Saturday, January 2, 2016

“በምስራቅ አፉሪካ የአሜሪካ አዲሱ የትኩረት እና ግንኙነት አቅጣጫ ኤርትራ!


ከአዲስ አበባ ከሚገኘው የአሜሪካ ኢምባሲ ላለፉት አስርት አመታት የሚወጡት ዲፕሎማቲክ ኮንቨርሴሽን ኬብሎች እንዳስነበቡን የአዲስ አበባወቹ መንግስት ተብየወች እጅግ ግራ የሚያጋባ እርስ በእራሱ የተምታታ ምንም አቋም የሌላቸው ሰወች መሆናቸውን ሲገልፁ ቆይተዋል። በተጨማሪም መንግስት ተብየወች ሆን ብለው ቦምብ እያፈነዱ አከሸፉን እንደሚሉም እነዚህ ኬብሎች አመልክተዋል።
ሌላው የአሜሪካን ዲፕሎማቶች ያስቆጣው የአዲስ አበባው መንግስት ተብየ ከሰሜን ኮሪያ እና ቻይና ጋር ያለው የአይዲዮሎጂ መመሳሰል እና የትኩረት አቅጣጫ ነው።
የአሜሪካ ዲፕሎማቶች የአዲስ አባባው መንግስት ተብየወች በምስራቅ አፉሪካ አሜሪካ ያላትን ስትራቴጂክ ጥቅም አደጋ ላይ የሚጥል የተምታታ ፓሊሲ የሚከተሉ እንደሆኑም ይህም እንዳሳሰባቸው ሲገልፁ ቆይተዋል።
የአሜሪካ መንግስትም አዲሱ የትኩረት አቅጣጫ ወደ ኤርትራው መንግስት መሆን እንዳለበት ዲፕሎማቶች ሲወተውቱ ቆይተዋል።
ለዚህም መልስ የአሜሪካ በኤርትራ የነበረው ቆንፅላ የማስፋፊያ ፕሮጀክቶችን በመስራት በአዲስ መልክ ስራውን እንዲጀምር ተደርጓል። በተጨማሪም ትውልደ-ኤርትራውያንን በመሰብሰብ የአሜሪካ ኢምባሲ ምክክር ሲያደርግ ቆይቷል። ”

No comments:

Post a Comment