የልዑኩ አባላት በአባ ዱላ ገመዳ ጠቛሚነት ተመርጠው የተዋቀሩ ሆድ አደር የኦህዴድ ካድሬዎች ሲሆኑ ሁለቱ በአዲስ አበባ ዪኒቨርስቲ በመምህርነት ያገለግላሉ። የጉዞ አላማቸው ለነ ጅዋር መሀመድ ማስተር ፕላኑን በተመለከተ ማብራርያ መስጠትና እነ ጅዋር የሚቃወሙት ነገር ካለ እንደሚቀር ማረጋገጫ መስጠት ነው ተብሎአል። እንደምንጮቸ ከሆነ ጅዋር የቀረበለትን ጥሪ ከወዲሁ ውድቅ አድርጎታል። ሰዎቹ ግን ዛሪ ማታ ከምሽቱ አራት ሰአት ላይ ከቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ይነሳሉ ከግርማ ብሩ ጋር በመሆንም እነ ጅዋርን ለማግኘት ከፍተኛ ጥረት ያደርጋሉ።

No comments:
Post a Comment