Thursday, January 7, 2016

ኦቦ በቀለ ገርባ በግፍ ወደ ማዕከላዊ ከመውረዳቸው በፊት በአዲስ ገፅ መፅሔት ይህን ጥሪ አስተላልፈው ነበር

በመከላከያ ሰራዊት፣ በፖሊስና ደህንነት ውስጥ ያሉ ወንድሞቻችን ቆም ብለው እንዲያስቡ፣ ከመግደል እንዲታቀቡና ማንም መብቱን ከመጠየቅ ወደኋላ እንደማይቀር እንዲያውቁ እፈልጋለሁ። ህዝቡ የጠየቀው ሌላ ሳይሆን መብቱን ነው። የሚሞተው ደሃው ህዝብ ነው፧ እየገደለ ያለው ደግሞ ከደሃው አብራክ የተገኘ ፖሊስና ወታደር ነው።
እናም
እባካችሁ! ወንድሞቻችሁን አትግደሉ፤ ራሳችሁ እየተራባችሁ ለእናንተም ጭምር እየታገለ ያለን ህዝብ አትግደሉ! እጃችሁን አታቆሽሹ! በታሪክም ራሳችሁን ተወቃሽ አታድርጉ! እባካችሁ እጃችሁን ሰብስቡ! በሰላማዊ ህዝብ ላይ ጠብ-መንጃችሁን አታዙሩ፤ ይህን ህዝብ አትጉዱ! ወደፊት በታሪክ ተጠያቂ እንዳትሆኑ አሁኑኑ ትክክለኛውን እርምጃ ውሰዱ!> የሚል መልዕክት ልናስተላልፍላቸው እንወዳለን።
Dawit Solomon Yemesgen's photo.

No comments:

Post a Comment