Saturday, February 27, 2016

ሰበር_ዜና በአዲስ አበባ ላይ የስራ ማቆም አድማ ተጠራ።


በአዲስ አበባ ላይ የሚገኙ ታክሲዎች ኮድ 1 እና 3 እንዲሁም ሀይገር ባሶችን በዋናነት የተጠራ ቢሆንም ሌሎችንም አሽከርካሪዎች ያካተተ ከሰኞ የሚጀምር ለሁለት ቀናት የሚቆይ የስራ ማቆም አድማ ተጠርቶዋል።
አዲሱን የትራንስፖርት ህግ በመቃወም የስራ ማቆም አድማው የተጠራ ሲሆን በሁሉም አቅጣጫ ለሚንቀሳቀሱ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች መልዕክቱ በበራሪ ወረቀት ተበትኖ እንዲደርስ ተደርጎዋል። በተጨማሪም በአለም ገበያ ላይ ከፍተኛ የነዳጅ ዋጋ ቅናሽ ቢታይም በኢትዮጵያ ግን ይሄ ነው የሚባል ቅናሽ አልተደረገም የሚል ጥያቄም አብሮ ተነስቶዋል።
የ1966 አብዮት ሲካሄድ ይሄ ሆነ የታክሲ አሽከርካሪዎች በነዳጅ ላይ የተጣለውን ጭማሪ በመቃወም የስራ ማቆም አድማ መቱ።
 

No comments:

Post a Comment