Thursday, February 18, 2016

ሰበር ዜና ወደ ጎንደር እና አምቦ የሚያደርሱ በርካታ መንገዶች በሰልፈኞች ተዘጋግተዋል::

እየተጋጋለ የመጣዉ የኦሮሚያ ክልል ህዝብ አመፅ ወደ መንገዶች መዘጋጋት ተሸጋግሯል በዚህ ተቃዉሞ አሁንም በርካታ አንድን ከተማ ከአንድ ከተማ የሚያገናኙ መንገዶችን በመዝጋት የቀጠሉ ሲሆን በደረሰን መረጃ መሰረት ወደ ጉንደር እና አምቦ የሚያደርሱ መንገዶች ሙሉ በሙሉ ተዘግተዋል::
ሰልፈኞች በፌደራል ፓሊስ ወታደሮች የሚደርስባቸዉን የጥይትና የዱላ ድብደባ ሳይበግራቸዉ አሁንም ይህንኑ የመንገድ መዝጋቱን ተቃዉሞ በተለያዩ ከተምችም እንደሚያደርጉት እየተጠበቀ ነዉ:: ወደ ጎንደር እና አምቦ ከሚያደርሱ መንገዶች በተጨማሪ በወለጋ ሆሮጉድሩ ጃራቴ ወረዳና በምእራብ አርሴ ዋዴና ኤዶ ከተሞች ምስራቅ ሀረርጌ መንገዶች በሰልፈኞች ተዘጋግተዋል::
 

No comments:

Post a Comment