Sunday, January 31, 2016

“ወታደሮቻችን ያሉት ኢትዮጵያ ውስጥ ነው፤ ትግላችንን ለመቀላቀል ካሁን በኋላ ለምትፈልጉ ወደ ሰሜን ብቻ መሄድ የለባችሁም” ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

Screen-Shot-2016-01-31-at-4.01.56-PM
የአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ዛሬ በዋሽንግተን ዲሲ ባደረጉት ሕዝባዊ ስብሰባ በኢትዮጵያ በተከሰተው ረሃብ; በኦሮሞ ተማሪዎች አመጽ እና ትግሉ ስላለበት ሁኔታ እንዲሁም ስለተቃዋሚዎች ተናግረዋል::
በኢትዮጵያ የተከሰተው ረሃብ የስርዓቱ ችግር ነው ካሉ በኋላ እርሳቸው የሚመሩት ተቋም ከዚህ ቀደም የገመተው የተራቢዎች ቁጥር አሁን ተግባራዊ እየሆነ እንደሆነ እንዲሁም ይህ አስተዳደር ከቀጠለ ከዚህ ቀደም እንደገመቱት በ2050 ዓ.ም 50 ሚሊዮን ሕዝብ እንደሚራብ ገልጸዋል::
በአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ዙሪያም እንዲሁ የተናገሩት ፕሮፌሰሩ በኦሮሚያ ክልል ህፃናት እና ነብሰጡርን ሳይቀር እየገደለ ያለውን ስርዓት ሕዝቡ እየሞተ ያለው ወገኔ ነው ብሎ ማውገዝ አለበት ብለዋል:: በተለይም በአሁኑ ወቅት ከኦሮሞ ድርጅቶች ጋር በህብረት ለመታገል ንግግሮች መጀመራቸውንም አስታውቀዋል::
ስለተቃዋሚዎችም የተናገሩት ፕሮፌሰሩ “የተቃዋሚዎች የምኞት ፖለቲካ ነው የሚከተሉት” ሲሉ ተችተው የምር መታገል እንዳለባቸው አስምረውበታል::
ወቅታዊውን የአርበኞች ግንቦት 7 ሁኔታ በተመለከተም “ወታደሮቻችን ያሉት ኢትዮጵያ ውስጥ ነው… ትግላችንን ለመቀላቀል ካሁን በኋላ ለምትፈልጉ ወደ ሰሜን ብቻ መሄድ የለባችሁም” ብለዋል::

Friday, January 29, 2016

ቋሚ ሲኖዶሱ ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ከፍተኛ ማስጠንቀቂያ መስጠቱ ተገለጸ፡፡


ቋሚ ሲኖዶሱ ፓትርያርኩን ያስጠነቀቀው፣ ባለፈው ሳምንት ረቡዕ፣ ሐምሌ ፪ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. ሳምንታዊ ስብሰባውን ባካሔደበት ወቅት ነው፡፡ የቤተ ክህነቱ የፋክትምንጮች እንደተናገሩት፣ የማስጠንቀቂያው መንሥኤ÷ አቡነ ማትያስ ምክራቸውን ለሥልጣነ ፕትርክናቸው አይመጥኑም ከተባሉ አማሳኝ ግለሰቦች እና የቤተ ክርስቲያኒቱን ተቋማዊ ክብርና ነፃነት በመጋፋት ከሚወቀሱ አፅራረ ሃይማኖት አካላት ጋራ በማድረግ የቅዱስ ሲኖዶሱን ውሳኔና ልዕልና የሚፃረር ተግባር በየጊዜው መፈጸማቸው የቅዱስ ሲኖዶሱን አባላት ክፉኛ በማሳሰቡ ነው፡፡
  • ተጠሪነቱ ለቅዱስ ሲኖዶስ የኾነው ቋሚ ሲኖዶስ፣ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ እየተወሰኑ የሚተላለፉ መመሪያዎችን ተግባራዊነት እንዲከታተል ካለበት ሓላፊነትና አሠራር ጋራ የማይጣጣሙ የፓትርያርኩ የአፈጻጸም አካሔዶችና አቋሞች መበራከታቸው፤
  • ቋሚ ሲኖዶሱ ሳይወስንና የመንበረ ፓትርያርኩ ጠቅላይ ጽ/ቤት ሳያውቀው የጽ/ቤት ሓላፊያቸውን አቶ ታምሩ አበበን ያለሞያቸው ወደ ሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የአካዳሚክ ምክትል ዲን አድርገው በማዘዋወር፣ በቦታቸው የቤተ ክርስቲያኒቱን ክብርና ነፃነት ከሚዳፈሩ ባለሥልጣናት ጋራ በሙሉ አቅማቸው በመሥራት የሚታወቁትን የአማሳኞች አለቃ ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃን መተካታቸው
  • ከፍተኛ ገቢና የአገልግሎት አቅም ባላቸው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ገዳማትና አድባራት የአማሳኞችን የምዝበራ ሰንሰለት እያጋለጡ ሙስናንና ብልሹ አሠራርን በመዋጋት፣ ካህኑንና ምእመኑን አንድ አድርጎ የአደረጃጀትና የአሠራር ለውጥ ጥናቱ አጋር በመኾን የተመሰገኑ አለቆች፣ ፓትርያርኩ ከአማሳኞች ጋራ እየመከሩ በሚያስተላልፉት ቀጥተኛ ትእዛዝ ከሓላፊነታቸው መነሣታቸው
  • አገልጋዩ እና ምእመኑ በአንድነት የውጤታማና ምስጉን አስተዳዳሪዎችን ያለአግባብ ከሓላፊነት መነሣት በተመለከተ ያቀረባቸው ጥያቄዎች፣ በቋሚ ሲኖዶሱ መመሪያ መሠረት አስፈላጊው ማጣራት ተደርጎ ተገቢ ምላሽ ሳይሰጥባቸው የፓትርያርኩ የዝውውር ውሳኔ ተፈጻሚ መኾኑና የመሳሰሉት ጉዳዮች፤
የቋሚ ሲኖዶሱ አባላት ከፓትርያርኩ ጋራ በከፍተኛ ደረጃ የተጠያየቁባቸውና ፓትርያርኩን ያስጠነቀቁባቸው ዐበይት ነጥቦች እንደነበሩ ምንጮቹ አስታውቀዋል፡፡
በሳምንታዊ መደበኛ ስብሰባው ላይ ለፓትርያርኩ ጥያቄ ያቀረቡት የቋሚ ሲኖዶስ አባላቱ፣ ሳይገባቸውና ደረጃቸውን ሳይጠብቁ ‹ፓትርያርኩን ያማክራሉ› ያሏቸውን ቀንደኛ አማሳኞች እነኃይሌ ኣብርሃን በስም በመጥቀስ፣ ‹‹ለመኾኑ ከማን ጋራ ነው የሚሠሩት? ማንን ነው የሚሰሙት? ምክርዎ ቤተ ክርስቲያኒቱን ከሚጎዱና ከሚያጠፉ ስማቸውም በመልካም ከማይነሣና ምግባር ከጎደላቸው ሰዎች ጋራ ነው፤ ከእነርሱ እየመከሩ አብረውን የወሰኑትን ውሳኔ ይገለብጣሉ፤ ዓላማዎ ምንድን ነው?›› በሚል ጠንክረው እንደጠየቋቸው በምንጮቹ መረጃ ተመልክቷል፡፡
ፓትርያርኩ በሰብሳቢነት በሚመሩት የቋሚ ሲኖዶሱ ስብሰባ አብረው የወሰኑበትን ጉዳይ በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ በስም ከተጠቀሱት ቀንደኛ አማሳኞችና አድርባይ ፖለቲከኞች ጋራ እየመከሩ በአፈጻጸም ስለሚገለብጡበት አካሔድ ለቀረበላቸው ጥያቄ፣ ‹‹የኔ ቃልና የነሱ ቃል አንድ ስለኾነ፣ የሚያመጡት ሐሳብ ስለሚመቸኝ›› የሚል ምላሽ መስጠታቸው ተዘግቧል፤ አብረዋቸው የሚሠሩትም ‹‹ዓላማዬን ስለሚያስፈጽሙልኝ ነው›› በማለት አቋማቸውን ለመከላከል መሞከራቸው ተዘግቧል፡፡
የቋሚ ሲኖዶስ አባላቱ በበኩላቸው፣ ‹‹አገልጋዩንና ምእመኑን ከሚዘርፉና ከሚያሠቃዩ ጋራ ምን ዓይነት ዓላማ ሊኖርዎት ይችላል? አገልጋዩና ምእመኑ የሚዘረፍበትና የሚሠቃይበት ዓላማ ሊኖርዎት አይችልም፤›› የሚል ጠንካራ ምላሽ በመስጠት ፓትርያርኩ ቤተ ክርስቲያኒቱን ከሚጎዳ ፀረ ሕገ ቤተ ክርስቲያን አካሔድ እንዲታረሙ አስጠንቅቀዋቸዋል፤ በዚኽ ዓይነቱ ድርጊታቸው የሚቀጥሉ ከኾነ ደግሞ ቋሚ ሲኖዶሱ ከእርሳቸው ጋራ የመሥራትን አስፈላጊነት እንደሚያጤነው፣ አስፈላጊም ከኾነ በሕገ ቤተ ክርስቲያኑ ድንጋጌዎች መሠረት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤን አስቸኳይና ድንገተኛ ስብሰባ ለመጥራት እንደሚገደድ በግልጽ እንደተነገራቸው ተገልጧል፡፡
በቋሚ ሲኖዶሱ ያልተለመደ ጽናትና ጠንካራ ማስጠንቀቂያ ፓትርያርኩ በአካላዊ ኹኔታዎች የሚገለጽ ከፍተኛ ድንጋጤ ይታይባቸው እንደነበርና በስብሰባው መጀመሪያ ላይ ለመከላከል የሞከሩት ፀረ ሕገ ቤተ ክርስቲያን አቋማቸው ስሕተት መኾኑን በማሔስ በፍጥነት የመሰብሰብ እርማት እንዳደረጉ ተመልክቷል፡፡ ‹‹ከእኛ[ቋሚ ሲኖዶስ] ጋራ ይሠራሉ ወይስ አይሠሩም?›› ለሚለው ርምጃ አዘል (consequential) መጠይቅም አዎንታዊ ምላሽ መስጠታቸው ተነግሯል፡፡
‹‹የቤተ ክርስቲያንን ሥራ ይጎዳል በሚል እንጂ ተመራጩ ነገር ከእሳቸው[ፓትርያርኩ] ጋራ መሥራትን ማቆም ነበር፤›› ማለታቸው የተጠቀሰላቸው አንድ የቋሚ ሲኖዶሱ አባል፣ ፓትርያርኩ በየአጋጣሚው በብፁዓን አባቶችና በቅርብ ወዳጆቻቸው* ጭምር ቢመከሩም ለመታረም ስላልፈቀዱና ከሚገኙበት አሳሳቢ የአሠራር ኹኔታ አንፃር ቋሚ ሲኖዶሱ በሕገ ቤተ ክርስቲያን አግባብ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤን አስቸኳይና ድንገተኛ ስብሰባ ለመጥራት የሚገደድበት ደረጃ ከመድረስም በላይ ተግባራዊ እንቅስቃሴም አድርጎ እንደነበር አረጋግጠው መናገራቸው ተዘግቧል፡፡
አቡነ ማትያስ በቋሚ ሲኖዶስ አባላቱ በተጠየቁባቸው ጉዳዮች ስሕተት መፈጸማቸውን አምነው መቀበላቸውና ‹‹ከቋሚ ሲኖዶሱ ጋራ ይሠራሉ ወይስ አይሠሩም?›› በሚል በቁርጥ ተጠይቀውበታል ለተባለው ጥያቄ አዎንታዊ መልስ መስጠታቸው፣ በቃለ ጉባኤውም ላይ መፈረማቸው የምልዓተ ጉባኤውን የአስቸኳይ ስብሰባ ጥሪ እንቅስቃሴ ለጊዜው እንደገታው የዜናው ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ ቋሚ ሲኖዶሱ የቅዱስ ሲኖዶሱን ልዕልናና የቤተ ክርስቲያኒቱን መብትና ጥቅሞች ከመሰል የውስጥ አማሳኞች ፈተናና የአፅራረ ሃይማኖት ተግዳሮቶች የማስጠበቅ ጥንቃቄውን በተተኪ ተለዋጭ አባላቱም አጠናክሮ እንደሚቀጥልበት አስታውቀዋል፡፡
ፓትርያርኩ የቅዱስ ሲኖዶሱን ውሳኔ በመጋፋት ስሕተት መፈጸማቸውን አምነው ከተቀበሏቸው ርምጃዎቻቸው መካከል፣ ብልሹ አሠራርንና ሙስናን በመዋጋት የአገልጋዩና ምእመኑ ከፍተኛ ተቀባይነት ማትረፋቸው የሚነገርላቸው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ደብረ ጽጌ ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ መልአከ ብርሃናት ቀሲስ ክብሩ ገብረ ጻድቅ ዝውውር ዋነኛው ነበር ተብሏል፡፡
ለአብነት ያኽል ከወቅቱ የቋሚ ሲኖዶስ አራት ተለዋጭ አባላት አንዱ የኾኑት የሰሜን ጎንደር ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ፣ የፓትርያርኩ አንደኛ ዓመት በዓለ ሢመት በተከበረበት የካቲት ፳፬ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. ምሽት የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ባዘጋጀው የራት መርሐ ግብር ላይ ለአባ ማትያስ የሰጧቸው ወንድማዊ ምክር የሚከተለው ነበር፡-
‹ቅዱስነታቸው በ፲፱፻፸፩ ዓ.ም. በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አንብሮተ እድ ኤጲስ ቆጶስነት ከተሾምነው 13 አባቶች አንዱ ናቸው፡፡ ከመካከላችን ወንድማችን ለዚኽ ክብር መብቃታቸው ኹላችንም ደስ  ይለናል፤ በተለይ እኔ ካለኝ ቅርበት ወንድምም ስለኾንኩ፤ የእግዚአብሔር ቃል ኹሌም አዲስ ነው፤ የሚመከረውም በእግዚአብሔር ቃል ነው፤ ፓትርያርክም ቢኾኑ ወንድም ነዎትና እንግዲኽ በእግዚአብሔር ቃል ልምከርዎ፡፡
አንድ ፓትርያርክ ከማን ጋራ ነው ምክሩ? ቅዱስ ሲኖዶስ ይህን ከፍተኛ የቤተ ክርስቲያን ሓላፊነት ሲሰጥዎ ዐዲስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፣ ዐዲስ የጠቅላይ ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ አድርጎ ሰጥዎታል፡፡ መምከር ያለብዎ ከእነርሱ ጋራ ነበር፤ ከዚያ ካለፈ ከቋሚ ሲኖዶስ ጋራ ነው፤ አስፈላጊም ከኾነ ጠቅላላ ጉባኤው ይሰበሰባል፡፡ እርስዎ ግን ወርደው ከማን ጋራ ነው እየተማከሩ ያሉ? ጌታችንኮ ምክር አስፈልጎት ባይኾንም ‹‹ስዎች ማን ይሉኛል?›› ብሎ የተጠያየቀውና የተማከረው ከሐዋርያት ጋራ ነው፤ የተማከረው ከ120 ቤተሰብ ጋራ ነው፡፡
ቅዱስነትዎ ረዥም ዘመን የኖሩት በውጭ አገር ነው፡፡ እንግዳ እንዳይኾኑ ዐዲስ ዋና ጸሐፊ ዐዲስም ዋና ሥራ አስኪያጅ ተመድቦልዎታል፡፡ ምክርዎት ከሌላ ጋራ ከኾነ ግን በጣም አስቸጋሪ ይኾናል፡፡ በአገራችን ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖትና ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አንድነት ሲያገልግሉ ከዬት መጣኽ አልተባባሉም፤ ዘር፣ ጎጥ አልጠያየቁም፡፡ ጎሳ፣ አገር ሳይለያያቸው በመላው ኢትዮጵያ ያገለገሉ አባቶች ናቸው፡፡ ከሥራ ጓደኞችዎ ጋራ ከየት መጣኽ ሳንባባል በጋራ በአንድነት እየተመካከርን ማገልገል ነው፡፡ ከዚያ ወርደን መገኘት የለብንም፡፡
የቤተ ክርስቲያን መጻሕፍት ከቅዱስ ወንጌል የቅዱሳን ሐዋርያት፣ ከቅዱሳን ሐዋርያት የሊቃውንት እያለ እንደሚሔደው ቅዱስነትዎም ከዋና ጸሐፊ፣ ከዋና ሥራ አስኪያጅ፣ ከቋሚ ሲኖዶስና ከምልዓተ ጉባኤ ጋራ ነው ምክርዎ ሊኾን የሚገባው፡፡ በቅዱስነትዎ ደረጃ ከብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ወርዶ ከታች መምከር ማለት ከሊቃውንት መጻሕፍት ወርዶ ልቦለድ መጽሐፍ እንደማንበብ ነው፡፡
በክብረ በዓሉ ምሽት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ፣ ብዙዎችን ደስ ያሰኘውን ይህን የብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ ወንድማዊ ምክር በአድንኖ (አንገታቸው ዝቅ አድርገው) በጸጥታ ሲያዳምጡ በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱና በበዓለ ሢመታቸው የራት መርሐ ግብር ታዳሚዎች ተስተውለው ነበር፡፡ አዳምጠው ሲያበቁም ‹‹እግዚአብሔር ይስጥልኝ፤ እንደዛሬው ለዓመቱ ያገናኘን›› በማለት በጸሎት ከማሳረግ በቀር የተናገሩት አልነበራቸውም፡፡
ሰሞኑን በልዩ ጽ/ቤታቸው ያደረጉት ዝውውርና ምደባ ግን ይህን ታላቅ ምክር አለመስማታቸውን ብቻ ሳይኾን በተለያዩ ዘገባዎች እንደታየው፣ ፀረ አማሳኝ መስለው ራሳቸውን ካስተዋወቁ በኋላ የአማሳኞች አጋርና ከለላ የመኾናቸውን ዓይነተኛ ፍፃሜ በማያሻማ መልኩ ያረጋገጠ ኾኗል፡፡
ፓትርያርኩ ሰሞኑን ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃን የጽ/ቤታቸው ሓላፊ በማድረግ መድበዋቸዋል፡፡ ዋና ሥራ አስኪያጁ የሚመሩትና ሠራተኛውን የሚመለከቱ ቅጥሮችን፣ ዕድገቶችንና ዝውውሮችን የማስጠናትና የማስፈጸም ሥልጣንና ተግባር ያለው ጠቅላይ ጽ/ቤት በግልባጭ እንኳ የማያውቀው ምደባው፣ ወትሮም ከመጋረጃ ጀርባ የውጭ ኃይል እጅና የተጽዕኖው አሳላፊ ኾነው በመንቀሳቀስ የሚታወቁትን የንቡረ እዱን የክፉ አማካሪነት ተግባር ይፋ የሚያወጣው ይኾናል፡፡
ቋሚ ሲኖዶስ ከግለሰቡ መሠሪነትና ከጉዳዩ አሳሳቢነት በመነሣት ከያዘው ጠንካራ አቋም አንጻር ቀጣዩ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ መደበኛ ስብሰባ የግለሰቡን ምደባ በቀላሉ እንደማያየው መገመት ቢቻልም፣ ከእንግዲኽ ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ የፓትርያርኩን ልዩ ጽ/ቤት በመደበኛነት በመቆጣጠር እንደሚከተሏቸው ለሚገመቱ ፀረ – ሲኖዶስና ፀረ – ሕገ ቤተ ክርስቲያን በኾኑ የአድርብዬ ፖሊቲከኝነት አሠራሮች ከፓትርያርኩ ጋራ የሚኖራቸውን የታሪክ ተጠያቂነት ከባድ እንደሚያደርገው ጥርጥር የለውም፡፡

የትግራይ ክልል መስተዳደር አቶ አባይ ወልዱ እየተቀጣጠለ ያለውን የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄን ለማዳፈን ነገ ወልቃይት ይገባሉ ተባለ


የትግራይ ክልል መስተዳደር አቶ አባይ ወልዱ ዛሬ ወይም ነገ ወልቃይት ይገባሉ እየተባለ ነው። በጉብኝታቸው ወቅት በአካባቢው ያሉ የህወሓት አመራሮችን እና በሰፈራ የመጡ የትግራይ ተወላጆችን ያነጋግራሉ ተብሎ ይጠበቃል። የጉብኝታቸው ዋና አላማ እንደ ሰደድ እሳት እየተቀጣጠለ ያለውን የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄን ለማዳፈን የቅስቀሳ እና የማስተባበር ስራ ለመሰራት እንደሆነ ታምኗል።
በተጨማሪም ሰሞኑን የትግራይ ክልል ቴሌቪዥን ከፍተኛ የሆነ ፀረ ወልቃይት ቅስቀሳ እያስተላለፉ ይገኛል። የወልቃይትን የአማራነት ጥያቄ ለመቀልበስ የትግራይ መገናኛ ብዙሃን በርተተው እዬሰሩ ነው። ሰሞኑን የትግራይ ክልል ልዩ ባንድ በአዲረመፅ እና በዳንሻ ከተማ የሙዚቃ ድግስ አዘጋጅቶ ያለ ምንም ውጤት በታዳሚ ድርቅ ተመቶ ተገዜን ተሻግሮ መመለሱን ምንጮቻችን ገልፀዋል።በአሁኑ ሰአት የወልቃይት አማሮች በግድ የተጫነባቸውን የትግራይ ማንነት የሚያስታውሳቸው የትግረኛ ሙዚቃ መስማት ፈፅሞ እንደማይፈልጉ የአካባቢው ተወላጆች በምሬት በመግለፅ ላይ ናቸው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በትናንትናው እለት ወደ ጎንደር በመምጣት ላይ በነበሩ ተጨማሪ ኮሚቴዎቻችን ላይ የህወሓት ካድሬዎች ወከባ እና እንግልት እንደ ፈፀሙባቸው መገንዘብ ችለናል። ለወደፊቱ ወከባው እየከፋ እንደሚሄድ የህወሓት እብሪተኞች በድርጊት እና በዛቻ ንግግር በመግለፅ ላይ ናቸው። ስለሆነም መላው አማራ ስለ ወልቃይት የአማራ ማንነት ጠያቂ ኮሚቴዎቻችን የየቀን ውሎ ትኩረት ሰጥቶ በንቃት እንዲከታተል እናሳስባለን።

“በአኮቦ ወረዳ ከ200 በላይ የሚሆኑ አኙዋኮች ህፃናት እና ሴቶች መጨፍጨፋቸው ተነገረ

ጥር 16 ቀን 2008 ዓ.ም
ሁላችንም እንደምንገነዘበው ባለፋት 25 አመታት ወያኔ ሲጠቀምባቸው የነበሩ ስሌቶችና ጭካኔና በተሞላበት ድርጊቶች መካከል የኢትዮጵያን ህዝብ በዘር በሀይማኖት እና በክልል እየከፋፈለ አንዱን ብሄረስብ በሌላው ላይ እያነሳሳና እያስታጠቀ ለመቆየት በመቻሉ ነው። በተናጠል ሌላውን ብሄረሰብ እያጠቃ በጠቅላላው የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የሚፈፅመው የኢሰብዓዊ ድርጊቶች ከማንኛውም ግዜ በላይ በመቀጠል ላይ ነው ያለሁ። ለዘመናት በሰላም እና በፍቅር ይኖር የነበሩትን ብሄረሰቦች እርስ በእርስ በማጋጨት በሌላው ብሔረሰብ ላይ የዘር ማጥፋት ዘመቻም እያወጀና እየጨፈጨፈ ሲያንስም የሕዝቡን ነፃነት እየሸረሸረ ዛሬ በበለጠ ግዜ የሀገሪቷን ሉዓላዊነት አወዛጋቢ ሁኔታ ላይ ጥሎዋታል።
መላው የአለም ህዝብ እንደሚያውቀው ታህሳስ 3፣1996 ዓ.ም (December 13, 2003) በጋምቤላ ከተማና በተለያዩ ወረዳዎች ዉስጥ ከሶስት ሺህ በላይ የሚበልጡ እኙዋኮች እንደ እንስሳ በወያኔ የታደኑበት ቀን ነች። ይህን ድርግት በተመሣሣይ ሁነታ በሌላው የኢትዮጵያ ብሕረሰብ ላይ እንዳይደገምና መላዉ የአለም ሕዝብ ይህን ታርካዊ ቀን እንድያስታውሳትና እንዳይረሱት ምክንያት ተደርጎ ይህንን ድርጅት በዚቹ ቀን እንድሠየም ተደርጓል። አሁንም ቢሆን በአኙዋኮች ላይ በሌላ መልኩ ተመሳሳይ ግድያ እየተካሄደ ነው። ባለፈው ወር ብቻ በአኮቦ ወረዳ ከ200 በላይ የሚሆኑ አኙዋኮች ህፃናት እና ሴቶችን ጭምር ወያኔ ባስጣጠቃቸው ከባድ የጦር መሳሪያዎች በስደተኛው ንዋር ብሄረሰብ ተጨፍጭፈዋል። እንዲሁም አኮቦ ወረዳ አልፎ በተመሳሳይ ሁኔታ ደግሞ በኢታንግ ወረዳ የሚገኙ ቀበሌዎች በነዚህ የጦር መሣርያዎች በመደብደብ በርካታ በቶችና ንብረቶችን ተጋይተው 18 በላይ የሚበልጡ አኙዋኮች መገደላቸው እና በርካቶች መቁሰላቸው ለአለም ተገልፆዓል።
በተጨማሪ አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝና የተቀሩት ከፍተኛ የወያኔ ባለሥልጣን በተገኙበት ለውሸት ፕሮፓጋንዳ ተብሎ በጋምቤላ የብሄርና ብሄረስቦች በሚከበርበት ቀን ለአኙዋኮች መግደያ እንዲሆን የታቀደው የጦር መሳሪያ የተከማቸበት ግምጃ ቤት እንዳይከፈት በትህዛዛቸው የተከለከለ ሲሆን ፣ ሳምንት ባልሞላ ጊዜ እነዚህን መሳሪያዎች ለአጋሩ የንዋሩ ብሕረሰብ ለማከፋፈል ስሞክሩ የጫኑበት መኪና ላይ በኬላ ላይ በመያዙ እስከ ዛሬ ድረስ ማንም በዚሁ ሽብር የተጠየቀ እንዳልነበረ ነው። በአለፋት ቀናት በዜና ምንጮች ስዘገቡ የነበረው የጋምቤላ አሳሳቢ ሁኔታ የንዋሩና የወያኔ ሴራዎች በመሆናቸዉ የአኝዋክ ብሕረሰብ ለዘመናት በዘግነቱ የኮራ ለአገሪቷን ሉዑላዊነት ከሚገባው መጽዋትነት የከፈለ በወያኔ የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ያልተበገረ አኩሪ ታሪክ ያለው ሕዝብ ነው። ይህን ሆኖ እያለ ወያኔና ግብረአበሮቹ የአቀዱትን የአኝዋኩ ብሕረሰብ የመጨፍጨፍ ሴራ ማንኛውም ኢትዮጵያዊና የአለም ሕብረተሰብ በጥብቅ እንድያወግዘውና እንድያከሽፍ ያስፈልጋል። በመቀጠልም በአዲስ አበባ አካባቢ የሚገኙ የታወቁ እና ያልታወቁ አስቃቂ እስር ቤቶች ክ200 በላይ የሚሆኑ አኙዋኮችና የመጀንገር ብሄረስብ ሀባላት በታህሳስ 3፣ 1996 ዓ.ም ወያኔ በፈፀመው የዘር ማጥፋት ወንጄል በግድያ ወቅጥ በመትረፋቸው ብቻ ተወንጅለው በእነዚህ እስር ቤቶች በመሰቃየት ላይ ናቸዉ።
ትላንት በአማራው በሱማሌው በኦሮሞው በአኙዋኩ በመጀንገር እና በሌሎችም የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ሲፈፀም የነበረው ግድያ፣ አሁንም ደግሞ በአዲስ አበባ ማስተርፕላን ጋር የተያያዘው ህዝባዊ እንቅስቃሴ ሰበብ በማድረግ የወያኔ አሸባሪ ሰራዊት የኢትዮጵያ ህዝብ ጭካኔ በተሞላበት ጭፍጨፋ የተፈፀመባቸዉ ናቸው። ከዚህም አልፎ የሀገሪቷን ንብረቶች እየዘረፈ፣ መሬቶችን እየነጠቀ እና ህዝቡን በማፈናቀል ለ25 ዓመታት ሁሉ የዘረጉትን የግድያ ስንስለቶች እንዲቆይ ያደረገው ህዝብን በመከፋፈል መሆኑ እየታወቀ አሁን ኦሮሞ ሕዝብ ለነፃነትና ለእኩልነት የሚያካሆደሁን እንቅስቃሴ የአንድ ብሄረሰብ ትግል ብቻ ሳይሆን የጠቅላላው የኢትዮጵያ ህዝብ በአንድነትን የተመረኮዘ ትግል እንደሆነ ሊታሰብበት ይገባል ።እስከ ዛሬ ድረስ ወያኔ በሌላውብሄረሰብ ላይ በጠናጥል ሲፈፅማቸው የነበሩትን ግድያዎች በጠቅላላው የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እንዳልተፈፀመ ተደርጎ ባለመወሰዱ የወያኔ አረመኔነትን እንድያራዝም አድርገናል። በመሆኑም ይህች አገር ከገባችበት ሰቆቃ ለማላቀቅ የመላው የኢትዮጵያ ብሄረስቦች በአንድነት በዘር በሀይማኖት ሳይከፋፈሉ ሁሉን ያካተተ ውህደት በመፍጠር ወያኔ የሚወገድበትን አንድ አላማ መቀየስ አስፈላጊ ብቻ ሳይሆን ግዴታም ጭምር ነው። ዛሬ በሁሉም አቅጣጫ ህዝቡ ታፍኖል ለነጌይቱ የሚያዘልቃቸውን የነፃነት ትንፋሽም ታግዷል ። ለዘመናት ኢትዮጵያ እንድትኖር ያበቁትን እነ አፄ ቴውድሮስ አፄ ምንሊክ እና ዘርዓይን እና ሌሎች ኢትዮጵያዊያን በከፈሉት መስዋትነት ሲሆን በሀገሬ ውስጥ ባርነትን አንቀበልም ብለውነውሞትንየተጋፈጡት።
ስለዚህ ነፃነት በልመና በነፃ እንደማይጎናፀፍ  በመሆኑ፣ ከሰማይ የሰላምና ነፃነት አምላክ  እሲኪወርድ ድረስ የምንጠብቅ ከሆነ ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር ትኖራለች የሚል ግምት እንደማይኖር ነው።
በመቀጠል ደግሞ ለመላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ለማስተላለፍ የሚንፈልገው፧ ወያኔ የሕዝቡን ደም ደፍቶ በዝርፊያ ያካበታቸውን ሀብቶች ፣ የንግድና የኢኮኖሚ አውታሮች [ትራንስፖርትና መገናኛ ዘርፎች]በዘረፋ የተገኙ በመሆናቸሁ በነፃነትና በሰብአዊነት የሚያምኑ በውስጥና በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን በወያኔና በደጋፊያቸ የንግድና የኢኮኖሚ አውታሮች ላይ ማእቀብ እንድጫንባቸው።
በተለያዩ ሀገሮች በድብቅ ያካበቱ የንግድ ዘርፎች የዉጭ ምንዛሬ ምንጭ በመሆናቸውና በነዚ ሀብት በሚሰበሰበሁ በመጠቀም ሕዝቡን የሚጨፈጭፋበትን የጦር መሣሪያ በመሆኑ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ አቅሙን በሚፈቅደው ሁነታ ከነዚህ ዘርፎች ጋር አንዳችም የንግድ ግንኙነቶችን እንዳይኖር እንድቆጠቡ።
መንግስት መንግስትነትን የሚያሰኘው ማሟላት የሚገባቸዉ አላፊነቶችና ድርግቶች በጥቂጡ ለመግለጽ፣ በሕዝቡን መካከል ሰላም እንድሰፍን መጣር፣ በሕብረተሰቡ መካከል የሚፈጠሩ አለመግባቶች በሰላማዊ እንድፈቱና በማድረግ፣ የአንድነት ስመት እንድኖርና የአገርቷን ደህንነትና ድምበር ማስከበር ሲሆን ወያኔ ግን በተቃራኒ ሕዝቡን በዘርና በጎሳ እየከፋፈለ፣ እየገደለና የአገርቷን ንብረቶችን እየዘረፈ፣ መሬቱን ለውጭ አገር እየለገሰ፣ ለሰውነት ለነፃነትና ለዲሞኪራሲ እሉኝታ የሌለው፣በጎሰኝነት በዘረኝነት በብሕረተኝነት አጥብቀው የሚያምኑበት በመሆኑ ይህን ስርኀት መንግሥት ባለመሆኑ በሕዝቡ ደምና አጥንት የነደፋቸው ፀረ ሰው ሕገ ወጥ ሕጎች ማንኛውም ኢትዮጵያዊ እንዳያከብራቸው ለጠቅላላው ሕዝብ ጥሪያችን እናስተላልፋለን።
በአንድነት በነፃነትና በእኩልነት በፍትህና በዲሞኪራሲ ላይ የተመሠረተ ስሪኀት እንድቋቋም የሚያስችል በጠቅላላዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ ትብብር ብቻ ነው። በዚሁ በመነሳት ዘረኛዉ የአረመኔ ስብስብ ሊፋለሙት የሚያችላቸውን አንድ ዓላማ በመነሳት፣ የፓለቲካ ድርጅቶች ልዩነቶች በማስወገድ፣ በአገር ስሜት ለአሁኑ አጣዳፊ የአገር ማዳን ጉዳይ በጋራ እንድንወጣ በአስቸኳይ ጥሪያችን ስናስተላልፍ፣ ለብዙ አመታት በተናጠል የተሞከሩ የነፃነት እንቅስቃሴዎች የትም እንዳላደረሱን የሚታሰብ ሲሆን አሁንም ከተለያዩ ድርጅቶች እና ብሄረስቦች መካከል የተጀመረውን የመተባበር መንፈስ በሰፊው እንዲቀጥል እና የጠቅላላው የኢትዮጵያ ህዝብ ምኞት በመሆኑ ድርጅታችን በዘር እና በክልል የተገደበ ባለመሆኑ ከጠቅላላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ተባብረን ለመስራት ዝግጁ መሆናችንን በዚህ አጋጣሚ ለመግለፅ እንወዳለን።
አንድ ኢትዮጵያ አንድ ህዝብ!
E‐mail: dec13codemo@gmail.com የታህሳስ ሶስት መታሰቢያ ዲሞክራሲያዊ እንቅስቃሴ

የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚደንት አቶ ሙክታር ከድር እየተገመገሙ እንደሆነና ስልጣናቸውን ሊለቁ እንደሚችሉ ተዘገበ


የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) ማዕከላዊ ኮሚቴ በስራ አስፈጻሚ ደረጃ አስቸኳይ ስብሰባ መቀመጡ ታወቀ። የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚደንት አቶ ሙክታር ከድር እየተገመገሙ እንደሆነና ስልጣናቸውን ሊለቁ እንደሚችሉ ለኢሳት የደረሰው መረጃ ያመለክታል። ከጨፌ ኦሮሚያ የውስጥ ምንጮች ለኢሳት የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ ኦህዴድ በመላው የኦሮሚያ አካባቢ የተቀጣጠለውን ህዝባዊ እምቢተኝነት ቁልፍ አመራር እየገመገመ መሆኑ ታውቋል። የድርጅቱ ማዕከላዊ ኮሚቴና ስራ አስፈጻሚው ግምገማውን በአቶ ሙክታር ላይ በማተኮር ግምገማ እያደረገ እንደሆነ ከስፍራው የደረሰው ዜና ያስረዳል። የግምገማው ውጤትም አቶ ሙክታር ከድርን ከፕሬዚደንትነት በማንሳት ሊጠናቀቅ እንደሚችል የውስጥ ምንጮች ለኢሳት ገልጸዋል። በአቶ ሙክታር ከድር ምትክ የገቢዎችና ጉምሩክ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ በክር ሻሌ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚደንት ይሆናሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ለማወቅ ተችሏል። ግምገማው ከአቶ ሙክታር ከድር በተጨማሪ የኦህዴድ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ዳባ ደበሌ ከስልጣናቸው ሊነሱ እንደሚችሉ የኢሳት የጨፌ ኦሮሚያ የውስጥ ምንጮች ግምታቸውን ገልጸዋል። በሌላ በኩል ደግሞ የኦህዴድ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የኦሮሞ ብሄረሰብ ተወላጅ የሆኑ ነጋዴዎችን ለይቶ ለማወያየት ውሳኔ ማሳለፉን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል። በክልል ደረጃ የኦሮሞ ባለሃብቶችን በመሰብሰብ በወቅታዊ የህዝብ ንቅናቄ ላይ ለማወያየት የታቀደው በየአካባቢው የተደረገው ተመሳሳይ እንቅስቃሴ ውጤት አልባ መሆኑን ተከትሎ ነው። በቅርቡ በአቶ ዱላ ገመዳና በሌሎቹ የኦህዴድ አመራሮች ተጠርቶ በነበረው የኦሮሞ ባለሃብቶች ስብሰባ ላይ ባለሃብቶቹ ጥቁር ለብሰው በመምጣት የመንግስት የግድያ ዕርምጃ መቃወማቸው ይታወሳል።

Thursday, January 28, 2016

ኢትዮጵያ “ነፃነት የሌለባት”፤ ኤርትራ “ከክፉዎች የከፋች” ተባሉ


በዓለም ዙሪያ የሚሰማው የምጣኔ ኃብት ድቀት እና የማኅበራዊ ነውጥ ፍራቻ አምባገነን መንግሥታት በአውሮፓ አቆጣጠር ባለፈው 2015 ዓ.ም ይበልጥ አፋኝና ጨቋኝ እንዲሆኑ ሰበብ ሳይሰጣቸው እንዳልቀረ ዛሬ የወጣ የዓለም የነፃነት ሁኔታ ሪፖርት አስታውቋል፡፡
ፍሪደም ሃውስ የሚባለው ነፃ ቡድን በዚህ ሪፖርቱ የሃገሮችን የዴሞክራሲያዊ የነፃነት ይዞታዎች ገምግሞ በደረጃ አስቀምጧቸዋል፡፡ አምባገነን አገዛዞች ባለፈው የአውሮፓ ዓመት በ2015 ዓ.ም ይበልጥ የከፉ መሆናቸውን ይህ ዛሬ የወጣ የዓለም የነፃነት ይዞታ ሪፖርት ይናገራል፡፡
መንግሥታቱ የሚጠቀሙባቸው እጅግ የከፉ የአፈና ዘዴዎች፣ የሽብር ፈጠራ ጥቃቶች መብዛት እና የምጣኔ ኃብት መላሸቅ፣ ነፃነት በዓለም ዙሪያ እየተጉላላች፣ ይዞታዋ ወደ አስፈሪ ሁኔታ እያዘገመ መምጣቱ እያሰጋ መሆኑን ሪፖርቱ ይጠቁማል፡፡
ተቀማጭነቱ ዋሺንግተን ዲሲ ዩናይትድ ስቴትስ የሆነው ፍሪደም ሃውስ የሚባለው የሰብዓዊ መብቶች ጥበቃ ተሟጋች ቡድን ባለፈው የአውሮፓ 2015 ዓ.ም የዓለም የነፃነት ይዞታ ለአሥረኛ ተከታታይ ዓመት እያሽቆለቆለ የመጣበት ዓመት እንደነበረ አስታውቋል፡፡
የፍሪደም ሃውስን ሪፖርት ለማግኘት ይኽንን ይጫኑና ይከተሉ፤ የሂዩማን ራይትስ ዋችን ሪፖርት ለማግኘት ይኽንን ይጫኑ

ኮንሶ በተነሳው ተቃውሞ በርካታ ሰዎች ለእስር መዳረጋቸው ተነገረ


የኮንሶ ህዝብ ራሱን ችሎ በዞን እንዲተዳደር ያቀረበው ጥያቄ ተከትሎ በተነሳው ተቃውሞ በርካታ ሰዎች ለእስር ከተዳረጉ በሁዋላ አሁንም አካባቢው በልዩ ሃይል ፖሊሶች እንደተከበበ መሆኑን ነዋሪዎች ከስፍራው ገልጸዋል። የልዩ ሃይል አባላት ከጥያቄው ጀርባ አርበኞች ግንቦት7ቶች አሉበት በማለት ቅስቀሳ ሲያደርጉ እንደነበር የገለጹት ነዋሪዎች፣ አሁን ደግሞ ” ጥያቄው የእኛ አይደለም” ብላችሁ ፈርሙ በማለት በግድ ለማስፈረም ሙከራ እያደረጉ ነው። የልዩ ሃይል አባላትና የወረዳው ሹሞች መግባባት አለመቻላቸውን፣ አስተዳዳሪዎቹ ጥያቄው የህዝብ ነው የሚል አቋም በማራመዳቸው አንዳንዶች ከሃላፊነት እንዲነሱ ተደርጓል። የህዝቡን ጥያቄ አቅጣጫ ለማስለወጥ ሆን ብለው በማቀነባበር ቡርጂዎች ግጭት እንዲቀሰቀስ ለማድርግ የተሞከረ ቢሆንም፣ በሁለቱም ወገን የሚገኙ ነዋሪዎች ይህ ሆን ተብሎ ግጭት ለመፍጠር የተቀነባበረ ነው በማለት ወደ ግጭት አለመግባቱን ነዋሪዎች ተናግረዋል። ከቡርጅና ከኮንሶ የሆኑ 2 ሰዎች መገደላቸውን፣ ግድያው የተፈጸመው ሆን ተብሎ ግጭት ለመቀስቀስ ታስቦ መሆኑን ነዋሪዎች ገልጸዋል፤ ግድያውን የልዩ ሃይሎች እንዳቀነባበሩት ሲታወቅ ግን ህዝቡ ወደ ግጭት አለመግባቱን ነዋሪዎች አክለው ተናግረዋል። የኮንሶ አገር ሽማግሌዎች ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያምን ለማነጋገር ወደ አዲስ አበባ መሄዳቸውና ለዛሬ ቀጠሮ ተይዞላቸው እንደነበር ቢታወቅም፣ ስለተሰጣቸው ምላሽ ይህን ዜና እስካቀናበርንበት ሰአት ድረስ ለማወቅ አልቻልም። በአካባቢው አሁንም ትምህርት ቤቶች እንደተዘጉ ነው። አንዳንድ የመንግስት መስሪያቤቶችም አገልግሎት መስጠት አቁመዋል።

ሀዋሳ ከመሬት መንቀጥቀጡ ሳታገግም አፍራሽ ግብረ ኃይል ተልኮ ገበያዋን እየናደው ነው።


በፖሊሶችና በነጋዴዎች መካከልም ግጭት ተቀስቅሶ ብዙ ሰዎች ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን የተወሰኑ ነጋዴዎችም ታፍሰው ታስረዋል።
ከሰሞኑ በርዕደ መሬት ለአምስት ጊዜ ያህል የተመታችው ሀዋሳ ከተማ ከአስደንጋጩ ሁኔታ ሳታገግም ሰፊው ገበያዋ ደግሞ በአፍራሽ ግብረ ኃይል መናድ ጀምሮዋል።
አረብ ሰፈር በተለምዶ አሮጌ ገበያ የሚባለው ቦታ ላይ ለረጅም አመታት እየነገዱ ራስቸውንና ቤተሰባቸውን ያስተዳድሩ የነበሩ ከ200 በላይ የሚሆኑ ነጋዴዎች የንግድ ቦታቸው ከትላንትና አመሻሽ ጀምሮ በዛሬው እለት ቀጥሎ እንዳልነበር ሆኖ ወዳድሞዋል።
ለማፍረስ እንደ ምክንያት የሚጠቅሱት ሌላምግዜ እንደሚሉት የከተማ ወበትና ህገወጥ የቤቶች ግንባታ ነው ነጋዴዎቹና አገልግሎት ሰጨዎቹ በሸራ በብረትና በጣውላየከለሉዋቸውን ቦታዎች መጠቀም ላልቻሉ እቃዎቻቸውበዝናብና በጸሃይ በመጎዳት ይበላሽባቸዋል በዚህም ምክኒያት እጅግ የከፋ ኪሳራና ጉዳት ደርሶባቸዋል ። ነጋዴዎቹ ሙሉ በሙሉ የቫትና ቲኦቲ ህጋዊ ግብር ከፋዮች ናቸው።
በገበያው በጣም ውጥረት ነግሷል ዳሶቹን የማፍረስ ስራው ዛሬም ተጠናክሮ ቀጥሏል በነጋዴዎቹናበፖሊሶች መሃል ግጭት ተነስቶ ብዙ ሰዎች ተጎደተዋልተቃውሞ ለማሰነሳት የሞከሩትን ሰዎች ሱቃቸውን በማሸግወደ ፖሊስ ጣቢያ አግዘዋቸዋል በመሃል መሰረቱ የተናጋ አንድ
ቤት ተደርምሶ በ አንድ ባጃጅና አንደ ሰው ላይ ከፈተኛ ጉዳትደርሷል የአካባቢው ገጽታ ሙሉ በሙሉ ማለት ይቻላልተቀይሯል በተፈጠረው ግር ግር የንግድ አገልግሎቱ ለግዜው
ተቋርጧል ።ም
Daniel Feyssa's photo.Daniel Feyssa's photo.

መንግስት በረሃቡ ላይ የያዘው አቋም የአለማቀፍ መንግስታት ተወካዮችን ግራ እያጋባ ነው


ኢሳት ዜና :- በያዝነው ፈረንጆች አመት ከ15 ሚሊዮን በላይ የሚሆን ህዝብ ለርሃብ የተጋለጠ መሆኑ እየታወቀ በመንግስት በኩል ሁሉም ነገር በቁጥጥር ስር እንደዋለ ተደርጎ የሚሰጠው መግለጫ በለጋሽ አገራት ዘንድ ብዥታ መፍጠሩን የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት ተናግረዋል።
ስማቸው እንደይገለጽ የገለጹ የዲፕሎማቲክ ምንጮች እንዳሉት በኢትዮጵያ የተከሰተው ድርቅ የሚሊዮኖችን ህይወት አደጋ ላይ መጣሉ በገሃድ እየታየ ቢሆንም፣ መንግስት ችግሩን አደባባይ በማውጣት በማሳወቅ እርዳታ ፈጥኖ የሚደርስበትን መንገድ ከመፈለግ ይልቅ፣ ችግሩ በቁጥጥር ስር ውሎአል፣ በቂ እርዳታ አለ በሚል የሚሰጠው መግለጫ፣ በለጋሽ አገራት ዘንድ ብዥታን ፈጥሮአል።
ለጋሽ አገራት እርዳታ ለመስጠት ዝግጁ ቢሆኑም፣ መንግስት ከአለማቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች ጋር በመተባበር የእርዳታ ጥያቄው አፋጣኝ መልስ እንዲያገኝ ጥረት ከማድረግ ይልቅ፣ ስምምነት የተደረገባቸውን ነጥቦች ሳይቀር በመጣስ በመገናኛ ብዙሃን በመቅረብ ሁሉም ነገር የተስተካከለ እንደሆነ የሚሰጠው መግለጫ፣ ብዥታን እየፈጠረ ነው። ባለፉት 10 አመታት ስለኢትዮጵያ የተነገረው አወንታዊ ዜና፣ ለጋሽ አገራት ኢትዮጵያ በራሱዋ ችግሩን ትወጣዋለች የሚል እምነት እንዲያሳድሩ እንዳደረጋቸውና ለጋሽ አገራቱን ማሳመን ቀላል ስራ አለመሆኑን በማወቅ መንግስት አደጋውን በግልጽ በመናገርና የውጭ የመገናኛ ብዙሃን ገብተው እንዲዘግቡ በማድረግ እርዳታ የሚገኝበትን መንገድ እንዲያፈላልግ መክረዋል።
አሁን የተያዘው አቋም የ15 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያንን ህይወት አደጋ ላይ የሚጥለው ይሆናል ሲሉም አስጠንቅቀዋል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ በድርቁ ሳቢያ ከ3 ሚሊዮን በላይ ህጻናት ትምህርት ማቋረጣቸው ታውቋል። አብዛኞቹ ተማሪዎች በውሃ እጥረት ሳቢያ ለማቋረጥ መገደዳቸውንና ድርቅ በተከሰተባቸው አካባቢዎች ያሉ መምህራን ትምህርት ቤቶችን ዘግተው ወደ ሌሎች አካባቢዎች ሄደዋል።

Tuesday, January 26, 2016

‹‹የትም ብሆን ስለመብቴና ሀገሬ ያገባኛል›› እስክንድር ነጋ


(ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በነገው ዕለት ለዘላለም ወርቃገኘሁ መከላከያ ምስክር ሆኖ ልደታ ፍርድ ቤት ይቀርባል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ይህን በማስመልከት ህዳር 19/2007 ዓ.ም ለ10 ደቂቃዎች ያህል እስክንድርን ቃሊቲ ስናገኘው የተናገረውን በሚመለከት ከተጻፈው ለማስታወስ….)
በላይ ማናዬ
‹‹መብቴን አሳልፌ አልሰጥም፤ የትም ብሆን ስለመብቴና ሀገሬ ያገባኛል፡፡ እዚህ ከሚጠይቁኝ ሰዎች ጋር የፈለኩትን ማውራት እችላለሁ፡፡ እናንተ ከፈለጋችሁ በር ላይ መልሷቸው እንጂ እኔ ጋር ከመጡ በኋላ ስለሀገሬ ከእነሱ ጋር መነጋገር መብቴ ነው፡፡ አዎ የትም ቦታ ብሆን፣ መቼም ቢሆን ስለ ሀገሬ ያገባኛል!››
ይህን ያለው ትንታጉ ጋዜጠኛና የፖለቲካ ተንታኝ እስክንድር ነጋ ነው፡፡ እስክንድር ነጋን ካወኩት ወዲህ እንደዛሬ በኃይለ ቃል ሲናገር ሰምቼው አላውቅም፤ ወይም ትዝ አይለኝም፡፡ ህዳር 19/2007 ዓ.ም እኩለ ቀን ላይ እስክንድርን ልጠይቀው ቃሊቲ ተገኝቼ ነበር፡፡ ሆኖም ሁኔታው ሁሉ እንደማንኛውም ቀን አልነበረም፡፡ በር ላይ ስደርስ በርከት ያሉ የአንድነት ፓርቲ አባላት ሰሞኑን እያካሄዱት ያለውን የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ በማስመልከት እስክንድር ነጋን፣ አንዱዓለም አራጌን እና ሌሎችንም ሊጠይቁ በቦታው ተገኝተው ነበር፡፡
በጠዋት ቂሊንጦ የሚገኙ ወዳጆቼን ጠይቄ አብረውኝ ከነበሩ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ጋር ነበር ወደ ቃሊቲ ያመራሁት፡፡ ቃሊቲ የተገኘው ሰው ሁሉ መጠየቅ የሚፈልገውን ሰው እና ሙሉ አድራሻውን እያስመዘገበ ሳለ በመሐል እኔም እስክንድርን መጠየቅ እንደምፈልግ ነግሬ ተመዘገብኩ፡፡ ከትንሽ ቆይታ በኋላ ግን ስማችሁ ከዚህ ቀደም ያልተመዘገባችሁ አሁን መግባት አትችሉም መባሉን መዝጋቢ ፖሊሱ አረዳን፡፡ እኔ እና ትንሽ ሰዎች መግባት ስንችል አብዛኛው ሰው ግን መግባት እንደማይችል ተነገረን፡፡
በዚህ ሁኔታ እስክንድር ጋር ደርሰን ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላ አንድ የአንድነት ፓርቲ አባል ሰሞኑን ፓርቲያቸው እስረኞችን በተመለከተ በማህበራዊ ድረ ገጽ ላይ እየተሰራ ያለውን ስራ ለእስክንድር ያብራራለት ጀመር፡፡ እስክንድር በተለመደ ጥሞናው ሲያዳምጠው ቆይቶ፣ በግሉ የተሰማውን እና መሆን ቢችል ያለውን ነጥብ ተናገረ፡፡ በመሐል ወጣቱ የአንድነት አባል ወደ እስክንድር ጠጋ ብሎ ሌሎች ተጨማሪ ጉዳዮችን ሲነግረው ድንገት አንድ የፖሊስ አዛዥ ጨዋታቸውን እንዲያቆሙና እስክንድር ወደ እስር ቤቱ እንዲገባ፣ ወጣቱ የአንድነት አባል ደግሞ ወደ ውጪ እንዲወጣ በትዕዛዝ ማጣደፍ ያዘ፡፡
ይህኔ እስክንድር ለስለስ ባለ አነጋገር ምንም እንዳላጠፋን በመግለጽ ፖሊሱ መረጋጋት እንዳለበት አስረዳ፡፡ የፖሊስ አዛዡ ግን ጭራሽ ብሶበት ወጣቱ በቶሎ እንዲወጣ አደረገ፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ‹ፖለቲካ ማውራት አቁሙ› የሚል ሆነ፡፡ ይህን ተከትሎ እስክንድር ድንገት በኃይለ ቃል ተናገረ፡፡ ‹‹መብቴን አሳልፌ አልሰጥም፤ የትም ብሆን ስለመብቴና ሀገሬ ያገባኛል፡፡ እዚህ ከሚጠይቁኝ ሰዎች ጋር የፈለኩትን ማውራት እችላለሁ፡፡ እናንተ ከፈለጋችሁ በር ላይ መልሷቸው እንጂ እኔ ጋር ከመጡ በኋላ ስለሀገሬ ከእነሱ ጋር መነጋገር መብቴ ነው፡፡ አዎ የትም ቦታ ብሆን፣ መቼም ቢሆን ስለ ሀገሬ ያገባኛል! የማወራው ስለ ሰላማዊ ትግል፣ ስለህጋዊ ትግል ነው!›› አለ እስክንድር በስሜት ውስጥ ሆኖ፡፡
በግሌ እስክንድር እንዲረጋጋ፣ ሁኔታው ግን ያልተገባ እንደሆነ ገለጽኩ፡፡ ፖሊሱ ግን ሊረጋጋ አልቻለም፡፡ እስክንድርን ይዞት ሄደ፡፡ ‹‹በርቱ! እንቅስቃሴያችሁ ህጋዊና ሰላማዊ ይሁን እንጂ ትግላችሁን ቀጥሉ!›› ሲል እስክንድር ወደ እስር ቤቱ እየገባ ተናገረ፡፡ የፖሊስ አዛዡም ከእስክንድር ጋር የነበረንን ቆይታ ሰዓቱ ሳይደርስ ገታው፡፡ የእስክንድር ያገባኛል ባይነት አስደመመኝ፡፡ እስር ቤት ሆኖም፣ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆኖም እስክንድር ስለ ሀገሩ እንደሚያገባው በስሜት ተናገረ፡፡ መብቱን መቼም ቢሆን አሳልፎ እንደማይሰጥ አስረገጠ፡፡
ስለ ያገባኛል ባይነት ሳስብ በጠዋት ቂሊንጦ ያገኘኋቸውን የዞን 9 ጦማሪዎች አስታወስኩ፡፡ ‹ስለሚያገባን እንጦምራለን!› ይላሉ ወጣቶቹ ጦማሪያን፡፡ ከአብርሃ ደስታ ጋር አብረው ያገኘኋቸው እነ በፍቃዱ ኃይሉ እና አጥናፍ ብርሃኔ ብዙ ጉዳዮችን እያነሱ አወጉኝ፡፡ ‹‹ህወሓት አንድ ወይም ሁለት ነባር የህወሓት ባለስልጣናትን በሽብር ከከሰሰ ስርዓቱ እንዳበቃለት እቆጥራለሁ፡፡ ምክንያቱም ሽብር ማታለያ መሆኑ ይቀራል›› አለኝ በፍቃዱ ኃይሉ፡፡ አብርሃ ደስታ ቀበል አድርጎ ‹‹እናት አልጋነሽ በሽብር ስትከሰስ በጣም ብዙ ሰው ተቃውሞ ነበር›› አለ፡፡ አጥናፍ በበኩሉ ‹‹ቄስና ሸህ ሽብርተኛ እየተባለ አይደለም እንዴ›› በማለት ጠየቀ፡፡
አብርሃ ደስታ አንድ ነገር በኃይል እንደሚቆጨው ተናገረ፡፡ ምን እንደሆነ ጠየቅሁት፡፡ ‹‹ብዙ የሰላማዊ ትግል እንቅስቃሴ ሳላደርግ መታሰሬ ይቆጨኛል!›› አለ፡፡ በፍቃዱ በበኩሉ፣ ‹‹እኔም የገባኝ ነገር ያለውን የሰላማዊና ህጋዊ የመስሪያ ልክ አለመስራታችን ነው፡፡ አሁን ላይ ሆኜ ሳስበው እንዲህ ለሚያስሩን ስንት ህጋዊና ሰላማዊ እንቅስቃሴዎችን እንኳ ሳናደርግ በትንሽ ነገር በርግገው እዚህ ሲያስገቡን ይቆጨኛል›› በማለት ሀሳቡን ቀጠለ፡፡ ‹‹በእርግጥ አንድ ሰው አሁን መጠንቀቅ ያለበት የሚሰራው ስራ ህጋዊ መሆን አለመሆኑን እንጂ፣ ይህን ካደረኩማ ያስሩኛል የሚለውን መሆን የለበትም፡፡ እነሱ ከፈለጉ ያስሩሃል፤ ስለዚህ መብትህን ተጠቅመህ መታሰሩ ይሻላል እንዲሁ ምንም ሳይሰሩ ከመግባት›› ሲል አብርሃ ሀሳቡን አካፈለ፡፡
ቂሊንጦ ከእነ በፍቃዱ ጋር ስንጨዋወት ስለእስክንድር ነጋ ትሁትነት፣ አስተዋይነት፣ ሰላማዊነት እያነሱ ሰላምታ እንዳደርስላቸው ጠየቁኝ፡፡ እኔም እስክንድር ነጋን ሳውቀው በትሁትነቱ፣ በአስተዋይነቱና በሰላማዊነቱ ነው፡፡ ዛሬ በነበረው ሁኔታ ግን ክፉኛ ተበሳጭቶ ነበር የተመለከትኩት፡፡ ያ ፈገግታው ከፊቱ ብን ብሎ ጠፍቶ ‹‹ያገባኛል!›› ሲልበት የነበረውን ስሜት ግር አለኝ፡፡ ካልነኩት የማይነካ ሰው ሲነኩት ትንታግ ነው፡፡ እስክንድር እዛ ስሜት ውስጥ የገባው ተገድዶ ነበር፡፡ ሊጠይቁት የመጡትን ሰዎች አብዛኞቹን አላስገባም ማለታቸው ሳያንስ ከገቡትም መካከል የምታወራውን እኔ ልምረጥልህ በሚል ግብዝነት አባርረዋል፡፡ እስክንድር ይህን አይቶ ዝም ማለት አልቻለም፡፡ ስለሆነም እንዲህ አለ፤ ‹‹…እዚህ ከሚጠይቁኝ ሰዎች ጋር የፈለኩትን ማውራት እችላለሁ፡፡ እናንተ ከፈለጋችሁ በር ላይ መልሷቸው እንጂ እኔ ጋር ከመጡ በኋላ ስለሀገሬ ከእነሱ ጋር መነጋገር መብቴ ነው፡፡ አዎ የትም ቦታ ብሆን፣ መቼም ቢሆን ስለ ሀገሬ ያገባኛል! የማወራው ስለ ሰላማዊ ትግል፣ ስለህጋዊ ትግል ነው! ስለሀገሬ ያገባኛል!››
Belay Manaye's photo.

ቱኒዚያ ተቃውሞ ቀጥሎ ሁለት መቶ ስልሳ ሰዎች ታሠሩ ::


ቱኒዝያ ለአራት ቀናት በዘለቀው ሀገር አቀፍ ብጥብጥ ተጠያቂ ናቸው ያለቻቸውን ሁለት መቶ ስልሳ ሰዎች ማሠሯን አስታወቀች። እስረኞቹ በአመጽ ድርጊት እና ነውጥ በመቀስቀስ እንደሚከሰሱ ሼምስ ኤፍ ኤም የተሰኘ የሀገሪቱ ሬዲዮ ዘግቧል። በቱኒዝያ ያለው የኢኮኖሚ ሁኔታ እና የሥራ አጥነት መባባስ በመላ ሀገሪቱ ለተቀሰቀሰው ተቃውሞ ሰበብ እንደሆነ ተነግሯል።
የቱኒዝያ መንግሥት ትናንት ከምሽቱ 2 ሰዓት እስከ ንጋቱ 11 ሰዓት የሚዘልቅ የሰአት እላፊ አዋጅ ደንግጓል። የሰዓት እላፊው ከተደነገገ በኃላ በቱኒዝያ አንዳንድ ከተሞች ትናንት ማምሻውን ብጥብጥ መከሰቱ ተዘግቧል። በበርካታ ከተሞች ቱኒዝያውያን አደባባይ በመውጣት የፖሊስ ጣቢያዎችን ማጥቃታቸው ፣ የፖሊስ ተሽከርካሪዎችንም በእሳት መለኮሳቸው ተገልጿል።
የቱኒዝያ ጠቅላይ ሚንሥቴር ሐቢብ ኤሲድ የሀገሪቱ ዲሞክራሲ «ምንም ያስከፍል ምንም» እንደተጠበቀ ይቆያል ሲሉ ተናግረዋል። በቱኒዝያ የተቀጣጠለው ተቃውሞ ከመዲናይቱ ቱኒስ አንስቶ በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች የተስፋፋ መሆኑም ተገልጻል።
Yesuf Brhan's photo.

የከሸፈው ዲፕሎማሲያችን፤ ከጠረፍ እስከ ከተማው!


በሳውዲ የመን የሚገኙ የሳውዲ ከተሞችን በስራ ጉዳይ ተዘዋውሮ የማየት እድል አጋጥሞኛል ። በተዘዋወርኩባቸው አጋጣሚዎች ቁጥራቸው በርከት ያሉ በህገ ወጥ ድንበር ሰብረው የገቡና በህጋዊው መንገድ ወደ ሳውዲ ገብተው በዚያው የከተሙ ቁጥራቸው ከፍ ያለ ኢትዮጵያውያን ወገኖቸን አግኝቼ ሳውዲ ስላደረሳቸው መንገድ ብዙ አውግተናል ። በተለይ በሕገ ወጡ የየመን ድንበር መጥተው በእረኝነትና በጉልበት ስራ ተሰማርተው የሚሰሩ ወንድሞቸን አግኝቼ በየመን ድንበር ሽግግር ስለሚያጋጥማቸው ክልትም ፣ በድለላ ስራ ላይ በናጠጡ የራሳችን ዜጎች ከአረብ አሸጋጋሪዎች ጀምሮ እስከ ከተማ ህግ አስጠባቂ ነን ባዮች ደርሶባችው ያሳለፉትን ሰቆቃ የተጎዳ ብልት ገላቸውን ሳይቀር እያሳዩ ሲናገሩት አድምጫለሁ ።
በየመን ድንበር ከባቢ በአሸጋጋሪዎች ከሚሰሩት ያልተነገሩ ወንጀሎች ተጠቂዎች የተሻለ ኑሮ ፍለጋ በሉት ከድህነት ፣ ኑሮ ውድነት ሸሽተው ወደ ሳውዲ የሚመጡት እህቶች ይገኙበታል ። በሴቶች ላይ የሚፈጸመው ግፍ ደግሞ በአይነቱ ለየት ያለና ሰቅጣጭ ነው ። እኒህ መከረኛ ኢትዮጵያውያት ተበድረውና ተቀድመው የየመን ሳውዲን ድንበር ለመሻገር ሲሞክሩ የአደንዛዥ እጽ ነጋዴዎች ማሸጋገሪያነት ኢላማ የወደቁ አውቃለሁ ። ጥቂት የማይባሉት እኒህ ወገኖች በወንጀል ተከሰውና ተፈርዶባቸው ለአመታት ኑሯቸውን በሳውዲ እስር ቤት ማድረጋቸው በገሃድ የማይበገር የ ኢትዮጵያውያን በሳውዲ ያልተነገረ ህይዎት ነው ። ይህ መሰሉን እውነት የምናገረው ከጉዳዩ ባለቤት ተገፊዎች ተደጋግሞ የምሰማው አቤቱታ ነው ። ድንበሩ ቀርቶ በመሐል ከተማው ፣ የመብት ገፈፋ የደረሰባቸውን ዜጎች በቆንስልና ኤምባሲው በር ላይ መጥተው ሲወድቁ በአግባቡ አይስተናገዱም ። … በየጉራንጉሩ በዜጎች ላይ ለሚደርሰው በደል ጠያቂ አጥተናል ። ጀሯችን ለማድመጥ አይናችን ለማየት ፤ እግራችን ለመሄድ ከቻለ እዚህም እዚያም በርካታ ልንናገረው የሚከብደውን መረጃ እንሰማለን ፤ እናያለን !ግን ለማን አቤት ይባላል ?… በምዕራብ ሳውዲ የተለያዩ እስር ቤቶች የሚገኙ ከ350 በላይ ከሚገመቱት እስረኞ መካከል የተወሰኑትን በተደጋጋሚ አግኝቻቸው የመንግስት ተወካዮቻችን ለአመታት በእስር ሲማቅቁ አንድም ቀን ጎብኝተዋቸው እንደማያውቁ አጫውተውኛል እንባ እያዘሩ አጫውተውኝ ያውቃሉ…
ያገባኛል ፣ ያስተምራልና ስለማውቀው የስደተኛ ህይዎት እውነተኛ ገጽታ አመሰክራለሁ ! የቀለም ቀንድ ጋዜጣ ዘወትር ማክሰኞ በሐገር ቤት የሚታተም ጋዜጣ ነው ። በዛሬው እትሙ የእኔን ማስታወሻና ሌሎች ዳጎስ ደጎስ ያሉ መረጃዎችን ይዟል ! ” ያነበበ ተጠቀም ” የቀለም ቀንድን ያንብቡ !
መልካም ቀን !
ነቢዩ ሲራክ

Monday, January 25, 2016

ሰበር መረጃ -የወያኔ ወታደራዊ ደህንነት ቢሮ የነፃነት አይሎች እንቅስቃሴ እንዳሳሰበው ገለፀ


የትግራይ ነጻ አዉጭ ቡድን ወታደራዊ ደህንነት ቢሮ በአርበኞች ግንቦት 7 እና በኦነግ ( በኦሮሞ ነጻነት ግንባር ) በተለይም በጥምር ሐይሉ ( ሐገር አድን የነጻነት ሐይሎች ) መካከል ከፍተኛ የሆነ ስምምነት ተደርሷል ዉህደትም ከተፈጸመ ቆይቷል ነገር ግን ይፋ ሳይደረግ ታፍኗል ሰራዊቱ በአንድነት ሆኖ የጀመረዉ ጉዞ በመላዉ ሔገሪቷ ላይ የበላይነትን እንዲቆናጠጡ እያደረጋቸዉ ነዉ በአስቸኳይ ወደ አንዳች ለዉጥ አምጪ የሐይል እርምጃ መሸጋገር እና ህዝብን በፕሮፓጋንዳ የማነጽ ስራ ካልተደረገ የዉድቀት ኪሳራዉ ወደእኛ በብርቱ ያደላ ነዉ በማለት በድጋሚ የመጨረሻዉን ደዉል አንቧርቋል፡
በተለያየ የሰሜን ጎንደር ቦርደር ግዛቶች ተደጋጋሚ ሽንፈትን እየተጎነጨ የሚገኘዉ የወያኔ ሰራዊት በምስራቅ ኢትዮጵያ በኩልም ተመሳሳይ ጽዋዎችን እየተጎነጨ ሲሆንበሞያሌ በኩል ወደ ኬንያ ከድተዉ በመግባት ጥገኝነት የጠየቁ ጥቂት የፖሊስ ሰራዊትን አሳልፎ የሰጠዉን የኬንያ ወታደር ላይ ቂም የያዙ የአካባቢዉ ነዋሪዎች እና የነጻነት ሐይሎች የኬንያ እና የወያኔ መከላከያ ተብዬዎች ላይ በወሰደት እርምጃ ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ ኬንያዎች እንዲፈረጥጡ ሲገደዱ የወያኔ ሰራዊት ደግሞ ለምርኮ ተዳርጓል።
አርበኞች ግንቦት 7 የጎሬላ ዉጊያዉን በማቀላጠፍ ግራ በሚያጋባ ሁኔታ ወያኔን መድረሻ እያሳጣዉ ሲሆን ትህዴን ( የትግራይ ህዝቦች ዲሞክራሲያ ዊንቅናቄ ) በተመሳሳይ የጎሬላ ዉጊያዉን በማቀላጠፍ ላይ ይገኛል በመሆኑም በትግራይ ግንባር ወረዳዎችና መሐል አካባቢዎች ከፍተኛ የሆነ የፕሮፓጋንዳና ቅስቀሳ ስራዎችን እያካሄደ የሚገኘዉ ትህዴን በየእለቱ እየተጠናከረ መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል።
በጋንቤላ በኩል እየተንቀሳቀሰ የሚገኘዉ የነጻነት ሐይልም ከምን ግዜዉም በላይ ተጠናክሮ የሽምቅ ዉጊያዉን በአዝማችነት በዚያዉ ክንፍ እየመራዉ ሲሆን በየአቅጣጫዉ አጣብቂኝ ዉስጥ የገባዉ የትግራዩ ነጻ አዉጭ ቡድን ወያኔ ሰራዊቱን በማሰባጠር በኩል አጣብቂኝ ዉስጥ መግባቱን የሚያሳዩ እዉነታዎች ግልጽ እየታዩ ነዉ የወያኔ መከላከያ ከመሐል ሐገር የተቀጣጠለውን ህዝባዊ አመጽ ለማፈን! እና ባለሳልጣናትን ለመጠበቅ እንዲሁም በተለያየ ዉጥረት ላይ ይገኛል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ! !
ጉድሽ ወያኔ
Gudish Weyane's photo.

የሰማያዊ ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ከህገ-ወጥ ተግባሩ እንዲታቀብ ማስጠንቀቂያ ተሰጠው


“ኮረም ሳይሞላ የተወሰነ ውሳኔ ስለሆነ ህገ ወጥነቱን ተቃውመናል” ኢ/ር ይልቃል

የሰማያዊ ፓርቲ ኦዲትና ምርመራ ኮሚሽን፤ የፓርቲው ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ከሥልጣኑ ውጭ በመሄድ ከሚፈጽመው ህገ-ወጥ ተግባር እንዲታቀብ አስጠነቀቀ፡፡ “የፓርቲው የስነ-ስርዓት ኮሚቴ በምክር ቤት አባላቱ ላይ ያስተላለፈው ውሳኔ ኮረም ያልተሟላበት ስለሆነ የስራ አስፈፃሚው ህገወጥነቱን ተቃውሟል” ብለዋል – የፓርቲው ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት፡፡
የሰማያዊ ኦዲትና ምርመራ ኮሚሽን ትላንት ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንዳመለከተው፤ ከጠቅላላ ጉባኤው ቀጥሎ ከፍተኛ ስልጣን ያለው ብሄራዊ ምክር ቤቱ፤ ከፓርቲው ህግና ደንብ ውጭ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ከፋፋይና በህዝቡ መካከል ጥላቻን የሚፈጥር ፅሁፍ አሰራጭተዋል ባላቸው 4 አባላት ላይ ክስ መስርቶ፣ የስነ ሥርዓት ኮሚቴው ጉዳዩን ከመረመረ በኋላ አባላቱ እንዲባረሩ መወሰኑን አስታውሶ፤ ሥራ አስፈፃሚው ከተሰጠው ስልጣን ውጭ  ውሳኔውን አልቀበልም ማለቱ ህገወጥነት ነው ብሏል፡፡
ኦዲትና ምርመራ ኮሚሽኑ፤ አንደኛው ተሰናባች አቶ ዮናታን ተስፋዬ አሁን ባለበት ሁኔታ ራሱን መከላከልም ሆነ ይግባኝ መጠየቅ ስለማይችል በሱ ላይ የተላለፈውን ውሳኔ እየመረመረ መሆኑን አስታውቋል፡፡
በጉዳዩ ላይ አስተያየት የጠየቅናቸው የፓርቲው ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት በበኩላቸው፤ “ስራ አስፈፃሚው፤ ችግር ሲፈጠር ለኦዲትና ምርመራ ኮሚሽኑ ይግባኝ አይባልም ወይም የስነ-ስርዓት ኮሚቴው የመወሰን መብት የለውም አላለም፤ ውሳኔው መተላለፍ ያለበት የስነ-ስርዓት ኮሚቴው ምዕላተ ድምፅ ሲሞላ ነው፤ ሆኖም ባልተሟላ ድምፅ ውሳኔው በመተላለፉ ህገወጥነቱን ተቃውመናል” ብለዋል፡፡ በፓርቲው ህግና ደንብ መሰረት ውሳኔ ለማስተላለፍ ምዕላተ ድምፁ 50 + 1 መሆን እንዳለበት ያብራሩት ኢ/ሩ፤ በምክር ቤት አባላቱ ላይ ውሳኔ ያስተላለፉት ከሰባቱ የስነ-ሥርዓት ኮሚቴ አባላት ሶስቱ ብቻ እንደነበሩና አንደኛው አባል በሂደቱም በፊርማውም እንዳልተሳተፈ ምስክርነቱን ሰጥቷል ይላሉ፡፡ “እኛ ተቃውሞ ያነሳነው ውሳኔ ባገኘ ጉዳይ ላይ እንጂ ገና በእንጥልጥል ላይ ባለ ጉዳይ ባለመሆኑ ህጉን ተከትለን እየሰራን ለመሆናችንን ማሳያ ነው” ሲሉም ኢ/ር ይልቃል – ተሟግተዋል፡፡ የፓርቲው የስነ-ስርዓት ኮሚቴው በአባላቱ ላይ ውሳኔ ሲያስተላልፍ ኮረም መሙላት አለመሙላቱን በተመለከተ የጠየቅናቸው የኮሚቴው ሰብሳቢ ወ/ሮ ሀና ዋለልኝ፤ በውሳኔው ላይ ከሰባቱ የኮሚቴ አባላት አራቱ መገኘታቸውንና አራቱም በውሳኔው መስማማታቸውን ገልፀው፣ ውሳኔው ከተላለፈ በኋላ ሲሳይ ካሴ የተባሉት አባል ከውሳኔው ማፈንገጣቸውን እንዲሁም ውሳኔውን መካዳቸውን ጠቁመዋል፡፡ “ያም ሆነ ይህ ውሳኔው ሲተላለፍ ከሰባት አባላት አራቱ መገኘታቸው ኮረም እንደሞላ ያሳያል” ያሉት ሰብሳቢዋ፤ አቶ ሲሳይ ካሴ ውሳኔውን ቢክዱም ሶስታችን በመስማማታችን ኮረም አልሞላም መባሉ አግባብ አይደለም ሲሉ አስተባብለዋል፡፡ addisadmas

ሕውሓት ይችን መልክዓ ምድር ከጎንደሬዎች ቀምቶ ወደትግራይ ለመጠቅለል እጅግ ዘርፈ ብዙ በደል በሰሜን ጎነደር ኗሪዎች ላይ ፈፅሟል።


ከሰሜን አውራጃ ተከዜን ተሻግሮ ፀለምትን እስከ አዳርቃይ የአርማደጋን ዋልድባን ጨምሮ በወረራ ይዞ ይገኛል በዛ የነበሩትን ታሪካዊ ነገሮች እያጠፋ የጎጥ ሥሞችን ሁሉ በትግርኛ አጠራር በመቀየር ላይ ሲሆን ።
በወገራ አውራጃ ላይ የወረረው መሬት ለትግራይ ክልል አንድ ዞን አስገኝቶላታል ።
የትግራይ መስተዳድር ይህን ከወገራ አውራጃ ሰዎችን አፈናቅሎ በያዘው ምድር ላይ ከመሀል ትግራይ የመጡ ሰዎችን ባንዴ ብቻ ከግማሽ ሚሊየን በላይ አስፍሮበታል የአርማጭሆን ድንግል ጫካ መዘጋ መንጥሮ የሽመል መብቀያ የነበረውን ወደምድረ በዳነት ቀይሮታል ይህ ምድር እጅግ መጠነ ሰፊ ነው ብዙ የወረዳ መስተዳድሮች ወጠውታል ፣የሰቲት ሁመራን ለምና ድንግል መሬት ለራሱ የትግራይ የግል ንብረት ሁኗል
ይህ የተግራይ ምዕራባዊ ዞን የቅፅል ሥሙም የልማት ኮሪደር ይሉታል ።
እነሱ የባለልማት ኮሪደር ሲፈልጉ የጎንደር ገበሬ የበሬ ግንባር የምታክል መሬት ተሰጥቶት በመኖርና ባለመኖር በድህነት እንዲማቅቅ ሲደረገ ።
ያችውንም ደጋፊ አይደለህም ተብሎ የመነጠቅ ዕድሉም ሰፊ ነው ።
መሬቱን ለጨካባቢው ሰው እንዳይጠቀምበት ተከልሎና ተከልክሎ ለኢንበስተር በሚል ውኃ እየጠጣ ቦዝኖ የሚኖር መሬትም አለ በቋራ በኩል የሚደረገው እንደዚህ ነው ።
ይህ በዚች ፅሁፌ ለመናገር የሞከርኩት የተጋነነ አይደለም በትክክል ራሱ ሕውሓት ማስተባበል የማይችልበት በደሉ ከጠቀስኩት በላይም የከፋና ተዘርዝሮ የማያልቅ ነው ።
በተለይ የጎንደርን ገበሬ በሱዳን ጠረፍ የሕውሓት ጦር ከሱዳን ጦር ጋር በመመሳጠር ለ25 ዓመት ብዙ በደል ተፈፅሟል ።
ከኘገበሬዎቹ ከአካባቢው ለቀው እንዲጠፉ አስቃቂ ግድያና ከነማሳቸው ሰዎች በእሳት እንዲጋዩ የተደረገበት አጋጣሚም በተደጋጋሚ የታየ ነው ።
ሱዳኖች በቀን እንደፈለጉ ማድረግ ሀብት
ከማውደም በላይ ዘረፋም ሲፈፅሙ የሕውሓት ጦር በትዝብት እንዲመመለከትና ። ይህን ግፍ ለመቋቋም የሚደራጁትን ገበሬዎች ጠንካራ ናቸው ተብለው በአካባቢው ሰዎች የሚታወቁትን ።የሕውሓት ጦር ሌሊት ሌሊት በየመኖሪያቸው እየታፈኑ ተወስደው የት እንደደረሱ ያልታወቁት አያሌ ናቨው አንታፈንም ያሉ በቤታቸው ሳሉ የተረሸኑትም ብዙ ናቸው ።
ባለፈው ዓመት እንደተፈፀመው ከሞት ያመለጠው የታች አርማጭሆው ነዋሪ ከመተማ ታፍኖ ወደሁመራ ተወስደው የራሳቸውን ቀብር እንዲቆፍሩ ከተደረገ በኋላ በተዓምር አምልጦ የሰጠው ምስክርነት በቂ መረጃ ነው ።

አዲስ መረጃ የቴዲ አፍሮን አዲስ አልበም በተመለከተ:-


የመጨረሻውን አልበም ካወጣ አራት አመት የሆነው ዝነኛው ቴዲ አፍሮ ቀጣዩን አልበም ኒዮርክ ስትዲዮ ለመስራት ዝግጅቱን ማጠናቀቁ ታወቀ። ቴዲ ከአዲሱ አልበም ውስጥ አምስት ዘፈኖቹን የሚያቀናብርለት ታዋቂውና የሶስት ግራሚ ተሸላሚ የሆነው ዝነኛው አሜሪካዊ አቀናባሪ ጎርደን ዊሊያምስ ነው።አዲስ አበባ ላይ የተጀመሩትን ስራዎቹን ይዞ ወደ ኒዮርክ ያመራው ቴዲ አፍሮ ዘፈኖቹ በጎርደን ስቲዲዮ እንዲቀናበሩለት ስምምነት ላይ ደርሰዋል።በአሁኑ ወቅት ለመድረክ ስራ ካሊፎርኒያ የሚገኘው ቴዲ ስራውን ሲጨርስ ወደ ኒዮርክ በመመለስ እዛው ባለው ግዙፍ ስቲዲዮ ስራውን እንደሚሰራ ታውቃል።ዝነኛው አቀናባሪ ጎርደን ዊልያምስ ከዚህ በፊት ለአሊሺያ ኪስ: ሎሬን ሂል: ካርሎስ ሳንታና: አሚ ዋይንሀውስ እና ለ50 ሴንት ምርጥ ስራዎችን የሰራና ሶስት የግራሚ ሽልማቶችን ያገኘ ትልቅ የሙዚቃ ሰው ነው።በተያያዘ ዜና ቴዲ በአዲሱ አልበሙ ከቦብ ማርሌ ልጅ ዳይመን ማርሊ ጋር በጋራ የሚጫወቱት የሬጌ ስራ እንዳለውም ለማወቅ ተችላል።

Saturday, January 23, 2016

ሰበር ዜና ህወሀት ዳግም ለሁለት ተሰነጠቀ ተባለ።

የ”መቀሌው” እና የ”አዲስ አበባው” ህወሀት ተብለ ጠርዝ ለጠርዝ ሆነው እየተሻኮት ይገኛሉ። ብአዴን ከመቀሌው ህወሀት በኩል የመወገን አዝማሚያ እያሳየ ሲሆን ኦህዴድ እና አሻጉሊቱን ጠ\ሚ ጨምሮ ዴህዴን ከአዲስአበባ ህወሀት ጎን በማሽቃበጥ ላይ ይገኛሉ። አቦይ ስብሃት ሁለቱንም አክራሪ ህወሀቶች ለማስታረቅ እየጣሩ ነው። በትናንትናው እለት የመቀሌው ህወሀት መሪ የሆነውን የትግራይ ክልል መስተዳድር የሆነው አባይ ወልዱን አቦይ ስብሃት ደውለው ማስጠንቀቂያ እንደሰጡት ታማኝ ምንጮች ነግረውናል አቦይ ስብሃት ቃል በቃል በስልክ ለአባይ ወልዱ “አሁን በዚህ ጊዜ ነፍጠኞች (አማራ) እና ጠባቦች (ኦሮሞ) ተባብረው በጋራ እየሰሩ ከአለም መንግስታ ጫና እያስፈጠሩብን ባሉበት ወቅት የእርስ በርስ ውጊያች ውድቀታችንን ያፈጥነዋል” ብለውታል። በተመሳሳይ በመከላከያ ሰራዊት ውስጥም ከፍተኛ ጫና መኖሩን እና ጦሩ አፈ ሙዙን ያዞርብናል የሚል ከፍተኛ ውጥረት መኖሩንም ምንጮቻችን አክልው ነግረውናል። በተያያዘ ዜና በኦሮሚያ የተነሳው የመብት ጥያቄ መቆጣጠር እንደተሳነው የመከላከያ ሰራዊቱ አዛዥ ለበላይ አካላት “አንድ ሰው በገደልን ቁጥር ሌሎች ሺዎች አመፁንን እየተቀላቀሉ ነው። ወታደሩም ወገኖቻችንን አንገልም የሚል አዝማሚያ እያሳየ ነው” ብለው አሳውቀዋል። እንዲሁም በቅርቡ ለሱዳን ሊሰጥ በታሰበው መሬትን ተከትሎ በአማራ ክልል ይቀሰቀሳላ ተብሎ ሚጠበቀው ብረት የቀላቀለ ህዝባዊ ተቃውሞ በወያኔ ቤት ውስጥ ከፍተኛ ፍረሀት መፍጠሩንም ማወቅ ችለናል።

የአለማቀፍ ድርጅቶች በኢትዮጵያ የተከሰተው ረሃብ ከአቅም በላይ ነው ቢሉም መንግስት እያጣጣለው ነው

ኢሳት ዜና :-ሪዩተርስ ዛሬ ባወጣው ዘገባ በኢትዮጵያ አስከፊ በተባለው ረሃብ 400 ሺ ህጻናት ከፍተኛ አደጋ አንዣቦባቸዋል። አንድ አስረኛ የሚሆነው ህዝብ ራሱን መመገብ በማይችልበት ደረጃ መደረሱን ዘጋባው አመልክቶ፣ የአለማቀፉ ማህበረሰብ የሚሰጠው ምላሽ አነስተኛ መሆን ችግሩን አሳሳቢ ደረጃ ላይ አድርሶታል።
በአሜሪካ የህጻናት አድን ድርጅት ፕሬዚዳንት ካሮሊን ማይልስ አፋርና አማራ ክልሎችን መጎብኘታቸውን ለዜና ምንጩ ገልጸው፣ በምግብ እጥረት የተነሳ ሆስፒታል የገቡ ህጻናትን ማየታቸውን ተናግረዋል።
በአማራ አካባቢ አንድ እናት የ3 ወር መንታ ልጆቻቸውን ማጥባት ተስኖአቸው ማየታቸውን የገለጹት ሃላፊዋ፣ መንግስት በየስድስት ሳምንቱ የሚሰጣቸው እርዳታ ለአንድ ሳምንት ብቻ የሚያቆይ መሆኑን ተናግረዋል።እርዳታው በፍጹም ህይወትን ለማቆየት የሚረዳ አይደለም በማለት መንግስት በቂ እርዳታ እየሰጠሁ ነው በማለት የሚሰጠውን መግለጫ አጣጥለውታል።
ረሃቡን ለመቋቋም 1 ቢሊዮን 400 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ቢያስፈልግም፣ የአለማቀፉ የምግብ ፕሮግራም እስካሁን ያገኘው ድጋፍ 13 በመቶውን ብቻ የሚሸፍን ነው። ድርጅቱ ለጋሽ አገራት ገንዘብ በመለገስ ከአገር ውስጥ ገበያ ገዝተው እንዲያከፋፍሉ ለማድረግ ፍላጎት ቢኖርም፣ በቂ ሸመታ ለማካሄድ የሚያስችል የእህል አቅርቦት ባለመኖሩ የምግብ እርዳታ እንዲደረግ እየጠበቁ ነው። እርዳታው አሁኑኑ ካልደረሰ ችግሩ ይባባሳል ሲል የአለም የምግብ ፕሮግራም አስጠንቅቋል።
መንግስት የውጭ ድርጅቶች እርዳታ ለማግኘት ሲሉ ችግሩን አጋነው እያቀረቡት ነው በማለት ወቀሳ ያቀርባል። የመንግስት መግለጫ የአለማቀፍ ማህበረሰቡ አፋጣኝ መለስ እንዳይሰጥ ማድረጉን ታዛቢዎች ይገልጻሉ።

Thursday, January 21, 2016

የአውሮፓ ህብረት ፕሬዘዳንት የኢትዮጵያ መንግሥት የሰብአዊ መብት ረገጣውን ካላቆመ እርዳታ እንዲከለክል የሚያዘውን ሞሽን አፀደቀ።


12509018_1660662390887815_4312725651662447292_n7ቱ ዋና ዋና የአውሮፓ ህብረት የፖለቲካ ድርጅቶች ኢትዮጵያን በተመለከተ የቀረበውን ውሳኔ ሙሉ በሙሉ አጽድቀዋል። አነስተኛ ቁጥር ያላቸው የቀኝ አክራሪዎች ብቻ ውሳኔውን ተቃውመውታል። ለህጉ መጽደቅ ከፍተኛ ትግል ሲያካሂዱ የሰነበቱት የህብረቱ የፓርላማ አባል ሚስ አና ጎሜዝ በውሳኔው መደሰታቸውን ተናግረዋል። “በጣም ጠቃሚ የሆነ ሰነድ ነው፣ በተለይ ዋና ዋና የሚባሉት የፖለቲካ ድርጅቶች የውሳኔው ሰነድ ሳይለወጥ እንዲቀጥል ማድረጋቸው ትልቅ ነገር ነው” ሲሉ አክለዋል። የተላለፈው ውሳኔ ምን ያክል ጠንካራ ነው የተባሉት አና ጎሜዝ፣ በኦሮሞ እና በሌሎችም ኢትዮጵያውያን ላይ የተፈጸመውን ግድያ ያወግዛል፣ እስክንድር ነጋን የመሰሉ ጋዜጠኞች፣ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ጨምሮ ሌሎች ፖለቲከኞችም እንዲፈቱ ይጠይቀዋል ብለዋል። ባለፉት 10 አመታት በኢትዮጵያ ላይ ከተላለፉት ውሳኔዎች ውስጥ የአሁኑ ጠንካራ መሆኑን የገለጹት ሚስ አና ጎሜዝ በተለይ ዋና ዋና የሚባሉት 7ቱ የፖለቲካ ድርጅቶች እንዳለ መቀበላቸው ትልቅ ውጤት ነው ብለዋል። የኢትዮጵያ መንግስት የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የህብረቱ ባለስልጣናትንና አዲስ አበባ የሚገኙ የህብረቱን ተወካዮች ለማግባባት ቢሞክርም፣ የህብረቱ የፓርላማ አባላት ግን አንቀበልም በማለት ማጽደቃቸውን አክለዋል ከዚህ በሁዋላ የአውሮፓ መንግስታት ፣ በ7ቱ ዋና ዋና የፖለቲካ ፓርቲዎች የተደገፈውን የፓርላማ አባላቱን ውሳኔ ሊያጣጥሉት አይተው እንዳላዩ ሊያልፉት አይችሉም” ያሉት አና ጎሜዝ ፣ ይህን ካደረጉ በራሳቸው የፖለቲካ ህይወት ላይ ተጽእኖ እንደሚያመጣባቸው አስረድተዋል ህብረቱ በቅርቡ የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች በኢትዮጵያውያን ላይ የፈጸሙትን ግድያና የሰብአዊ መብት ጥሰት በጽኑ አውግዟል። የ140 ሰዎች ግልጽ፣ ተአማኒ እና ገለልተኛ በሆነ አካል እንዲመረመር ጠይቋል። ጋዜጠኞችና የሰብአዊ መብት ድርጅቶች በነጻ እንዲንቀሳቀሱ ሁኔታዎች እንዲመቻቹም አሳስቧል።ለኢትዮጵያ የሚሰጠው እርዳታ የሰብአዊ መብት ጥሰቱን እንዳያባብሰው፣ ቁጥጥር ሊደረግ ይገባል ብሎአል። በሌላ በኩል ደግሞ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ኤክስፐርቶች የጸጥታ ሃይሎች በንጹሃን ዜጎች ላይ የሚወስዱትን እርምጃ እንዲያቆም ጠይቀዋል። “የተገደለውና የታሰረው ህዝብ ቁጥር መንግስት ህዝቡን እንደ አጋር ሳይሆን እንደእንቅፋት እንደሚያየው” የሚያመለክተው ነው ያሉት ኤስፐርቶች፣ ምንም እንኳ መንግስት እቅዱን መተውን ቢናገርም ግድያው ፣ ማሰሩና ከልክ በላይ ሃይል መጠቀሙ አሁንም አሳስቦናል ብለዋል። የታሰሩት በሙሉ በአስቸኳይ እንዲፈቱ እንዲሁም ድርጊቱን የፈጸሙት የጸጥታ ሃይሎች በገለልተኛ ወገን ተጣርቶ ለፍርድ እንዲቀርቡ ጠይቀዋል

በሳውድ አረቢያ በሂጅራ አቆጣጠር ረቢ አሳኒ 27 1437 አ•ሒ ጀምሮ በአይነቱ ልዩ የሆነ ከበድ ያለ ፍተሻ እንደሚደረግ ታወቀ


በመከ በሪያድ መዲና እና ጀዳ በሚካሄደው ተፍቲሽ ላይ የሳውድ አረቢያ የመከላከያ ሀይል የፖሊስ ሀይል ጀዋዛት የውስጥ ጉዳይ ሚኒስተር ቀይ ጨረቃ እንደሚሳተፉበት ተነግሮዋል
ፍተሻው የሚያተኩረው የኢቃማን ህግ በመጻረር ህጉ በማይፈቅደው የስራ መስክ ላይ በተሰማሩ ማለትም ሳዒቅ ኻስ ሆነው እያሉ አሚልነት የሚሰሩ እንዲሁም ኢቃማቸው የተበለገባቸው እና ኢቃማ በሌላቸው ሰዎች ላይ እንደሆነ ተጨምሮ ተገልጾዋል
ይህ በእንዲህ እንዳለ የመካ ሙከረማ ከተማ ፖሊስ ከረቢዐል አወል ወር መጀመሪያ ጀምሮ በአንድ ወር ግዜ ውስጥ ብቻ 98890 የኢቃማ ህግን የጣሱ እና ኢቃማ የሌላቸውን መጅሁሎች መያዙን አስታውቆዋል
ከተያዙት 98890 ሰዎች መሀከል 388 የስራ ህግን የጣሱ የመኖሪያ ፍቃድ ያላቸው ሲሆኑ ፖሊስ ከሰራተኛ ጉዳዮች ሚኒስተር ጋር በመተባበር በቁጥጥር ስር አውሏቸዋል
4090 የሚሆኑ የኢቃማ ህግን የጣሱ እንደሆነ ጨምሮ አስታውቆዋል
በሌላ በኩል ከዚህ በፊት በሌላ ስራ ዘርፍ በመስማራት የሚታወቁት ደውሪያ ወይም 999 ፖሊሶች የጀዋዛት ሹርጣዎች የሚሰሩትን ስራ እንዲሰሩ ህገወጥ ስደተኞችን መያዝ እንዲችሉ ተፈቅዶላቸዋል
ከዛሬ ሀሙስ 21/1/2016 ጀምሮ ሁሉም የሳውድ አረቢያ ፖሊሶች የውጭ ሀገር ዜጎችን እያስቆሙ ኢቃማ መጠየቅ እንዲችሉ ትዕዛዝ እና ፍቃድ ተሰጥቷቸዋል
ማነኛውም የኢቃማ እና የስራ ህግን በመጻረር ሳውድ አረቢያ ላይ የሚኖሩ የውጭ ዜጎችን ለመያዝ ያስችል ዘንድ 987 የነጻ ስልክ ይፋ ማድረጋቸውን ይፋ አድርገዋል

የአውሮፓ ህብረት የኢትዮጵያን መንግስት ለማውገዝ በተዘጋጀው የውሳኔ ሃሳብ ላይ ድምጽ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል


ኢሳት ዜና :- የህብረቱ አባላት አዘጋጅተው ባቀረቡት ሰነድ ላይ ህብረቱ ነገ ሃሙስ 11 ሰዓት ላይ ድምጽ ይሰጥበታል ተብሎ ይጠበቃል።
ለህብረቱ የቀረበው የውሳኔ ሃሳብ የኢህአዴግ መንግስት በኦሮሞ ተወላጆች ላይ የወሰደውን ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ እንዲሁም በመላ አገሪቱ የሚፈጽመውን ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት ያወግዛል። በእስር ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞች፣ ፖለቲካኞችና ሰብአዊ መብት ተሟጋቾች እንዲፈቱ ይጠይቃል። ለኢትዮጵያ መንግስት የሚሰጠው እርዳታ በቅድመ ሁኔታ ላይ እንዲቀመጥም ያሳስባል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ራፖርተር በኦጋዴንና በሌሎችም የአገሪቱ ክፍሎች የተፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን ወደ አገሪቱ ገብቶ እንዲያጣራ ከመንግስት ፈቃድ እንዲያገኝ በውሳኔ ሃሳቡ ላይ ተጠቅሷል።
ጠንካራ የተባለውን ውሳኔ ሃሳብ ለማሳለፍ ዛሬ በተለያዩ የፓርላማ አባላት መካከል ክርክር ተካሂዷል። የውሳኔ ሃሳቡ ሳይቀየር እንዳለ ከተላለፈ፣ በአውሮፓ ህብረትና በኢትዮጵያ መካከል ባለው ግንኙነት ላይ ከፍተኛ ተጽኖ ይፈጥራል። የኢህአዴግ መንግስት የውሳኔ ሃሳቡ እንዳይጸድቅ በደጋፊዎቹ በኩል ከፍተኛ የዲፐሎማሲ ስራ እየሰራ ነው።
የህብረቱ አባላት በቅርቡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩን ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖምን ጠርተው በኢትዮጵያ ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ ጥያቄ አቅርበውላቸው ነበር፡፡ የአርበኞች ግንቦት7 ሊ/መንበር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋም ከወራት በፊት ከተለያዩ የህብረቱ ባለስልጣናት ጋር ተገናኝተው ስለኢትዮጵያ ውቅታዊ ሁኔታ ገለጻ ማድረጋቸው ይታወሳል።

Tuesday, January 19, 2016

በጎንደር 14 ሰዎች ተገደሉ፣ የመንግስት ሃይሎች የዘር ግጭት ለመፍጠር እየተንቀሳቀሱ ነው ተባለ


የህወሃት አመራር በጎንደር በአማራና በቅማት ብሄረሰቦች መካከል በድጋሚ የዘር ግጭት ለመፍጠር እየሞከረ እንደሆነ ከአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን ለኢሳት የደረሰው መረጃ አመለከተ።
ባለፈው ሳምንት አጋማሽ ተገድለው የተገኙ 6 የአማራ ብሄር ተወላጆች በህወሃት የደህንነት ሃይላት የተገደሉ ቢሆንም ገዳዮቹ ቅማንቶች ናቸው በሚል ቅስቀሳ የአማራ ህዝብ በቅማንት ላይ እንዲነሳ ሆን ተብሎ ታስቦ የተሰራበት እንደነበር ኢሳት ከስፍራው ያነጋገራቸው እማኞች አስረድተዋል።
አብዛኞቹ ሟቾች ወጣቶች ሲሆኑ ተገድለው ከተጣሉ ከ 1 ቀን በኋል ሬሳቸው እንደተገኘ ለማወቅ ተችሏል።
ግድያው ከተፈጸመ በኋላ የአማራ ብሄር ተወላጆች ለበቀል ባለመነሳሳታቸው የተበሳጩት የህወሃት/ኢህአዴግ የደህንነት ካድሬዎች፣ ከቅማንት ወገን ሌሎች 8 ሰዎችን የገደሏቸው ሲሆን፣ ለቅማንቶች ደግሞ “አማራ ገደላቸው” የሚል ወሬ በመንዛት የቅማንትን ህዝብ ለበቀል እንዲነሳ ሲቀሰቅሱ እንደነበር ታውቋል።
ሆኖም የአካባቢው ነዋሪዎች ስሜታዊ ሳይሆኑ ወንጀለኞቹ ለፍርድ እንዲቀርቡ በተደጋጋሚ ቢጠይቁም፣ የህወሃት/ኢህአዴግ የደህንነት ሃላፊዎች ግን ገዳዮቹ ለመያዝ ወይም ለፍርድ ለማቅረብ አለመፈለጋቸው ተመልክቷል።
ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ በአካባቢው የሚኖሩ አንድ ሰው ለኢሳት እንደገለጹት፣ በአሁኑ ሰዓት ንጹሃንን እየገደለ የዘር ግጭት ለመፍጠር እየተንቀሳቀሰ ያለው የህወሃት ኢህአዴግ መንግስት እንደሆነ ህዝቡ በሚገባ ተረድቷል ብለዋል። የአካባቢው ህብረሰብ በግድያው የህወሃት እጅ እንዳለበት እንደተገነዘበ ለማወቅ ተችሏል።
ህወሃት ኢህአዴግ ከዚህ በፊት በሁለቱ ህዝቦች መካከል በተደጋጋሚ ግጭት ለመፍጠር ሞክሮ የነበረ ቢሆንም፣ በሁለቱ ህዝብ ውይይት ለአጭር ጊዜም ቢሆን እርቅ እርቅ ተፈጥሮ በአካባቢው ሰላም ሰፍኖ እንደነበር ይታወሳል። ሆኖም ህወሃት አሁን የቀሰቀሰው የዘር ግጭት በአካባቢው ሰላም በማደፍረስ የእራሱን አላማ ለማሳካት እንደሆነ ታውቋል።

በሀዲያ ዞን ሆሳዕና ከተማ የከተማ ታክሲዎችን ጨምሮ የህዝብ ማመላለሺያ ተሽከርካሪዎች ከትላንት ጀምሮ የስራ ማቆም አድማ አደረጉ


ዜና ከደቡብ ኢትዮጵያ
በሀዲያ ዞን ሆሳዕና ከተማ የከተማ ታክሲዎችን ጨምሮ የህዝብ ማመላለሺያ ተሽከርካሪዎች ከትላንት ጀምሮ የስራ ማቆም አድማ አድርገዋል። መንግስት በአሽከርካሪዎች ላይ ያወጣው አዲስ መመሪያን ተከትሎ በተነሳ ቁጣ አሽከርካሪዎችና ባለንብረቶች የስራ ማቆም አድማ መምታቸውን ለኢሳት ከአከባቢው የደረሰው መረጃ አመልክቷል። ከትላንት ጀምሮ ምንም አይነት የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ከሆሳዕና መግባትም መውጣትም እንዳልቻለ በአድማው የተሳተፈ አንድ አሽከርካሪ ገልጿል። ከወራቤ ወደ ሆሳዕና 16 ሰዎችን ጭኖ ሲያመራ የነበረ መለስተኛ የህዝብ ማመላሺያ ተሽከርካሪ በአድመኞቹ ጥቃት ተሰንዝሮበት እንደወደመ ያገኘነው መረጃ ያመልክታል። አድማውን ህዝቡ እየተቀላቀለው እንደሆነ ተገልጿል። ለነገ ሰላማዊ ሰልፍ መጠራቱንም ለማወቅ ተችሏል።
Mesay Mekonnen's photo.

ማስተር ፕላኑ ወደፊት እንደሚተገበር እትየ ሚሚ ስብሃቱ ገለጹ


“በኦሮሚያ ክልል ተከስቶ የነበረው ግርግር እና ሁከት እኛ ባለን መረጃ መሰረት እ እ እ … ዛሬ ጠዋትም በቅርቡ የተለያዩ አካባቢዎች ደዉለን ስናጣራ ነበረ፤ እ እ እ … የመማር ማስተማር ሂደቱ ቀጥሏል እ እ እ … ከአለፈው ሳምንት ወዲህ ሰላም መስፈኑንና የተረጋጋ … ይበልጥ እየተረጋጋ መሄዱን በተለያዩ የማጣራት ሂደቶች አጣርተናል፡፡”
ነገር ግን አሉ ሚሚ ቆምጨጭ ባለ ድምጸት፤
“ነገር ግን ይሄ ጉዳይ ደግሞ እንዲቀጥል የሚፈልጉ ወገኖች አሁንም ዉሸትና አሉባልታ ከማራገብ አልታቀቡም፡፡ በተለያዩ በሚጠቀሙባቸው መገናኛ ብዙሃን በማኅበራዊ ድህረገጾች የሌላ አገር፣ በአገራችን ሳይሆን በሌላ አገር የተፈጠሩ ሁኔታዎችን ፎቶግራፍ የተነሱ ነገሮችን ፖስት እያደረጉ አሁንም ህብረተሰቡን ለማደናገር እና እንትን ለማለት እ እ እ… መሯሯጡ ተጧጡፏል፡፡ እ እ እ … አንዳንዶቹ ከፍተኛ ብስጭት ዉስጥ ወድቀዋል ሁኔታዎች በመረጋጋታቸው፡፡”
እዚህ ላይ እርሳቸው እራሳቸው በስጨት ወደ ማለት ሄደዋል፡፡ ቀጠሉ እትየ ሚሚ
“እ እ እ … ከዛ ደግሞ፤ ተከትሎ ደግሞ፤ የክልሉ መንግስትና የክልሉ ገዢ ፓርቲ ይሄ ችግር ነው ተብሎ የተነሳው ጉዳይ ሙሉ ለሙሉ ላልተወሰነ ግዜ መቋረጡን፤ ይሄ ጉዳይ ህዝቡ ሙሉ በሙሉ እንዲነጋገርበት እና እንዲወስንበት ብሎ ደግሞ እ እ እ … መግለጫ መስጠቱና ዉሳኔዎችን ማሳለፉ ምንጣፉን ከስራቸው ዉስጥ እንደጎተተው ያህል ነው፡፡ ጥሏቸዋል፡፡”
ወዳጄ እንዴት ነው ነገሩ? እኛ እኮ ሙሉ ለሙሉ ቆመ ሲባል ነገርየው ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜም እንዳይነሳ ሆኖ ሊቆም ይችላል ብለው አባዱላ እዚቸው ክብ ጠረጴዛ ላይ ባስታወቁት መሰረት መስሎን ነበር፡፡
እትየ ሚሚ ግን ለጊዜው ቆም ብሎ ወደፊት ሊቀጥል ነው በማለት ሲፈሩ የነበሩ ሰዎችን ስጋት ልክ እንደሆነ በክቡ ጠረጴዛቸው ላይ እያረጋገጡልን ነው፡፡ በርግጥ አባዱላም በዕለቱ ያን መልዕክት አስተላልፈው ሲሄዱ፤ እንዴት ነው እሱ ፕላኑን ለማስጠናት ይሄን ያክል ወጪ ወጦ፤ ከፈረንሳዩዋ ማንትስየ ከተማ ተኮርጆ፤ ይቅር የሚባለው? እያሉ አባዱላን ሳይቀር ሲወርፉዋቸው ነበር፡፡
እትየ ሚሚ ንግግሯቸው አሁንም እንደቀጠለ ነው፡፡
“በዚያች ላይ ነበር የተንጠለጠሉት፡፡ ተገቢ በሆነችው የህዝብ ጥያቄ ላይ ተንጠላጥለው ነበር፡፡ ግን አሁንም እየተገፋ ያለው ይሄ ሂደት ህዝቡ እንዲተላለቅ ሁከቱ እንዲቀጥል እሳት የማቀጣጠል ስራ ነው እያየን ያለነው በአንዳንድ አካባቢዎች”
ከዛ “ፀጋ!” ስሙ ይጠራል፡፡
ፀጋም አቤት እትየ እንደማለት እየቃጣው የትየ ሚሚን ሃሳብ ለማጠናከር ጉሮሮውን ስሎ ይነሳል፡-
በነገራችን ላይ በትምህርተ ጥቅስ ዉስጥ ያስቀመጥኩላችሁ የክቧን ጋዜጠኞች ንግግር ቃል በቃል በመውሰድ ነው፡፡
“እንግዴ ያው በኦሮሚያ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች የተፈጠረው … ” የሚለውን የተለመደ የመግቢያ ሃረግ አስረዝሞ ካነበነበ በኋላ፤
“ህዝቡ የራሱ ልማት እና እድገት ነውና እየተጎዳና እየተደናቀፈ ያለው ይህንን ጸረ ልማት የሆነ ተግባር የሚፈጽሙትን አካላት አሁንም ሊታገላቸው ሊያጋልጣቸው ይገባል የሚል እምነት አለኝ” የሚለውን ሌላ ሰሞነኛ ሃረግ አስከትሎ (ይታያችሁ እንግዴህ፤ ጥያቄው ተገቢ የህዝብ ጥያቄ ነው ብለው እንደጨረሱ እኮ ነው ይሄ ሁሉ ፍረጃ እና ዉንጀላ ህዝብ ላይ ተመልሶ የሚዥጎደጎደው)
“ብዙም ሚዲያ አልተከታተልኩም ሰሞኑን ስራ ላይ ስለነበርኩ” የሚል አከለበት፡፡ ነገር ግን ብሎ የተነሳበትን የአለቃውን ሃሳብ ያለቅድመ ሁኔታ የማራገብ ስራን መተወኑን ተያያዘው፤
“ከዚህ በኋላ የጋራ ልማት ይኖራል፡፡ ወደፊት መልማታችን አይቀርም፡፡ ሁላችንም ከድህነት ለመውጣት እየተሯሯጥን ነው፡፡ ይሄ ገና ውይይት የሚደረግበት የረጅም ግዜ ጉዳይ ነው፡፡”
በማለት ይሄ የተቀናጀ የጋራ ፕላን ተብየው ወደፊት ወደድንም ጠላንም መተግበሩ እንደማይቀር ነግሮን ንግግሩን ቋጨ፡፡ ወዳጄ? እነዚህ ሰዎች የመንግስት ደጋፊዎች ናቸው እየተባሉ የሚታሙት ዉሸት ነበር እንዴ? ይህን ነገር ሌሎች የግል ሚዲያዎች ቢናገሩት እኮ “ለህብረተሰቡ የተሳሳተ አሉባልታን በማናፈስ፤ ውዥንብር ዉስጥ የከተቱ” የሚባለው ክስ ይከታተልባቸውም አልነበር እንዴ? ተመስገን ደሳለኝ ከተከሰሰባቸው ጉዳዮች አንዱ “የህብረተሰቡን አስተሳሰብ በማናወጥ” የሚል መሆኑ ትዝ አሎት አይደል?
እትየ ሚሚ ፀጋን ተቀብለው እራሳቸው ድምጻቸውን ከፍ አድርገው በማውራት ላይ ናቸው፤
“በሌላ በኩል ግን፤ በአጭሩ ግን፤ እንዲህ አይነት ነገር ሁለተኛ እንዳይደገም! (እዚህች ላይ ቁጣና ግልምጫ ድምጸቷ ዉስጥ ይታይበታል) ጥያቄ እንኳን ቢኖር በእንደዚህ አይነት መንገድ አይደለም መቅረብ ያለበት፡፡ እንዲህ አይነት ሁኔታ እንዲኖር ያደረጉ ወገኖች አሉ ማለት ነው፡፡ እነዚህ ወገኖች መፈለግ አለባቸው፡፡ ዝምብሎ ብቻ የዉጪ ሃይል፤ ዝምብሎ ብቻ እንትን ነው እየተባል አይደለም፡፡ በትክክል እነማን ናቸው የሚለውም ነገር አንደኛው የመፍትሄው አካልና ሁለተኛ ዳግም እንደዚህ አይነት ነገር (አሁንም ሌላ የማመናጨቅ ድምጸት) እንዳይከሰት የሚደረግበት ነገር ሊሆን ይገባዋል፡፡” የሚል ግልምጫና ምንጭቂያ የታከለበት ማስፈራሪያን አስከተሉ፡፡
“መሰረት ሰአታችን እየተጠናቀቀ ነው አንድ ሁለት ደቂቃ አለህ” በሚል ለመሰረት አየሩን ለቀቁለት (ለቀቁበት አላልኩም)
እ እ እ … ብሎ ጉሮሮውን ከጠረገ በኋላ
“የኦሮሚያ ክልል ችግር ቅድም እንዳልሽው በክልሉ ገዚ ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ዉሳኔ ተሰጥቶበታል፡፡ የመአከላዊ ኮሚቴው ዞሮ ዞሮ ባብዛኛው የመንግስት አስፈጻሚዎች ያሉበት ስለሆነ ባብዛኞቹ ዉሳኔውን መንግስትም ተቀብሎ እንደሚፈጽመው ምንም ጥያቄ የለዉም ብለን እንገምታለን፤ የክልሉ መንግስት፡፡ ስለዚህ መልካም ነገር ነው፡፡”
በሚል ንግግሩን ከፈተ፡፡ ቀጥሎም “ባለፈውም እኛ ተናግረናል ይሄ የህዝብ ጥያቄ ይህ ህዝብ ካልፈለገው እስከሚፈልገው ድረስ ባነበረበት እንዲቆም ማድረጉ የግድ ተገቢ መሆኑን ስንነጋገር ነብር፡፡ ይሄ ማለት ግን ያ ልማት ልማታዊ እንጂ — አይደለም ብሎ መገምገም እንዳልሆነ ህዝብም ማወቅ አለበት፡፡
“ማለት አንዳንድ ወገኖች አሁን፤ በተለይ ተቃዋሚ የሚባሉ ወገኖች በቃ በአጠቃላይ መጀመሪያ መቆሙን ነው የሚፈልጉት ያለው፤ መቆሙን ግን ዉጤት እንዲያመጣላቸው ይፈልጋሉ፤ የራሱ ዉጤት፡፡ ማለት ሲቆም ሌላ ምስቅልቅል ነገር እንዲፈጠርና በቃ የሆነ ዉዝግብ እንዲነሳ ይፈልጋሉ፡፡ ስለዚህ አሁንም ህዝብን እየቀሰቀሱ ነው ያሉት፡፡ ዉሳኔውን የሚያጣጥሉ ወገኖች አሉ አሁንም፡፡ ስለዚህ ያ እንተን ምንድን ነው መነሻው ስትይ፤ ቅንነትም የጎደለው መነሻ ነው፡፡ ዞሮ ዞሮ የህዝብ በተለይም ደግሞ የአስ… ወጣቶች፤ ብዙ የማያገናዝቡ ልጆች እዛ በተለያየ ምክንያት ገብተው ህይወታቸውን እንዳያጡ ጥሩ መከላከያ ጥሩ መገደብያ ነው፡፡ ይህ ከሆነ በኋላ ግን ምንም ነገር ሊቀጥል አይገባም በዚያ መንገድ፡፡ በቃ ጥይቄው ይህ ከሆነ፤ ይህ ጥያቄ ተፈትዋል፡፡”
ይሄ ሰውየ ዞሮ ዞሮ ካላለ ያወራ አይመስለውም፡፡ እሱ ዞሮ ዞሮ ሲል እኔ ዞር ዞር ብሎ መምጣት ያምረኛል፡፡ ሃ ሃ! ዞሮ ዞሮ ታድያ የትየ ሚሚን ለጊዜው ቆመ እንጂ ለወደፊቱ መምጣቱ አይቀርምን ሃሳብ በሚከተለው መልኩ አጠናክሮታል፡፡
“በሌላ ጊዚያት ደግሞ ህዝቡ እራሱ ጥያቄ ያነሳል፡፡ ልልማ ይላል፡፡ አብረን እንልማ ይላል፡፡ ያኔ … (የሆነ የማይሰማ ቃል) ይደረጋል፡፡ አለዛ አሁንም ሌላ ነገር እናደርጋለን የሚሉ ከሆነ፤ አሁንም እንደዚህ አይነት ነገር የሚሉ ከሆነ ሌላ ነው ምክንያቱ ማለት ነው፡፡”
ታዲያ እንዴት ነው ነገሩ? የዛሬ የክቧ ጠረጴዛ ውሎ የኦህዴድን የስራ አስፈጻሚዎች መግለጫ ማስተባበል ነው እንዴ?
መሰረት ንግግሩን ቀጥሏል፤
“ፍላጎታቸውም ሌላ ነው፡፡ ህዝቡም ባለፈው እንደተነጋገርነው የኦሮሚያ ህዝብ ጥያቄ ብቻ አይደለም፡፡ የኢትዮጵያ፣ መላው ኢትዮጵያ ጥያቄ ነው የሚሆነው፡፡ ጥያቄውን ህዝቡን በጋራ ይመለከተዋል፡፡ መንግስትም በዚህ ጉዳይ ላይ ሲሪየስ የሆነ አቋም ሊወስድ የሚገባበት ሁኔት ይኖራል ብየ አስባለሁ፡፡”
እዚህ ላይ ደግሞ አቶ መሰረት ጥያቄውን ሌሎች ኢትዮጵያውያንም ይዘው ይነሱ የሚል ይመስላል፡፡ ወይንስ የኦሮሞ ጥያቄ የሌሎችም ኢትዮጵያውያንን ጥያቄን የሚጠይቅ ከሆነ “አይ ይህማ ያንተ ብቻ ሳይሆን የሁሉም ችግር ነው፤ ዝምበል!” ሊባል ነው፡፡
መሰረት ከላይ ምን ለማለት እንደፈለገ ግልጽ ባይሆንም እሱ መናገር ቀጥሏል፤
“አሁን ይሄኛው እየፈለጉ ያሉት አንዳንድ ተቃዋሚዎች አልበረደም ምናምን ሲሉ ተስሚያለሽ፡፡ ነገር ግን በኔ ባለሁበትም አካባቢ አሁን ምንም ጸጥ እረጭ ያለ ነገር ነው፡፡ ነገር ግን ምንድን ነው የሚወራው? እኛ ያለንበት ሳንናገር ከሌላ ቦታ ወሬ መጦ ትሰሚያለሽ፡፡ አሁንም አለ! አሁንም ተማሪዎች አልገቡም፡፡ አሁንም ግርግር አለ። አሁንም ብለው የሚያስወሩ ወገኖች አሉ፡፡ ያ የሚፈልጉት ምንድነው? እንዲቀጥል ስለሚፈልጉ ነው፡፡ አላማ ካላቸው አላማዉን በዚህ መንገድ ለማስቀጠል ስለሚፈልጉ ነው፡፡ …… ተጠያቂ መሆን አለባቸው በይሉኝታ እየታለፈ ዝም መባል የለበትም …”
ወዳጄ አልደከሞትም፡፡ እኔ እራሱ እጅ እጅ አለኝ፡፡
“የተከበራችሁ አድማጮቻችን የዛሬ የክብ ጠረጴዛ ሰአታችን (ውሸታችን) ተጠናቋል፤ ስላዳመጣችሁን እናመሰግናለን” አሉ ሴትየዋ በመጨረሻ፡፡
እነዚህ ይክብ ጠረጴዛ ጉዶች ግን አሁን እንደዚህ በየመንገዱና በየከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ህይወቱን ነፍጥ ባነገቱ ጉልበተኞች ከሚነጠቀው ዉስጥ አንዱ የእነርሱ ልጅ ቢሆን፤ አይ ሁሉም ሰላም ነው! የሚሰማው ወሬ ሁሉ ዉሸት ነው! የመማር ማስተማሩ ሂደት በተረጋጋ ሁኔታ ቀጥሏል ይሉን ይሆን?
ቸር እንሰንብት!
እውነት ከምድርቤት
ጎልጉል: የድረገጽ ጋዜጣ

ፍ/ቤቱ የአቃቤ ህግ የደህንነት መ/ቤት ማስረጃ ‹ኦርጅናሉ› እንዲቀርብ አዘዘ


በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
በእነ ዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ በሽብር ከተከሰሱበት በሥር ፍርድ ቤት በነጻ ተሰናብተው አቃቤ ህግ በጠየቀባቸው ይግባኝ ጉዳያቸው በጠ/ፍ/ቤት እየታየ የሚገኙት የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮች ከብሄራዊ ደህንነት ተገኘ የተባለው የአቃቤ ህግ ማስረጃ ‹ኦርጅናሉ› እንዲቀርብ ትዕዛዝ ተሰጠ፡፡
በእነ ሀብታሙ አያሌው መዝገብ የተከፈተው ይግባኝ ላይ የተካተቱት አቶ ሀብታሙ አያሌው፣ አቶ አብርሃ ደስታ፣ አቶ ዳንኤል ሺበሽ፣ አቶ የሺዋስ አሰፋ እና አቶ አብርሃም ሰለሞን ዛሬ ጠ/ፍ/ቤት ቀርበው ብይን ያገኛሉ ተብሎ ሲጠበቅ ተለዋጭ ቀጥሮ ተሰጥቶባቸዋል፡፡
ፍርድ ቤቱ እንዳለው አቃቤ ህግ በስር ፍርድ ቤት አልተመረመረልኝም ያለው ከብሄራዊ ደህንነትና መረጃ ማዕከል የተገኘው ማስረጃ፣ ማስረጃ ሳይሆን የመረጃ ትንተና የተሰጠበት ስለሆነ ‹ኦርጅናሉ› መረጃ ቀርቦ እንዲመረመር ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡
‹‹መረጃው እንደወረደ መቅረብ አለበት፤ ከስልክም ሆነ ከፌስቡክ ወይም ከኢሜል ተገኘባቸው የተባለው ማስረጃ ቃል በቃል ይቅረብ፡፡ ትንታኔ የተሰጠበት ሳይሆን ቀጥታ ቃሉ ይቅረብልን›› ብሏል ፍርድ ቤቱ፡፡
አቶ አብርሃም ሰለሞንን በተመለከተ በስር ፍርድ ቤት የተሰማባቸው 3ኛ የአቃቤ ህግ ምስክር ሙሉ ቃልም አቃቤ ህግ ይዞ እንዲቀርብ ታዝዟል፡፡ ፍ/ቤቱ አቃቤ ህግ የታዘዘውን ማስረጃ ይዞ መቅረቡን ለመጠባበቅ ለጥር 24/2008 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

Monday, January 18, 2016

የኢትዮ ሱዳን ድንበር ማካለሉ በዚህ አመት ይጠናቀቃል ተባለ


ድንበር ማካለሉ በዚህ አመት ይጠናቀቃል። የህወሀት መንግስት በቅርቡም ስለድንበሩ ምንም ዓይነት ነገር የለም ሲል የሚመራው ሀገርና ህዝብን አታሏል። በጀርባ ስለድንበሩ እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ ሊያጠናቅቅ እንደሆነ በሰፊው ይነገራል። ሱዳን ትሪቡን እንደዘገበው የቴክኒክ ኮሚቴው ተግባሩን አጠናቆ በዚህ ዓመት ውስጥ በመሬት ላይ ማካለሉ ይከናወናል። አሁንም ህወሀት ስለድንበር ጉዳይ ምንም እያደረኩ አይደለም የሚል ምላሽ መስጠቱ ይጠበቃል። Mesay Mekonnen
ለበለጠ መረጃ ከስር ያለቅን ሊንክ በመክፍት ያንብቡ 👇
Samuel Ali's photo.

የትግራይ ነጋዴዎችን ለመጥቀም አዲስ የበርበሬ አዋጅ በጎጃም

ኢትዮጵያን በነጻ አውጪ ስም እየገዛ ያለው የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሃት) በተለይ በምዕራብ ጎጃም አካባቢ የደነገገው አዲስ የበርበሬ አዋጅ ችግር እያስከተለ መሆኑን የጎልጉል እማኝ ዘጋቢ (ireporter) በላኩልን መረጃ አስታውቀዋል፡፡ እንደ እማኝ ዘጋቢው ከሆነ አዋጁ የወጣው በ2002ዓም ሲሆን በሥራ ላይ መዋል የጀመረው በዚህ ዓመት እንደሆነ ያስረዳሉ፡፡ ይህ በበርበሬ ላይ ብቻ የተደነገገው አዋጅ ዋና ምክንያቱን በውል ለማወቅ የሚያዳግት ቢሆንም እንደ እማኝ ዘጋቢው አስተያየት በርበሬው ወደ ትግራይና አዲስ አበባ የሚላክ በመሆኑ በተለይ የትግራይ ነጋዴዎችን በከፍተኛ ሁኔታ ለመጥቀምታስቦ እንደሆነ ከሚሰጡት ግምቶች የላቀው መሆኑን ያስረዳሉ፡፡
እማኝ ዘጋቢያችን የላኩልን መረጃ እንዲህ ይነበባል፡-
“በአማራ ክልል በምዕራብ ጎጃም ዞን በቡሬ በፍኖተ ሰላም በሺንዲ ወረዳዎችና አካባቢዎች በበርበሬ ንግድ ላይ አዲስ አዋጅ አውጥተው ህዝቡን ለችግር ነጋዴውን ደግሞ ለኪሳራ እየዳረጉት ነው። አዲስ ያወጡት አዋጅ ለጎጃም ብቻ ሲሆን፡-
1ኛ. ሁሉም ነጋዴዎች በሚሸጡበት ቦታ ሁሉ ቅርንጫፍ እንዲኖራቸው ያስገድዳል። ለምሳሌ የቡሬ ነዋሪ የሆነ ነጋዴ መቀሌ መሸጥ ቢፈልግ ቅርንጫፍ ሊኖረው ግድ ነው፤ አዲስ አበባ ቢሆን ሌላ ተጨማሪ ቅርንጫፍ ሊኖረው ያስፈልጋል፤ ሽሬም ቢፈልግ እንዲሁ፤
2ኛ. ማንኛውም ነጋዴ ከነጋዴ ላይ መግዛት አይችልም፤ ለምሳሌ 90 ኩንታል መጫን የፈለገ 85 ኩንታል ኖሮት 5 ቢጎለው 5 ከነጋዴ ላይ ገዝቶ መሙላት አይችልም፤
3ኛ. ቫት እንዲጀምሩ ማለትም በቫት እንዲገዙ፤
4ኛ. ከ6 ወር በላይ መከዘን ወይም ማስቀመጥ አይቻልም።
ለምሳሌ 1 ኪሎ 60 ብር ቢገዛና በቀጣይ ጊዜ ቢቀንስ 50 ብር ቢሆን ከስሮም ቢሆን መሸጥ ግዴታው ነው።”
በማለት የአካባቢው ነጋዴና ሕዝብ እየተጋፈጠ ያለውን ችግር እንድናሰማላቸው ልከውልናል፡፡ (ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ)

ጎንደር በብአዴን ከፍተኛ ባለስልጣናት ተወራለች


የቤተ አማራ የውስጥ አዋቂዎች እንደገለፁት ሰሞኑን የብአዴን ከፍተኛ ባለስልጣናት ጎንደር ላይ ከትመው ሰንበታዋል። ከብአዴን ወጣት አባላት፣ ከኦርቶዶክስ ሃይማኖት አባቶች እና በከተማው ውስጥ ተሰሚነት አላቸው ከሚባሉ ግለሰቦች ጋር የተለያዩ ዝግ ስብሰባዎችን እያካሄዱ ነው። የስብሰባው ዋና አጀንዳ ከጥምቀት በዓል ጋር ተያይዞ የህዝብ አመፅ በጎንደር ከተማ ውስጥ እንዳይቀሰቀስ ቅድመ ዝግጅት ለማድረግ ነው ተብሏል።
የወልቃይት የአማራነት ጥያቄ፣ ለሱዳን ሊሰጥ የታቀደው ሰፊ እና ለም የአማራ መሬት፣ ከቅማንት ማህበረሰብ የአስተዳደር ይገባኛል ጥያቄ ጋር ተያይዞ የተነሳው ደም ያፋሰሰ ግጭት፣ በአጠቃላይ በግልፅ እዬታዬ ያለው ከፍተኛ የሆነ የአማራ ህዝብ በደል የጎንደር እና የአካባቢውን ኗሪዎች በጥምቀት እለት ወደ ህዝባዊ አመፅ እናዳያመሩ በብአዴኖች ላይ ከፍተኛ ፍርሃት አሳድሯል። የጎንደር ጥምቀት በዓል በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ህዝብ በየአመቱ እንደሚያከብረው ይታወቃል።
ብአዴኖች ከፍርሀታቸው የተነሳ በተለይ ጥር 12 የሚከበረውን የቅዱስ ሚካኤልን ንገሰ በዓል ለመሰረዝ የታሰበ እቅድ አቅርበው ነበርም ተብሏል። ከጥር አስራ አንዱ የጥምቀት በዓል በኋላ በማግስቱ የሚከበረው ይሄው በዓል እጅግ ደማቅ በሆነ መልኩ ለዘመናት ሲከበር እንደኖረ የሚታወቅ ነው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አንዳንድ የህዝብ ብሶቶች በተለይ በቅዱስ ሚካኤል ታቦት የማስገባት ቀን ሲንፀባረቁ ተስተውሏል። የብአዴን ፍራቻ የመጣውም ከዚህ ጋር ተያይዞ መሆኑ ታውቋል። ይሄን የብአዴን ሃሳብ ተስብሳቢው መሉ ለሙሉ በምሬት ውድቅ እንዳደረገባቸው ምንጮቻችን አያይዘው ገልጸዋል።
ሌላው ለብአዴን የጎን ውጋት የሆነበት ችግር እሱ ባላሰበው መልኩ ከቁጥጥሩ ውጭ እየወጣ ያለ ጠንካራ የአማራ ብሔርተኝነት እየተቀጣጠለ መሆኑ ነው። ብአዴን በሕወሓት የሚመራ የይስሙላ ብሔርተኝነት እንጂ እንዲህ አይነቱን የአማራ ብሔርተኝነት እንደማይፈልገው በተዘዋዋሪ ለተሰብሳቢው ሲገልፅ ተደምጧል።
ብአዴን በተደጋጋሚ የአማራን ህዝበ ጥቅም ማስጠበቅ ሳይችል የቀረ ደካማ ፓርቲ መሆኑ የአደባባይ ሚስጥር ከሆነ ሁለት አስርተ አመታት ተቆጥሩ።
ድል ለአማራ ህዝብ!

Sunday, January 17, 2016

ህዝባዊ አመጽ ቤተመንግስት ዳጃፍ ላይ መድረሱን በርግጠኝነት የሚጠቁሙት መረጃዎች አፈትልከዉ እየወጡ ነዉ፦


ሰበር መረጃ፡
በሄራዊ መረጃ የተባለዉ የወያኔ አንጃ በትግራይ ነጻ አዉጭ ቡድን ላይ በአሁኑ ወቅት የተቀጣጠለበትን የህዝብ አመጽ ተንተርሶ በመላዉ ሐገሪቱ የነገሰዉን የለዉጥ ነዉጥ ለመቀየር ይቻል ዘንድ፦ በእስር ላይ የሚገኙ ከፍተኛ የሐይማኖትና፣ የፖለቲካ እስረኞች፣ በተለይም ፍርድ የተበየነባቸዉ! ይለቀቁ፦ የሚል እቅድ አዉጥቶ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ታማኝ ምንጫችን የሰጡን መረጃ ያመለክታል።
በደህንነት ቢሮዉ ዳይሬክተር የሚመራዉ ይህዉ ክንፍ በግፍ የታሰሩ ታራሚዎችን ስም ዝርዝርና እንዴት በህዝቡ ዘንድ መነጋገሪያ ሊሆኑ እንደሚችሉ እና ለዉጥ ሊፈጥሩ ሐይል እንዳላቸዉ ዘርዝሮ አስቀምጧል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ መረጃ፦ ወቅታዊ በሆነዉ ህዝባዊ አመጽ ምክንያት ታድነዉ እንዲያዙ የተወሰነባቸዉ ግለሰቦች ለጊዜዉ በጥብቅ ዉጫዊ ክትትል ስር እንዲቆዩ፡ ነገር ግን ከሐገር እንዳይወጡ ሲወስን በተጨማሪ ሕዝብን ሊቀሰቅሱና ሊያነሳሱ ይችላሉ ተብለዉ የሚገመቱ ሙዚቃዎችና፣ ሙዚቀኞች፣ ላይ ትኩረት እንዲስጥ ይህዉ ወንጀለኛ የወያኔ ወንበር ጠባቂ ክንፍ ሰላዮቹን አሰማርቶ እየተንቀሳቀሰ የሚገኝ ሲሆን መጽሐፍት ማተሚያ ቤቶች ላይ ሰላዮችን በማሰማራት ከምን ግዜዉም በላይ የነጻዉን ፕሬስ በብርቱ አፍኖ ተቆጣጥሮታል።
ዉድና የተከበራችሁ ኢትዮጵያዊያን የጀመርነዉ ህዝባዊ አመጽ ቤተመንግስት ዳጃፍ ላይ መድረሱን በርግጠኝነት የሚጠቁሙት መረጃዎች አፈትልከዉ እየወጡ ነዉ፦ ባለስልጣናት ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ይፈረጥጣሉ ያፈነግጣሉ በሚል ፍራቻ የተወጠረዉ ብሔራዊ መረጃ በያንዳንዱ ባለስልጣናት ጥበቃዎች ላይ አንድ አንድ ሰላዮችን የመደበ ሲሆን የብሔራዊ መረጃ ባልደረባን ይዛ ከማይጸብሬ የተንቀሳቀሰች የጦር ሄሊኮፍተር ሐሙስ እለት ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ከተከዜ ወንዝ ባሻገር በረሐ ላይ ተከስክሳለች።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !
ጉድሽ ወያኔ
Gudish Weyane's photo.

Friday, January 15, 2016

ዩናይትድ ስቴትስ የኦሮሞ ብሄረሰብ ብሶትን በተመለከተ ትርጉም ሰጪ ድርድር እንዲካሄድ ጥሪ አቀረበች

የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችን እየያዙ የማሠር እርምጃዎች በኦሮሚያ የቀረቡ ተገቢ የፖለቲካ ብሶቶችን በምክክር ለመፍታት በሚያስችሉ መንገዶች ላይ ከባድ ተፅዕኖ ይኖራቸዋል።
ዩናይትድ ስቴትስ በኢትዮጵያ የኦሮሞ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችን ማሠር ጨምሮ ሃሳብን በነፃ የመግለጽ መብቶችን ማፈን መቀጠሉ ይበልጥ እያሳሰባት መጥቷል። እነኚህ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችን እየያዙ የማሠር እርምጃዎች በኦሮሚያ የቀረቡ ተገቢ የፖለቲካ ብሶቶችን በምክክር ለመፍታት በሚያስችሉ መንገዶች ላይ ከባድ ተፅዕኖ ይኖራቸዋል።
የኢትዮጵያ መንግሥት በወሰዳቸው እርምጃዎች ከተጎዱት ማህበረሰቦች ጋር በይፋ ለመወያየት ባለፈው ታህሳስ የገባውን ቃል እንደግፋለን። እነዚህ ውይይቶች ትርጉም ሰጪ እንዲሆኑ ደግሞ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሃሳባቸውን በነጻነት መግለጽ መቻል አለባቸው።
የኢትዮጵያ መንግሥት፥ በነጻ የመሰብሰብ፥ የመጻፍ፥ እና ዜጎች ሃሳብን በነጻ የመግለጽ ሕገ መንግሥታዊ መብቶቻቸውን ማክበርን ጨምሮ ተቃውሞን ከማፈን ተግባሩ እንዲታቀብ ያቀረብነውን ጥሪ ዳግም እናስተጋባለን።
እነዚህን መብቶቻቸውን ለመጠቀም ሲሞክሩ እንደ ፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችና ጋዜጠኞች ያሉትን ጨምሮ የታሠሩት ሁሉ እንዲፈቱ ጥሪ እናቀርባለን።

በረሃብ ምክንያት በሰሜን ወሎ ወረዳዎች የሚኖሩ አርሶአደሮች ቀያቸውን እየለቀቁ ወደ ባህርዳር በመፍለስ ላይ ናቸው


ኢሳት ዜና :- በአካባቢያቸው በተከሰተው ድርቅ የሚበሉትና የሚቀምሱት እንዳጡ የሚናገሩት ስደተኞች፣ ሰሞኑን ባህርዳር ገብተዋል፡፡ በየመንገዱ በመለመን የእለት ምግባቸውን ለማግኘት እየሞከሩ መሆኑን በፎቶ አስደግፎ ዘጋቢያችን የላከው መረጃ ያሳያል፡፡ የክልሉ መንግስት ምንም አይነት እገዛም አላደረገላቸውም፣ ማረፊያ ቦታም አላዘጋጀላቸውም ፡፡ አብዛኞቹ ስደተኞች ሴቶችና ህጻናት ናቸው። ህብረተሰቡ ለዜጎቹ እገዛ በማደረግ ላይ ቢሆንም፣የአለማቀፍ ድርጅቶችም ሊጎበኙዋቸው እንደሚገባ ዘጋቢያችን አስተያየቱን አስፍሯል። በሌላ በኩል ግን በኢትዮጵያ የተከሰተው ድርቅ ወደከፋ የረሃብ ደረጃ እየተሸጋገረ ነው በሚል በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚንቀሳቀሱ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የሚያሰራጩት ወሬ ገንዘብ ለማግኛ እንጂ ትክክለኛ አይደለም በሚል ኮምሽነር ምትኩ ካሳ አስተባብለዋል፡፡ በቅርቡ በአዲስ መልክ የተቋቋመው የብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮምሽነር አቶ ምትኩ ካሳ ማክሰኞ ዕለት የመንግስትን አንድ ኣመት የስራ ዕቅድ ይፋ ባደረጉበት ወቅት እንደተናገሩት ድርቁ ወደከፋ ደረጃ መሸጋገሩን የዓለም ምግብ ፕሮግራምን (ፋኦ) የመሳሰሉ ኣለም አቀፍ ድርጅቶች የሚያሰራጩት ወሬ ዕርዳታ ለማሰባሰብ እንዲጠቅማቸው እንጂ እውነታው እነሱ እንደሚሉት አለመሆኑን እነሱም ያውቁታል በሚል አስተባብለዋል፡፡ በተለይ በሀገር ውስጥ የሚገኙ መገናኛ ብዙሃንም ይህንኑ በማስተጋባት ላይ መሆናቸውን በመጥቀስ ወቀሳ አቅርበዋል፡፡ ኮሚሽነሩ ችግሩ ከመንግስት አቅም በላይ አልሆነም በሚል በተናገሩበት በዚሁ መድረክ፣ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለመንግስት ይፋዊ የእርዳታ ጥያቄ አፋጣኝ ምላሽ ባለመስጠቱ ትልቁን ድርሻ ብቻውን እየተወጣ ያለው መንግስት ነው በማለት እርስ በእርሱ የሚጋጭ ሃሳብ ሰንዝረዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት 10 ነጥብ 2 ሚሊየን ዜጎች ለምግብ እጥረት መጋለጣቸውን ያስታወሱት ኮምሽነሩ፣ ድርቁን ለመከላከል ለቀጣይ አንድ ኣመት ብቻ 1 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላር ወይንም 30 ቢሊየን ብር ገደማ እንደሚያስፈልግ ይፋ አድርገዋል፡፡ ከኣለም አቀፍ ረጂ ድርጅቶችና መንግስታት የተገኘው ድጋፍ እጅግ አነስተኛ ቢሆንም፣ መንግስት በራሱ አቅም እስካሁን 300ሚሊየን ዶላር ገደማ ወጪ መድቦ ችግሩን ለመቋቋም እየሰራ ነው ብለዋል፡፡ ቀሪውን 1 ቢሊዮን 100 ሚሊዮን ዶላር ማን እንደሚሸፍነው ግን ያሉት ነገር የለም። ዓለም አቀፍ የረድኤት ድርጅቶች የተረጂውን ቁጥር ወደ 20 ሚሊየን የሚያደርሱት ሲሆን ችግሩን ለመቋቋም በመንግስት አቅም የሚደረገው ጥረት በቂ ካለመሆኑ ጋር ተያይዞ ችግሩ በአጭር ጊዜ ሊባባስና ወደከፋ ቀውስ ሊሸጋገር እንደሚችል ሲያስጠነቅቁ ቆይተዋል፡፡ መንግስት የረድኤት ድርጅቶቹን ማሳሰቢያ ተከትሎ አፋጣኝ እርምጃ ከመውሰድ ይልቅ ችግሩን ወደመሸፋፈን ማድላቱ በራሱ ቀውሱን ያባብሳል በሚል እየተተቸ ነው፡፡ በሌላም በኩል ኦክስፋም እና ዩኒሴፍ በቅርቡ ባወጡት የጋራ መግለጫ ድርቁን ተከትሎ በሁሉም ክልሎች ያለዕድሜ ጋብቻ እየጨመረ መምጣቱን ይፋ አድርገዋል፡፡ በድርቅ በተጎዱ አካባቢዎች የሚገኙ ወላጆች ልጆቻቸውን ለመታደግ ሲሉ ያለዕድሜያቸው ለመዳር እየተገደዱ መሆኑን እንዲሁም ሴቶችና ህጻናት ውሃ ፍለጋ ብዙ ርቀት ሲጉዋዙ ለጾታ ጥቃቶች እየተጋለጡ መሆኑን በቅርቡ ባካሄዱት ጥናት ማረጋገጣቸውን ገልጸዋል።

የህወሓት አገዛዝ ዜጎች መግደል፣ መደብደብና ማሰር መደበኛ ሥራው አድርጎታል።

ሁለት ወራት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በኦሮሚያ ውስጥ ብቻ ከ150 በላይ ዜጎች ሕይወታቸውን አጥተዋል፤ በአማራ፣ በጋምቤላና በሶማሌ ቁጥራቸው የማይታወቅ በርካታ ወገኖቻችን ተገድለዋል፤ በሌሎችም ክልሎች ወገኖቻችን እየተገደሉ ነው። ከዚህም በተጨማሪ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ተደብድበዋል፤ ታስረዋል። የህወሓት አገዛዝ ዜጎች መግደል፣ መደብደብና ማሰር መደበኛ ሥራው አድርጎታል።
በተለይ በኦሮሚያ ክልል እየቀጠለ ያለው ሕዝባዊ እምቢተኝነት ትልቅ ትምህርት የሚወሰድበት እና ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆን የሁላችንም ተሳትፎ የሚሻ ነው። ሕዝባዊ እምቢተኝነቱ በክልሉ ውስጥ የሚገኙ ትናንሽ የገጠር ከተሞችን ሳይቀር ያዳረሰ መሆኑ የበርካታ ሕዝብ ስሜትንና ጥቅምን የሚነካ አጀንዳ በፍጥነት እንደሚሰራጭና ሕዝብን እንደሚያደራጅ አመላካች ነው። ከዚህ ሕዝባዊ ትግል በርካታ ድሎች የተገኙ ቢሆኑም ሁለቱ መሠረታዊ በመሆናቸው አጽንዖት ሊሰጣቸው ይገባል።
አንደኛ
በአለፉት ሁለት ወራት በኦሮሚያ የተቀጣጠለው ሕዝባዊ እምቢተኝነት የኢትዮጵያን ማኅበረሰብ አቀራርቧል። ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከተው ሕዝብ ያልመከረበት የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን መቃወም ፍትሃዊ መሆኑ በሰላማዊም ሆነ በአመፅ መንገድ የህወሓትን አገዛዝ መታገል የመረጡ የዲሞክራሲ ኃይሎችን በሙሉ ያስማማ፤ በኦሮሞና በአማራ ማኅበረሰብ መካከል መልካም የሆነ መግባባትን የፈጠረ መሆኑ ትልቅ ድል ነው። ይህ ማለት ግን አፍራሽ ጽንፈኛ አስተያየቶች ከወዲህም ከወዲያም መወርወራቸው ቀረ ማለት አይደለም፤ ያም ሆኖ ግን በሕዝቡና በፓለቲካ ልሂቃኑ መካከል ያለው መናበብ ከቀድሞው በጣም በተሻለ ሁኔታ መገኘቱ ተስፋ ሰጪ ነው። ይህንን ድል ማስከንና አድማሱን ማስፋት ያስፈልጋል። በተለይም የነፃነት ትግሉ አካል የሆኑትን የትግራይ ወገኖቻችንን ማቀፍ እና ህወሓትን ከትግራይ ሕዝብ መነጠል ያስፈልጋል። ወደ ህወሓት የሚወረወሩ ፍላፃዎች ወደ ትግራይ ሕዝብ የተወረወሩ መስለው እንዳይታዩ በንግግሮቻችንና ጽሁፎቻችን ሁሉ ግልጽ ማድረግ ይኖርብናል። ሶማሌን፣ አፋርን፣ ሲዳማን እና ሌሎችን ማኅበረሰቦችን በተመለከተ ተመሳሳይ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል። በዚህ ወሳኝ ወቅት በማኅበረሰቦች መካከል እየተፈጠረ ያለው መግባባትን የሚቀለብስ ወይም ጥርጣሬ ውስጥ የሚያስገባ አንዳችም ተግባር እንዳይፈፀም ነቅቶ መጠበቅ የሁላችንም ኃላፊነት ነው። ይህ ትግል፣ እስካዛሬ አጥተነው የነበረው የኢትዮጵያውያንን ማኅበረሰብ መቀራረብን አምጥቶልናል፤ በሚገባ ከተጠቀምንበት ለሁላችንም የምትሆን ኢትዮጵያን የመገንባት አቅማችንን በከፍተኛ ሁኔታ ያጠነክርልናል። ስለሆነም፣ ከግራ እና ቀኝ በሚወረወሩ ዘረኛ አስተያየቶች እና ተግባራት ይህንን ስሜት ለማደፍረስ የሚጥሩትን በጋራ ልንታገላቸው ይገባል።
ሁለተኛ
ከእንግዲህ የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ተፈፃሚ ማድረግ አይቻልም፤ አስፈፃሚም የለውም። ይህ አንድ ትልቅ ድል ነው፤ ሆኖም ህወሓት የአገዛዙ ወንበር ላይ እስካለ ድረስ ይህ ድል መሠረታዊ የፓለቲካ ሥርዓት ለውጥ አያመጣም። እስከ አሁን ከአንድ መቶ አምሳ በላይ ዜጎች ተገለውብናል፤ የሟቾች ቁጥር በየቀኑ እየጨመረም ነው። ገዳዮች በመግደላቸው ሲሸለሙ እንጂ ሲጠየቁ አላየንም። በግልባጩ የሟች ቤተሰቦች የጥይት ወጪ ካልከፈላችሁ አስከሬን አንሰጥም እየተባሉ ነው።
ገዳይን እየሸለመ፤ ሟችን የሚቀጣ ኋላ-ቀር ፍርደ-ገምድል ሥርዓት ማብቃት ይኖርበታል። ስለሆነም የወቅቱ ጥያቄ መላዋን ኢትዮጵያ ከህወሓት አገዛዝ ነፃ ማውጣትን ዓላማው ያደረገ መሆን ይኖርበታል። “ኦሮሚያ አምባገነንነትን እንቢኝ ብላለች!” ከሚለው መሪ መፈክር “ኢትዮጵያ አምባገነንነትን እንቢኝ ብላለች!” ወደሚለው መሪ መፈክር መሸጋገር ድላችንን ያቀርባል።
አርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ፣ የወገኖቻችን ደም በከንቱ ፈሶ መቅረት የለበትም፤ ገዳዮች በህግ ሊጠየቁና ሊቀጡ፣ ተበዳዮች ደግሞ ሊካሱ ይገባል ብሎ ያምናል። ሆኖም ህወሓት ስልጣን ላይ ሆኖ እያለ እነዚህ ነገሮች ሊፈፀሙ ይችላሉ ብሎ አያምንም። በአርበኞች ግንቦት 7 እምነት ኢትዮጵያ አምባገነንነትን አሻፈረኝ ብላለች፤ ይህም በሕዝባዊ እምቢተኝነት እና በሕዝባዊ አመፅ እየታየ ነው። ሕዝባዊ እምቢተኝነትና ሕዝባዊ አመፅ ሲደጋገፉ ባነሰ ኪሳራ አምባገነኑን አገዛዝ ከጫንቃችን ለማውረድ ያስችለናል ብሎ ያምናል። ስለሆነም ኢትዮጵያ አምባገነንነትን እምቢ ትበል!
አንድነት ኃይል ነው!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!.

ፓትርያሪክ አቡነ ማቲያስ “እስከምሞት እዋጋዋለኹ፤ እጅ እግሩን አስረዋለኹ” ሲሉ በማኅበረ ቅዱሳን ላይ ዛቱ –

Dn . Abayneh kassie 
በአወዛጋቢ ውሣኔዎቹ እየታወቀ የመጣው የፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት ከመሻሻል ይልቅ ቁልቁል መውረዱን ሥራየ ብሎ የተያያዘው እንደኾነ ሂደቶቹ ኹሉ ምስክሮች ናቸው፡፡ ለዚህም ማሳያ የሚኾነው በኅዳር ፲፮ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም. በቁጥር 951/16187/2008 ማኅበረ ቅዱሳን “ኢቢኤስ” እየተባለ በሚጠራው የሳተላይት ቴሌቪዥን ያሠራጭ የነበረውን መርሐ ግብር በተመለከተ ማብራሪያ እንዲሰጥበት ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ለቀረበለት ጥያቄ የሰጠው ምላሽ ነው፡፡
ፓትርያርኩ ራሳቸው ፈርመውበት ባወጡት ደብዳቤ ለጥያቄው ምላሽ ሲሰጡ የተጠቀሙት ቃል እጅግ አነጋጋሪ እና በቸልታ ሊታይ የማይገባ ነው፡፡ በቀን ፳፫/፫/፳፻፰ በቁጥር ል/ጽ/117/ 300/2008 ግልባጭ ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት በማድረግ የተጻፈው ይህ ደብዳቤ እውን ቀኖናዊት፣ ሐዋርያዊት ከኾነች ቤተ ክርስቲያን ጽ/ቤት የሚወጣ ነውን? ያሰኛል፡፡
ደብዳቤው “የማኅበሩ ሕገ ደንብ ቀርቦ ያልጸደቀ ከመኾኑም በላይ” የሚል ማጣፊያ ያጠረው ሐረግ በዋና ማብራሪያነት ተሰንቅሮ ይነበብበታል፡፡ ይህ አባባል በጥቂቱ ሁለት መሠረታዊ ችግሮች ይታዩበታል፡፡ አንደኛው የማኅበሩን ሕልውና መካድ እና ሁለተኛው ኢ-ቀኖናዊነት!
በእርግጥ ማኅበሩ ደንቡ እንዲሻሻልለት ለሚመለከተው አካል አቅርቦ በተሰጠው ይሁንታ መሠረት ቅዱስ ሲኖዶስ ተወያይቶበት ውክልና በተሰጠው አካል እየታየ መኾኑ ይታወቃል፡፡ ይኽ ማለት ግን ማኅበሩ አሁን “ደንብ አልባ” ነው ማለትን ፈጽሞ አያስከትልም፡፡ አሠራርን የማያውቁ አካለት እንዲህ ብለው ቢናገሩ አለማወቅ ነው ይባል ነበር፡፡ “ሕግ ይወጽእ እም ጽዮን” የሚባልላት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ለዚህ አሠራር እንግዳ አይደለችም፡፡ ደረጃዋን ያገናዘበ ተዋናይ ካላጣች በስተቀር!
በረቂቅነት ቀርቦ በመታየት ላይ ያለው ደንብ እስኪሻሻል ድረስ ነባሩ ሕገ ደንብ እንደሚሠራ በየትኛውም አሠራር የታወቀ ነው፡፡ ነባሩ ሕገ ደንብ እንዳይሠራ የሚወሠንበት ጊዜም አለ፡፡ እርሱም በቂ ምክንያት ቀርቦበት ሥልጣን ባለው አካል ጊዜአዊ ማዕቀብ /Temporary Suspension/ ሲደረግበት ነባሩ ሕግ ለተወሰነ ወይም ላልተወሠነ ጊዜ እንዳይሠራ የሚደረግባቸው ጊዜያት አሉ፡፡ ይኸም የሚደረገው ነባሩ ሕግ በሥራ እንዲውል ከተደረገ ሊያመጣ የሚችለውን አደጋ ግምት ውስጥ ያስገባ እንደኾነ ነው፡፡
ሲጀመር ማሻሻያውን የጠየቀው ራሱ ማኅበሩ እንጂ ከላይ በትዕዛዝ መልክ ያልወረደ መኾኑ ምንም ለስጋት የሚያበቃ ክስተት ሊፈጠር እንደማይችል ያመላክታል፡፡ ሲቀጥልም ረቂቁን የተመለከተው የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ለዝርዝር ጥናት እና ምልከታ ወደኮሚቴ ሲመራው የታየው ምንም ዓይነት ስጋት ስላልነበር ነባሩን ሕግ ማቀብ አላስፈለገውም፡፡ በዚህ ሁኔታ “የማኅበሩ ሕገ ደንብ ቀርቦ ያልጸደቀ” ነው ብሎ መናገር ከየትኛው ምንጭ ሊቀዳ እንደሚችል ለመገመት ያስቸግራል፡፡ አንድ ነገር ግን እርግጥ ነው – ከጤናማ አመለካከት እንዳልተቀዳ!
ረቂቁ ሕገ ደንብ ሊሻሻልም ላይሻሻልም ይችላል፡፡ እስከዚ ድረስ ግን ነባሩ ምንም ሳይጨመርበት ምንምም ሳይቀነስበት የመሥራት ሙሉ ሥልጣን አለው፡፡ ስለዚህ ማኅበረ ቅዱሳን የጸደቀ ደንብ ያለው አካል እንጂ በደብዳቤው ላይ እንደተባለው ደንብ አልብ ማኅበር አይደለም፡፡ ማኅበረ ቅዱሳንን መጥላት ሕልውናውን መካድ ሊኾን አይችልም፡፡ ማኅበረ ቅዱሳንን መቃወም ማለት ደንብ የለውም ብሎ ከኾነ ራስን ከግምት በታች ማውረድ ይኾናል፡፡ ሰይጣንን መጥላት ማለት ሰይጣን የለም ከማለት ጋር እኩል አይኾንም፡፡ ሰይጣን መኖሩን ዐውቆ ሰይጣንን መቃወም ይገባል፡፡ ሰይጣንን የምንቃወመው በአድማ ሳይኾን በዓላማ ነው፡፡ ስለዚህ ለመቃወማችን በቂ አመክንዮ ለማቅረብ አንቸገርም፡፡ ማኅበረ ቅዱሳንን የሚጠሉ ሰዎችም ማኅበሩ የለም ወይም ሕገ ደንብ የለውም ከማለት የሚጠሉበትን ምክንያት ቢነግሩ ምላሹን ባገኙ ነበር፡፡ በሚበቃ ምክንያት የሚጠሉት ወይም የሚቃወሙት ካሉ ከእነርሱ አመክንዮ በመነሣት ራሱን ለማረም ችግር የለበትም፡፡ በማይበቃ ምክንያት የሚጠሉት ካሉ ደግሞ ራሳቸውን እንዲያርሙ ዕድሉን ይሰጣቸዋል፡፡ ከሁለቱ አፈንግጦ “ሕልውናውን መካድ” ግን የማያዋጣ የፈሪ ብትር ይኾናል፡፡
የማኅበረ ቅዱሳን ደንብ ሲጸድቅ በግርግር ሳይኾን ሥርዓቱን እና ደረጃውን ጠብቆ ነው፡፡ መጀመሪያ ረቂቁ ለሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ቀረበ፡፡ መምሪያው ማሻሻያ እና ማረሚያውን ካደረገበት በኋላ ለጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ቀረበ፡፡ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ አስፈላጊውን እርምት እና ማሻሻያ ካደረገበት በኋላ ለቅዱስ ሲኖዶስ ተመራ፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ በምልዓተ ጉባኤው አንቀጽ በአንቀጽ ከተወያየበት በኋላ ተገቢውን ማሻሻያ አድርጎበት በ፲፱፻፺፬ ዓ.ም. አጸደቀው፡፡ በጉባኤው ላይ የነበሩ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ፊርማቸውን አኑረውበት ሥራ ላይ እንዲውል ለሚመለከታቸው ሁሉ ተሠራጨ፡፡ ለዚህም ራሴ የዐይን እማኝ ቋሚ ምስክርም ነኝ፡፡
በዚህ ሥርዓታዊ አካሄድ የጸደቀ ሕገ ደንብ ያለውን ማኅበር ደንብ የለውም ብሎ መናገር እንደምን ይቻላል? ደንብ የለውም ብሎ መናገር የማይቻል ከኾነ ደግሞ የለውም ማለት ኢ-ቀኖናዊነት ነው፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ ራሱ ያጸደቀውን በፊርማው ያተመውን ሕገ ደንብ የለም ብሎ የሚያስብ አካል መኖሩ በራሱ አነጋጋሪ ነው፡፡ በምልዐተ ጉባኤ የተወሠነን ሕገ ደንብ እንደ ቀልድ በአንዲት ብጣሽ ወረቀት የለም ማለት የቅዱስ ሲኖዶስን ውሣኔ አልቀበልም ከማለት በቀር ሌላ ፍቺ አንፈልግለትም፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ ለወሠነው ውሣኔ መገዛት እንጂ ማመጽ አይቻልም፡፡ አመጻው ካለ ግን ኢ-ቀኖናዊነት ስለኾነ ፈጣን እርማት ያስፈልገዋል፡፡
ሕልውናው የተካደው ማኅበርም አለሁ ማለት ሳይበጀው አይቀርም፡፡ ምክንያቱም እርምጃዎቹ ሁሉ ሲደመሩ ወደ አንድ አቅጣጫ እያመሩ እንደኾነ ያሳብቃሉና፡፡ ራሱ ሳይናገር ሌሎች ሊናገሩለት አይችሉም፡፡ እናም መጠበቅ የለበትም፡፡ ምክንያቱም የታሰበበት እና ኾን ተብሎ እየተደረገ ያለ ጉዳይ ስለኾነ፡፡ በማኅበሩ ላይ በዚህ መንገድ የሕልውና ጥያቄ ማንሣት ከመሳሳት በላይ ነው፡፡ “ሕልሙ እና ፍቺው” ከዚህ በጣም ይርቃል፡፡ በየትኛውም አቅጣጫ ማኅበሩን ለመውጋት ከሚቆሙ አማሳኞች እና ሐራጥቃ ተሐድሶዎች ጋር ለመቆም የማይዳዳው አካል ርቆ ሳይሄድ ሳይቃጠል በቅጠል ሊባል ይገባል፡፡

Thursday, January 14, 2016

የወልቃይት ኮሚቴ ተወካዮች ኮሚቴ አባላት ወደ አካባቢቸው በሰላም ለመመለስ መቸገራቸው




ኢሳት ዜና :- “የወልቃይት ሕዝብ አማራነቱ ይከበርለት” በማለት ካለፉት ስድስት ወራት ወዲህ በፌዴራልና በአማራ ክልል እየቀረቡ አቤቱታ ሲያሰሙ የነበሩ የኮሚቴ አባላት ወደ አካባቢቸው በሰላም ለመመለስ መቸገራቸው ታውቋል። “የወልቃት ሕዝብ አማራ ነው፣ በትግራይ ክልል ሊተዳደር አይገባም” በማለት ጥያቄ ያነሱት ተወላጆች፣ የትግራይ ክልል አሁንም ጥያቄ የሚያቀርቡ ወገኖችን በተናጠልና በጋራ በማጥቃትና በማሳደድ ስራ በመጠመዱ ምክንያት የኮምቴ አባላቱ ያለስጋት ለመንቀሳቀስ አለመቻላቸው ታውቋል። ባለፈው ህዳር ወር 2008 ዓ.ም የወልቃይት ተወካዮች በአዲስአበባ በመገኘት ቅሬታቸውን ለፌዴሬሽን ምክርቤት እና ለመንግስታዊው የሰብኣዊ መብት ኮሚሽን በጹሑፍ ያቀረቡ ሲሆን፣ በፌዴሬሽን ም/ቤት በኩል አቤቱታው በቅድሚያ ለትግራይ ክልል ቀርቦ በክልሉ በኩል ለፌዴሬሽን ም/ቤት መቅረብ እንዳለበት በቃል ምላሽ ማግኘታቸው ታውቋል፡፡ ሆኖም የኮሚቴ አባላቱ የማንነት ጥያቄውን ከአርበኞች ግንቦት ሰባት አባልነት ጋር አያይዞ ከሚያየው የትግራይ ክልል ጋር ለመነጋገር የደህንነት ዋስትና ችግር ስለገጠማቸው አቤቱታውን ለማቅረብ እንዳልቻሉ እየገለጹ ነው። የወልቃይት ሕዝብ አማራነቱ እንዲከበር ለአማራ ክልል በተደጋጋሚ አቤቱታ ያቀረቡ ቢሆንም፣ የክልሉ መንግስት ችግሩን ለመፍታት አቅም ማነስ ብቻ ሳይሆን ጥያቄያችሁን አንሱ በማለት እያሳደረ ያለው ጫና ይበልጥ አበሳጭቷቸዋል። የአካባቢው ሹማምንቶች ህዝቡ ትግራዋይነቱን እንዲቀበል ለማድረግ የጠሩት ስብሰባ በተቃውሞ ተበትኗል። የአካባቢው ህዝብ ምንም አይነት ስብከት አንቀበልም፣ ጥያቄያችንን ብቻ መልሱልን ማለቱን የደረሰን ዜና ያመለክታል። ወልቃይት በሰሜን ተከዜ፣ በደቡብ ጠገዴ፣በምስራቅ የተከዜ ወንዝ፣ በምዕራብ አርማጮህና ሱዳን የሚያዋስኑት ሲሆን የአካባቢው ሕዝብ ባለፉት 23 ዓመታት የማንነት ጥያቄ አጠንክሮ በማቅረቡ ምክንያት ለእስርና ለሰብዓዊ መብት ረገጣ መጋለጡን ተወላጆች ይገልጻሉ።