Sunday, February 21, 2016

የኦፌኮ የአዲስ አበባ ቢሮ በወታደሮች ተወረረ -መረራ ጉዲና ቢሮ አልነበሩም

በዛሬው የክብ ጠረጴዛ ውሎዋ ሚሚ ስብሐቱ በኦሮሚያ በመካሄድ ላይ የሚገኘውን ተቃውሞ በገንዘብና በቁሳቁስ በውጪ የሚገኙ ኃይሎች እንደሚረዱ ይህንን እርዳታም በአገር ውስጥ በሰላማዊ መንገድ ለመታገል የተመዘገቡ ፓርቲዎች ህጋዊነታቸውን ከለላ በማድረግ ገንዘቡንና ቁሳቁሱን እንደሚያከፋፍሉ ገልፃ ነበር ።
ከነበረኝ ልምድ በመነሳትም የሚሚን ቱልቱላ ተከትሎ አንድ ፓርቲ ኢላማ እንደሚሆን እየጠበቅሁ ነበር ።ጥበቃዬ ብዙ ሳይቆይ የፕሮፌሰር መረራ ኦፌኮ በድጋሚ የስርዓቱ ጡጫ ሊያርፍበት መንገድ መጀመሩን የሚያሳይ ዜና ተገኝቷል ።
የኦሮሚያውን ተቃውሞ ተከትሎ ኦፌኮ ብዙ ዋጋ ከፍሏል ።አባላቱ ተገድለውበት አመራሮቹ እነበቀለ ገርባ ወህኒ ወርደውበታል።
ዛሬ ደግሞ ሸገር የሚገኘው ዋና ቢሮው በወታደሮች ተወርሮ ፅህፈት ቤቱ ውስጥ የነበሩ ሰዎች ድብደባ ተፈፅሞባቸው ተወስደዋል ።መረራ ጉዲና በቢሮው አለመኖራቸው ቢታወቅም በቀጣይ ምን ሊደረግ እንደሚችል አይታወቅም ።

No comments:

Post a Comment