ወያኔ ከህዝቡ አመፅ በስተጀርባ አርበኞች ግንቦት ሰባት /ሻብያ ወዘተ አሉበት ይለናል። እና ታዲያ እኒህ ድርጅቶች የወያኔን ጎፈሬ ሊያበጥሩ የተፈጠሩ ይመስለዋል?
ወያኔ ማስመሰሏን ቀጥላለች። ወያኔ አለሁ፣እየው ታንክ፣ ሁሉንም እየሰራን ነው ማንም እኛን የሚያህል የለም ወዘተ አሮጌ ተረቱን ይተርታል።
ወያኔ ያልገባው ወይም ጆሮውን የደፈነው ህዝቡ በድፈን ብትፈልግ ታንክ ወይም ሚሳኤል ጥመድ እኛ እንደሆነ ላለፉት 24 አመት ሞት እና እርዛት የለት ተለት ገፅታችን ናቸው።
ሞት፣እስራት፣እንግልት ሰላማዊ ነን ያሉትም አላመለጡትም። ህዝብ ከሚኖረው እውነታ ተማረ። በኑሮ እና በሞት መካከል ልዮነት አጣ። እናም እየሞተ እስከ መጨረሻው ለነፃነት ሊፋለም ሆ ብሎ ተነሳ።
ወያኔም አሮጌ ቲሪኳን እና ቱልቱለዋን ትንፋ። ህዝብ ግን ላይመለስ ወደ ፊት እየገፋ ነው። ወንድ የሆንክ ጫካው ያውልህ ብላቹህ የቀለዳቹህበት ህዝብ በምታውቁት ሊያናግራቹህ በውስጥም በውጭም ላይመለስ ሊፋለማቹህ ተነሳ።
አሁን ይህን እየሰራን ነው ታንኩ ሁሉ የእኛ ብትሉ የሚሰማቹህ የለም።
No comments:
Post a Comment