Saturday, February 27, 2016

በደብረ ብርሃን ከተማ የህዝብ ማመላለሻ ሚኒባስ ከሲኖትራክ የጭነት መኪና ጋር ተጋጭተው የ15 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለጸ ፡፡


በደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ቀበሌ 08 ልዩ ስሙ አዲስ አምባ አካባቢ አንድ የህዝብ ማመላለሻ ሚኒባስ ከሲኖትራክ የጭነት መኪና ጋር ተጋጭተው የ15 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለጸ ፡፡
የደ/ብርሃን ከተማ አስተዳር ፖሊስ በጽህፈት ቤቱ የመንገድ ትራፊክ ደህንነት አስተበባሪ ዋና ኢንስፔክተር ረጋሳ ኤዶሳ እንደተናገሩት የሰሌዳ ቁጥር አማ ኮድ 3 07902 የሆነ የህዝብ ማመላለሻ ሚኒባስ ከከሚሴ ወደ ደብረ ብርሃን በመጓዝ ላይ እያለ ከደ/ብርሃን ወደ ቀይጥ ሲጓዝ ከነበረ ኢቲ 72320 ሲኖትራክ የጭነት መኪና ጋር በግምት ከጠዋጡ 3፡10 ገደማ ተጋጭተው የ14 ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ በደ/ብርሃን ሪፈራል ሆስፒታል እርዳታ እየተደረገላት የነበረች የአንዲት መንገደኛም ህይወት ደግሞ በተጨማሪ አልፏል፡፡
አደጋው የ15 ሰዎች ህይወት ያለፈበትና ሁለት ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት ያደረሰ ነበር፡፡ የአደጋው መስኤ የህዝብ ማመላለሻው ሚኒባስ ከፊቱ የነበሩትን ሁለት ተሸከርካሪዎችን ደርቦ ያለመስመሩ ለማለፍ ባደረገው ሙከራ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ይህ ዘግናኝ አደጋ የተከሰተው ከአሽከርካሪዎች የጥንቃቄ ጉድለት ስለሆነ በቀጣይም ሌላ ተመሳሳይ አደጋ እንዳይከሰት አሽከርካሪዎች ለሚያጓጉዙት ሰው ህይወት ትልቅ ዋጋ ሰጥተው በጥንቃቄና በኃላፊንት ስሜት ማሽከርክር ይጠበቅባቸዋል ሲሉ ዋና ኢንስፔክተር ረጋሳ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
የደ/ብርሃን ከተማ አስተዳደርም በደረሰው ዘግናኝ የመኪና አደጋ በእጅጉ ያዘነ ሲሆን በአደጋው ምክንያት ህይወታቸው ላለፈ ቤተሰቦች መጽናናትን ይመኛል፡፡

No comments:

Post a Comment