Friday, February 5, 2016

አቶ በከር ሻሌ በዝግ ስብሰባ የኦሮሚያ ክልል አዲስ ርእሰ መስተዳደር ሆነው ተሾሙ


በኦሮሚያ እየተፈፀመ ያለውን ኢሰብአዊ ድርጊት ለመደበቅ እየሞከረ ያለው ህወሀት ኢህአዴግ ማክሰኞ እለት በዝግ በተካሄደው የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ስብሰባ ላይ ሙክታር ከድርን በማንሳት አቶ በከር ሻሌ የክልሉ ፕሬዚዳንት እንዲሆን በህወሀቶች መወሰኑን ታማኝ መረጃዎች አረጋግጠዋል
አቶ በከር ሻሌ ከዚህ ቀደም የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ከመሆናቸው በፊት በሚኒስትር ዴኤታነት የገቢዎችና ጉምሩክ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሆነው ለወራት የሰሩ ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተርነት ተነስተው ወደ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ተዛውረው እንዲሰሩ ተደርገው የነበሩት አቶ በከር፣ በጽሕፈት ቤቱ ለተወሰኑ ወራት በሚኒስትር ዴኤታነት ካገለገሉ በኋላ የአዳማ ከተማ ከንቲባ ሆነው መሾማቸውም የሚታወስ ነው፡፡
ከግንቦት 21 ቀን 2005 ዓ.ም. ጀምሮ ደግሞ በሙስና ወንጀል በሕወሐት ተከሰው የታሰሩትን አቶ መላኩ ፈንታ ተክተው የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዳይሬክተር የተደረጉ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በተመሣሣይ ሁኔታ የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት ባላወቀበት ሁኔታ የክልሉ ፕሬዚዳንት እንዲሆኑ በህወሀቶች የተወሰነ ሲሆን ምክር ቤቱም ከሰሞኑ ያፀድቀዋል ተብሎ ይታሰባል ከዚሁ ጋር በተያያዘ አቶ ሙክታር ከድር ወደሲቪል ሠርቪስ ሚኒስቴር ተዛውረው እንደሚሰሩም የተገኘው መረጃ ያስረዳል። አቶ ሙክታር ከድር በጅማ እና ኢሉ አባቡራ አካባቢ ከፍተኛ ደጋፊ የነበራቸው ሲሆን በአንፃሩ አቶ በከር ሻሌ ኦቦ ገብረመድህን እስከመባል ያደረሰ ሥር የሰደደ የሕወሐት ተላላኪ መሆናቸውንም ለማወቅ ተችሏል።

No comments:

Post a Comment