----------------------------------------------------
በአዲስ አበባ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ቢሮ በወታደራዊ ኮማንዶዎች ተከቦ እየተፈተሸ ይገኛል፡፡
በአዲስአበባ የሚገነው እና በዶክተር መረራ ጉዲና የሚመራው የኦሮሚያ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ቢሮ በወታደራዊ ኮማንዶዎች ተከቦ እየተበረበረ ሲሆን የጽ/ቤቱን ሃላፊ ጨምሮ የቢሮ ሰራተኞች እንዲሁም በቢሮ ውስጥ የነበሩ አባላት በወያኔ ኮማንዶዎች ቁጥጥር ስር ውለዋል::የተያዙት አባላት ከፍተና ድብደባ እና መጉላላት እየተደረገባቸው መሆኑን ከአካባቢዉ የሚገኙ የአይን እማኞች ገልጸዋል፡፡ የድርጅቱ ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና በቢሮ ውስጥ አልተገኙም፡፡
በኦሮሚያ እየተካሄደ ያለዉ ሕዝባዊ እንቢተኝነት ዛሬም ተቀጣጥሎ ቀጥሏል፡፡ በምሰራቅ ሀረርጌ ዞን በበደኖ ከተማ መገዶች ሁሉ የተዘጋጉ ሲሆን በጉራዋ ወረዳ ተቃውሞ በተጠናከረ መልኩ ቀጥሎዋል በዛሬው እለት 6:30 ሃራ ሆርዳ በሚባል በቀበሌ በገንዳ ሸንዳ ከተማ ውስጥ የሚገኝ የመንግስት ሃይሎች በአስከፊ ሁኔታ እርምጃ እየወሰዱ መሆኑን ከአካባቢዉ የተገኙ መረጃዎች ለማወቅ ተችሏል፡፡ በዚሁ የመንግስት ልዩ ሃይሎች በወሰዱት እርምጃ ሙስአብ አብዱረዛቅ የተባለ ሰው የገደሉ ሲሆን ሌላም ሰውም ያቆሰሉ በከፍተኛ ደረጃ መቁሰሉ ታዉቁአል፡፡ በየክፍለ ሃተሃገሩ የሚገኙ የወንጌላውያን ቤተክርስቲያናት በሰንበት ፕሮግራማቸው ግድያውን በማውገዝ በጸሎት ሟቾችን እያሰቡ መሆኑ ታውቋል፡፡
ድል ለጭቁን ሕዝቦች !!!
No comments:
Post a Comment