Monday, January 18, 2016

ጎንደር በብአዴን ከፍተኛ ባለስልጣናት ተወራለች


የቤተ አማራ የውስጥ አዋቂዎች እንደገለፁት ሰሞኑን የብአዴን ከፍተኛ ባለስልጣናት ጎንደር ላይ ከትመው ሰንበታዋል። ከብአዴን ወጣት አባላት፣ ከኦርቶዶክስ ሃይማኖት አባቶች እና በከተማው ውስጥ ተሰሚነት አላቸው ከሚባሉ ግለሰቦች ጋር የተለያዩ ዝግ ስብሰባዎችን እያካሄዱ ነው። የስብሰባው ዋና አጀንዳ ከጥምቀት በዓል ጋር ተያይዞ የህዝብ አመፅ በጎንደር ከተማ ውስጥ እንዳይቀሰቀስ ቅድመ ዝግጅት ለማድረግ ነው ተብሏል።
የወልቃይት የአማራነት ጥያቄ፣ ለሱዳን ሊሰጥ የታቀደው ሰፊ እና ለም የአማራ መሬት፣ ከቅማንት ማህበረሰብ የአስተዳደር ይገባኛል ጥያቄ ጋር ተያይዞ የተነሳው ደም ያፋሰሰ ግጭት፣ በአጠቃላይ በግልፅ እዬታዬ ያለው ከፍተኛ የሆነ የአማራ ህዝብ በደል የጎንደር እና የአካባቢውን ኗሪዎች በጥምቀት እለት ወደ ህዝባዊ አመፅ እናዳያመሩ በብአዴኖች ላይ ከፍተኛ ፍርሃት አሳድሯል። የጎንደር ጥምቀት በዓል በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ህዝብ በየአመቱ እንደሚያከብረው ይታወቃል።
ብአዴኖች ከፍርሀታቸው የተነሳ በተለይ ጥር 12 የሚከበረውን የቅዱስ ሚካኤልን ንገሰ በዓል ለመሰረዝ የታሰበ እቅድ አቅርበው ነበርም ተብሏል። ከጥር አስራ አንዱ የጥምቀት በዓል በኋላ በማግስቱ የሚከበረው ይሄው በዓል እጅግ ደማቅ በሆነ መልኩ ለዘመናት ሲከበር እንደኖረ የሚታወቅ ነው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አንዳንድ የህዝብ ብሶቶች በተለይ በቅዱስ ሚካኤል ታቦት የማስገባት ቀን ሲንፀባረቁ ተስተውሏል። የብአዴን ፍራቻ የመጣውም ከዚህ ጋር ተያይዞ መሆኑ ታውቋል። ይሄን የብአዴን ሃሳብ ተስብሳቢው መሉ ለሙሉ በምሬት ውድቅ እንዳደረገባቸው ምንጮቻችን አያይዘው ገልጸዋል።
ሌላው ለብአዴን የጎን ውጋት የሆነበት ችግር እሱ ባላሰበው መልኩ ከቁጥጥሩ ውጭ እየወጣ ያለ ጠንካራ የአማራ ብሔርተኝነት እየተቀጣጠለ መሆኑ ነው። ብአዴን በሕወሓት የሚመራ የይስሙላ ብሔርተኝነት እንጂ እንዲህ አይነቱን የአማራ ብሔርተኝነት እንደማይፈልገው በተዘዋዋሪ ለተሰብሳቢው ሲገልፅ ተደምጧል።
ብአዴን በተደጋጋሚ የአማራን ህዝበ ጥቅም ማስጠበቅ ሳይችል የቀረ ደካማ ፓርቲ መሆኑ የአደባባይ ሚስጥር ከሆነ ሁለት አስርተ አመታት ተቆጥሩ።
ድል ለአማራ ህዝብ!

No comments:

Post a Comment