ህግ ምስክር ሰምቷል፡፡ ምስክሩም ከ1ኛ፣ 2ኛ እና 3ኛ ተከሰሾች ጋር ሰማያዊ ፓርቲ በሰላማዊ ትግል ውስጥ ሆነው እንደሚተዋወቁ፣ የካቲት 12/2007 ዓ.ም በ1ኛ እና 2ኛ ተከሳሽ አማካኝነት ሰላማዊ ትግሉ እንዳላዋጣ በመጥቀስ ግንቦት ሰባትን ለመቀላቀል ወደ ኤርትራ መጓዝ ማሰባቸውን ገልጸውለት
በዚያው ቀን ማታ 3ኛ ተከሳሽን ጨምሮ ወደ ባህር ዳር እንደተጓዙ ለችሎቱ አስረድቷል፡፡
ባህር ዳር ሲደርሱ ጠዋት ላይ ግን ምስክሩ ሀሳቡን በመቀየር ወደ አዲስ አበባ መመለስ እንደሚፈልግ እንደገለጸላቸው፣ 1ኛ
ተከሳሽ በበኩሉ ‹ጎንደር ላይ የምናገኘው ሰው ስላለ ቢያንስ እሱን ካገኘኸው በኋላ መመለስ ትችላለህ› እናዳለው፣ ነገር
ግን ምስክሩ በሀሳቡ ባለመስማማት ወደ አዲስ አበባ መመለሱንና ሌሎቹ ሦስቱ ግን ጉዟቸውን መቀጠላቸውን አስረድቷል፡፡ ‹‹ባህር ዳር ላይ ለምን ለመመለስ ወሰንህ›› የሚል መስቀለኛ ጥያቄ ከ1ኛ ተከሳሽ የቀረበለት ምስክሩ፣ ‹‹በወቅቱ ስሜታዊ የሚያደርጉ የግል ጉዳዮች ስለነበሩብኝ በስሜታዊነት የወሰንኩት ውሳኔ በመሆኑ ነው›› ሲል ተናግሯል፡፡
ምስክሩ ‹‹ለምስክርነት ያስገደደህ አካል የለም ወይ›› ተብሎ ሲጠየቅ ‹‹የለም›› የሚል መልስ ሰጥቷል፡፡ ‹‹ግንቦት ሰባት ነጻ
አውጭ ድርጅት ነው ወይስ አሸባሪ›› ተብሎ በተከሳሾች መስቀለኛ ጥያቄ ተነስቶ፣ አቃቤ ህግ ተቃውሞውን በማሰማት
‹‹ድርጅቱ በተወካዮች ም/ቤት አሸባሪ ተብሏል፡፡ ይህ የህግ ጉዳይ ነው›› በማለት ጥያቄውን ምስክሩ የመመለስ ግዴታ
እንደሌለባቸው አስረድቷል፡፡ ፍርድ ቤቱም ይህን ተቃውሞ ተቀብሎ ምስክሩ ጥያቄውን እንዲያልፉት ተደርጓል፡፡
‹‹ማዕከላዊ ታስረህ ነበር፣ ድብደባም እንደደረሰብህ በሚዲያ ሳይቀር ተዘግቧል፡፡ ልክ ነው?›› ተብሎ በመስቀለኛ ጥያቄ
ሲጠየቅ ምስክሩ ‹‹ማዕከላዊ ቃል እንድሰጥ ተደርጌያለሁ፤ ግን አልታሰርኩም›› የሚል መልስ ሰጥቷል፡፡
ፍርድ ቤቱ የምስክሩን ቃል ከሰማ በኋላ የአቃቤ ህግን አስተያየት የጠየቀ ሲሆን፣ አቃቤ ህግ የምስክሩ ቃልና የሰነድ
ማስረጃውን መርምሮ ፍርድ ቤቱ ብይን እንዲሰጥለት ጠይቋል፡፡ ፍርድ ቤቱም ብይኑን ለማሰማት ለመስከረም 5/2008 ዓ.ም
ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

የአርበኞች ግንቦት 7 መልዕክት


የግል ኑሮን ለማደላደል ሲባል የወያኔ አባል መሆን “ወይን ለመኖር” የሚል ስያሜ ከተሰጠው ዓመታት ተቆጥሯል። “ወይን ለመኖር” ዜጎች ነፃነታቸውን ለጥቅም አሳልፈው የሚሸጡበት፤ የሰው ልጅ ክብር የሚዋረድበት ገበያ ነው። በወይን ለመኖር “የገበያ ህግ” መሠረት እያንዳንዱ ዜጋ ሊያገኘው መብቱ የሆነውን አገልግሎት እንዲያገኝ የህወሓት፣ የብአዴን፣ የኦህዴግ፣ የደህዴግ፣ የአብዴፓ፣ የቤጉህዴፓ፣ የጋህአዴን፣ የሀብሊ ወይም የኢሶዴፓ አባል መሆን፤ አልያም መደገፍ ግዴታ ነው። እነዚህ ሁሉ ድርጅቶች የህወሓት ተቀጽላ ወያኔዎች ናቸው። የእነዚህ ድርጅቶች አባል ወይም ደጋፊ ያልሆነ እንኳስ የመንግሥት አገልግሎት ሊያገኝ ጥሮ ግሮ ያፈራውንም ይነጠቃል።
በዚህም ምክንያት፣ በገጠር ያለው አርሶ አደር ቁራጭ የእርሻ መሬት፣ የግብርና ባለሙያዎች የምክር እገዛ፣ የማዳበሪያና ዘር ግዢ፣ ብድር ወይም እርዳታ ለማግኘት በአካባቢው ባለ የወያኔ ድርጅት አባልነት መመዝገብ፤ አንድ ለአምስት መደራጀት እና የወያኔን የስልጣን እድሜ የሚያራዝሙ ነገሮችን መሥራት ይጠበቅበታል። በከተሞች ውስጥም ሥራ ለመቀጠር፣ ለደረጃ እድገት፣ የመኖሪያ ቤት (ኮንዶሚንየም) ለመግዛት ሲባል መወየን አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታ ሆኗል:: በንግዱም ዘርፍ የንግድ ፈቃድ፣ የሥራ ቦታ እና የባንክ ብድር ለማግኝት፣ የመንግሥት ጨረታዎችን ለማሸነፍ፣ ከጉምሩክ እቃ ለማስለቀቅ፣ የውጭ ምንዛሪ ለማግኘት መወየን ግዴታ ነው።
“ወይን ለመኖር” የኢትዮጵያን ሕዝብ ያዋረደ፤ ለትውልድ የሚተርፍ የማኅበራዊ ስነልቦና ኪሳራ ያደረሰ እና ደካማውን ወያኔን ጠንካራ በማስመሰል በሕዝብ የትግል መንፈስ ውስጥ ፍርሃትን የረጨ መሆኑ ግንዛቤ እየዳበረ በመጣ መጠን እየቀነሰ የመጣ ክስተት ነው። በአሁኑ ሰዓት ከቀድሞው እጅግ በተሻለ ኢትዮጵያ ውስጥ የምንገኝ ኢትዮጵያዊያን ራሳችንን ከህወሓት ባርነት እያላቀቅን ምሬታችንን በግልጽ መናገር የጀመርንበት ወቅት ነው፤ ከዚያም አልፎ የህቡዕ ተግባራዊ የትግል እንቅስቃዎችን ማድረግ ደረጃ ላይ ደርሰናል።
አገር ውስጥ እየተዋረደ የመጣው “ወይን ለመኖር” በአገዛዙ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አማካይነት በውጭ አገራት ከሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን (ዲያስፓራ) መካከል ነፃነታቸውን በጥቅም የሚለውጡ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያንን ፍለጋ ተሠማርቷል። አገዛዙ ተስፋ ያደረገው ያህል ባይሆንም ጥረቱ የተወሰነ ውጤት እያስገኘለት ነው። በጥቅማ ጥቅም እየደለለ ካመጣቸው ውስጥ በስርዓቱ ብልሹነት ያዘኑና የተሰማቸውን በግልጽ የተናገሩ መኖራቸው የሚያስደስትና የሚያበረታታ ቢሆንም ከመንደር ካድሬዎች ባነሰ ተለማማጮችና አጎብዳጆች በማየታችን ተሸማቀናል። ኢትዮጵያ ውስጥ ካለነው አብዛኛው ሕዝብ አንፃር ሲታይ በተሻለ የኑሮ ደረጃ ላይ ከሚገኙት ዲያስፓራዎች መካከልም ነፃነታቸውን በጥቅም ለመለወጥ የሚፈቅዱ መገኘታቸው አሳዛኝ ነው። እነዚህ ክብራቸውን በጥቅም የለወጡ ዲያስፓራዎች ዓለም ባንክንና የዓለም የገንዘብ ድርጅትን (IMF) ተክተው ህወሓት ስላስገኘው ፈጣን እድገት በአገዛዙ ራድዮ እና ቴሌቪዥን ሲነግሩን መስማት ያሳፍራል። የህወሓት አገዛዝ “ፍትህን፣ መልካም አስተዳርንና ዲሞክራሲን አስፍኗል፤ ይህንንም መጥተን በዓይኖቻችን ተመልክተናል” እያሉ የግፉን ገፈት እየቀመስን ላለነው ሲነግሩን መስማት ያማል።
እነዚህ ወገኖቻችን ህወሓትን በማሞካሸት የሚያገኙት መሬት ብዙ ድሆች የተፈናቀለቡት፤ ለእነሱ በብላሽ የተሰጠው ብድር በረሃብ ለሚጠቃ ወገን የተላከ እርዳታ መሆኑ ማሳሰብ ይገባል። ከህወሓትና አጫፋሪዎቹ ጋር ተስማምተው ባገኙት ገንዘብ የሚቆርሱት እያንዳንዱ እንጀራ የብዙ ወገኖቻችን ደምና እንባ የፈሰሰበት መሆኑ ማስገንዘብ ያሻል። ከህወሓት ጋር በማበር በወገኖቻችን ድህነትና ችጋር እየከበሩ ያሉ የዲያስፓራ ማኅበረሰብ አባላት ከዚህ እኩይ ሥራቸው እንዲታቀቡ ማስጠንቀቅ ይገባል። እኚህ ወገኖች የራሳቸው ክብር ማጉዳፋቸውን ብቻ ሳይሆን የልጅ ልጆቻቸውም የሚያፍሩባቸው መሆኑን ማስታወስ ይገባል። ከዚህም አልፎ የዛሬ ተግባራቸው ነገ በህግ የሚያስጠይቃቸው መሆኑን ሊያውቁ ይገባል።
አርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ለግል ጥቅማቸው ሲሉ የአገዛዙን እድሜ በማራዘም ላይ የተሰማሩ፤ በድሆች ድህነት ለመክበር በመሯሯጥ ላይ ያሉ፤ ለግል ጥቅማቸው ሲሉ ለአገዛዙ ጥብቅና የቆሙ የዲያስፓራ አባላት ከዚህ ተግባራቸው እንዲታቀቡ ያሳስባል።
አርበኞች ግንቦት 7 “ከህወሓት ውድቀት በኋላ ያለው ጊዜ ለእናንተም ከዛሬው የተሻለ ይሆናል። ዛሬ ከህወሓት ጋር ያላችሁን ሽርክና አቋርጡ። ለነፃነት የሚደረገውን ትግል እርዱ፤ መርዳት ባትችሉ እንቅፋት አትሁኑ፤ አለበለዚያ ግን ከተጠያቂነት የማታመልጡ መሆኑን እወቁ” ይላል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!! !

በእነ ብርሃኑ ተ/ያሬድ ላይ የአቃቤ ህግ ምስክር ተሰማ


የኢትዮ-ኤርትራ ድንበርን አቋርጠው ኤርትራ የሚገኘውን ግንቦት ሰባት የተባለ በተወካዮች ም/ቤት ሽብርተኛ የተባለ ድርጅትን ሊቀላቀሉ ሲሄዱ ተይዘዋል በሚል የሽብር ክስ የተመሰረተባቸው እነ ብርሃኑ ተ/ያሬድ ላይ የአቃቤ ህግ ምስክር ተሰማ፡፡
ዛሬ ነሀሴ 22/2007 ዓ.ም በፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 14ኛ ወንጀል ችሎት የቀረቡት አንደኛ ተከሳሽ ብርሃኑ ተ/ያሬድ፣ ሁለተኛ ተከሳሽ እየሩሳሌም ተስፋው፣ ሦስተኛ ተከሳሽ ፍቅረማርያም አስማማው እንዲሁም አራተኛ ተከሳሽ ደሴ ካህሳይ ‹‹አቃቤ ህግ በጻፈውና ለተከሳሽ በደረሰው የክስ ማመልከቻ ላይ አቃቤ ህግ የሰው ማስረጃ (ምስክር) አልጠቀሰም፤ እኛም መቃወሚያ ስናስገባም ሆነ እምነት ክህደት ቃል ስንሰጥ ይህን ግምት ውስጥ በማስገባት ነው፤ በመሆኑም የአቃቤ ህግ ምስክር ሊሰማብን አይገባም›› በሚል ተቃውሞ ቢያቀርቡም አቃቤ ህግ ለፍርድ ቤቱ ባስገባው ክስ ላይ ምስክሩን መጥቀሱን በማስረዳት ምስክሩ እንዲሰሙለት ጠይቋል፡፡
ፍርድ ቤቱ የደረሰው የክስ ማመልከቻ ላይ ምስክር እንደተመዘገበ በማረጋገጥም ብቸኛ ሆነው የቀረቡትን አንድ የአቃቤ ህግ ምስክር ሰምቷል፡፡ ምስክሩም ከ1ኛ፣ 2ኛ እና 3ኛ ተከሰሾች ጋር ሰማያዊ ፓርቲ በሰላማዊ ትግል ውስጥ ሆነው እንደሚተዋወቁ፣ የካቲት 12/2007 ዓ.ም በ1ኛ እና 2ኛ ተከሳሽ አማካኝነት ሰላማዊ ትግሉ እንዳላዋጣ በመጥቀስ ግንቦት ሰባትን ለመቀላቀል ወደ ኤርትራ መጓዝ ማሰባቸውን ገልጸውለት በዚያው ቀን ማታ 3ኛ ተከሳሽን ጨምሮ ወደ ባህር ዳር እንደተጓዙ ለችሎቱ አስረድቷል፡፡
ባህር ዳር ሲደርሱ ጠዋት ላይ ግን ምስክሩ ሀሳቡን በመቀየር ወደ አዲስ አበባ መመለስ እንደሚፈልግ እንደገለጸላቸው፣ 1ኛ ተከሳሽ በበኩሉ ‹ጎንደር ላይ የምናገኘው ሰው ስላለ ቢያንስ እሱን ካገኘኸው በኋላ መመለስ ትችላለህ› እናዳለው፣ ነገር ግን ምስክሩ በሀሳቡ ባለመስማማት ወደ አዲስ አበባ መመለሱንና ሌሎቹ ሦስቱ ግን ጉዟቸውን መቀጠላቸውን አስረድቷል፡፡ ‹‹ባህር ዳር ላይ ለምን ለመመለስ ወሰንህ›› የሚል መስቀለኛ ጥያቄ ከ1ኛ ተከሳሽ የቀረበለት ምስክሩ፣ ‹‹በወቅቱ ስሜታዊ የሚያደርጉ የግል ጉዳዮች ስለነበሩብኝ በስሜታዊነት የወሰንኩት ውሳኔ በመሆኑ ነው›› ሲል ተናግሯል፡፡
ምስክሩ ‹‹ለምስክርነት ያስገደደህ አካል የለም ወይ›› ተብሎ ሲጠየቅ ‹‹የለም›› የሚል መልስ ሰጥቷል፡፡ ‹‹ግንቦት ሰባት ነጻ አውጭ ድርጅት ነው ወይስ አሸባሪ›› ተብሎ በተከሳሾች መስቀለኛ ጥያቄ ተነስቶ፣ አቃቤ ህግ ተቃውሞውን በማሰማት ‹‹ድርጅቱ በተወካዮች ም/ቤት አሸባሪ ተብሏል፡፡ ይህ የህግ ጉዳይ ነው›› በማለት ጥያቄውን ምስክሩ የመመለስ ግዴታ እንደሌለባቸው አስረድቷል፡፡ ፍርድ ቤቱም ይህን ተቃውሞ ተቀብሎ ምስክሩ ጥያቄውን እንዲያልፉት ተደርጓል፡፡ ‹‹ማዕከላዊ ታስረህ ነበር፣ ድብደባም እንደደረሰብህ በሚዲያ ሳይቀር ተዘግቧል፡፡ ልክ ነው?›› ተብሎ በመስቀለኛ ጥያቄ ሲጠየቅ ምስክሩ ‹‹ማዕከላዊ ቃል እንድሰጥ ተደርጌያለሁ፤ ግን አልታሰርኩም›› የሚል መልስ ሰጥቷል፡፡
ፍርድ ቤቱ የምስክሩን ቃል ከሰማ በኋላ የአቃቤ ህግን አስተያየት የጠየቀ ሲሆን፣ አቃቤ ህግ የምስክሩ ቃልና የሰነድ ማስረጃውን መርምሮ ፍርድ ቤቱ ብይን እንዲሰጥለት ጠይቋል፡፡ ፍርድ ቤቱም ብይኑን ለማሰማት ለመስከረም 5/2008 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

Thursday, August 27, 2015

“እኛ ውጪ ሆነን ተጨንቀናል፤ እነርሱ ውስጥ ሆነው ያልቀላፋሉ!”


የህወሓት ደጋፊ አለ የተባለዉ
የፓርቲዎች ጉባኤ በኢትዮጵያቸን አስጨናቂ እየሆነ መጥቷል፡፡በተቃዉሞ ጎራዉም በገዢ ፓርቲዎችም ዉስጥ ማለት ነዉ፡፡በተቃዉሞዉም እጁ ስላለበት ተረጋግቶ ጉባኤ ማካሄድ አልተቻላቸዉም(አንዳንዶቹ በተፈጥሮኣቸዉ ያዉ ቢሆኑም)፡፡በገዥዉ ፓርቲ አባልና አጋር ፓርቲዎች መካከል ፉክክሩ ድብቅ ነዉ፡፡ጸረ ዲሞክራሲያዊና በጥቅም ላይ የተመሰረተ ነዉ፡፡ይህ የታፈነ ዉድድር የት ቦታ እንደሚበጠስና የአሸናፊና ተሸናፊ ወገን እንደሚፈጥር አይታወቅም፡፡ፍጻሜዉ ግን ይህ ሃቅ ይመስለኛል፡፡ የኢህኣዴግ አባል ፓርቲዎች ወደላይም ወደ ጎንም ማደግ አይችሉም፡፡ካደጉ ዉድቀት ይከተላል፡፡እድገታቸዉ ቀድሞዉኑ የተወሰነባቸዉ ናቸዉ፡፡ታድያ እዚህ ከተደረሰ መጪዉን ማሰብ ነዉ፡፡ማእበሉም ይበሉት ናዳዉ ሲነሳ የሚጠርገዉን በዋንኝነት ቢለይም ቅድሚያ የሚጎዳዉ ግን የአሁኑን ጎጅዎችን ነዉ፡፡ታሪክ እያሳየን ያለፈዉ ይህንን ነዉ፡፡በዚህ ማእበልና ናዳ የሚጠቀም ያለ አይመስለኝም፡፡በበኩላችን የሚጠቅመዉን ልናሳይ ባቅማችን ስንቀሳቀስ መንገዱን ዘግተዉ በደል ላይ በደል ጨምረዉ ቀብረዉም ቁመዉብናል፡፡
የብአዴንና ኦህዴድ ከፍተኛ የአመራር አባላት ጭምር እንወክለዋለን ስለሚሉት ሀዝብና ምድር የሚያቀርቡት እሮሮ የታመቀ በደል እንዳለ ያመኑ መሆኑን ይጠቁመናል፡፡ጉዳየ ተከድኖ ይብሰል አይነት ነዉና በሂደት እናየዋለን፡፡ድሮ ድሮ ህወኃት ለሁሉም የሚያለብሳቸዉ የረዕዮተ አለም ልባስ ነበረዉ፡፡ልባሱን አዉልቆ ከጣለዉ ሰንብቷል፡፡በኣንዳድንድ ልምድና ቀለም ቀመስ አመራር አባላቱ ለምኞት የሚሆን የተለጋገበ ርእዮት አለም ያላቸዉ ለማስመሰል ለአባሉና ህዝቡ በማይሰርጽበት ሁኔታ በሚድያዎቻቸዉ ሲግቱት ታዝበናል፡፡ኣባሉ ወድያዉ ይተፋወል፤ህዝቡ መስሚያ የለዉም፡፡መርህም የለም፤ለነገሩ ድሮም አልነበረም፡፡ተገፍተን ወጥተን ነበር ያሉትም የሚተካ አጥተዉ፤ተኩን ባዮችም ጠፍተዉ ወደ እርካቡ መጥተዋል፡፡ምንም አዲስ ነገር የለም!
“እኛ ውጪ ሆነን ተጨንቀናል፤ እነርሱ ውስጥ ሆነው ያልቀላፋሉ!” የህወሓት ደጋፊ የሆነ ሰዉ ተናገረዉ የተባለዉ ነዉ(የዋህ መሆኑ እንጂ የሚያንቀላፉትና ፖለቲካዉን የሚጫወቱት፤እዚያ አምሽተዉም ቤታቸዉ ገብተዉ የማይተኙትን ማየት ነበረበት)፡፡ዉስጡን ስለሚያዉቅ የጨነቀዉ አባል ነዉ፡፡ከቲፎዞነት ተነስቶ ለጥቅሙ ተጨንቆ ከማለት ይልቅ እንደ አባልና ዜጋ ጉዳዩ አሳስቦት ነዉ ብሎ ማሰብ ይሻላል፡፡ግን ይህ አባልና ሌሎች የህወሓት/ኢህኣዴግ ደጋፊዎች ደም የተገበረበትን ትግል ዲሞክራሲን በመግደል እንደተባበሩ በቅዲሚያ ሊረዱት ይገባል፡፡አገሪቱ የጋራ እንደመሆንዋ ተጸጽቶም ቀናዉን መንገድ መያዝ እንደህዝብ ለቀጣዩ ጉዞኣችን ይጠቅማል የሚል እምነት አለኝ፡፡እናንተ የለዉጥ ሃይሎች ሆይ ለዉጥን ፓርቲ እንደማይገድበዉ ልተረዱ ይገባል፡፡ከፓርቲ በላይ ሃገርና ህዝብ ነዉ፡፡ለዉጥ ፈላጊ የድርጅቱ አባላት ለዉጡ እንዳማራችሁ እንደቀረ ብናስተዉልም፤ለዉድቀታችሁ ተጠያቅዎች ግን ራሳችሁ መሆናችሁን ልትክዱት አይገባም፡፡ የህዝብ ድምጽን ደፍጥጦ በስልጣን ለመኖር ላሰበዉ ድርጅታቸችሁ በጭካኔ ሙሉ ድጋፍ ሰጥታችኃል፤በኛ በኩል የምንጠየቅበት ካለ የድርሻችንን ለመዉሰድ ዝግጁ ነን!የህዝባችንን መስዋእትነት አክብረን፤ህገ ምንግስቱን ተቀብለን ልናድግ ስንጥር ባለበሌለ አቅማችሁ ደፍጥታችሁን እዚህ ደርሳችኋል፤መልካም ጉዞ!!!!!!
Tekle Bekele's photo.
Tekle Bekele's photo.

መቀሌ ላይ የፌዴራል ፖሊስና የክልሉ ልዩ ሀይል ከፍተኛ ጥበቃ እያካሄደ ነው


የህወሓት 12ኛ ጉባኤ መካሄድ ተከትሎ የሊቀ መንበርነት ስልጣን ሽኩቻ እየተካሄደበት ይገኛል። ኣብዛኛው የትግራይ የፌስቡክ ኣክትቪስቶች፣ ወጣቶችና ሙሁራን የህወሓት ኣባላት፣ ሌሎች ለውጥ ፈላጊ ኣክትቪስቶችና ሌሎች ፖለቲከኞች በጉጉት እየጠበቁት ይገኛሉ ። የኣርከበ በድምፅ በጉባኤው መሳተፍ ለብዙዎች የኣዲስ ኣበባው ኣንጃ ወደ ኣሸናፊነት የተጠጋ ቢመስላቸውም ጉዳዩ ሌላ ነው። ኣርከበ ተመልሶ የማይወዳደር መሆኑ ስላረጋገጡ የትግራዩ ኣንጃም እንዲሳተፍ በኣንድ ለ ኣምስት ኔትወርክ ታስረው የመጡት የወረዳ ተሳታፊዎች(ማንበብና መፃፍ የማይችሉ የሚገኙባቸው ሴቶችና ገበሬዎች የሚገኙባቸው የኣባይ ወልዱ ታማኞች ) እንዲፈቅዱለት ኣድርገዋል። እንዲሳተፍ የተቀሰቀሰው ” ኣርከበ የመጣው ለሊቀ መንበርነት ሳይሆን በባቡርና ኢንዳስትሪ ከፍተኛ ስራ እንዲሰራ ነው። ስለዚ ቢሳተፍ ችግር የለውም ” የሚል ተነግሮሯቸው ነው።
“ኣባይ ደራ” የሚል የበረሃ ስሙ በመጥራት ” ከመለስ ሞት በሗላ ድርጅቱ ኣጋጥሞት የነበረው ከፍተኛ ችግር ያለ ኣባይ ደራ ምርጥ መሪነት ድርጅታችን ለመበታተን ይዳርጋት ነበር ” የሚል ፕሮፖጋንዳ ተምረው ኣጥብቀው በመያዝ ኣሁንም ሌላ ኣማራጭ እንደሌለ ኣምነው ለማስፈፀም ተዘጋጅተዋል። ወፍ የለም “ኣባይ ደራ ” የኣንድ ለ ኣምስት ኔትወርክ ሲቆጣጠሩ የቴሌው ኔትወርክ ደግሞ ዶክተር ደብረፅዮን በእጃቸው ይገኛል። ኣባይ ወልዱ የቴሌው ኔትወርክ ለመቆጣጠር ሞባይል ስልክ ወደ ኣዳራሽ እንዳይ ገባ ኣድርገዋል። እነ ዶክተር ደብረፅዮን ደግሞ የኣንድ ለ ኣምስት ኔትወርክ እንዳይሰራ መበተን ይጠበቅባቸዋል። ለውጥ ……………… የምትጠብቁ የዋሆች እርማቹ ኣውጡ። በስብሰባው ኣንድ ተሳታፊ ህዝቡ ክፉኛ ተቀይሞናል፣ የመረጠንም ዕሬት ዕሬት እያለው ነው። ስለዚ ለውጥ የህልውናችን ጉዳይ ነው። ኣለበለዚያ ጥፋት ቅርብናት በማለት የተናገረው ደማቅ ጭብጨባ ኣስገኝቶለታል። ስብሰባው ከተያዘለት ግዜ በላይ እንደሚፈጅ ታውቋል። የመቐለ ከሓወልቲ እስከ ኣክሱም ሆቴል ያሉ ጎዳናዎች በቖልዑ ኣሸንዳ ምትክ ብሬን የጫኑ ፓትሮል የፌደራል ፖሊስና የክልል ልዩ ሃይል እየጠበቁ ነው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ አስቀድሞ በህብር ሬዲዮ ህወሓት መሪዎችን የስልጣን ሽኩቻ ከጥቂት ሳምንታት በፊት በዘገብንበት ወቅት የህወሓት ታዣዥ የሆኑት የብአዴንና የኦህደዴድና የዸህዴግ አመራሮችን ሁለቱም ቡድኖች የየራሳቸውን ደጋፊ ለማሰባሰብ ሲሚክሩ ተስተውሏል። ህወሓት በ1993 ለሁለት የተከፈለ ሲሆን የአቶ መለስ ቡድን ከባድመ መልስ ሊዘምትበት ተነሳውን ቡድን አንጃ የሚል ስም ለጥፎ ማባረሩ የሚታወስ ሲሆን ከተባረሩት ውስጥ አቶ አባይ ጸሐዬ ይቅርታ ጠይቀው ሲመለሱ አቶ ገብሩ አስራትን ጨምሮ ተባረው የቀሩ እንደ አቶ ስዬ በሙስና ታስረው የወቱ ነበሩ።
የአቶ መለስን ሞት ተከትሎ ህወሓት ተከፍሎ የነበረ ሲሆን ጠላቶቻችን ብሎ የፈረጀው ሌላው የኢትዮጵአ ሕዝብ ስልታን ሊያገኝ ይችላል በሚል ጉዳዩን በሽምግልና ፈቶ አብሮ በክልልና በፌዴራል ዋና ዋናውን ስልታን ተቆጣጥሮ የቆው ሀይል ለዘንድሮውም ክፍፍል ተመሳሳይ <<ሽምግልና>> ሊአካሂድ ይችል ይሆናል። የቀሩት የይስሙላ ስልጣን የሚይዙ የሌሎች ድርጅት መሪዎች እንደተለመደው አሸናፊውን ቁጭ ብለው መጠበቃቸው አንዳንዶችን አስገርሟል።

አቶ ማሙሸት አማረ ለውሳኔ ተቀጠሩ ‹‹ምስክርነቱ የሀሰትና የተጠና ነው!›› ጠበቃው


አይ ኤስ አይ ኤስን ለመቃወም መንግስት ከጠራው ሰልፍ አንድ ቀን ቀድሞ ከለቅሶ ቤት ወደ ቤተ መንግስት ለተደረገውና ለዋናው (ለሚያዝያ 14/2007 ዓ.ም) ሰልፍ አነሳስቷል በሚል ክስ የተመሰረተበት አቶ ማሙሸት አማረ ዛሬ ነሃሴ 20/2007 ዓ.ም አራዳ ምድብ ችሎት ቀርቦ ለነሃሴ 22/2007 ዓ.ም ለውሳኔ ተቀጠሯል፡፡ አቶ ማሙሸት አማረ ሚያዝያ 14/2007 ዓ.ም በተካሄደው ሰልፍ ላይ ሁከትና ብጥብጥ ፈጥሯል በሚል ተከሶ የነበር ቢሆንም በወቅቱ ከምርጫ ቦርድ ጋር በነበረው ክርክር ሰልፉ ላይ አለመገኘቱን የሚያጋግጥ መረጃ በማቅረቡ በነፃ እንዲለቀቅ ተወስኖ ነበር፡፡ ነገር ግን ክሱ ወደማነሳሳት ተቀይሮ እስር ቤት እንዲቆይ ተደርጓል፡፡
አቶ ማሙሸት በአዲሱ ክስ የአቃቤ ህግን ምስክሮች ለመስማት ከ5 ጊዜ በላይ ፍርድ ቤት እንደተመላለሰ የተገለፀ ሲሆን በተለይ አንዱ ምስክር በፖሊስ ተይዞ እንዲመጣ ቢጠየቅም ፖሊስ ሳያስፈፅም ቀርቷል፡፡ ከአራቱ ምስክሮች መካከል ሶስቱ ዛሬ የመሰከሩ ሲሆን ‹‹አቶ ማሙሸት አማረ 300 ብር ከፍሎ ሰልፍ እንድንወጣ አድርጎናል›› ሲሉ መስክረዋል፡፡
ይሁንና ምስክሮቹ ከማሙሸት ጋር በተገናኙበት ወቅት እንዲሁም ገንዘቡ ሲሰጣቸው፣ ሰልፉ ያለፈባቸውን ቦታዎችና ስለ ሌሎችም ጉዳዮች ሲጠየቁ ‹‹አላስታውሰውም›› ከማለት ባለፈ ዝርዝር የምስክርነት ቃል ሳይሰጡ ቀርተዋል፡፡ ከምስክሮቹ መካከል ሁለቱ አቶ ማሙሸትን ያስያዙ ደህንነቶች መሆናቸውን አቶ ማሙሸትና ጠበቃው በችሎቱ የገለፁ ሲሆን ምስክሮቹ በበኩላቸው ስራቸውን ሲጠየቁ ‹‹የግል›› እያሉ ከመመለስ ውጭ የመንግስት ስራ እንደማይሰሩ ተናግረዋል፡፡ ሆኖም የመንግስት ሰራተኛ መሆናቸውን የሚያሳይ መታወቂያ ሲጠየቁ ሊያሳዩ አልቻሉም፡፡ ከሶስቱ ምስክሮች መካከል አንደኛው ስራውን ሲጠየቅ ‹‹የግል›› ብሎ የነበር ቢሆንም በመስቀለኛ ጥያቄ የቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ጥቃቅንና አነስተኛ አመራር መሆኑን አምኗል፡፡
ከምስክሮቹ መካከል ሁለቱ የመኢአድ ደጋፊዎች መሆናቸውን ሲጠቅሱ አንደኛው አቶ ማሙሸት ባቀረቡበት የመስቀለኛ ጥያቄ ከምርጫ በኋላ የወጣቶች ሊግና የኢህአዴግ አባል መሆኑን አምኗል፡፡ የኢህአዴግ አባል ሆኖም ቢሆን መኢአድን እንደሚደግፍም ገልጾአል፡፡ ዳኛው ‹‹በሁለት ወር ውስጥ እንዴት ብለህ የወጣቶች ሊግ አባል መሆን ቻልክ?›› ሲሉት መልስ ሳይሰጥ አልፎታል፡፡
የአቶ ማሙሸት አማረ ጠበቃ ሶስቱም ምስክሮች አብዛኛዎቹን ጉዳዮች እንደማያስታውሱ በመግለፃቸው የተጠና የምስክርነት ቃል መሆኑን ለችሎቱ አስረድተዋል፡፡ በተጨማሪም ከ7 አመት በላይ አዲስ አበባ ውስጥ ኖረው መስቀል አደባባይን ጨምሮ ሰልፉ አመራባቸው የተባሉትን ቦታዎች አናውቃቸውም ማለታቸው፣ መተዳደሪያ ስራቸውን መደበቃቸውና መታወቂያ ለማሳየትም ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ምስክርነቱ የሀሰት እንደሆነ ስለሚያረጋግጥ ደንበኛቸው በነፃ እንዲለቀቁ ጠይቀዋል፡፡

በሆቴል ባለቤቶች ቸልተኝነት የተነሳ የደረሰ እጅግ አሳዛኝ አደጋ ።


ለልጆችህ ቃል ገብተሀል ፣ ት/ት ከመከፈቱ በፊት ከአዲስ አበባ ወጣ አርገህ ልታዝናናቸው እናም በቃልህ መሰረት 3 ልጆችህን ይዘህ አሪፍ አድርጎ ሊያዝናችሁ እንደሚችል ወዳሰብከው ወደ ወሊሶ ትነዳና ነጋሽ ሎጅ ትገባለህ ትንሽ አረፍ ብለህም ወደ መዋኛው ቦታ ከደቂቃዎች በፊት ከሄዱት ሁለት ወንድሞቿ ጋር ለመቀላቀል የፈለገችውን ሴቷን ልጅህን ይዘህ መዋኛው ገንዳ ጋር ስትደርስ የሁለት ልጆችህን ሬሳ በመዋኛ ገንዳው ላይ እየተንሳፈፈ ትደርሳለህ ። ምን ይውጥሀል ከደቂቃ በፊት ይስቁ ይቦርቁ የነበሩ ልጆች አሁን ሬሳ ሆነው ስታይ ምን ታደርጋለህ ? ለማን ነው አቤት የምትለው ? ትናንት የሆነው ይሄ ነው ። ይሄ አሳዛኝ ነገር ነበር የተከሰተው ። አባት ላዝናና ብሎ ሳቂታ በ 13 እና በ 12 አመት አመት የሚገመቱ ቆንጅዬ ልጆች ከቤት ይዞ ወጣ ፣ በደቂቃዎች ውስጥ በጨካኝ ሞት ሁለት ልጆቹን አጣ ምን ይዞ ይመለስ ?
በሆቴሉ ውስጥ ላይፍ ሴቨር ባለመኖሩ ምክንያት ብቻ ታዳጊ ህፃን ነብዩ ዳንኤልና ፣ ታዳጊ ህፃን ቅዱስ ዳንኤል ሊዝናኑ በወጡበት ቦታ ቀሩ ፣ ገንዘባቸውን እንጂ የደንበኛ ህይወት ግድ በማይሰጣቸው ንዝህላል የ ነጋሽ ሎጅ አስተዳደሮች በፈፀሙት መቼም የማይካስ ስህተት በደቂቃ ሁለት ልጆቹን ያጣውን አባትና ሀዘኗን መቋቋም ያልቻለችውን እናት ማየት ምንኛ ልብ ይነካል ? ለመሆኑ ይህን ፈቃድ የሚሰጠው ቢሮ አንድ መዋኛ ገንዳ በውስጡ ያካተተ መዝናኛ ሲሰራ ላይፍ ሴቨር እንዲቀጠር የሚያስገድድ ህግ የለም እንዴ ? መንግስት ይህን በሆቴሉ አስተዳዳሪዎች ንዝህላልነትየተፈፀመን ከግድያ የማይተናነስ ወንጀል እንዴት ያየው ይሆን ? ይህን አሳዛኝ ነገር ከሰማን በሁዋላ ስለ ጉዳዩ ተጨማሪ ማብራሪያ ለመጠየቅ በ 011 3410002 ወሊሶ ወደሚገኘው ነጋሽ ሎጅ ደውለን ፣ ስልካችንን የተቀበለው ሰው ጉዳዩ ከሚመለከተው ሰው ጋር እንደሚያገናኘን ቃል ገብቶ ፣ መልሰን ስንደውል ስልካቸውን አጥፍተዋል ። በርግጥ እንዳሰቡት ከኛ መሸሽ ችለዋል ። ከህሊና ፍርድስ ኸረ ከህግስ ማምለጥ ይችሉ ይሆን ?
እንደወጣችሁት ለቀራችሁት ታዳጊዎች እግዚያብሄር ነብሳችሁን በአፀደ ገነት ያኑረው ።
.
note ፥ ይሄን አሳዛኝ ሁኔታ ለሌላው ት/ት ይሆን ዘንድ ሼር ማድረግ ብንችል መልካም ነው ። ነገም ሌላ እናት ፣ ነገም ሌላ አባት ልጆቹን ሊያዝናና ይዞ ወጥቶ ባዶ እጁን እንዳይመለስ ሊረዳ ይችላል
(ዋሲሁን ተስፋየ )

የህወሓት አገዛዝ ታጣቂዎች የስርዓቱ ደጋፊ ያልሆኑ ኢትዮጵያዊያንን ቤት ሰብረው በመግባት አሰቃቂ ግድያ በመፈፀም ላይ ናቸው!


የህወሓት አገዛዝ ታጣቂዎች ማንነታቸው እዳይታወቅ ጭምብል ለብሰው በሌሊት የስርዓቱ ደጋፊ ያልሆኑ ኢትዮጵያዊያንን ቤት ሰብረው በመግባት አሰቃቂ ግድያ በመፈፀም ላይ ናቸው!
በጎንደርና አካባቢው በተለይም ደግሞ በደምቢያ ወረዳ ቆላድባ ከተማ ውስጥ የህወሓት ታጣቂ ኃይሎች ጭምብል አጥልቀው በሌሊት እየተንቀሳቀሱ የሰፈር ቤት ሰርሳሪዎችን በመምሰል የአገዛዙ ደጋፊ ያልሆኑ ግለሰቦችን ቤት ሰብረው በመግባት ሰዎቹን በጩቤና በጥይት በመግደል ንብረታቸውን በመዝረፍ ስራ ላይ በሰፊው ተሰማርተዋል፡፡
ራሱን በመንግስትነት የሚጠራው ህወሓት የማፊያ ቡድን በውድቅት ሌሊት የሚፈፅመው አሰቃቂ ግድያና ዘረፋ በርካታ የስርዓቱ ደጋፊ ያልሆኑ ሰላማዊ ዜጎች ሰለባ የሆኑ ሲሆን የሰ/ጎንደር ደምቢያ ወረዳ ቆላድባ ከተማ ቀበሌ 02 ነዋሪ የሆነው የሰባት ልጆች አባት አቶ አብዬ ታረቀኝ አንደኛው ነው፡፡
ከጥቂት ዓመታት በፊት የህወሓት የአየር ኃይል አዛዥ የነበረው ሜ/ጀነራል ሞላ ኃ/ማሪያም ከነበረበት የኃላፊነት ቦታው ተወግዶ በአሁኑ ጊዜ የት እንዳለ እንደማይታወቅ የመከላከያ ምንጮቻችን ገለፁ፡፡
ገና ከበርሃ ጀምሮ እነመለስ ዜናዊና ስብሃት ነጋን በአጃቢነት እያገለገለ ጥሩ ቅርርብ የነበረውና ከመከላከያ ኤታማጆር ሹሙ ሳሞራ የኑስ ጋር ዶሮና ጥሬ ሆኖ የቆየው ሞላ ኃ/ማሪያም የመለስን ሞት ተከትሎ ከአየር ኃይል አዛዥነቱ የተወገደ ሲሆን እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የብላቴ ማሰልጠኛ ማዕከል አዛዥ ቀጥሎም የጦላይ የበታች ሹም ማሰልጠኛ አዛዥ ሆኖ የቆየ ሲሆን አሁን ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ ደግሞ በአጠቃላይ ከመከላከያ ተወግዷል፡፡ በምን ሁኔታ ላይ እደሚገኝም በውል እደማይታወቅ የመከላከያ ምንጮቻችን ጨምረው አስታውቀዋል፡፡

Wednesday, August 26, 2015

አሳዛኝ ዜና በቨርጂኒያ ኢነተርቪው በማድረግ ላይ የነበሩ ወጣት ሪፖርተር እና ካሜራ ማን ተገደሉ።


ዛሬ ጥዋት በኢትዮጵያ አቆጣጥር 12: 45 ላይ በቀጥታ ለሚተላለፍ ለቴሌቪዥን ስርጭት WDBJ 7 ዋሽንግተን አቅራቢያ በሚገኜው እስቴት በቨርጂኒያ ኢነተርቪው በማድረግ ላይ የነበሩ ወጣት ሪፖርተር እና ካሜራ ማን ተገደሉ።
አልሰን ፖርከር እድሜ 24 ሪፖርተር
አደም ዋርድ እድሜ 27 ካሜራ ማን
8 ጊዜ በተተኮሰባቸው ጥይት ሒወታቸው አልፏል።ድርጊቱን የፈፀመው ሰው በፍለጋ ላይ ነው።
ለሞቱት ነፍስ ይማር ፣ ለቤተሰባቸውም መጽናናትን እመኛለሁ
ልያ ፋንታ
ከዋሽንግተን ዲሲ

Tuesday, August 25, 2015

ሰበር መረጃ ውጥረቱ እያገረሸ መሆኑ ተሰማ

መከላከያ ሰራዊቱ ጥቃት ወይም ወረራ ለማድረግ ከፍተኛ ሰራዊት እያከማቸባቸዉ በሚገኙት በሰሜኑ አካባቢዎች አለመረጋጋት ነግሰዋል።
በትናንትናዉ እለት አንድ ጓድ መሪ 9 የሰራዊት አባላትን ከመመሪያ ዉጭ ይዞ በመንቀሳቀሱ እርሱን ለመከተል ፍለጋ ላይ የነበረ አነስተኛ የጦር ክፍል የኤርትራን ቀጠና አልፎ በመሄዱ ተደምስሷል።
ኤርትራም ያለው ሀይል በኢትዮጵያ በድንበር ላይ ተሰድሮ ዉጥረቱ እጅግ ተባብሶ መቀጠሉን ከስፍራዉ የደረሰን መረጃ ይጠቁማል።
ድል ለጭቁኖች!

ዛሬ፣ በእነሀብታሙ አያሌው ጉዳይ ማረሚያ ቤት ላይ ክስ ቀረበ


ሰኔ 01 ቀን 2006 ዓ.ም በሽብርተኝነት ወንጀል ከተጠረጠሩ በኋላ፤ በእነዘላለም ወርቅአገኘሁ የክስ መዝገብ፣ ከአንድ ዓመት በላይ ጉዳያቸው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ሲታይ ቆይቶ ባለፈው ሳምንት ነሐሴ 14 ቀን 2007 ዓ.ም በነጻ እንዲሰናበቱ በችሎቱ ትዕዛዝ ከተሰጣቸው አምስት ግለሰቦች መካከል 2ኛ ተከሳሽ ሀብታሙ አያሌው እና 7ኛ ተከሳሽ አብርሃም ሠለሞን እስከአሁን ድረስ ከቂሊንጦ እስር ቤት መፈታት ባለመቻላቸው የተነሳ፣ በዛሬው ዕለት ማረሚያ ቤቱ ላይ ክስ መቅረቡ ለማወቅ ተችሏል፡፡
ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት የቀረበው ክስ እንደሚያስረዳው ከሆነ፣ ከላይ በተጠቀሰው ቀን፤ ፍርድ ቤቱ፣ በክሱ ከተራ ቁጥር 2-5 እና 7ኛ ተከሳሽ ክሱን መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነጻ እንዲሰናበቱ በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት የመፍቻ ትዕዛዙን በ15/12/2007 ዓ.ም ለማረሚያ ቤቱ ቢደርስም ተከሳሾቹ እስከአሁን ድረስ ከእስር ሊለቀቁ አለመቻላቸውን ይጠቅሳል፡፡
በመሆኑም ‹‹ፍርድ ቤቱ ይህንን ባደረጉ የማረሚያ ቤቱ ኃላፊዎች ላይ የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ ባለማክበራቸው ሕጋዊ እርምጃ ከመውሰድ ጋር ተከሳሾቹን እንዲለቅ ጥብቅ ትዕዛዝ እንዲሰጥልኝ በማክበር አመለክታለሁ›› ሲሉ ለ2ኛ ተከሳሽ ሀብታሙ አያሌው ባለቤቱ ወ/ሮ ቤተልሄም አዛናው እና ለ7ኛ ተከሳሽ አብርሃም ሠለሞን ወላጅ እናቱ ወ/ሮ መሠረት ገ/ጊዮርጊስ በዛሬው ዕለት ትዕዛዙን ለሰጠው ችሎት ክሳቸውን ማቅረባቸው ታውቋል፡፡
ፍርድ ቤቱ በነጻ ካሰናበታቸው ተከሳሾች መካከል አብርሃ ደስታ፣ የሺዋስ አሰፋና ዳንኤል ሺበሺ ችሎት በመድፈር ወንጀል ሁለት ጊዜ ያህል መቀጣታቸው የሚታወስ ሲሆን ባለፈው ሳምንት ፍርድ ቤቱ የሰጠውን ውሳኔ ተከትሎ አቃቤ ሕግ በአምስቱም ተከሳሾች ላይ ይግባኝ ጠይቆ ከእስር እንዳይፈቱ ዕግድ አቅርቦ ነበር፡፡ እንዲሁም የተቀሩት አምስት ተከሳሾች እንዲከላከሉ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ መስጠቱ ይታወቃል፡፡

ሰበር ዜና በኦጋዴን ነጻ አዉጭ በአርበኞች ግንቦት 7 እና በጥምር ሐይሎች በሁለት አቅጣጫዎች ከፍተኛ ጦርነት ተቀሰቀሰ


በኦጋዴን ነጻ አዉጭ በርበኞች ግንቦት 7 እና በጥምር ሐይሎች በሁለት አቅጣጫዎች ከፍተኛ ጦርነት ተቆስቁሶ ነገር ግን የመጨረሻ የማጥቃት እርምጃ ለመዉሰድ ታግደናል እየተደበደብን ነዉ፤፤
ይላል የወያኔ መንግስት የሰሜኑ እና የምስራቁ እዝ።
ዛሬ ለሊት ከ23፡00 ሰአት ጀምሮ በሰሜን ጎንደር ልዩ ኮዱ 13.274645/ 37. 878478 በሰሜን ኦጋዴን ጋላዲ ጠረፍ አካባቢ ከባድ ዉጊያ ገጥሞናል በተለይ ሰራዊታችን በአየር ሐይሉ ላይ ምንም እምነት የለዉም፤፤
ዞሮ ሁሉ ሊደበድበን ይችላል ቃኘዉ አየር ሐይል በረራዎችም እያመጡ ያለዉ መረጃ ምንም የትም የማያደርስ ነዉ።
በየ ወቅቱ በሚቆሰቆሱ ግጭቶች ጉዳት እየደረሰብን ነዉ።
ከመከላከያ መሳሪያ ግምጃ ቤት የመጡልን መሳሪያዎች ያረጁና ከፍተኛ እድሳት ይፈልጋሉ።
ከፍተኛ ተጠሪነቱ ለመአከላዊ መንግስት የሆነ ሐይል ተቋቁሞብን እርስ በእርሳችን መግባባት አቅቶናል፤፤
የመሳሰሉት የዛሬዉ የወያኔን መከላከያ ቢሮ ደህንነትን ያጨናነነቀ ጩህት ነዉ፡፡
መከላከያ ሰራዊቱ ጥቃት ወይም ወረራ ለማድረግ ከፍተኛ ሰራዊት እያከማቸባቸዉ በሚገኙት በሰሜኑ አካባቢዎች አለመረጋጋት ነግሰዋል፤፤
በትናንትናዉ እለት አንድ ጓድ መሪ 9 የሰራዊት አባላትን ከመመሪያ ዉጭ ይዞ በመንቀሳቀሱ እርሱን ለመከተል ፍለጋ ላይ የነበረ አነስተኛ የጦር ክፍል የኤርትራን ቄጠና አልፎ በመሄዱ ተደምስሷል።
ኤርትራም ሰራዊቷን በኢትዮጵያ ቦርደሮች ላይ አጠራቅማለች ዉጥረቱ እጅግ ተባብሶ መቀጠሉን ከስፍራዉ የደረሰን መረጃ አመለከተ!!! 
ጉድሽ ወያኔ

ብአዴን በተለያዩ ክልሎች እና በውጭ አገር የሚገኙ የአማራ ተወላጆችን ለማደራጀት ያደረገው ሙከራ መክሸፉን አስታወቀ።


ድርጅቱ በ11ኛው ድርጅታዊ ጉባኤ ላይ እንደገለጸው፣ ለረጅም ጊዜ በአመራርነት ቆይቶ ስልጣኑን በመተካካት ሂደት ባስረከበውና ቁልፍ ስልጣኑን በተረከበው መካካል የመግባባት ችግር መኖሩን ገልጿል። ነባሩ አመራር ሁሉንም ሃላፊነት አስረክቦ ድርጅቱን የመልቀቅና ራሱን ገለል አድርጎ ለመኖር ይፈልጋል ያለው ብአዴን፣ በዚህም ላይ ነባሩ አመራር በአዲሱ አመራር እንደማይረካና ተደጋጋሚ ቅሬታ እንደሚያቀርብም ገልጿል። ቁልፍ ስልጣን የተረከበው አዲሱ አመራርም የራሱን አቅም የማያውቅ፣ ስልጣኑን ካስረከበው ነባር አመራር ለመማር ፍላጎት የሌለው ነው ብሎአል። በአዲሱ እና በነባሩ አመራር በኩል ለታየው አለመግባባት ምንጩ ዲሞክራሲያዊ ትግል አለመጎልበት፣ አድባርይነት ፣ ፊት ለፊት ለመታገል አለመፈለግ፣ ድክመቶችን ለመቀበል ፍላጎት አለመኖር፣ ሂስና ግለሂስን አለመቀበልና የድርጅቱን አሰራሮችን በተግባር ለማዋል ፍለጎት አለማሳየት ናቸው ብሎአል።
በቅርቡ ቁልፍ የሃላፊነት ቦታዎችን በተረከበው አመራርና በቆየው አመራር መካከል መደጋገፍ የሰፈነበት ግንኙነት ካልተፈጠረ መተካካቱ ህይወት አይኖረውም ብሎአል። በአዲሱ አመራርና እና ሃላፊነቱን ባስረከበው አመራር መካካል የታየው ልዩነት፣ ነባር አመራሩ የመተካካት መርሆ ከነባራዊ ሁኔታዎች ጋር እንዲዛመዱ እየጠየቀ ነው።
ምንም እንኳ አቶ በረከት ስምኦን በ11ኛው የድርጅቱ ጉባኤ ከስራ አስፈጻሚነት ቦታቸው እንደሚነሱ ቢታወቅም፣ ከዚህ ቀደም በተገለሉት በእነ አቶ አዲሱ ለገሰ፣ ተፈራ ዋልዋ እና ሌሎችም አመራሮችና በአዲሱ አመራር መካካል የተፈጠረው ክፍተት ስጋት ላይ ሳይጥላቸው አይቀርም። አዲሱ አመራር ነባሩን አመራር የሚንቀው ሲሆን፣ ነባሩ አመራር ደግሞ አዲሱ አመራር የትግል ወኔ የለውም ሲል ይተቻል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ብአዴን በተለያዩ ክልሎች እና በውጭ አገር የሚገኙ የአማራ ተወላጆችን ለማደራጀት ያደረገው ሙከራ መክሸፉን አስታውቋል። በተለያዩ አካባቢዎች የሚኖሩ የክልሉ ተወላጆች የድርጅቱን አስተሳሰብ እንደማይደግፉና ተወላጆቹን ለማደራጀት ቀደም ብሎ ያደረጋቸው ሙከራዎች መክሸፋቸውን አስታውቋል።
ኢሳት ዜና

በአዲስ አበባ የሚኖሩ የትግራይ ባለ ሃብቶች ሀብታቸውን እያሸሹ ነው


በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩ የትግራይ ባለ ሃብቶች በትግራይ ክልል ኢንቨስት እንዲያደርጉ የተደረገላቸው ቅስቀሳ በክልሉ ውስጥ ያለው ስር የሰደደ ብልሹ የአስተዳደር ሁኔታመጀመሪያ ይስተካከል ማለታቸውን ተገለፀ።
በምንጮቻችን መረጃ መሰረት- በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጅ ባለሃብቶች ያላቸውን ሃብት በትግራይ ክልል እንዲያሰማሩ ይርዳው በተባለ ከፍተኛ የህወሃት ካድሬ ነሓሴ 3/2007 ዓ/ም በተካሄደው ቅስቀሳ የተሞላበት ስብሰባ በብልሹ አሰራራችሁ የተጨማለቀውን አሰራራችሁ ካልተስተካከለ ገንዘባችንና ግዚያችንን አናባክንም ብለው እንደተቃወሙ ታወቀ።
እኛ ሃብታችን ልናሰማራ ከሆነ በመጀመሪያ ከላይ እስከታች ያለውን የክልሉ ብልሹ አካሄድ አስቁሙት፤ የፍትህና የመልካም አስተዳድር ጠንቅ የሆኑ መሪዎችን አስወግዷቸው፤ በአባልነት ሰውን መለየት አቋርጡት፤ ኃላ ቀርነትና ድህነት በማስወገድ ዴሞክራሲና ልማት ለማግኘት የታገለውን ህዝብ ልክ እንዳለፉት ስርዓቶች እየገረፋችሁት ነው። ይህ አይነት አካሄድ ሳይወገድ ትግራይ ውስጥ ሄደን የምናሰማራው ሃብት አይኖርም ማለታቸውና በወቅቱ የነበረው የመድረኩ መሪም ሃሳባቸው ከመቀበል ውጭ የሰጣቸው ማብራሪያ ሃሳብ ስላልነበረ ስብሰባው ያለ ፍሬ እንደተበተነ መረጃው አክሎ አስረድቷል።

በሶማሊያ ሀገር ህይወታቸው እያለፈ የሚገኙትን የኢትዮጵያ ወታደሮች ከቀን ወደ ቀን ቁጥራቸው እየጨመረ ነው


ethiopia millitary in somalia
በሶማሊያ ሀገር  እየተላኩና ህይወታቸው እያለፈ የሚገኙትን የኢትዮጵያ ወታደሮች ከቀን ወደ ቀን ቁጥራቸው እየጨመረ እንደሆነ ከተለያዩ ያገራችን አካባቢዎች የደረሰን መረጃ አስታወቀ።በሶማሊያ ሃገር እየሞቱ ያሉትን የኢትዮጵያ ወታደሮች ቁጥራቸው ከግዜ ወደ ግዜ እየጨመረ ባለበት በአሁኑ ሰዓት የሟቾቹ ቤተሰብ በየግዜው በቴለፎን መርዶ እየደረሳቸው እንደሆነ የገለፀው መረጃው በተለይም የኦሮሚያ ክልል ህዝብ ለምንድነው ስልጣን ላይ ያለው ስርዓት የሞቱት ልጆቻችን የማይነግረን በመሰረቱ ልጆቻችን ወደ ሶማልያ አገር ሂደው እንዲያልቁ የሚደረገውስ ለምን ዓላማ ነው? የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያውቀው ግልፅ በሆነ መንገድ መነገር አለበት በማለት ጥያቂያቸውን እያቀረቡ መሆናቸው ተገለጸ።
ይሁን እንጂ የኢህአዴግ ባለስልጣን አልሸባብን ለማጥፋት በሚል ምክንያት ከሃያላን መንግስታት የሚያገኙትን ዶላር ለመሰብሰብ ካልሆነ ከአገሩ ውጭ እየሄደ ህይወቱን እያጣ ላለው ወጣትና ቤተሰቦቹ ግን ምንም ዓይነት ደንታ እንደሌላቸው የሟቾች ቤተሰብና አንዳንዱ የአገራችን ምሁራኖች አስተያየታቸው እየሰጡ መሆናቸው አስታውቋል።
በተመሳሳይ አንድ በትግራይ ማእከላዊ ዞን፤ ተምቤን ዓብይ ዓዲ ውስጥ የሚኖሩ ወላጅ ልጃቸው በሶማልያ ሃገር ሄዶ መሞቱ ለምን አላማ ሲባል ነው ብለው መጠየቃቸው ባለፈው የዜና እወጃችን መገለፁ ይታወቃል።

ህወሀት ቴዲ አፍሮን ከልክ በላይ እየገፋው ነው:


ህወሀት ቴዲ አፍሮን ከልክ በላይ እየገፋው ነው:: ለቴዲ የህወሀት ኢትዮጵያ አላስቀምጥ ብላዋለች:: ምናልባትም ቴዲ ከሀገር ተሰደደ የሚል መራር ዜና ልንሰማ የምንችልበት ጊዜ እየቀረበ እንደሆነ ይሰማኛል:: በግሌ በተለይ ሰሞኑን የሚደርሱኝ መረጃዎች የህወሀትን የዕብሪት ለከት ማጣት የሚያሳዩ ቴዲንም ከሚወደው ህዝብና ከሚሳሳላት ሀገሩ እንዲለያይ የሚገፋፉ ናቸው:: ቴዲ መሰደድ እንደማይፈልግ የትኛውንም በደል ተቋቁሞ በሀገሩ መኖር ለምርጫም የማይቀርብ ጉዳይ እንደሆነ ባውቅም ትዕግስትም ልክና ድንበር አለውና የሰሞኑ ግፊትና ግፍትሪያ ከመራር ውሳኔ ሊያደርሰው እንደሚችል አምኜአለሁ::
ቴዲ ከእናቱ ቤት መሀል አዲስ አበባ እሱ ወደ ሚኖርበት ሲ ኤም ሲ በየጊዜው ሲመላለስ በደህንነቶች ታጅቦ: በመንገድ ላይ እያስቆሙ መከራውን አሳይተው በሚፈትሹት የህወሀት ሰዎች ተንገላቶ መሆኑ አስገራሚ ነው:: ቤቱ በደህንነቶች እጅ ላይ ወድቋል:: ዙሪያውን ይቆጣጠሩታል:: እንዳሻቸው እየጠሩ ያስፈራሩታል:: ከተቃዋሚዎች ጋር ትገናኛለህ በሚል ክብረ ነክ ምርመራ ያደርጉበታል:: በቅርቡ ባለቤቱ ታማ ወደ ኬኒያ ይዟት ሊሄድ ሲል መንቀሳቀስ የጀመረን አውሮፕላን እንዲመለስ አድርገው እንደ ወንጀለኛ በተሳፋሪ ፊት እየገፈተሩ ወስደውታል:: በተደጋጋሚ የውጭ ጉዞዎቹ እንዲሰረዙ አድርገዋል:: በርካታ ሌሎች ጥቃቶችን ፈጽመውበታል:: ለፊታችን አዲስ ዓመት በላፍቶ ያዘጋጀው ኮንሰርትም ሊሰረዝ እንደሆነ ከውስጥ ያገኘሁት መረጃ ያመለክታል:: በአዲስ አበባ ለህወሀት የሚጮሁ ኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያዎች የላፍቶው ኮንሰርት የሚሰረዘው በስፖንሰር እጦት ነው በሚል ቢያራግቡም እውነታው ግን የምንመርጥልህን እንጂ የመረጥካቸውን ዘፈኖች አታቀርብም ብለው ጣልቃ በገቡ የደህንነት ሰዎች ግፊት ነው::
ቴዲን ህወሀት ከሀገር ገፍትሮ ሊያስወጣው እየሞከረ ነው:: መንፈሰ ጠንካራ የሆነው ቴዲ እስከአሁን በትዕግስት እየመከተ ነው:: ሰው ነውና መንግስትን የሚያክል ሃይል ተነስቶበት ብቻውን ይመክታል ማለት አይቻልም:: ከጎኑ መቆም ግድ ይላል:: ህወሀት ቴዲ ላይ አይደለም ሰይፍ የመዘዘው:: ትውልዱ ላይ ነው:: ኢትዮጵያዊነት ላይ ነው::

የደኢህዴን አመራር የህዝብ ቁጣ ላይ እሳት እየጨመረ እንደሚገኝ ርዕሰ መስተዳደሩ ተናገሩ


‹‹በአመራሩ መካከል ትርምስና ጥርጣሬ ተፈጥሯል››
‹‹ሰማያዊና መድረክ ማሸነፍ ይችሉ ነበር›› አቶ ደሴ ዳልኬ
በቅርቡ ታደለ ቱፋ የተባለ ግለሰብ በጋሞ ብሄር ላይ የጻፈውን መፅሃፍ አስመልክቶ በደኢህአዴን አመራሮች መካከል የተፈጠረውን ውጥረት ለማርገብ በተደረገ ሚስጥራዊ ስብሰባ ላይ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ደሴ ዳልኬ የደኢህዴን አመራር የህዝብ ቁጣ ላይ እሳት እየጨመረ ነው ሲሉ መግለፃቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ የደረሰው የድምፅ ማስረጃ አረጋገጠ፡፡
የጋሞ ጎፋ ዞን በተለይም የአርባ ምንጭ የደኢህዴን አመራር በፌደራል ደረጃ በጥርጣሬ እንደሚታይ የገለፁት አቶ ደሴ ዳልኬ የጋሞ ጎፋ ዞን የደኢህዴን አመራሮች ከመጽሐፉ ፀሐፊ ጀርባ አሉ በሚል አመራሩ እርስ በእርስ ጥርጣሬ ውስጥ እንደሚገኝም ነገረ ኢትዮጵያ እጅ የገባው ድምፅ አረጋግጧል፡፡ በዚህም ምክንያት በክልሉ ርዕሰ መስተዳደርና በሌሎች አመራሮች መካከል ግልፅነት እንደሌለ ገልጸው ‹‹እናንተ ለእኔ ግልፅ ሁኑ!›› ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
የደኢህዴን በተለይም የጋሞ ጎፋ ዞን አመራሮች ከክልሉና ከዞኑ ያልወረዱ አጀንዳዎችን እንደሚያስፈፅሙና በጎን አመራሩ ያልተስማማባቸውንና የማያውቃቸውን ወረቀቶችም እንደሚያሰራጩ ተገልጾአል፡፡ በተለይም የአርባ ምንጭ አመራር መርህ እየተጣሰ ዝም ብሎ እንደሚያይ የገለፁት አቶ ደሴ ዳልኬ በዚህም ምክንያት ትርምስና አደጋ መፈጠሩን ጠቁመዋል፡፡
በስብሰባው ላይ የተገኙት የደኢህዴን አመራር በህዝቡ መካከል አንድነት እንዳይኖር ማድረጋቸውን፣ እንዲሁም ህዝብ ከአመራሩ እንደተነጠለ በመግለፅ ለችግሮቹ ድርጅቱን ተጠያቂ ሲያደርጉ ርዕሰ መስተዳደሩ በበኩላቸው ደኢህዴን ላይ ትችት ያቀረቡትን አመራሮች ሀሳብ በማጣጣል ችግሩን በጋሞ ጎፋ ዞን የሚገኙ ጥገኛ አመራሮች ችግር መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ሆኖም በክልሉና በፓርቲው ላይ አደጋና ትርምስ እንዳለ፣ እንዲሁም የደኢህዴን አመራር ችግር በህዝቡ ቁጣ ላይ እሳት እየጨመረ እንደሚገኝ አቶ ደሴ ዳልኬ ገልጸዋል፡፡
የጋሞ ጎፋ ዞን የደኢህዴን አመራሮች ችግሩን ለማርገብ ስብሰባው ላይ የተገኙትን የደኢህዴንን ከፍተኛ አመራር ‹‹የት ነበራችሁ? ለምንድን ነው ዛሬ የመጣችሁ?›› የሚል ጥያቄ ያነሱ ሲሆን አቶ ደሴ ዳልኬም ‹‹እስካሁን እናንተ አላችሁ ብለን ነው፡፡ አሁን ግን የመጣነው የዞኑ አመራር ሲተራመስ ጊዜ ነው›› ብለዋል፡፡
የደኢህዴን አመራር ‹‹አባቴ፣ አያቴ፣ ሰፈሬ የት ነኝ›› የሚል ክፍፍል መፈጠሩን በመግለፅ ወቀሳ አቅርበዋል፡፡ የደኢህዴን አመራሮች ከመፅሐፉ በስተጀርባ እንዳሉበት ጥርጣሬ መፈጠሩንና የተፈረጁ አመራሮች መኖራቸውም በስብሰባው ወቅት ተገልጾአል፡፡ ፍረጃው መቆም እንዳለበት የጠቆሙት ርዕሰ መስተዳደሩ ተጣርቶ እጁ እንዳለበት የታወቀ አመራር ላይ እርምጃ ይወሰዳል ብለዋል፡፡ ከመፅሐፉ ጋር ተያይዞ ህዝብ ሰላማዊ ሰልፍ የወጣ ሲሆን የህዝብን ጥያቄ ያነሱ ምሁራን እንዲፈቱ ጥያቄ አቅርቧል፡፡ ይሁንና ከታሰሩት መካከል አንድ ግለሰብ ተፈትቶ የነበር ቢሆንም በድርጅቱ ውሳኔ እስር ቤት እንዲቆይ ተደርጓል ብለዋል፡፡
በሌላ በኩል የደኢህዴን አመራሮች ‹‹ጥገኛ›› በሚል ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ግንኙነት እንዳላቸውና የተቃዋሚዎችን ሀሳብ እንደሚቀበሉ የተጠቆመ ሲሆን ይህን አስተሳሰብ ባይታገሉት መድረክና ሰማያዊ በጋሞ ጎፋ ዞን በተለይም አርባ ምንጭ ማሸነፍ ይችሉ እንደነበር ገልጸዋል፡፡ በስብሰባው ወቅት የዞኑ አመራሮች ጥያቄ እንዳላቸው በተጠየቁበት ወቅት ቅሬታቸውን ለመግለፅ ሲሞክሩ አቶ ደሴ መድረኩን ሳይሰጧቸው ቀርተዋል፡፡ ‹‹ጥገኛ›› ካሉት አስተሳሰብ ካልተላቀቁም እርምጃ እንደሚጠብቃቸው በመግለፅ አስጠንቅቀዋል፡፡

Monday, August 24, 2015

የወያኔ የመከላከያ ሰራዊት አባላት “የተቃዋሚዎች ሬድዮ ታዳምጣላቹ በሚል እየታሰሩ ነው


በገዢው ስራዓት የመከላከያ ሰራዊት ውስጥ እየተካሄደ ባለው ሰፊ የዓመቱ ግምገማ “የተቃዋሚዎች ሬድዮ መስማት” እንደዋነኛ
መገምገሚያ ነጥብ ሆኖ መነሳቱን ተገለፀ።በምንጮቻችን መረጃ መሰረት- በሁሉም የስርዓቱ መከላከያ ሰራዊት ውስጥ እየተካሄደ ያለውን
መጠነ ሰፊ የዓመቱ ግምገማ ወታደሩ ያለማቋረጥ እየፈረሰ በመጥፋት ላይ ያለው የትጥቅ ትግል እያካሄዱ በሚገኙ ድርጅቶች የሚሰራጨውን ሬድዮ መስማት ዋናው ከሆኑ ምክንያቶች አንዱ ስለሆነ ለምን ታዳምጣላችሁ፤ እነማን ናቸው የሚያዳምጡት መታወቅ አለባቸው በማለት እየተካሄደ ባለው ስብሰባ የሰራዊቱ አዛዦች ራሳቸው የስብሰባው መሪዎችና ገምጋሚዎች ሆነው በመቅረብ ለበርካታ የሰራዊቱ አባላት እያባረሩና እያሰሩ መሆናቸው ተገልጿል።
በተለይ በሰሜን እዝ እየተካሄደ ባለው የዓመቱ ግምገማ ላይ የሰራዊቱ አባላት ሓቀኛና ገምቢ ግምገማ ነው ብለው ስላላመኑበት ማንኛውም ሃሳብ ከመስጠት እንደተቆጠቡና የስርዓቱ ተጠቃሚዎች የሆኑት የበላይ መኮነኖች “እዚህ የተሰበሰብነው ሰራዊቱ አንዣቦበት ካለው የመበታተን አደጋ ለማዳን ስለሆነ የተቃዋሚዎች ሬድዮ ለምን ትሰማላችሁ ብለው ላቀረቡት ሃሳብ በተሰብሳቢዎቹ ማንኛውም ሚድያ መከታተል የዜጎች ህገ መንግስታዊ መብት ነው” ብለው የተቃወሙትን የናንተ አመለካከት ከተቃዋሚዎች ጎራ ነው በማለት
እንድፋሰርዋቸው መረጃው ጨምሮ አስርድቷል።

የዞን9 ጦማርያን የፍርድ ቤት ውሎ በድጋሚ ለጷግሜ 2 ተቀጠረ።


በነሶልያና ሽመልስ የክስ መዝገብ ለመከላከል ወይም ሳይከላከሉ በነፃ ለመሰናበት ውሳኔ ዛሬ ለ35ተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀርበው የነበሩት አራቱ በእስር የሚገኙት ጦማርያን በድጋሚ በተለዋጭ ቀጠሮ ተሸኝተዋል።
በዛሬው ውሎ ችሎቱ ያልተሰየመ ሲሆን ተከሳሾች እና ጠበቆች በቢሮ ተጠርተው ዳኞች ተሟልተው ስላልተገኙ ችሎቱ ለመሰየም አለመቻሉን ዶክመንቶችን ማየትና ውሳኔውን ፅፎ ማጠናቀቅ አሁንም እንዳልቻሉ በመግለፅ ዳኛ ዘሪሁን ለጷግሜ 2 ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠታቸውን አሳውቀዋል።
መደበኛ የወንጀል ችሎት ከነሃሴ 15 ጀምሮ የተዘጋ ሲሆን የዞን9 ጦማርያን ከመዘጋቱ በኃላ በሁለተኛ ልዮ ቀጠሮ እና በአጠቃላይ 36ተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ተመልሰው ይቀርባሉ ።

ከተሞቻችን ቆሸሹ ያሉ ሊባኖሳዊያን አመጽ አስነሱ


ሊባኖስ (ቤሩት) ከአንድ አመት በላይ ያለፕሬዘዳንት ኖራለች በዚህች ሀገር መንግስቱ እየተልፈሰፈሰ የሚገኝ ሲሆን የከተሞችን ቆሻሻ እንኳ በቅጡ መሰብሰብ አቅቶታል ነው የሚባለው ይህን ተከትሎ ከተሞቻችን በቁሻሻ ተወረሩ ያሉ ሊባኖሳዊያን ትናንትናና ሰሞኑን ከባድ አመጽ ማስነሳታቸው ነው የተነገረው አመጹ ዛሬ ጋብ ቢልም ከፖሊስም ሆነ ከተቃዋሚዎቹ ወገን የበርካታ ሰዎችን መቁሰልና መጎዳትን ማስከተሉ ነው የተነገረው እናንት ቁሻሾች በተባለው ሊባኖወሳውያኑ በዚህ አመጻቸው መንግስቱ ከስልጣኑ ውረድ እስከማለት መድረሳቸው ነው የተነገረው
Anger Over Uncollected Garbage Sparked Riot in Lebanon
 
Lebanon is a country who lives without a president for more than a year. And now, this country is in riot due to uncollected garbage trashes. Time reported “You stink” protests which started in the country is going serious and protestors are now demanding the overthrow of the government. Here is the report

እነ ማቲያስ መኩሪያ ለነሃሴ 27 ተቀጠረባቸው


አይ ኤስ አይ ኤስ በኢትዮጵያውያን ላይ የፈፀመውን አሰቃቂ ግድያ ለመቃወም መንግስት በጠራው ሰልፍ ሰበብ የታሰሩት እነ ማቲያስ መኩሪያ ለነሃሴ 27/2007 ዓ.ም ተቀጠረባቸው፡፡ ፖሊስ በጊዜ ቀጠሮ ወቅት ‹‹የቪዲዮ ማስረጃም አለን›› በማለቱ ተከሳሾቹ ‹‹ቪዲዮው ይቅረብልን፡፡ የቪዲዮ ማስረጃው ለእኛም የመከላከያ ምስክርነት ይጠቅመናል›› ብለው ጠይቀው የነበር በመሆኑ፤ ፍርድ ቤቱ የቪዲዮ ማስረጃው መቅረብ እንዳለበትና እንደሌለበት ብይን ለመስጠት ለነሃሴ 5/2007 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቶ ነበር፡፡ ይሁንና በዚህ ቀን የመናገሻ ፍርድ ቤት የማይሰራ በመሆኑ ችሎቱ በአራዳ ፍርድ ቤት በተረኛ ዳኛ ታይቶ ‹‹ጉዳዩ አልተመረመረም፡፡›› በሚል ብይን ለመስጠት ለነሃሴ 18/2007 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቶ ነበር፡፡ በዛሬው ቀጠሮም ተረኛ ዳኛው ‹‹የምንሰራው በተራ ስለሆነ አላየሁትም፡፡ አልተመረመረም›› በሚል ለብይን ለሃሴ 27/2007 ዓ.ም ሌላ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
ተከሳሾቹ 4 ወር ሙሉ በመጉላላት ላይ መሆናቸውን በመግለፅ በቶሎ ፍርድ እንዲሰጣቸው ገልጸዋል፡፡ አንደኛ ተከሳሽ ማቲያስ መኩሪያ ‹‹4 ወር ሙሉ ያለ ፍርድ እየተጉላላን ነው፡፡ በቶሎ ፍርድ ሊሰጠን ይገባል›› ሲል ቅሬታውን አቅርቧል፡፡ ፍርድ ቤቱ ቪዲዮው ላይ ብይን ለመስጠት ቀጠሮ ሲሰጥ የዛሬው ለአራተኛ ጊዜ ነው፡፡ ተከሳሾቹ ባለፈው ችሎትም የፍርድ ሂደቱ መጓተቱን አስመልክተው ቅሬታ ማቅረባቸው ይታወሳል፡፡
በማቲያስ መኩሪያ መዝገብ የተከሰሱት 1ኛ ማቲያስ መኩሪያ፣ 2ኛ መሳይ ደጉሰው፣ 3ኛ ብሌን መስፍን፣ 4ኛ ተዋቸው ዳምጤ ሲሆኑ ከመሳይ ደጉሰው ውጭ ያሉት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ናቸው፡፡
Ethio Hagere's photo.

Sunday, August 23, 2015

የደቡብ ሱዳን ግጭት መባባሱ ተዘገበ


የደቡብ ሱዳን ጦርነት በእስከአሁን ሂደት ከ 10 ሺህ በላይ ዜጎችን ህይወት መቅጠፉና በመቶ ሺህዎች ለሚቆጠሩ ዜጎች ስደት መንስኤ መሆኑ አይዘነጋም ይሁን እንጂ ለሀገሪቱ ሰላም ያመጣል ተብሎ ትልቅ ተስፋ የተጣለበት የቅርብ ጊዜው የአዲስ አበባ ድርድር ውጤቱ የተጠበቀውን ያክል መሆን ሳይችል ቀርቷል
በሰላም ስምምነቱ ሰነድ ላይ ተቃዋሚው ሪክ ማቻር ፊርማቸውን ቢያኖሩም የሀገሪቱ መንግስት ፕሬዘዳንት ሳልቫ ኪር ግን ጊዜ ይሰጠኝ በሚል ፊርማቸውን ሳያኖሩ ነው የተመለሱት ይህን ተከትሎ አሁን ላይ በሀገሪቱ ከባድ ጦርነት መቀስቀሱ ​​የተነገረ ሲሆን የሀገሬው ዜጎች እልቂት ከድጡ ወደማጡ እንዳይባባስ ከወዲሁ እየተሰጋ ይገኛልአቀፉ ማህበረሰብ የማእቀብ አለም ማስፈራሪያዎችን በተደጋጋሚ ለተፋላሚዎቹ ከመስጠት በዘለለ እስከአሁን ቁርጥ ያለ የመፍትሄ እርምጃ አልወሰደም ተብላል

ለሰላም አስከባሪ 11 ሺህ የኢትዮጵያ ሰራዊት የሚከፈለው ደምወዝ ከ90 በመቶ በላይ የህወሀት ካዝና ውስጥ የሚገባ ነው::


ዛሬ ለኢሳት የደረሰው ጥብቅ መረጃ 11ዓመታትን ወደ ኋላ በትዝታ ወሰደኝ:: ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከዋናው ጸሀፊ ቢሮ አፈትልኮ የወጣው መረጃ እንደሚያጋልጠው ለሰላም አስከባሪ 11 ሺህ የኢትዮጵያ ሰራዊት የሚከፈለው ደምወዝ ከ90 በመቶ በላይ የህወሀት ካዝና ውስጥ የሚገባ ነው:: በወር 13 ሚሊዮን ዶላር(500 ሚሊዮን ብር ገደማ) የወታደሩን ገንዘብ ህወሀቶች ይቀራመቱታል:: ይህን ጉዳይ የመንግስታቱ ድርጅት የሚያውቀው ይመስለኛል:: ለዚህም እኔ የተሳተፍኩበትን የሰላም አስከባሪ ዘመቻ አጋጣሚ በአስረጂነት ማሳየት እችላለሁ::
እኤአ በ2003-2004 በመንግስታቱ ድርጅት የበላይነት: በአፍሪካ ህብረት አስፈጻሚነት ከተላከው የኢትዮጵያ የሰላም አስከባሪ ሰራዊት ጋር ወደ ቡሩንዲ ሄጄ ነበር:: ወደ 18 የምንሆን አስተርጓሚዎች ከ8 ወር እስከ 1 ዓመት ቆይተናል:: ዝርዝሩን ሌላ ጊዜ በሰፊው እመለስበታለሁ:: ከገንዘብ ጋር በተያያዘ የተፈጸመውን የህወሀቶችን ለከት ያጣ ስግብግብነትን ላጫውታችሁ::
በዘመቻው በUN ደረጃ ወርሃዊ ደምወዝ ከ1000 ዶላር ያላነሰ: የመስክ ክፍያ በቀን 60 ዶላር: የበዓል ክፍያ በአንድ በዓል 1000 ዶላር: የላብ መተኪያ: …..በጣም ብዙ ዓይነት ክፍያዎች ነበሩት:: አብዛኛው የሰላም አስከባሪ ሰራዊት አባላት በተስፋ ነበር ወደ ቡሩንዲ የተጓዘው:: እዚያ እንደደረስን ነገሮች ሁሉ የተገላቢጦሽ ሆኑ:: ቃል የተገባው: በውል የታሰረው( የሚገርመው የውሉን 3 ኮፒዎች አንሰጥም ብለው እዚያው መከላከያ ግቢ ቀርቷል:: መንግስትን አምነን ነው የተጓዝነው) ክፍያ የለም:: በወር 40 ዶላር ለኪስ እየተሰጠን: ምግብና መጠጥ በአላሙዲን እየቀረበልን: እየበላንና እየጠጣን መኖር ብቻ ሆነ:: ከኢትዮጵያ ሌላ የደቡብ አፍሪካና ሞዛምቢክ የሰላም አስከባሪ ሃይሎችም ለተመሳሳይ ዘመቻ ቡሩንዲ ገብተዋል:: ለእነሱ የሚገባቸው ክፍያና ጥቅማጥቅም ሀገራቸው በባንክ አካውንታቸው የሚገባላቸው ይህንንም የሚያረጋግጥ ደረሰኝ በየወሩ እንደሚደርሳቸው በነበረን ቅርበት ተረዳን:: እኛ ግን ምንም የለም:: ስንጠይቅ ኢትዮጵያ ይጠራቀምላችኋል የሚል መልስ ከማስፈራሪያ ጋር ይሰጠናል:: በእኛና በሌሎቹ ለተመሳሳይ ዘመቻ በመጡ ሀገራት የሰላም አስከባሪው ዘመቻ አባላት መሃል ያለው የኑሮ ሁኔታ የሰማይና የምድርን ያህል የሚራራቅ ነበር:: በህወሀት ስግብግብነት የተነሳ በጣም በሚያሳፍር የኑሮ ገጽታ መቀለጂያ ሆንን:: በሰራዊቱ ውስጥ ቅሬታው ስር ሰደደ:: ተስፋው ጨለመ:: በወር 40 ዶላር እየወረወሩ እዚያ ይጠራቀምላችኋል በምትል ከቃል ያለፈ በደረሰኝ ያልተረጋገጠች ተስፋ ብቻ ይዘን በብስጭት ገፋን:: በመሃል ሲብስብን አስተርጓሚዎች ተነጋግረን ቡጁምቡራ በሚገኝ የUN ጽ/ቤት አቤቱታ ልናቀርብ ሄድን:: የተሰጠን ምላሽ ተስፋችንን ይበልጥ ገደለው:: “ስለ እናንተ የተፈራረምነው ከመንግስታችሁ ጋር በመሆኑ አይመለከተንም:: መንግስታችሁን ጠይቁ::” የሚል ወሽመጥ የሚቆርጥ ምላች ተሰጠን::
በመሃሉ መለስ ዜናዊና ሳሞራ የኑስ ሊጎበኙን ቡጁምቡራ መጡ:: ሳሞራ ሰብስቦን ችግር ካለ ንገሩኝ አለ:: ሰራዊቱ የክፍያው ነገር ሲያንገበግበው ስለከረመ ሳሞራን ሲያገኝው በየተራ እየተነሳ ጠየቀው:: ሳሞራ ጀት ሆነ:: ባለጌ አፍ እንዳለው ያረጋገጥኩት የዚያን ዕለት ነው:: የኢትዮጵያን የችግር መዓት ሲዘረዝር: መዓት ሲያወራ ቆየና ” ሰው እንደ ቤቱ እንጂ እንደ ጎረቤቱ አይኖርም:: የሌሎችን እያያችሁ እንደነሱ እንሁን ማለት አደጋ አለው:: እዚህ ገንዘብ ምንም አያደርግላችሁም:: በብር ኢትዮጵያ እየተጠራቀመላችሁ ነው:: ለሸርሙጣ ፈልጋችሁ ከሆነ ኢትዮጵያ ስትመለሱ ትደርሱበታላችሁ…..” እያለ ወረደብን:: ሰራዊቱ ቅስሙ ተሰበረ:: ብዙ የምንሰራው ስራ አለ:: ትምህርት ቤት እንገነባለን:: ….እያለ ተንዘባዘበ:: የዚያን ዕለት ሌሊት ከአምቦ የመጣ የሰራዊቱ አባል በታጠቀው መሳሪያ ራሱን አጠፋ:: ባርቆበት ነው የሚል ሪፖርት እንድናዘጋጅ በህወሀት የጦር አዛዦች መመሪያ ተሰጥቶን የውሸት ሪፖርት አዘጋጅተን ለUN ተላከ:: ይህ የሆነበትም ራሱን ካጠፋ UN ካሳ አይከፍልም:: እርግጠኛ ነኝ በዚህ የተገኘውን በብዙ መቶ ሺህ የሚቆጠር ዶላር ህወሀቶች ኪስ ገብቷል::
ወደ ኢትዮጵያ ስንመለስ እየተጠራቀመላችሁ ነው እየተባለ ስንሸነገል የከረምንበትን ገንዘብ ሊሰጡን ተዘጋጁ:: ለአንድ የሰላም አስከባሪ ሰራዊቱ አባል በትንሹ ከ250ሺህ ብር በላይ ወይም በወቅቱ ምንዛሪ 10ሺህ ዶላር መከፈል ነበረበት:: በጣም የሚያሳፍር የሚያስደነግጥ ነገር ነበር የጠበቀን:: እንደ ቆይታ ጊዜ ከ15ሺህ እስከ 25ሺህ የኢትዮጵያ ብር ሰጥተው አሰናበቱን:: ከእያንዳንዳችን ከ200ሺህ ብር በላይ ህወሀቶች ተቀራመቱት:: …በሌላ ጊዜ በስፋት እመለስበታለሁ::

የትግራይ ምእራባዊ ዞን አስተዳዳሪ የሆነው ፍስሃ በርሀ ከ44 ሚልዮን ብር ለግል ጥቅሙ ማዋሉ ተጋለጠ


AMEHADAR ZOBA MERAB AYTEFISHA BERHE
የትግራይ ምእራባዊ ዞን አስተዳዳሪ የሆነው ፍስሃ በርሀ ከ44 ሚልዮን ብር በላይ ለግል ጥቅሙ በማዋሉ የተነሳ የዞኑ ነዋሪዎች ምሬታቸውን በማሰማት ላይ መሆናቸው ተገለፀ። ለደህሚት በደረሰው መረጃ መሰረት የምእራብ ትግራይ ዞን አስተዳዳሪ የሆነው ፍስሃ በርሀ ለሁመራ ከተማ መሰረተ ልማት ተብሎ በተለያየ መልኩ ከህዝብ የተዋጣው 44 ሚሊዮን ብር ስልጣኑን ተገን በማድረግ ለግል ጥቅሙ ማዋሉን ታውቆ እያለ እስከ አሁን ድረስ ሊጠየቅ አልቻለም በሚል የሁመራ ከተማ ከንቲባ አቶ አለሙ አየነው ይመራው በነበረው ስብሰባ ላይ ጉዳዩ ቢነሳም አጥጋቢ የሆነ ምላሽ እንዳልተሰጠበት ለማወቅ ተችሏል። መረጃው በማከል ይህ በትክክል የተመደበውን በጀት ያጠፋፋው ፍስሃ በርሀ እንደሆነ አስቀድሞ በማስረጃ አስደግፈው ቢያቀርቡም የተጠፋፋው ገንዘብም የክልል ከፍተኛ ባለስልጣናት እጅ ሰላለበት ገንዘቡን ያጠፋፋው ሃላፊ አንድ ጊዜ ወደ ሌላ ስራ ሄደዋል። ሌላ ጊዜ ደግሞ ታምመዋል በማለት እርስ በርሳቸው የሚጋጩ ምክንያቶችን በመደርደር እስከ አሁን ድረስ ወደ ህግ ሊቀርብ ባለመቻሉ ምክንያት ነዋሪውን ህዝብ እንዳስቆጣው መረጃው አስረድቷል።

የአዲሱ ህውሀት መንግስት መጥፎ አጋጣሚ!! – ከኤርሚያስ ለገሠ (ክፍል አንድ )


1• ደስታ እና ሀዘን
ሰሞኑን ፍቺ በፍቺ ሆነናል። የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን ከፊል አካል ተፈታ። ደስ አለን። የተፈቱት ካልተፈቱት ያላቸው ልዩነት ለብዙዎች ግራ ቢያጋባም!…ዛሬ ደግሞ እነ ሀብታሙ አያሌው ተፈተዋል። ይህም በግለሰብ ደረጃ ደስ የሚል ዜና ነው። ቢያንስ በቅርብ የማውቀው ሀብታሙ (” ሀብትሽ!”) ክፋ ደጉን የማታውቀው ልጁ እጁ ላይ ስታንቀላፋ፣ ወደ አልጋዋ ወስዶ ሲያስተኛት፣ ከእንቅልፏ ስትነቃ አቅፎ ሊያነሳት በመቻሉ ደስ ይለኛል። እንኳን ለዚህ አበቃህም ማለት እፈልጋለሁ።
በሌላ በኩል ገዥው ቡድን በምክንያት እያሰረ በምክንያት የሚፈታበት ሁኔታ ለራሱ ስልጣን መቆያ ትክክል ቢሆንም ለኢትዬጲያ የፍትህ ስርአት ምን ያህል ንቀት እንዳለው የሚያሳይ ተደርጐ ሊወሰድ የሚችል ነው። ሰዎች በህውሀት ላይ አደጋ ሲጋርጡ በፓለቲካ ውሳኔ ይታሰራሉ…ህውሀታዊ ምክንያት !። ገዥው ቡድን ላይ የተጋረጠው አደጋ በሌላ ጐን ሲያጋድል ደግሞ በእጁ ይዞ የሚያሰቃያቸውን ይፈታል…ህውሀታዊ የመፍታት ምክንያት!!
ሀብታሙ አያሌውና ድርጅቱ ” አንድነት” ህውሀትን በሰላማዊ ትግል ፈተና ውስጥ ለመክተት ስትራቴጂ ነድፈው ሰፊ እንቅስቃሴ ጀመሩ። የለውጥ ንፋስም በስሱ መንፈስ ጀመረ። እነ ሀብታሙ በአደባባይ ” እመኑኝ ኢህአዴግም ይወድቃል! ኢትዬጲያም ነጳ ትወጣለች!” በሚል መሪ መፈክር ገዥዎችን አስጨነቁ። የስርአቱን ባህሪያት በቅርብ የምናውቅ ሰዎች የእነ ሀብታሙ እድሜ አጭር እንደሚሆን አሳወቅን። ርግጥም ” ይቺ ባቄላ ካደረች አትቆረጠምም!” በሚል መርህ የሚመራው ገዥ ቡድን እነ ሀብታሙን የውሸት ክስ በማዘጋጀት ወደ ማእከላዊ ወረወረ። ” አንድነት” ፓርቲንም አፈረሰ። ኩሸቱን በመደጋገም የራሱን እውነት ፈጠረ። እነ ሱዛን ራይዝን “በ100%” ጦሽ ብለው እንዲስቁ አደረገ።
በሌላ በኩል ለውጥ በሁሉን አቀፍ ትግል ብቻ መምጣት እንዳለበት የሚያምኑ ኢትዬጲያውያን የለውጥ እንቅስቃሴውን በግላጭ ማቀጣጠል ጀመሩ። ምሁራን ዱር ቤቴ በማለት ወደ በረሀ ተመሙ። አዲስ ህልምና አዲስ አቅጣጫ ይዘው የነጳነት ትግሉን ዙር አከረሩት። እናቶች ከጣታቸው ቀለበት፣ ከአንገታቸው ሀብላቸውን እያወለቁ ትግሉን ወደማገዝ ተሸጋገሩ። የመኪናቸውን ቁልፍ ለአርበኞች አስረከቡ። በየቦታው አዳራሽ ሞልቶ እስኪፈስ ድረስ ” እኔ አርበኞች ግንቦት ሰባት ነኝ!”፣… ” እኔ አንዳርጋቸው፣ ብርሀኑ፣ ኤፍሬም፣ ንአምን… ነኝ!” የሚል ቃልኪዳን ከመግባት ባሻገር እስከ መቶ ሺህ ዶላር መዋጣት ተጀመረ። ይህን የለውጥ ስሜት በስማ ስማ ሳይሆን በአይኔ በብረቱ ተመልክቻለሁ። ቆም ብዬም ለማሰላሰል ሞክሬያለሁ።
እንደ እውነቱ ከሆነ ህውሀት ቆም ብሎ ለትክክለኛው መፍትሔ የማሰቢያው ግዜ ነበር። ይሁን እንጂ አፈጣጠሩ፣ ባህሪውና የበታችነት ስሜቱ ይህን ስለማይፈቅድለት ሌላ መፍትሔ ማሰብ ነበረበት። ከእነዚህም ውስጥ በቁጥጥሩ ስር ባሉት አንዳርጋቸው ጵጌ ስም መጵሀፍ መጳፍና እንደ ሀብታሙ አያሌው ያሉትን የፓለቲካ እስረኞች መፍታት የሚጠቀሱ ናቸው። በበረከት ፀሀፊነት በአንዳርጋቸው ስም የሚወጣው መጵሀፍ ” የሶስት ምርጫዎች ወግ!” ( ስያሜው የእኔ ነው) ገና ባይወጣም በቅርብ ቀን እንደሚወጣ ይጠበቃል። ምርቃቱም ሸራተን አዲስ አንዳርጋቸው በሌለበት ይሆናል። …እነ ሀብታሙ አያሌውም ተፈተዋል።
( ” የሶስት ምርጫዎች ወግ” በተመለከተ ” የነጳነት ትግሉና ስድስት የህውሀት ማደናገሪያ ነጥቦች” በሚለው ሀሳብ ውስጥ አካትቼ በዳላስ ቴክሳስ በተዘጋጀ ስብሰባ ላይ አቅርቤ ነበር። ብዙዎች እንዲለጠፍ ስለጠየቁኝ በሌላ ክፍል እንደምመለስበት ተስፋ አደርጋለሁ።)
2• ” መውጫ መንገድ ያሳጣ ሰላማዊ ትግል”
አዲሱ የህውሀት መንግስት ሁለተኛው መጥፎ አጋጣሚ በኢትዬጲያ ሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊዎች ላይ የወሰደው እርምጃ ነው። እነዚህ ለሀይማኖታቸው ነጳነት የሚታገሉ ታጋዬች የያዙት አቋም ገዥው ቡድንን ወደ ከፍተኛ ፈተና ጐትቶ ወስዶታል። ይህን ለማለት ያስደፈረኝ ያለምክንያት አይደለም። ከልምድ በመነሳት እንጂ!
የዛሬ ሰባት አመት በዚህ አካባቢ የአዲስ አመት መምጫ በድርቡም የኢትዬጲያ ሚሊኒየም መግቢያ ነበር። በመላው ኢትዬጲያ በተለይም በከተሞች የቅንጅት መሪዎች ካልተፈቱ ” በሚሊኒየም ምንም የለም!” የሚሉ መፈክሮች ተስተጋቡ። ሁኔታዎች አጣብቂኝ ውስጥ የከተተው የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር (” ታላቁ መሪ” ባለማለቴ እቴጌን ከወዲሁ ይቅርታ እየጠየኩ) መውጫ መንገድ ፈለገ። “የኢትዬጲያ ሚሊኒየም የፈጠረው መልካም አጋጣሚ መጠቀም” የሚል የውስጠ ድርጅት ሰነድ እንዲዘጋጅ አደረገ። ይህ ሰነድ የታሰሩ ተቃዋሚዎችን በይቅርታ የመፍታት ፋይዳውን የሚተነትን ነበር። በዚህ ጵሁፍ ህዝቡ የይቱልን ጥያቄ ያለማቋረጥ እያነሳ ያለው ከአርቆ አስተዋይነት የመነጨ እንደሆነ ዘረዘረ። ህዝቡ ይፈቱልን የሚል ጥያቄ እያነሳ ያለው ” እኔው መርጬ ለዚህ አደረስኳቸው” ከሚል የህሊና ፀፀት እንደሆነ ተገለፀ። በመሆኑም ታሳሪዎችን በይቅርታ መፍታት ህዝቡን ከፀፀት የማውጣት ሁኔታ ስለሚፈጥር መንግስት የሚፈታበት ሁኔታ ማማተር እንዳለበት በሰፊው ተነገረ።
ታሳሪዎች የይቅርታ ጥያቄ እንዲያቀርቡ የፍርዱ ሂደት እንዲፋጠን ተደረገ። በአስቂኝና ባዶ ማስረጃ ታሳሪዎች ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ እንዲወሰን አደረገ። ( በነገራችን ላይ በመስካሪነት የቀረቡት የቀበሌ ካድሬዎች የነበሩት እነ አበባ ሽመልስ ከማል ልምምድ የሚያደርግላቸው በኢህአዴግ ቢሮ ነበር) ። የፍርድ ውሳኔውን አስደንጋጭ በሆነ ሁኔታ እስከ እድሜ ይፍታህ አምዘገዘገው። ይህ ውሳኔ ታሳሪዎችና ቤተሰባቸው ተደናግጠው ወደ ይቅርታ ሂደቱ በፍጥነት ይገባሉ የሚል ታሳቢን የወሰደ ነበር። በወቅቱ በታሳሪዎች መስመር ያለውን ተጵእኖ በቀጥታ ከራሳቸው መስማት የምችልበት እድል ባይኖርም በአንዳንድ የቅንጅት አመራሮች እና ቤተሰባቸው ዘንድ ተጵእኖ እንዳሳደረ ሰምቻለሁ። በሌላም በኩል እንደ አንዱአለም አራጌ ያሉ አመራሮች ውሳኔውን ከመቄብ ባለመቁጠር ይቅርታ ለመጠየቅ እንዳስቸገሩ በተባራሪ ሰምተናል።
ዞሮ ዞሮ ህውሀት የገባበት አጣብቂኝ የኢትዬጲያ ሚሊኒየም የፈጠረው መልካም አጋጣሚ መፍትሔ ሊያገኝ ቻለ። ይህን አስመልክቶ አቶ በረከት በጳፈውና የህውሀትን ገድል በሚያሳየው መጵሀፋ ገጵ 233 ላይ እንደሚከተለው አስፍሮ እንመለከታለን፣
” …የፍርድ ሂደቱ ነጳ መሆን በግልፅ መታየቱና መንግስት የቅንጅት መሪዎች የተከሰሱባቸውን ወንጀሎች ከበቂ በላይ በማስረጃ አቅርቦ በማረጋገጡ ህብረተሰቡ የሰዎቹን ጥፋተኝነት በጥያቄ ውስጥ የሚጥልበት አልነበረም። በመሆኑም መንግስት በህዝቡ የቀረበው የይፈቱ ጥያቄ ፣ ማንኛውም ህዝብ በአርቆ አስተዋይነቱ የሚያደርገው… እኔ መርጬ ለእስር አበቃኃቸው ከሚል የህሊና ፀፀት ነጳ ለመውጣት በመፈለግ ያቀረበው ጥያቄ እንደሆነ ተገንዝቧል። ለዚህ አይነቱ የህዝብ ጥያቄ በጐ ምላሽ መስጠት ምንግዜም ቢሆን ግዴታው እንደሆነ የሚገነዘበው መንግስት፣ ጥያቄው የህግ የበላይነት ለድርድር ሳያቀርብ ሊመለስ እንደሚችል አምኗል። እናም በአንድ በኩል የህግ የበላይነትን እያስከበረ፣ በሌላ በኩል ደግሞ የህዝብን የይፈቱ ጥያቄ ለማስተናገድ የሚችልበትን ሁኔታ ማማተር ነበረበት። በዚህ አኳኃን ነው የኢትዬጲያ ሚሌኒየም ራሱን እንደ መልካም አጋጣሚ የከሰተው” ይለናል።
እንግዲህ ከዚህ ልምድ በመነሳት የኢትዬጲያ ሙስሊሞች መፍትሔ አፈላላጊ የኮሚቴ አባላት የጥፋተኝነት ውሳኔ ተሰጣቸው። ውሳኔውን መሰረት በማድረግ እስከ ሀያ አመት የሚደርስ እስራት ተፈረደባቸው። ይህ ለመጥራት የሚዘገንን ቁጥር የተበየነበት ምክንያት ታሳሪዎችን ለማስደንገጥ እና ወደ ይቅርታ ሂደቱ በፍጥነት እንዲገቡ ታስቦ እንደሆነ በቀላሉ መገንዘብ ይቻላል። አንድ ግጥም አቅርበሀል የተባለ ወጣት የተፈረደበትን አመት ለተመለከተ ደግሞ በህውሀት የተጠነሰሰውን ሴራ ለመገንዘብ የእነሱን ያክል ማሰብ ከቻለ በቂው ይሆናል።
ይሁን እንጂ ይህ “የይቅርታ ይደረግልን” ሴራ ቅንጅት ላይ እንደሰራው በሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊዎቹ ላይ የሚሰራ አይደለም። ሲጀመር የመጀመሪያዉ ፓለቲካዊ፣ የአሁኑ ደግሞ ሀይማኖታዊ ነጳነትን በግንባር ቀደምትነት ያስቀመጠ በመሆኑ በባህሪ የተለያዩ ናቸው። ርግጥ ፓለቲካዊ መብቶች ባልተከበረበት ሀይማኖታዊ መብቶች ይከበራሉ ብሎ ማሰብ አስቸጋሪ ቢሆንም። ከዚህም በተጨማሪ የሀይማኖታዊ ነጳነታዊ ጥያቄዎች ለድርድር የመቅረብ እድላቸው እጅግ ጠባብ ተደርጐ ሊወሰድ የሚችል ነው።
ከላይ የተቀመጠውን ከግምት በመውሰድ የሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴው አባላት አጥፍተናል እና ይቅርታ ይደረግልን የሚሉ ከሆነ እስከዛሬ ያነሷቸው ሶስት ጥያቄዎች ( ለጊዜው የማውቃቸው) ትክክል አልነበሩም፣ አሊያም ምላሽ አግኝተዋል የሚል እንድምታ ይኖረዋል። ይህም የህውሀትን ድል አድራጊነት ከማረጋገጥ ባሻገር የኢትዬጲያ ሙስሊሞችን የሶስት አመት ትግል ውሀ ይቸልስበታል። ወደ ኃላ የመመለስና በቀላሉ የመክሰም እድል ያጋጥመዋል። የኮሚቴዎቹ አባላት ይህን በመገንዘብ ይመስላል አስደንጋጩ ብይን ሲሠጣቸው ያለምንም መደናገጥ የትግል ጵናታቸውን ለማሳየት የቻሉት። ቤተሰቦቻቸውም ቢሆን የኮሚቴው አባላት እየከፈሉ ያሉት መስዋእትነት ለሀይማኖታቸው ነጳነት መሆኑን በመገንዘብ ከጐናቸው የቆሙት።
ስለዚህ እነዚህ የኮሚቴ አባላት እንደ ቡድን የይቅርታ ጥያቄ ያቀርባሉ ብሎ ማሰብ ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ እንደመውጣት ይሆናል። በግለሰብ ደረጃ በተለያዩ ምክንያቶች የይቅርታ ሂደት ውስጥ የሚገቡ ሰዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ የሚጠበቅ ቢሆንም። ይህ አማራጭ ዝግ ሆነ ማለት ህውሀት መራሹ አዲሱ መንግስት ዝም ብሎ ይቀመጣል ማለት አይደለም። በሁኔታዎች አስገዳጅነት ያለ ይቅርታ ጥያቄ ምህረት የማድረግ ግን ደግሞ በፍርድ ቤት እንዲወሰን ያደረገውን የህዝብ እንቅስቃሴ ገደብ ያለማንሳት ሊኖር ይችላል። ይህም ኮሚቴዎቹን በአይነ ቁራኛ በመከታተል የቁም እስረኛ ወደ ማድረግ መሸጋገር ይሆናል። ይህም ቢሆን ለገዥው ቡድን የሚያመጣለት አንዳችም ፓለቲካዊ ትርፍ አይኖረውም።
ግራም ነፈሰ ቀኝ የኢትዬጲያ ሙስሊሞች መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ የአላማ ጵናት ለአዲሱ የህውሀት መራሹ መንግስት የእግር እሳት እንደሆነ ይቀጥላል። የኢትዬጲያ ሙስሊሞች የነጳነት ትግልም በኢትዬጲያ ታሪክ ውስጥ የሚኖረውን የላቀ ደረጃ እንደጠበቀ ይኖራል!…”መውጫ መንገድ ያሳጣ ሰላማዊ ትግል” ይሉሀል ይህ ነው!!

Friday, August 21, 2015

የአለም ታላቋ ጓንታናሞ–ኢትዮጵያ


ከታሳሪ የህሊና ሰዎች መካከል አብጦ ሊፈነዳ የተቃረበውን የፖለቲካ ድባብ ለማስተንፈስ ሲባል ወዳጄን፣ ጓዴንና የቀድሞ ባልደረባዬን አብርሀ ደስታን፣ የሽዋስ አሰፋን፣ ሐብታሙ አያሌውን፣ ዳኤል ሽበሽንና አብሃም ሰለሞንን «በነፃ» መለቀቅ በሰማሁ ጊዜ ደስታ ቢሰማኝም፤ ንጹሓኑ «በነጻ» መለቀቃቸው ከጠባቡ ጓንታናሞ ወደ ሰፊው ጓንታናሞ መዛወራቸው እንጂ አሁንም ነጻ አለመሆናቸውን፤ እንዴውም አሁን ያለንበት በነጻነት የመናገርና የመጻፍ ሁኔታ እነሱ ከመታሰራቸው በፊት ከነበረው በባሰ ተዳፍኖ መገኘቱን ባሰብሁ ጊዜ ሀዘኔ ይበዛል። በተለይ በተለይ አብርሀ ደስታ ከመታሰሩ በፊት የነበረውን የነጻነት መንፈስና የነበረውን አንጻራዊ «ነጻነት» ዛሬ ካለው የነጻነት ምህዳር አኳያ ለመዘነ፤ ስርዓቱ «በነጻ» ከተለቀቁት ንጹሓን ጋር እንዳይደርስ በህግ የማይታገድ ስርዓት አልበኝነቱ በከፋ ደረጃ ላይ እንደመገኘቱ መጠን ከበፊቱ በባሰ ዛሬ «ነጻ» ናችሁ ተብለው የተለቀቁቱ የነአብርሀ ደስታ ጉዳይ ያሳስበዋል።
የነሐብታሙ አያሌውና አብርሀ ደስታ «መፈታት» የወያኔን «የፍትህ» ሂደት ፍጹም ግፈኛነት ይለውጠዋል የሚል የዋህ ያለ አይመስለኝም። እነ አብርሀ የተፈቱት የፍትህ ስርዓቱ ተሻሽሎ ሳይሆን የተጨማለቀው የፍትህ ስርዓት የወለደው ህዝባዊ እልህና እምቢተኝነት በማየሉ ሳይፈነዳ ለማስተንፈስ ታስቦ ነው። በእውነቱ አሁን ያለው ሁኔታ እነ ሐብታሙ አያሌው ሲታሰሩ ከነበረው የሚካፋ እንጂ የተሻለ አይደለም።
ወያኔዎች ከመለኮት ተዛምዶ ያለውን መንፈሳቸውን ከአራዊት ባህሪ ተዛምዶ ባለው ጡንቻቸው ስልጣን ስር ካዋሉት ብዙ ዘመን ሆኗቸዋል። ንጹሓንን ከሰውና ከእግዚያብሔር ህግጋት በላይ በእስር ሲያሰቃዩ ከርመው ዛሬ «በነጻ» መለቀቃቸውን ማስነገራቸው አገሪቱ ውስጥ የቆመው ስርዓት አይን ያወጣ፤ ጭካኔ የተሞላበትና ህዝብ የማጥቂያ የአውሬዎች መንግስት መሆናቸውን የሚያሳይ እንጅ ፍትህ የሚሰጥበት፤ ህጋዊ ስርዓት የሰፈነበት መንግስታዊ አቅዋም መዘርጋታቸውን የሚያረጋግጥ አይደለም።
በመሰረቱ አገር የምትሻሻለው፤ የጥበብ ፍላጎታቸውን ድካምና ችግር ወይንም ምቾትና ተድላ በማይመልሳቸው ጠቢባን፤ ሰብኣዊ ከፍተኛነታቸውንና ጽኑ ሞራላቸውን የግል ደስታና ድሎት፤ ወይንም መከራና ስቃይ በማይሰብራቸው በነሐብታሙ አያሌው አይነት አዋቂ የሐሳብ ሰዎች እንጂ በእንደ ወያኔዎች አይነት የሰዎችን የማመዛዘኛ አእምሮ በሚያደነዝዘው በዘረኝነት በተደራጁ፤ ካለፉት መንግስታት የከፉ ሆነው ሳለ ባለፉት መሪዎች ላይ የሚያወርዱትን ርግማን ብቻ ለህዝቡ መመገብን እንደ መልካም ስራ በሚቆጥሩ፤ የግል ጥቅም አሳዳጅ ደንቆሮና ጨካኝ አውሬዎች አማካኝነት አይደለም።
እነሐብታሙ ከታሰሩ ከአንድ አመት በኋላ ያለንበት ሁኔታ የፍትህ ስርዓቱና መንግስታዊ መዋቅሩ ሙሉ በሙሉ በአገዛዙ ቁጥጥር ስር የወደቀበት፤ ያልተሰደደው ገበሬው፣ ነጋዴውና ሌላውም ሰርቶ ኗሪ ህዝብ በኑሮ ውድነት እየተቆላ ግብርና ቀረጥ እየተደራረበበት በአገሩ መኖር ተስኖት እስኪያንገሸግሸው እየተመተረ በባርነት እየኖረ ይገኛል። ወጣቱ ደግሞ በአገሩ ተስፋ አጥቶ ባህር በማቋረጥ እግሬ አውጭኝ እያለ የባህር አሳ ሲሳይና የውስጥ እቃው እየወጣ የአሞራ ቀለብ እየሆነ ነው። ከፊሉ ወጣት ደግሞ ነፍሱን በጥርሱ ይዞ የሰው ጠል አራጆች የጭካኔያቸው ማርኪያ እንዲሆን ሲዳረግ፤ ቀሪው ደግሞ በየጎረቤት አገሮች ኬላ እየተያዘ የባእድ ማጎሪያ ቤቶችን እያጨናነቀ ይገኛል። በተቃራኒው የስርዓቱ ባለቤቶች የሆኑት ወያኔዎች ግን አገሪቱን አጥንቷ እንኪታይ በመጋጥ በበለጠ ድሎት ሲቀማጠሉ የተረፋቸውን ደግሞ የግፍ ዘመናቸውን ለማራዘም የሚያስችላቸውን የጦር መሳሪያዎች ለማደርጃነትና ለማባዣነት እያዋሉት ይገኛሉ።
የሕዝቡም ጠቅላላ ኑሮ ሰላም ከማጣቱና የፍርሀት መንሰራፈፊያ ከመሆኑ በቀር ከአመት በፊት ከነበረው በምንም አልተሻለም። የግል ጋዜጦች ሁሉ ተዘግተው፤ ስለህዝቡ ኑሮ ጥቂት ማጉረምረም የሚያሳዩ የፖለቲካ ሰዎች ሁሉ እየተያዙ ያለፍርድ ታስረዋል። እነ አብርሀ ከታሰሩ ከአንድ አመት በኋላ አንድ ሰው በጽሁፍም ሆነ በንግግር ወያኔን ከማመስገንና ለዛሬው ችግር የድሮዎችን መሪዎች ከመርገም ያለፈ የተለየ ሐሳብ የመግለጽ መብት የለውም። እነ ሐብታሙ አያሌው ከታሰሩ ከአንድ አመት በኋላ ማንም ሰው ሰላማዊ ሰልፍ አድርጎ መቃወም ቀርቶ የአቤቱታ ድምጽ ማሰማት አይችልም። እነ የሽዋስ ከታሰሩ ከአንድ አመት በኋላ የአገዛዙ ትኩረት የህዝቡን ኑሮ ወደተሻለ መንገድ ለመምራት ቆርጦ መነሳት ሳይሆን የአገዛዙን መሰረት ለማጠንከር አብዝቶ ከመታገል በቀር ሌላ የመሻሻል ሙከራ አላሳየም። በአጠቃላይ የዛሬዋ ኢትዮጵያ ዘጠና ሚሊዮን ሰዎች የታሰሩባት የአለም ሰፊዋ ጓንታናሞ ሆናለች።
አሁን ባለንበት መስቀለኛ መንገድ ያለን ሁለት አማራጭ ብቻ ነው። አንድም ከሰሜን እስከ ደቡብ፤ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ በአንድነት በምናሰማው የጭንቅ ምጥ በሚወልደው ጣምራ ጩኸት በጋራ ነጻ ወጥተን ከታሪካዊ ችግራችን እንገላገላለን፤ አሊያም በጎሰኛነት ልክፍት አብደን እውር ድንብራችንን እየሄድን ከዘመነ መሳፍንት በባሰ ሁኔታ ርስበርስ እየተከሳከስን ሞትን እናነግሳለን። በዚህ ጉዳይ ሌላ ጊዜ እመለስበታለሁ።
በመጨረሻም እንዲህ እላለሁ፤ በነካ እጃችሁ ተመስገን ደሳለኝንም ፍቱት! እውነትን ከመጋፈጥ በስተቀር እሱም ቅዱስ ነው! እስክንድር ነጋንም ፍቱት፤እሱም ፍጽም ንጹህ ነው። እነ አቡበከር አህመድንም ፍቷቸው እነሱም ሰላም ወዳድ ደግ የሐይማኖት መምህሮች ናቸው! ሌሎችን ንጹሓንንም ፍቷቸው። አለበለዚያ የፍትህ ስርዓቱ ልዕልና ተገፍፎና አገር ታስራ፡ አሸባሪ ብላችሁ በግፍ ካጎራችኋቸው አንድ የጭካኔ አመት በኋላ ከምታሰቃዮዋቸው ሚሊዮን ንጹሓን መካከል እነሐብታሙ አያሌውንና አብርሀ ደስታን በጠባብ እስር ቤት ከነበሩበት ወደሰፊው ጓንታናሞ እንዲዘዋወሩ በረጅሙ አስራችሁ «ስለለቀቃችኋቸው»፡ «የፍትህ» ሂደታችሁን ሙሉ በሙሉ ወንጀለኛነትና በቃላት ከሚገለጸው በላይ መጨማለቁን ሊለውጠው አይችልም።
አቻሜለህ ታምሩ

ወጣቶቹን እየበላ ያለው ስርዓት … ግርማ ሠይፉ ማሩ


ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማሪያም ደሳለኝ በቀጣይ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ላይ የተመረጡ እና የተለመዱ ፊቶችን ስብስበው ጥያቄ ሲያቀርቡና ማብራሪያ ሲሰጡ ነበር፡፡የእኔን ቀልብ የሳበው ግን አውቀውም ይሁን ሳያውቁት ወጣቶችን እየበላ ያለ ስርዓት ባለቤት እና መሪ መሆናቸውን የገለፁበት አስተያየት ከታዳሚው ሞቅ ባለ በተደጋጋሚ ጭብጨባ መታጀቡ ነው፡፡ ባለፈው የኦባማ ጉብኝት ወቅት ዲሞክራሲ ማላት ምርጫ በስላም ማጠናቃቅ ብቻ አይደለም፡፡ ጋዜጠኞችን አክቲቪሰቶችን እስር ቤት እያወረዱ አማራጭ ፖለቲካን እየከለከሉ ዲሞክራሲ የተሟላ አይሆኑም ብለው ሲሞልጯቸው በጭብጨባ ያጅቡ ነበር፡፡ ዛሬም ተመሳሳይ ነገር ነው የሆነብኝ፡፡
ይህን ፅሁፍ ከመለጠፌ በፊት ግን በእስር ላይ ያሉ ጓዶቻችን ከእስር እንዲፈቱ ፍርድ ቤት መበየኑን ሰምቻለሁ፡፡ ንፁህ ናችሁ ብሎዋቸዋል፡፡ ንፁህ ነበሩ እና አይገርምም፡፡ ይህን ማበረታታት አለብን፡፡ እነ አንዱዓለም፣ ናትናኤል፣ እስክንድር፣ ተመስገን ደሳለኝ ፣ ወዘተ መለቀቅ አለባቸው፡፡ ይህን ጥሩ እርምጃ ኦባማ ተቆጥቷቸው ነው እያሉ ከማንቋሸሽ ይህን እያጣጣምን ተጨማሪ መጠየቅ ይኖርብናል፡፡ ለማነኛውም ለቤተሰቦች ዕዳ ሆነው የነበሩት ታጋዮች ነፃ ወጥተዋል፡፡ ከቂሊንጦ!!! እንኳን ደስ ያላችሁ ደስ ያለን!!!
ወደ ተነሳሁብ ነጥብ ሰመለስ ጠቅላይ ሚንስትሩ ጉቦ የሚበላባቸው መስሪያ ቤቶች እንዳሉ ማወቅ ብቻ አይደለም ወጣቶችንም ጉበኛ አድርጎ ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ አስልጥኖ ወደ ተግባር እንደሚያስገባ በግልፅ ነግረውናል፡፡ በተጨማሪ ምንም ዓይነት የተሟላ ማስረጃ ቢኖረን ጉዳያችንን መጨረስ የማንችልባቸው የመንግስት ተቋማት እንዳሉም ጠቅላይ ሚኒስትራችን ጠንቅቀው ያውቃሉ እነዚህም ተቋሞች የሰለጠኑ አዲስ ምሩቃን ወጣቶች ስራ እንዲሰሩ ሲመደቡላቸው በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዴት ጉዳይ ማለቅ እንደሌለበት ጠንቅቀው ይማራሉ፡፡ ይህንንም በተግባር ይፈፅሙታል፡፡ እነዚህ መስሪያ ቤቶች የመንግስት አገልግሎት መስጫ ነው፡፡
ባለጉዳይን በአግባቡ እና በስርዓት ያለማስተናገድ በእርሰቸው ቃል አመናጫቂና አንጓጣጭ መስሪያ ቤቶችም እንዲሁ የተመደቡላቸውን ወጣት ምሩቃን በፍጥነት ቀይረው ተገዶ አገልግሎት ፍለጋ የመጣውን ተገልጋይ ያመናጭቃሉ፣ ይሳደባሉ፡፡ ይህን ስስማ የጤና ባለሞያዎቻችን ወላዶችን በምጥ ወቅት ማን አርግዥ አለሽ አትጩሂ ሲሉ ተሰማኝ፡፡ ሌሎች የሚሉትን ፀያፍ ቃል ለዚህ ፅሁፍ ስለማይመጥን ዘልየው ነው፡፡
የሀገር ውስጥ ገቢ ኦዲተሮች እና ገማቾች በግብር ከፋይ ዜጎች ላይ ያላቸውን “ቬቶ ፓውር” ማወቅ ብቻ አይደለም፣ ጠቅላይ ሚኒስትረ ተሰፋ የቆረጡበት ሁኔታ ያለ የሚመስል አስተያየት ነው የሰጡት፡፡ ሂሳብ ሰርታችሁ ካልመጣችሁ እንደፈለጉ ያድርጓችሁ የሚሉን ይመስላል፡፡ ለአፋቸው እንኳን እነዚህን ልክ ማስገባት አለብን የሚል ተሰፋ አልሰጡንም፡፡ እኔ በግሌ የሀገር ውስጥ ኦዲተር ብሆን ስራ አቆም ነበር፡፡ ደግነቱ እግዜር አንድኖኛል፡፡ በእኛ ሀገር መስሪያ ቤቱ ሲሰደብበት ኃላፊነቱን የሚለቅ ባለስልጣን ስለሌለን ነው፡፡ እራሴ እለቅ ነበር ያልኩት፡፡
እነዚህን ሁሉ ወጣቶችን የሚበሉ መስሪያ ቤቶች የሚተዳደሩት በመንግሰት በጀት፣ በምርጫ አሸንፌ ስልጣን ያዝኩ በሚል መንግሰት በሚሾሙ የፖለቲካ ሾመኞች መሆኑን የዘነጉት ይመስላሉ፡፡ ይህን ለማለት ያስቻለኝ ደግሞ መፍትሄው የታጋይ ዜጋ መኖርና የፖለቲካ ቁርጠኝነት ነው በማለት አስቀምጠው፣ የፖለቲካ ቁርጠኝነት በተመለከት ጠንካራ ፓርቲና አመራር በመኖሩ ተገባራዊ ማድረግ ይቻላል በሚል አሹፈውብናል፡፡
ይህን ፕሮግራመ የተከታተልን ሰዎች ታጋይ ዜጎችን በእኔ ትርጉም እንቢ ሙሰኝነት ….. ያሉትን፣ የመልካም አስተዳደር እንዲሰፍን የጮሁትን እና የዘመሩትን፣ መንግሰት ይህን ጉዳይ የማያውቅ ከሆነም እንዲገባው የጦመሩትን፣ የፖለቲካ ሙሰኝነት እንዲቀር እንቅልፉን አጥቶ ጋዜጣና መፅሄት በማዘጋጀት የሚተጉትን ጋዜጠኞችን እስር ቤት እያጎሩ እንዴት ታጋይ ዜጋ እንደሚፈራ አልታይህ አለኝ፡፡
ታጋይ ዜጋ እንዳይፈራ ዜጎችን አንገት እያስደፉ ፖለቲከኞች በሚፈነጩበት ሀገር ኪራይ ስብሳቢነት አንገቱን እንዴት እንደሚደፋ ማወቅ አይቻልም፡፡ ታጋዮችን አንገት አስደፍቶ ሌቦች ፖለቲከኞችን ቁርጠኞች ናቸው ማለት ፌዝ ነው፡፡
ታጋይ ዜጋ እናፍራ – ታጋይ የሆነ ዜጋ ጉቦ አይከፍልም በዚህ ጊዜ ኪራይ ስብሳቢነት ይደፈቃል ነው ብለው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ነገር ግን ጉቦ አልሰጥም የሚል ዜጋ ለማፍራት፣ ከፖለቲከና ዱላ የሚጠብቅ ሲቪል ማህበረሰብ፣ ጋዜጠኛ የግድ ይለናል፡፡ ፍርድ ቤት ያስፈልገናል፡፡ ያስቸገሩንን ወሰደን የምንገትርበት፡፡ የመርጊያ በቃናን ውሳኔ የሚያፀና ፍርድ ቤት አለን ብለን ጉቦ አንከፍልም በሉ ብለን እዝቡን ለጅብ አንሰጥም፡፡ መልዕክቴ ስርዓቱ ከፖለቲካ ሙሰና ከፀዳ እርገጠኛ ይሁኑ ሌሎች ሙስናዎች ተራ ናቸው፡፡ ለማነኛውም ይህ ወጣቶችን እየበላ ያለው የፖለቲካ ስርዓት ይገራልን፡፡
ቸር ወሬ ያሰማን!!!!! ዛሬ ደስ ብሎኛል ደስ ይበላችሁ!!!!

ጎጃም ውስጥ በድርቁ ምክንያት በእንሰሳትና ሰው ላይ ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰ ነው ተባለ


‹‹እንሰሳት በዋሉበት እየቀሩ ነው›› ነዋሪዎች
በሀገሪቱ በተፈጠረው የዝናብ እጥረት ምክንያት በተለይ በአፋር፣ በሶማሊና በሌሎች አካባቢዎች የተከሰተው ድርቅ ጎጃም ውስጥም በመከሰቱ በርካታ እንሰሳት እየሞቱ መሆኑንና ሰውም ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን ነዋሪዎቹ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለፁ፡፡ በተለይ ድርቁ በሶማ፣ አራራ፣ እነገ እና ሰንጠርጌ ቀበሌዎች ለበርካታ እንሰሳት ሞት ምክንያት ከመሆኑም ባሻገር ነዋሪዎችም ለከፍተኛ ችጋር ተጋልጠዋል ተብሏል፡፡
ድርቁ አስከፊ ደረጃ እንደደረሰ መንግስትም ማመኑን የገለፁት ነዋሪዎች ነሃሴ 7/2007 ዓ.ም የእናርጅ እናውጋ የንግድና ኢንዱስትሪ ፅ/ቤት እንዲሁም የደብረወርቅ 01 ቀበሌ ሊቀመንበር የድርቁን አስከፊነት በመግለፅ ከህዝቡ እንዳታ ማሰባሰባቸውን ስብሰባው ላይ የተገኙት ነዋሪዎች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡ ከእናርጅ መስቀለ፣ አረጋሚትና ሌሎችም ቀበሌዎች ገለባና ሌሎች ለከብቶች በምግብነት የሚውሉ መኖዎች ተሰባስበው በድርቅ ወደተጠቁት ቀበሌዎች መላኩን ምንጮች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡
መንግስት እርዳታ ለማሰባሰብ የተገደደውና እርዳታ ማሰባሰብ የጀመረው በድርቁ የተጠቁት ቀበሌዎች ነዋሪዎች በዝናብ እጥረት የደረቀውን ሰብላቸውን በመያዝ፣ እንዲሁም በእንሰሳትና ሰው ላይ እየደረሰ ያለውን ጉዳት በመግለፅ ደብረወርቅ ላይ ሰላማዊ ሰልፍ በመውጣታቸውና በተደጋጋሚ አቤቱታ በማቅረባቸው ነው ተብሏል፡፡ በድርቁ የተጠቁት ነዋሪዎች ስለ ድርቁ ለመንግስት ሪፖርት ለማድረግ ወደ አካባቢው ያቀኑ የግብርና ሰራተኞችንና መኪናዎቻቸውን ለተወሰነ ጊዜ በመያዝም መንግስት መፍትሄ እንዲሰጣቸው በቶሎ ሪፖርት እንዲያደርጉ እንደጠየቁም ምንጮች ገልጸዋል፡፡
የእናርጅ እናውጋ ወረዳ እስተዳደር ለድርቁ ሁለት መቶ ሽህ ብር መመደቡንና በስብሰባው ወቅትም 28 ሺህ ብር ተዋጥቶ በቆሎ ተገዝቶ እንዲላክላቸው ቢወሰንም እስካሁን እርዳታው ለድርቁ ተጠቂዎች እንዳልደረሰላቸው የገለፁት ምንጮች ሰው የሚበላው አጥቶ፣ እንሰሳትም በዋሉበት እየቀሩ ነው ብለዋል፡፡ አንድ የደብረወርቅ ነዋሪ ለነገረ ኢትዮጵያ እንደገለፁት በዝናብ እጥረት ምክንያት በድርቅ ከተጠቁት ባሻገር ሌሎች የእናርጅ እናውጋ አጎራባች ቀበሌዎች ላይም ድርቁ በመከሰቱ በሰውና በእንሰሳት ላይ ጉዳት እንደረሰ ነው ብለዋል፡፡

Thursday, August 20, 2015

ሀምታሙ አያሌው :ተከሳሽ ዳኤል ሽበሽ:አብርሃ ደስታና የሸዋስ አሰፋ ነፃ እንዲለቀቁ ተወሰነ


ዛሬ ነሃሴ 14/2007 ዓ.ም የልደታ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት በዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ የተከሰሱትን 2ኛ
ተከሳሽ ሀምታሙ አያሌው፣ 3ኛ ተከሳሽ ዳኤል ሽበሽ፣ 4ኛ ተከሳሽ አብርሃ ደስታና 5ኛ ተከሳሽ የሸዋስ አሰፋ እንዲሁም 7ኛ
ተከሳሽ አብሃም ሰለሞን በነፃ እንዲለቀቁ ወስኗል፡፡ በአንፃሩ አንደኛ ተከሳሽ ዘላለም ወርቃገኘሁ ከአሁን ቀደም
ተከሶበት በነበረውና ከ15 አመት በላይ እንደሚያሳስር የሚታወቀው የፀረ ሽብር ህጉ አንቀፅ አራት ‹‹ማሴር፣ ማቀድ
ተግባረት›› ላይ መረጃ ስላልተገኘበት አንቀፁ ወደ 7/1 ላይ በተመለከተው ላይ ተቀይሮ እንዲከላከል ተበይኖበታል፡፡ በዚህ
አንቀፅ ለግንቦት ሰባት በመመልመል ተግባር ተሰማርቷል በሚል እንደተከሰሰም ተገልጾአል፡፡ በተመሳሳይ 6ኛ፣ 8ኛ፣ 9ኛ ፣10ኛ
ተከሳሾች ከአንደኛ ተከሳሽ ጋር እንዲከላከሉ ተብለዋል፡፡
ፍርድ ቤቱ አራቱ ፖለቲከኞች ሲታሰሩ በኢግዚቢት የተያዘባቸው ተለቆላቸው እንዲፈቱ ሲወንስ እንዲከላከሉ ያላቸው የመከላከያ
ምስክር እንያስመዘግቡ በይኗል፡፡