Tuesday, February 16, 2016

በፀገዴ ህወሓት ድባቅ የተመታችበት መድረክ ሁናለች።


ሰሞኑን በወልቃይት ጉዳይ ለመነጋገር የህወሓት ሊቀ መንበርና የትግራይ ኣስተዳዳሪ ኣቶ ኣባይ ወልዱና የብኣዴን ምክትል ሊቀመንበርና የኣማራ ክልል ኣስተዳዳሪ ኣቶ ደጉ ኣንዳርጋቸው በጎንደር ከተማ ከፍተኛ ፍጥጫ የተሞላበት ውይይት እንዳካሄዱ እየተገለፀ ነው።
በወልቃይት ጉዳይ ወደ ከረረ ፍትግያ የገቡት ሁለቱ መሪዎች በመጨረሻ ሰዓት ድል ወደ ኣቶ ደጉ ኣዘንብላለች።
ኣቶ ኣባይ ወልዱ ለ24 ዓመታት በትግራይ ክልል መስተዳድር ስር የነበሩት የፀገዴ ቀበሌዎች ወደ ኣማራ ክልል እንዲጠቃለል ሳይወዱ በግድ መፍቀዳቸው እየተገለፀ ይገኛል።
በዚህ መሰረት ማይደልየ፣ እምባገላ፣ ግጨው የሚባሉና ሌሎች ቀበሌዎች ለደጉ ለማስረከብ እንደተስማሙ እየተገለፀ ነው።
ፀገዴ ህወሓት በብኣዴን ድባቅ የተመታችበት መድረክ ሁናለች።
ኣየ ህወሓት………… ????
ነፃነታችን በእጃችን ነው።

No comments:

Post a Comment