Monday, February 29, 2016

በሰሜን ጎንደር ዳባት ሕዝባዊ እምቢተኝነት ተቀሰቀሰ | ወደ መቀሌና ሽሬ የሚወስዱ መንገዶች ተዘጋግተዋል


በሰሜን ጎንደር ዳባት ሕዝባዊ እምቢተኝነት መቀስቀሱን ከአካባቢው የሚመጡ መረጃዎች አስታወቁ:: ምንጮች  እንደሚገልጹት ወደ መቀሌና ሽሬ የሚወስዱ ወይም ከዚያ ወደ ዳባት የሚያመጡ መንገዶች ተቃውሞውን ባነሳው ሕዝብ በድንጋይ እና በ እንጨት መዘጋጋቱ ተሰምቷል::
በዳባት ከተማ ሕዝቡ ሕዝባዊ እምቢተኝነቱን ያነሳው ከወልቃይት መሬት እና ከመልካም አስተዳደር ጋር በተያያዘ እንደሆነ ከስፍራው የሚመጡ መረጃዎች ጠቁመው ሕዝባዊ ቁጣው እስከ እኩለሊት ድረስ እንደቀጠለ  ምንጮች አስታውቀዋል::
ይህን ጉዳይ ተከታትለን እንዘግባለን::

No comments:

Post a Comment