Friday, February 5, 2016

በሐዋሳ ከተማ ትናንት ለሊት የተቃውሞ ወረቀቶች ሲበተኑ አደሩ::


በሐዋሳ ከተማ ትናንት ለሊት የተቃውሞ ወረቀቶች ሲበተኑ አደሩ:: በተለይ በመንግስታዊ ተቋማት; ፖሊስ እና ወታደሮች በሚኖርባቸው ቦታዎች እንዲሁም በየትምህርት ቤቱ የተበተነው ወረቀት እንደሚያሳየው የሕዝቡን መቆጣትና በ ስር ዓቱ መሰላቸቱን ነው::
ሐዋሳ
የተለያዩ መፈክሮችን የያዘው ይኸው ወረቀት “ሙሰኛ መንግስት መልካም አስተዳደር የማስፈን አቅም የለውም!” “የዜጎች ጅምላ ፍጅት ዛሬውኑ ይቁም!”; “በግፍ ለተገደሉ ንፁሀን ዜጎቻችን ቤተሰቦች የደም ካሳ ይከፈል”; “የኢትዮጵያ ህዝብ ከወንጀለኛው ፋሽሽት የወያኔ መንግስት ጋር አይደራደርም!” ; “የኦሮሚያ ነፃነት ትግል የሁሉም ክልሎች ትግል አካል ነውና በሰላማዊ ሰልፍ እንደግፍ” እና “ህዝባዊ መንግስት ይቋቋም” የሚሉ መል ዕክቶችን የያዘ ነው::
አንዳንድ ወገኖች ወረቀት መበተኑ ዋጋ የለውም በማለት በየቦታው የሚደረጉትን ወረቀት ብተናዎች ቢቃወሙም መንግስት ሚድያውን ዘጋግቶና ተቆጣጥሮ ሕዝብ ድምጹ ሲታፈን በ እንዲህ ያለው ሁኔታ ወረቀት እየበተኑ ድምጽን ማሰማት የሚደገፍ ነው የሚሉ በርካቶች ናቸው::
ተዛማጅ ፅሁፎች:
በራሪ ወረቀት የበተነው የሰማያዊ አባል 2 ወር ከ10 ቀን ቅጣት ተበየነበት
በአዲስ አበባ በተለያዩ አካባቢዎች መፈክር የተፃፈባቸው ወረቀቶች ተበትነው አደሩ
ነገ አርብ ሜይ 9 በሚኒሶታ በሚደረገው ሰልፍ ኢትዮጵያውያን ተገኝተው ድምጻቸውን በጋራ እንዲያሰሙ ጥሪ ቀረበ
ኢሕአፓ ወክንድ “በኤርትራ በኩል ትግል ማድረግ ይቻላል ወይስ አይቻልም?” በሚለው ጉዳይ ለመወያየት በቺካጎ ሕዝባዊ ስብሰባ ጠራ

No comments:

Post a Comment