Friday, January 29, 2016

የትግራይ ክልል መስተዳደር አቶ አባይ ወልዱ እየተቀጣጠለ ያለውን የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄን ለማዳፈን ነገ ወልቃይት ይገባሉ ተባለ


የትግራይ ክልል መስተዳደር አቶ አባይ ወልዱ ዛሬ ወይም ነገ ወልቃይት ይገባሉ እየተባለ ነው። በጉብኝታቸው ወቅት በአካባቢው ያሉ የህወሓት አመራሮችን እና በሰፈራ የመጡ የትግራይ ተወላጆችን ያነጋግራሉ ተብሎ ይጠበቃል። የጉብኝታቸው ዋና አላማ እንደ ሰደድ እሳት እየተቀጣጠለ ያለውን የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄን ለማዳፈን የቅስቀሳ እና የማስተባበር ስራ ለመሰራት እንደሆነ ታምኗል።
በተጨማሪም ሰሞኑን የትግራይ ክልል ቴሌቪዥን ከፍተኛ የሆነ ፀረ ወልቃይት ቅስቀሳ እያስተላለፉ ይገኛል። የወልቃይትን የአማራነት ጥያቄ ለመቀልበስ የትግራይ መገናኛ ብዙሃን በርተተው እዬሰሩ ነው። ሰሞኑን የትግራይ ክልል ልዩ ባንድ በአዲረመፅ እና በዳንሻ ከተማ የሙዚቃ ድግስ አዘጋጅቶ ያለ ምንም ውጤት በታዳሚ ድርቅ ተመቶ ተገዜን ተሻግሮ መመለሱን ምንጮቻችን ገልፀዋል።በአሁኑ ሰአት የወልቃይት አማሮች በግድ የተጫነባቸውን የትግራይ ማንነት የሚያስታውሳቸው የትግረኛ ሙዚቃ መስማት ፈፅሞ እንደማይፈልጉ የአካባቢው ተወላጆች በምሬት በመግለፅ ላይ ናቸው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በትናንትናው እለት ወደ ጎንደር በመምጣት ላይ በነበሩ ተጨማሪ ኮሚቴዎቻችን ላይ የህወሓት ካድሬዎች ወከባ እና እንግልት እንደ ፈፀሙባቸው መገንዘብ ችለናል። ለወደፊቱ ወከባው እየከፋ እንደሚሄድ የህወሓት እብሪተኞች በድርጊት እና በዛቻ ንግግር በመግለፅ ላይ ናቸው። ስለሆነም መላው አማራ ስለ ወልቃይት የአማራ ማንነት ጠያቂ ኮሚቴዎቻችን የየቀን ውሎ ትኩረት ሰጥቶ በንቃት እንዲከታተል እናሳስባለን።

No comments:

Post a Comment