Tuesday, January 26, 2016

ቱኒዚያ ተቃውሞ ቀጥሎ ሁለት መቶ ስልሳ ሰዎች ታሠሩ ::


ቱኒዝያ ለአራት ቀናት በዘለቀው ሀገር አቀፍ ብጥብጥ ተጠያቂ ናቸው ያለቻቸውን ሁለት መቶ ስልሳ ሰዎች ማሠሯን አስታወቀች። እስረኞቹ በአመጽ ድርጊት እና ነውጥ በመቀስቀስ እንደሚከሰሱ ሼምስ ኤፍ ኤም የተሰኘ የሀገሪቱ ሬዲዮ ዘግቧል። በቱኒዝያ ያለው የኢኮኖሚ ሁኔታ እና የሥራ አጥነት መባባስ በመላ ሀገሪቱ ለተቀሰቀሰው ተቃውሞ ሰበብ እንደሆነ ተነግሯል።
የቱኒዝያ መንግሥት ትናንት ከምሽቱ 2 ሰዓት እስከ ንጋቱ 11 ሰዓት የሚዘልቅ የሰአት እላፊ አዋጅ ደንግጓል። የሰዓት እላፊው ከተደነገገ በኃላ በቱኒዝያ አንዳንድ ከተሞች ትናንት ማምሻውን ብጥብጥ መከሰቱ ተዘግቧል። በበርካታ ከተሞች ቱኒዝያውያን አደባባይ በመውጣት የፖሊስ ጣቢያዎችን ማጥቃታቸው ፣ የፖሊስ ተሽከርካሪዎችንም በእሳት መለኮሳቸው ተገልጿል።
የቱኒዝያ ጠቅላይ ሚንሥቴር ሐቢብ ኤሲድ የሀገሪቱ ዲሞክራሲ «ምንም ያስከፍል ምንም» እንደተጠበቀ ይቆያል ሲሉ ተናግረዋል። በቱኒዝያ የተቀጣጠለው ተቃውሞ ከመዲናይቱ ቱኒስ አንስቶ በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች የተስፋፋ መሆኑም ተገልጻል።
Yesuf Brhan's photo.

No comments:

Post a Comment