Friday, February 19, 2016

አምቦ እስር ቤት ተቃጠለ | ከተማዋ በጥይት ድምጽ ተወጥራለች


በአምቦ ከፍተኛው ተቃውሞ በቀጠለበት በዚህ ወቅት በከተማዋ የሚገኘው እስር ቤት በ እሳት እየነደደ መሆኑን የዘ-ሐበሻ ምንጮች አስታወቁ::
በተለምዶው ቀበሌ 06 ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚገኘው ይኸው የፖለቲካ እስረኞች ማሰቃያ እስር ቤት ውስጥ ከኦሮሞ ሕዝብ ንቅናቄ ጋር በተያያዘ የታሰሩ በርካታ ወገኖች እንደደሚገኙበት ምንጮች አስታወቀዋል::
በአምቦ ከተማ በአሁኑ ወቅት የጥይት እሩምታ እየተሰማ ሲሆን  ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስም በ እስረኞች ላይ ከባድ ጉዳት ስለመድረሱ የታወቀ ነገር የለም:: ሆኖም ግን እሳቱ እየተዛመተ ባለበት ወቅት እንኳ እስረኞቹ እሳት እንዳያጠቃቸው ከቦታ ቦታ ለማዘዋወር ከበላይ ት ዕዛዝ ካልመጣ በስተቀር የአካባቢው ፖሊሶች ፈቃደኛ እንዳልሆኑ ይነገራል::

No comments:

Post a Comment