Monday, February 29, 2016

የኢትዮጵያ ስደተኖች ማህበር ሊቀመንበር ከስውዲን ሃገር ለቀው እንዲወጡ የስውዲን ኢምግሬሽን ቦርድ ወሰነ። ይህ ያልተጠበቀ ውሳኔ ብዙ ኢትዮጵያዊያኖችን አስቆጥቶል።


አቶ ኤፍሬም አክሊሉ የኢትዮጵያ ስደተኖች ማህበር ሊቀመንበር ከመሆናቸዉም በተጨማሪ ምንም እንኩዋን በአም ሃገራት ተቀባይነትን ባያገኝም በኢትዮጵያ መንግስት በሽብርተኝነት ከተፈረጀዉ አርበኞች ግንቦት 7 አባል በመሆን ድርጅቱ በሚያካሂዳቸዉ እንቅስቃሴዎች ዉስጥ በከፍተኛ ንቃትና ተሳትፎአቸዉ የሚታወቁ ሲሆን በስዊድን ሃገር የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ላይ በተመሰረተው ክስ ላይም የጎላ ተሳትፎ ማድረጋቸዉ የአደባባይ ምስጢር ናቸዉ።
አቶ ኤፍሬም አክሊሉ በስዊድን እስቶኮልም እና በአከባቢው በሚደረጉ የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች ንቁ ተሳታፊ በመሆን በኢትዮጵያ ሃገራችን ላይ የተንሰራፋውን እጅግ አስከፊ አንባገነናዊ አገዛዝ ከሃገራችን እንዲነቀል ባለበት ሃገር በሙሉ አቅማቸዉ የሚሰሩ ጠንካራና ፀኑ አላማ ያነገቡ የግፈኛዎች እራስ ምታት የሆኑ ኢትዮጵያዊ መሆናቸዉ  በዚህም ምክንያት ግፈኛዉ ኢትዮጵያ መንግስት በስዊድን ሀገር በሚገኘዉ ኤንባሲዉ አማካኝነት ከዚህ ስራቸዉ እንዲታቀቡ በተደጋጋሚ የማስፈራራት ጥረቶችን ማድረጉ ይታወቃል። ከዚህም በተጨማሪ ኤንባሲዉ በሚያዘጋጃቸዉ ማናቸዉም ዝግጅቶች ላይ እንዳይገኙ እቀባ ተደርጎባቸዋል። እንደማሳያነትም  በ12/12/2015 ቀን የኢትዮጵያ ኤንባሲ ባዘጋጀዉ የብሔር ብሔረሰቦች በዓል ላይ አቶ ኤፍሬም እንደ አንድ ዜጋ በቦታዉ በተገኙበት አጋጣሚ በአንባሳደር ወይንሸት ታደሰ ቀጥተኛ ትእዛዝ የኤንባሲ ቅትረኞች ክብራቸዉን በማዋረድ ስብናቸዉን በመግፈፍ ከአዳራሽ ተጎትተዉ እንዲወጡ መደረጉ የቅርብ  ጊዜ ተዝታ ነዉ።
በዚህ ደረጃ በኢትዮጵያ አንባገነናዊ መንግስት የሚፈለን ግለሰብ ወደ ኢትዮጵያ መመለስ ማለት ለጅብ ስጋ እንደማቅረብ ነው! ይህ ፍፁም ሰብዓዊነት የጎደለው እና ኤፍሬም አክሊሉ ለግፈኛ ጨቃኝ መንግስት ለሞት አሳልፎ የሚሰጥ ውሳኔ ለሰብአዊነት ትኩረት ከምትሰጥ ሃገር ስዊድን የማይጠበቅ ነው።  ይህም የዓለም አቀፍ የስደትኞች መብትን የሚፃረር ከመሆኑም በላይ በስውዲን ሀገር የተወለዱ ልጆቹን ከአባታቸው ጋር አብረው የመኖር መብትንም የሚጋፋ ነው።
የኢትዮጵያ የስደተኖች ማህበር በሊቀመንበሩ ላይ የስዊድን ማይግሬሽን ቦርድ የወሰነውን ውሳኔ አጥብቆ የቃወማል ጉዳዩንም በጥሞና ተመልክቶ ውሳኔውን  እንደሚቀይር እምነቱ የፀና ነው።
20150530_223137
20151218_133700
20150530_222948
20150501_140807
20150501_140807
20150501_140820
20150501_140820
944034_182822462075886_156154842781888844_n
image-62e69fe2ebfedd51525b29bed659675a2cea6226537493a0fbb6b633211a298e-V[1]
image-781241ca66e34d0a87d401e4a7ff28aa6cc74f5c82e28b17f45115b941aee54e-V[1]
image-e7d15b448597b66de6823f563f71c3132e6cf1f70df368d7cd8fa5ff8617c82f-V[1]

ሰበር ዜና በአዲስ አበባ ታክሲዎች የስራ ማቆም አድማ አደረጉ


በትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰሩ ታክሲዎች በወሰዱት የስራ ማቆም አድማ መንግስት ለማስፈራራትና ወደ ስራ እንዲገቡ ከፍተኛ ዛቻዎችን ቢያደርግም የቆረጡት የታጅሲ ሹፌሮች አድማውን ተግባራዊ አድርገዋል።
በተያያዘም በአውቶቢስ ተራ አካባቢ ከአድማው አፈንግጠው ለመስራት የሞከሩ አምስት ታክሲዎች ላይ በአደራጆቹ በተደራጃ እርምጃ ወሳጅ ኃይል እርምጃ ተወስዶባቸዋል። የካቲት21/2008

በሰሜን ጎንደር ዳባት ሕዝባዊ እምቢተኝነት ተቀሰቀሰ | ወደ መቀሌና ሽሬ የሚወስዱ መንገዶች ተዘጋግተዋል


በሰሜን ጎንደር ዳባት ሕዝባዊ እምቢተኝነት መቀስቀሱን ከአካባቢው የሚመጡ መረጃዎች አስታወቁ:: ምንጮች  እንደሚገልጹት ወደ መቀሌና ሽሬ የሚወስዱ ወይም ከዚያ ወደ ዳባት የሚያመጡ መንገዶች ተቃውሞውን ባነሳው ሕዝብ በድንጋይ እና በ እንጨት መዘጋጋቱ ተሰምቷል::
በዳባት ከተማ ሕዝቡ ሕዝባዊ እምቢተኝነቱን ያነሳው ከወልቃይት መሬት እና ከመልካም አስተዳደር ጋር በተያያዘ እንደሆነ ከስፍራው የሚመጡ መረጃዎች ጠቁመው ሕዝባዊ ቁጣው እስከ እኩለሊት ድረስ እንደቀጠለ  ምንጮች አስታውቀዋል::
ይህን ጉዳይ ተከታትለን እንዘግባለን::

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ተፈቅዶ የነበረው ጥየቃ በድጋሚ ተከለከለ፡፡


የካቲት 20/2008 ከወደ ዝዋይ-ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ -ውብሸት ታዬ ጨምሮ በዝዋይ የሚገኙ የህሊና እስረኞች ለመጠየቅ የቀድሞ አንድነት ፓርቲ አመራሮች እና አባላት ዝዋይ ማረሚያ ቤት በጠዋቱ ቢደርሱም ትንታጉ ብዕረኛ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ- እሱን መጠየቅ አይፈቀድም በማለት ተከለከሉ፡፡ ከተመስገን ውጪ ያሉትን የህሊና እስረኞች በመጠየቅ ተመልሰዋል፡፡ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በህመም እየተሰቃየ በወዳጅ ዘመን አድናቂዎቹ እንዳይጎበኝ ህገ-መንግስታዊ መብቱን በድብቁ የህውሓት ማፊያ ቡድን የክልከላ ወንጀል እየተፈጸመበት እንደሚገኝ ከወደ ዝዋይ የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ ክብር ለህሊና እስረኞቻችን ነገም ዛሬ መናገራችን አናቆምም፡፡
 

Saturday, February 27, 2016

ዓረና_መድረክ የጠራው ሰለማዊ የተቃውሞ ሰልፍ በህወሓት መሪዎች ታገደ።


ሰልፉ ከኤርትራ በመጡ ታጣቂዎች ታግተው ስለተወሰዱ ወጣቶች መታገት፤ የህግ ልእልና እንዲከበር፤ በረሃብ እያለቁ ስላሉ ወገኖቻችንና የኦሮምያ ክልል ስለተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ( ‪#‎Oromo_protest‬ ) ና እየተወሰደ ያለው ግድያና እስር ቆሞ መንግስት ከሚመለከታቸው እንደ መድረክ የመሰሉ ፖለቲካዊ ድርጅቶችና የህብረተሰብ ክፍሎች ድርድር እንዲጀምር የሚጠይቁ ኣጀንዳዎች ናቸው።
ህወሓቶች ለእገዳው የሰጡት ምክንያት፦
ሀ) “ወቅቱ ያልተረጋጋና ለግርግር የተመቸ ስለሆነ በኣሁኑ ስዓት የተቃውሞ ሰልፍ መፍቀድ ለሰላም ሲባል ኣይመረጥም።”
ለ) “በኣሁኑ ሰዓት መንግስት የግምገማ መድረኮች(ፅሬት) እያካሄደ ስለሆነ የፕሮግራም መደራረብ ያጋጥማል” የሚል መልስ ከከንቲባ ፅህፈት ቤት ሓላፊ ኣቶ ዘመንፈስቅዱስ ፍሰሃ ትናንት ወደ ፅህፈት ቤታቸው ጠርተው ገልፀውልኛል።
ኣቶ ዘመንፈስቅዱስ የእገዳው ውሳኔ በፅሁፍ ስጡን ብየ ስጠይቃቸው ” እኔ በቃል እንዳሳውቅ ነው ከኣለቆቼ የተነገረኝ ስለዚ በፅሑፍ ኣልሰጥህም። የሆነ እንቅስቃሴ ብታደርጉ ሰለማዊ ሰልፍ ሳይሆን ብጥብጥና ሁከት በከተማው ለማስነሳት እንደተሞከረ ይቆጠራል። ለዚህ የፀጥታ ሃይሎች ኣስፈላጊ እርምጃ እንዲወስዱ ታዝዘዋል” የሚል ዛቻ ኣዘል መልእክት ነግረውኛል።
ይሄ ነገር በፅሑፍ ካላሳወቃቹን ሰለማዊ ሰልፉ እናካሂዳለን። ብየ ከፅህፈት ቤቱ ወጥቼ ስሄድ ኣቶ ወላይ (ወላይ ጎት) የመቐለ ዞን የድህንነትና ፀጥታ ፅህፈት ቤት ሃላፊ ከህንፃው በር ጠብቆ “ምን ምላሽ ተሰጣቹ? ” ብሎ ጠየቀኝ።
እኔም ኣቶ ዘመንፈስቅዱስ “ሰለማዊ የተቃውሞ ሰልፉ ታግደዋል” ብሎ ብቃል ብቻ እንደነገረኝ ገለፅኩለት።
ኣቶ ወልዳይም “እና ምን ኣሰባቹ?” ኣለኝ።
እኔም ሰለማዊ ሰልፉ ለማካሄድ ወስነናል። በህጉ መሰረት ኣስተዳደሩ ደብዳቤው ከደረሰው በ12 ሰዓት ውስጥ ምላሽ መስጠት ነበረበት ይሁን እንጂ ኣላደረገውም።
ኣሁንም ውሳኔው በፅሑፍ ኣድርገው ስንለው “በቃል ብቻ እንድነግራቹ ነው ከኣለቆቼ የታዘዝኩት ብሎናል።
ስለዚ እኛ በኣንድ ኣለቃ የተሰጠ የቃል መመርያ ሳይሆን ህገ መንግስቱ በሰጠን መብት መሰረት ሰልፉ እናካሂዳለን። ለሰልፉ ተሳታፊዎች የጥሪ ቅስቀሳው ለመጀመር መኪና፣ ጀነሬተርና ምንታርቦ ድምፅ ማጉልያ ተከራይተናል። ስለዚ በእቅዱ መሰረት ሰልፉ ይካሄዳል ኣልኩት።
ኣቶ ወላይ ” በቃል ይሁን በፅሑፍ ሰለሚዊ ሰልፉ ኣታካሂዱም ከተባላቹ ኣታካሂዱም ነው። ማንኛውም ሰው ለሰልፉ ቅስቀሳ ኣካሂዳለው፣ ሰልፍ እወጣለው ካለ ኣስፈላጊ እርምጃ እንወስዳለን። የሚደርሰው ጉዳትም ዓረና_መድረክ ተጠያቂ ይሆናል። በዚህ ሰዓት ሰልፍ ማካሄድ ማለት ሁከትና ብጥብጥ ኣንስቶ የህዝቡ ሰላም መበጥበጥ ነው” በማለት ዛቻው ገልፆልኛል።
እኔም ሰልፉ ለማካሄድ የህግ ክፍተት ስለሌለን እናካሂደዋለን። ብየ ህንፃው ጥየ ወጣው።
በነገራችን ላይ ኣቶ ወላይ ማለት ከዓመት በፊት ከቤቴ ኣፍነው በመውሰድ የኣብራሃ ደስታ ኣሸባሪነት እንድመሰክር፣ እኔ ራሴም ኣሸባሪ እንደ ሆንኩና ትግራይ ሙሉ እየዞርኩ ህዝቡን ይቅርታ ካልጠየቅኩ በፈለጉት ሰዓት መጥተው ኣስረው በመውሰድና በኣሸባሪነት ክስ ከሰው እንደሚያስቀጡኝ በመግለፅና በጉዳዩ እንዳስብበት ኣስጠንቅቀው ከለቀቁኝ 4 የህወሓት የድህንነትና የፀጥታ ባለ ስልጣናት ኣንዱ ናቸው።
በሉ እንግዲህ “ለተቃውሞ ሰለማዊ ሰልፍ ግዜው ምቹ ኣይደለም ብጥብጥ ሊነሳ ይችላል?” የሚልና “ህወሓት የህዝብ ግምገማ(ፅሬት) እያካሄደ ስለሆነ” የሚሉ ተልካሻ ምክንያቶች በመደርደር ኣግደውታል።
ይሁንጂ በነሱ መስዋእትነት ወደ ስልጣን የወጡት የህወሓት ባለስልጣናት ህዝቡ ብሶቲ ለመግለፅ ኣንድ ሰለማዊ ሰልፍ ለማድረግ እንኳን ኣላስቻሉትም።
የትግራይ ህዝብ የውድ ልጆቹ መስዋእትነቱ ኣንድ ሰለማዊ ሰልፍ ለማድረግ ያህል እንኳን ዋጋ እንኳ ኣለመስጠታቸው ኣዝነዋል።
ኣቶ ጌታቸው ኣሰፋ የብሄራዊ ድህንነት ሃላፊ በ12ኛ የህወሓት ጉባኤ ” የትግራይ ህዝብ የፈለገው ኣጀንዴ ኣንግቦ ሃሳቡ በሰለማዊ ሰልፍ የመግለፅ መብቱ እስካሁን ኣልተከበረለትም። ካሁንዋ ሰዓት ጀምሮ መብቱ እንዲጠቀም መፍቀድ ኣለብን” ያለውና ጉባኤተኛው ያጨበጨበለት ንግግሩ ውሃ በልቶታል።
እና ሰለማዊ ስልፉ ከትናንት 10: 00 ጀምሮ እገዳ ተጥሎበታል።
የሰላም በር ሲዘጉ የዓመፅ በሮች ይከፈታሉ።
ነፃነታችን በእጃችን ነው።
it is so.

ከሕይወት ሞትን ለምን? ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም

ዓይን ያለው ያያል፤ ጆሮ ያለው ይሰማል፤ አእምሮ ያለው ያስባል፤ ልብ ያለው ስሜቱ ይነካል፤ ዓይን ካላየ፣ ጆሮ ካልሰማ፣ አእምሮ ካላሰበ፣ ልብ ካልተሰማው ሰውን ሰው የሚያደርገው ምንድን ነው? የትናንቱ ችግር መልኩን ለውጦ ሲመጣ፣ ትናንት ተሞክሮ ያልተሳካው የሕገ አራዊት መፍትሔ ዛሬ ዘመን ከተለወጠ በኋላ ይሠራል ብሎ መወራጨት ጥፋት ነው፤ ዓይን እያለ አለማየት ነው፤ ጆሮ እያለ አለመስማት ነው፤ አእምሮ እያለ አለማሰብ ነው፤ ልብ እያለ ስሜት ሲጠፋ ሰዎች ነን ወይ? ብሎ መጠየቅ ግድ ቢሆንም ያሳፍራል፤ካላፈርን ይበልጥ ያሳፍራል፡፡
ከአርባ ዓመት በፊት ለመላው አፍሪካ የሽማግሌና የአስታራቂ አገር የነበረችው ኢትዮጵያ በተከታታይ የአረም ጎረምሶች ትውልድ ተወርሳ እንኳን ለአፍሪካ በአጠቃላይና ለራስዋም የምትበቃ አልሆነችም፤ በአረም የተወረረች አገር!
ይኸ ሁሉ ትርምስ፣ ይኸ ሁሉ ጭካኔ፣ የማንን ጥቅም ለማስከበር ነው? ማንን ገድሎ ማንን ለማዳን ነው? ማንን አደህይቶ ማንን ለማበልጸግ ነው?
ትርፉ በአሜሪካም ሆነ በአውሮፓ የሚከተል ለልጅ ልጅ የሚተላለፍ ችኮ ጥላቻ፣ ቂምና በቀል ነው፤ የተገኘውም ሀበት ቢለብሱት እከክ፣ ቢበሉት ቃር እየሆነ በጸጸት አለንጋ እየተገረፉ መኖር ነው
Abel Shiferaw's photo.

ሰበር_ዜና በአዲስ አበባ ላይ የስራ ማቆም አድማ ተጠራ።


በአዲስ አበባ ላይ የሚገኙ ታክሲዎች ኮድ 1 እና 3 እንዲሁም ሀይገር ባሶችን በዋናነት የተጠራ ቢሆንም ሌሎችንም አሽከርካሪዎች ያካተተ ከሰኞ የሚጀምር ለሁለት ቀናት የሚቆይ የስራ ማቆም አድማ ተጠርቶዋል።
አዲሱን የትራንስፖርት ህግ በመቃወም የስራ ማቆም አድማው የተጠራ ሲሆን በሁሉም አቅጣጫ ለሚንቀሳቀሱ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች መልዕክቱ በበራሪ ወረቀት ተበትኖ እንዲደርስ ተደርጎዋል። በተጨማሪም በአለም ገበያ ላይ ከፍተኛ የነዳጅ ዋጋ ቅናሽ ቢታይም በኢትዮጵያ ግን ይሄ ነው የሚባል ቅናሽ አልተደረገም የሚል ጥያቄም አብሮ ተነስቶዋል።
የ1966 አብዮት ሲካሄድ ይሄ ሆነ የታክሲ አሽከርካሪዎች በነዳጅ ላይ የተጣለውን ጭማሪ በመቃወም የስራ ማቆም አድማ መቱ።
 

መምህር ግርማ ወንድሙ የማጥመቅ ስራቸውን በዛሬው ዕለት ጀመሩ!

ከእስር ከወጡ በሆላ የመጀመሪያ አገልግሎታቸውን ፉሪ ባለእግዚአብሄርና ኡራኤል ቤተክርስቲያን ስራቸውን በዛሬው ዕለት የጀመሩ ሲሆን በሺህ የሚቆጠሩ የእምነቱ ተከታዮች ወደስፍራው በመሄድ ስራቸውን በመጀመራቸው የተሰማቸውን ደስታ በዝማሬ ገልፀዋል!
እንደሚታወቀው የማጥመቅ ፍቃድ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክህነት እንደተሰጣቸው መዘገባችን የሚታወስ ነው;::

በዛሬ እለት ከመንግስት ቢሮ አፈትልኮ በወጣ መረጃ መሰረት አጠቃላይ የኦሮሚያ ክልል ከሲቪል አስተዳደር ወደ ወታደራዊ አስተዳደር መሸጋገሩ ታወቀ።


በዛሬ እለት የካቲት 19 /2008 በከፍተኛ የወያኔ የጦር መኮንኖችና : የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዘደንት በሆኑት በአቶ ሙክታር ከድር መካከል በተደረገ አስቸኳይ ስብሰባ ፣ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ከሲቪል አስተዳሩ ቁጥጥር ውጪ በመሆኑ የማስተዳደሩ ኃላፊነቱ በስምንተኛው የምድር ጦር ዲቪዥን ስር በሚገኙ የምድር ጦር ብርጌዶች እንዲሆን መወሰኑ ታወቀ ።
በስብሰባው ላይ የተገኙ የኦሮሞ ተወላጅ የሆኑ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ሃሳቡን የተቃወሙ ቢሆንም የሚሰማቸው ጠፍቶ ውሳኔው መወሰኑ ታውቋል ።
ከፍተኛ ሀይል በመጠቀምና ህዝቡን በመጨፍጨፍ ተቃውሞን ለማስቆም ታስቦ የተወሰነ ነው በተባለለት በዚህ ውሳኔ ቀድሞም ለይስሙላ እንደነበር የሚታወቀው የነ አቶ ሙክታር ስልጣን ሙሉ ለሙሉ ተቀምቶ በወያኔዎች ለሚመራው በስምንተኛው የምድር ጦር ስር ለሚገኙ የምድር ጦር ብርጌዶች ተላልፏል ።
ለህዝብ ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ቀጥቅጬ እገዛለው በሚል ያረጀ ያፈጀ እሳቤ እየተንቀሳቀስ ያለው የወያኔ መንግስት ያሰበው ጭፍጨፋ እንዳይሳካ መላው የኦሮሞ ህዝብና ሌሎች ሃገር ወዳድ ዜጎች በአንድነት በመቆም በቃህ ሊሉት ይገባል በማለት አንዳንድ አስተያየት ሰጭዎች መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ።

አምነስቲ ኢንተርናሽናል ኖርዌይ ለሰብዓዊ መብቶች መከበር ተገዢ እንድትሆን ጠየቀ


የኖርዌይ መንግስት በመቶዎቹ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ያለፍላጎታቸው ወደሃገራቸው ለመመለስ የያዘውን እቅድ ተከትሎ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ሃገሪቱ ለሰብዓዊ መብቶች መከበር ተገዢ እንድትሆን አሳሰበ። ሃገሪቱ በስደተኞች ላይ እየያዘች የመጣችውን አዳዲስ አቋሞች የተቸው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ ኖርዌይ ለአለም አቀፍ ህግጋት ተገዢ ያለመሆን አቅጣጫ እየተከተለች እንደሆነም አስታውቋል። ኖርዌይ ተግባራዊ ለማድረግ ያሰበችውን የስደተኞች አዲስ እቅድ ምክንያት በማድረግ የሃገሪቱ ባለስልጣናት ከ500 የሚበልጡ ኢትዮጵያውያን ያለፍላጎታቸው ወደሃገራቸው ለመመለስ መወሰናቸውን የኖርዌይ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆንስ ስቶልተንበርግ ስደተኞችን በአግባቡ ለመለየት በሚደረገው አካሄድ ወደሃገራቸው የሚመለሱ ሰዎች እንዳሉ በቅርቡ ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል። ይሁንና፣ ስደተኞችን ያለ-ፍላጎታቸው ወደሃገራቸው እንዲመለሱ ማስገደዱ ተገቢ አይደለም በሚል የተለያዩ አካላት በኖርዌይ መንግስት ላይ ቅሬታን እያቀረቡ የሚገኙ ሲሆን ውሳኔውም ማሻሻያ እንዲደረግበት አሳስበዋል። በኖርዌይ የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ፀሃፊ የሆኑት ጆን ፔደር ሃገሪቱ ልትነፃፀር የማይገባቸውን ሃገራት ድርጊት እየተከተለች ነው ሲሉ ተቃውሞ ማቅረባቸውን ኖርዌይ ቱዴይ የተሰኘ ጋዜጣ ዘግቧል። “እርምጃው አስፈሪ ነው” ሲሉ የገለጹት ሃላፊው ሃገሪቱ በስደተኞች ላይ የያዘችውን ዘመቻ በአስቸኳይ እንድታጤነው ጠይቀዋል። በኢትዮጵያ በኦሮሚያ ክልል የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ ተከትሎ ኖርዌይ ዜጎቿ በክልሉ እንዳይንቀሳቀሱ በተደጋጋሚ ማሳሰቢያን ስትሰጥ መቆየቷ ይታወሳል።

በደብረ ብርሃን ከተማ የህዝብ ማመላለሻ ሚኒባስ ከሲኖትራክ የጭነት መኪና ጋር ተጋጭተው የ15 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለጸ ፡፡


በደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ቀበሌ 08 ልዩ ስሙ አዲስ አምባ አካባቢ አንድ የህዝብ ማመላለሻ ሚኒባስ ከሲኖትራክ የጭነት መኪና ጋር ተጋጭተው የ15 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለጸ ፡፡
የደ/ብርሃን ከተማ አስተዳር ፖሊስ በጽህፈት ቤቱ የመንገድ ትራፊክ ደህንነት አስተበባሪ ዋና ኢንስፔክተር ረጋሳ ኤዶሳ እንደተናገሩት የሰሌዳ ቁጥር አማ ኮድ 3 07902 የሆነ የህዝብ ማመላለሻ ሚኒባስ ከከሚሴ ወደ ደብረ ብርሃን በመጓዝ ላይ እያለ ከደ/ብርሃን ወደ ቀይጥ ሲጓዝ ከነበረ ኢቲ 72320 ሲኖትራክ የጭነት መኪና ጋር በግምት ከጠዋጡ 3፡10 ገደማ ተጋጭተው የ14 ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ በደ/ብርሃን ሪፈራል ሆስፒታል እርዳታ እየተደረገላት የነበረች የአንዲት መንገደኛም ህይወት ደግሞ በተጨማሪ አልፏል፡፡
አደጋው የ15 ሰዎች ህይወት ያለፈበትና ሁለት ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት ያደረሰ ነበር፡፡ የአደጋው መስኤ የህዝብ ማመላለሻው ሚኒባስ ከፊቱ የነበሩትን ሁለት ተሸከርካሪዎችን ደርቦ ያለመስመሩ ለማለፍ ባደረገው ሙከራ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ይህ ዘግናኝ አደጋ የተከሰተው ከአሽከርካሪዎች የጥንቃቄ ጉድለት ስለሆነ በቀጣይም ሌላ ተመሳሳይ አደጋ እንዳይከሰት አሽከርካሪዎች ለሚያጓጉዙት ሰው ህይወት ትልቅ ዋጋ ሰጥተው በጥንቃቄና በኃላፊንት ስሜት ማሽከርክር ይጠበቅባቸዋል ሲሉ ዋና ኢንስፔክተር ረጋሳ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
የደ/ብርሃን ከተማ አስተዳደርም በደረሰው ዘግናኝ የመኪና አደጋ በእጅጉ ያዘነ ሲሆን በአደጋው ምክንያት ህይወታቸው ላለፈ ቤተሰቦች መጽናናትን ይመኛል፡፡

Tuesday, February 23, 2016

የትግራይ ነጻ አወጭ ቡድን ላይ አስደንጋጭ የሆነ ዉድቀት ተከስቷል።


በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዉስጥ የኢትዮጵያን ሰራዊት ይዘዉ ሲንቀሳቀሱ የነበሩት ሉተናንት ጄኔራል ዮሃንስ ገብረመስቀል ተስፋማርያም በመላዉ ሐገሪቱ ላይ የተነሳዉን ህዝባዊ አመጽና በጎንደር ዙሪያ የተቀሰቀሰዉን ጦርነት በተመለከተ ለከፍተኛ ወታደራዊ ምክክክር ተቀምጠዉ በሚገኙበት በዚህ ወቅት ላይ የትግራይ ነጻ አወጭ ቡድን ላይ አስደንጋጭ የሆነ ዉድቀት ተከስቷል።
የወታደራዊ ደህንነት ቢሮዉ ከተላያዩ ክልሎች መርጦ ያሰለጥናቸዉ እና የአበኞች ግንቦት 7 ወታደራዊ የደንብ ልብስ የለበሱ 11 ወታደሮች እጅግ አዉዳሚ የሆኑ መሳሪያዎችን ታጥቀዉ በታች አርማጭሆ ዳንሻ በኩል ሰብረዉ በመዝለቅ ህዝብ ላይ አደጋ በመጣልና አርበኞች ግንቦት 7ን አሸባሪ በሚል ሴራ በሐዉዜን ህዝብ ላይ በደርግ ዘመን የፈጸሙትን ወንጀል ለመተግበር እንዲንቀሳቀሱ የተሰጠዉን ትእዛዝ አርበኞች ግንቦት 7 ጆሮ እና ህዝብ ዘንድ ደርሷል በሚል ምክንያት ትእዛዙ እንዲሰረዝ ቢደረግም ከ11ዱ 8 ያህሉ የድረሱበት አልታወቀም።
ሉተናንትንት ጀነራል ዮሐንስ ገብረመስቀል ተስፋማርያም ለወታደራዊ ደህንነቱ ከእንግዲህ ያበቃለት ጉዳይ ነዉ! ሲሉ መናገራቸዉን ተንተርሶ በከፍተኛ ሁኔታ እግረኛዉን እንኳን ያግዘዋል የተባለዉ አየር ሐይል ላይ እምነት ከሌለን ለመዋጋት ያለን ብቃት ብቻ ሳይሆን አቅምም ደካማ ነዉ! በማለት የወታደራዊ ደህንነቱን አጣጥለዉታል፡፤
በአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት ዙሪያ ጎንደር እየተወጠረ ነዉ ያለዉ መርጃ….. የህወሃት ሰራዊት ፖለቲካዊ ዝግጅት ላይ ብቁ አይደለም በሚል ድምዳሜ ወታደራዊ ደህንነቱ አሉ የሚባሉ ከፍተኛ ጄኔራሎቹን በመሰብሰብ የድረሱልኝ እርብርብ እያካሄደ ሲገኝ በሰሞኑ ብቻ የህወሃት ሰራዊት በጎንደር ዳንሻ እና ሳንጃ አካባቢ ላይ የደረሰበትን ከባድ ምት ተንተርሶም ምክሩ ቀጥሏል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ! !
ጉድሽ ወያኔ
Gudish Weyane's photo.

በኦሮሚያ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ አድማሱን በማስፋት ወደሌሎች አካባቢዎች እየተዛመተ ነው


ሰሞኑን በምሽራቅና ምዕራብ ሃረርጌ በሚገኙ የገጠር መንደሮች ዳግም የተቀሰቀሰው ተቃውሞ በሳምንቱ መገባደጃ ወደ በርካታ አካባቢዎች በመዛመት ላይ መሆኑ ተገልጿል።
በስፍራው በመካሄድ ላይ ያለን ግድያና እስራት ለማውገዝ አደባባይ በወጡ ነዋሪዎች ላይ እሁድና ሰኞ የጸጥታ ሃይሎች በወሰዱት እርምጃ ቁጥሩ በአግባቡ ሊታወቅ ያልቻለ ሰው መገደሉን ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል።
ይኸው ተቃውሞ ሰኞ በአዲስ መልክ በምስራቅ ወለጋ አካባቢም ሲካሄድ የዋለ ሲሆን በርካታ ሰዎች ለእስር መዳረጋቸውንና ድብደባ እንደተፈጸመባቸውም ታውቋል። 
የክልሉና የፌዴራል ባለስልጣናት ተቃውሞው በቁጥጥር ስር ዉሏል ቢሉም ሂውማን ራይትስ ዎችና ሌሎች አለም አቀፍ ድርጅቶች ተቃውሞው በመቀጠል ላይ መሆኑን ገልጸዋል።
በሃገሪቱ የሚዲያ አፈና በመኖሩ ምክንያት በየዕለቱ የሚገደሉ ሰዎችን ቁጥር በአግባቡ ማወቅ እንዳልተቻለም እነዚሁ ድርጅቶች አስታውቀዋል።
ሶስተኛ ወሩን የያዘው ይኸው ተቃውሞ ሰኞ በተለያዩ የክልሉ ከተሞች ማገርሸቱንም ከሃገር ቤት ከተገኙ መረጃዎች ለመረዳት ተችሏል።
Haregeweyn Abeje's photo.Haregeweyn Abeje's photo.

ኦሮሚያ የጦርነት ቀጠና ሆናለች::ለሕዝብ ሰላማዊ ተቃውሞ ከባባድ የጦር መሳሪያዎች በክልሉ ሰፍረዋል::


በኢትዮጵያ የኦሮሚያ ክልል የተቀሰቀሰው የሕዝብ ጭቆና በቃኝ ንቅናቄ ዛሬ ከጠዋቱ ጀምሮ እስከ ምሽቱ ድረስ የቀጠለ ሲሆን ሕጻናት አዛውንት ወጣት ሳይለዩ የሚገድሉ እና የሚያፍሱ የአግኣዚ ሰው በላ ወታደሮች ጭፍጨፋቸውን ቀጥለዋል::ባልተተገበረ ሕገመንግስት ከለላነት አምባገነን ተግባራትን የሚፈጽመው የወያኔው ማፊያ ገዳይ አገዛዝ በርካታ ኢትዮጵያውያንን በመግደል እና በማቁሰል ላይ ይገኛል:: እምቢ ለነጻነቴ እምቢ ለመብቴ ያሉ የኦሮሞ ልጆች ትግላቸውን ከበፊቱ በበለጠ አጠናክረው ቀጥለዋል::
በደንቢ ዶሎ ለሰላማዊው ሕዝቡ የአይሮፕላን መጣያ ዙ23 የጦርነት ነጋሪት የሚጎስመው አገዛዝ በሕዝብ ላይ ጠምዶ እየተንቀሳቀሰ ሲገኝ በየአከባቢው እንዲሁ ከባድ መሳሪያዎችን የታጠቁ ወታደራዊ ካሚዮኖች ተሰማርተዋል::የመብቱን ጥያቄ ይዞ አደባባይ የወጣን ሕዝብ በጥይት መግደል ወንጀል መሆኑ ሲታወቅ ማንም ከተጠያቂነት እንደማያመልጥ የሕወሓት መሪዎች ሊያውቁ ይገባል::ተቃውሞ በዛሬው እለት ከወለጋ እስከ ሃረርጌ ጉጂ ከሸዋ እስክ ኢሊባቦር ተስፋፍቶ ቀጥሏል::ወያኔ እንደለመደው በሚዲያዎቹ የሃሰት ፕሮፓጋንዳ እየነዛ የሚገኝ ሲሆን ታማኝነት ያሌላቸ እጅግ አሳፋሪ ሃሰቶችን በሕዝብ ላይ እየረጨ ይገኛል::
ድል ለጭቁን ሕዝቦች!!!

Sunday, February 21, 2016

የኦፌኮ የአዲስ አበባ ቢሮ በወታደሮች ተወረረ -መረራ ጉዲና ቢሮ አልነበሩም

በዛሬው የክብ ጠረጴዛ ውሎዋ ሚሚ ስብሐቱ በኦሮሚያ በመካሄድ ላይ የሚገኘውን ተቃውሞ በገንዘብና በቁሳቁስ በውጪ የሚገኙ ኃይሎች እንደሚረዱ ይህንን እርዳታም በአገር ውስጥ በሰላማዊ መንገድ ለመታገል የተመዘገቡ ፓርቲዎች ህጋዊነታቸውን ከለላ በማድረግ ገንዘቡንና ቁሳቁሱን እንደሚያከፋፍሉ ገልፃ ነበር ።
ከነበረኝ ልምድ በመነሳትም የሚሚን ቱልቱላ ተከትሎ አንድ ፓርቲ ኢላማ እንደሚሆን እየጠበቅሁ ነበር ።ጥበቃዬ ብዙ ሳይቆይ የፕሮፌሰር መረራ ኦፌኮ በድጋሚ የስርዓቱ ጡጫ ሊያርፍበት መንገድ መጀመሩን የሚያሳይ ዜና ተገኝቷል ።
የኦሮሚያውን ተቃውሞ ተከትሎ ኦፌኮ ብዙ ዋጋ ከፍሏል ።አባላቱ ተገድለውበት አመራሮቹ እነበቀለ ገርባ ወህኒ ወርደውበታል።
ዛሬ ደግሞ ሸገር የሚገኘው ዋና ቢሮው በወታደሮች ተወርሮ ፅህፈት ቤቱ ውስጥ የነበሩ ሰዎች ድብደባ ተፈፅሞባቸው ተወስደዋል ።መረራ ጉዲና በቢሮው አለመኖራቸው ቢታወቅም በቀጣይ ምን ሊደረግ እንደሚችል አይታወቅም ።

የፌደራል ፖሊስ ከፍተኛ አዛዦች በአዲስ አበባ ስብሰባ አካሄዱ፡፡ ስብሰባው ያለምንም ውጤት በግጭት ተቋጭቷል፡፡

የፌደራል ፖሊስ ከፍተኛ አዛዦች በአዲስ አበባ ከየካቲት 9 እስከ 12 2008 ዓ.ም የተሰበሰቡ ሲሆን የመልካም አስተዳደር ችግር፣ የፀጥታ ሁኔታ እና የአባላት መክዳት እያነሱ ከተወያዩባቸው አጀንዳዎች መካከል ዋነኞቹ ናቸው፡፡ በስብሰባው ላይ የአማራና የኦሮሞ ተወላጅ አዛዦች “እኛ ከእናንተ የተሻለ የትምህርት ደረጃና ልምድ እያለን ሁሉንም ቦታ ጠቅልላችሁ ይዛችሁት ተገቢው ቦታ አልተሰጠንም…” በማለት ህወሓቶችን ልካቸውን ነግረዋቸዋል፡፡
ህወሓቶች በፌደራል ፖሊስ ተቋም ውስጥ ባሰፈኑት ዘረኝነት ምክንያት ሰራዊቱ በመፍረስ ላይ እንደሚገኝ ስብሰባው ላይ በተደጋጋሚ ተወስቷል፡፡ በውይይቱ ላይ ተቃውሟቸውን ያሰሙ የኦሮሞና አማራ ተወላጅ አመራሮች ከህወሓቶች “የእናስራችኋል” ማስፈራሪያ ደርሷቸዋል፡፡
በመጨረሻም ስብሰባው ወደ ለየለት ንትርክና አምባጓሮ በማምራቱ አብዛኞቹ አዛዦች እንዲበተኑ ተደርገው ውይይቱ በጥቂት ዋና፣ ዋና አመራሮች ለተጨማሪ ጊዜ ተካሂዷል፡፡ የፌደራል ፖሊስ አደረጃጀት ሊፈርስ እንደሚችልም ጭምር ጭምጭምታ ተሰምቷል፡፡
በተያያዘ ዜና የሚከዱ የፌደራል ፖሊስ አባላት ቁጥር አሁንም ከቀን ወደ ቀን እየናረ መምጣቱ እየተነገረ ነው፡፡ በጎንደር ብቻ ቢያንስ በቀን 3 የፌደራል ፖሊስ አባላት እንደሚከዱ የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ ዜና ምንጮች ገልፀዋል፡፡

ሰበር ዜና


----------------------------------------------------
በአዲስ አበባ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ቢሮ በወታደራዊ ኮማንዶዎች ተከቦ እየተፈተሸ ይገኛል፡፡
በአዲስአበባ የሚገነው እና በዶክተር መረራ ጉዲና የሚመራው የኦሮሚያ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ቢሮ በወታደራዊ ኮማንዶዎች ተከቦ እየተበረበረ ሲሆን የጽ/ቤቱን ሃላፊ ጨምሮ የቢሮ ሰራተኞች እንዲሁም በቢሮ ውስጥ የነበሩ አባላት በወያኔ ኮማንዶዎች ቁጥጥር ስር ውለዋል::የተያዙት አባላት ከፍተና ድብደባ እና መጉላላት እየተደረገባቸው መሆኑን ከአካባቢዉ የሚገኙ የአይን እማኞች ገልጸዋል፡፡ የድርጅቱ ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና በቢሮ ውስጥ አልተገኙም፡፡
በኦሮሚያ እየተካሄደ ያለዉ ሕዝባዊ እንቢተኝነት ዛሬም ተቀጣጥሎ ቀጥሏል፡፡ በምሰራቅ ሀረርጌ ዞን በበደኖ ከተማ መገዶች ሁሉ የተዘጋጉ ሲሆን በጉራዋ ወረዳ ተቃውሞ በተጠናከረ መልኩ ቀጥሎዋል በዛሬው እለት 6:30 ሃራ ሆርዳ በሚባል በቀበሌ በገንዳ ሸንዳ ከተማ ውስጥ የሚገኝ የመንግስት ሃይሎች በአስከፊ ሁኔታ እርምጃ እየወሰዱ መሆኑን ከአካባቢዉ የተገኙ መረጃዎች ለማወቅ ተችሏል፡፡ በዚሁ የመንግስት ልዩ ሃይሎች በወሰዱት እርምጃ ሙስአብ አብዱረዛቅ የተባለ ሰው የገደሉ ሲሆን ሌላም ሰውም ያቆሰሉ በከፍተኛ ደረጃ መቁሰሉ ታዉቁአል፡፡ በየክፍለ ሃተሃገሩ የሚገኙ የወንጌላውያን ቤተክርስቲያናት በሰንበት ፕሮግራማቸው ግድያውን በማውገዝ በጸሎት ሟቾችን እያሰቡ መሆኑ ታውቋል፡፡
ድል ለጭቁን ሕዝቦች !!!

Friday, February 19, 2016

አምቦ እስር ቤት ተቃጠለ | ከተማዋ በጥይት ድምጽ ተወጥራለች


በአምቦ ከፍተኛው ተቃውሞ በቀጠለበት በዚህ ወቅት በከተማዋ የሚገኘው እስር ቤት በ እሳት እየነደደ መሆኑን የዘ-ሐበሻ ምንጮች አስታወቁ::
በተለምዶው ቀበሌ 06 ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚገኘው ይኸው የፖለቲካ እስረኞች ማሰቃያ እስር ቤት ውስጥ ከኦሮሞ ሕዝብ ንቅናቄ ጋር በተያያዘ የታሰሩ በርካታ ወገኖች እንደደሚገኙበት ምንጮች አስታወቀዋል::
በአምቦ ከተማ በአሁኑ ወቅት የጥይት እሩምታ እየተሰማ ሲሆን  ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስም በ እስረኞች ላይ ከባድ ጉዳት ስለመድረሱ የታወቀ ነገር የለም:: ሆኖም ግን እሳቱ እየተዛመተ ባለበት ወቅት እንኳ እስረኞቹ እሳት እንዳያጠቃቸው ከቦታ ቦታ ለማዘዋወር ከበላይ ት ዕዛዝ ካልመጣ በስተቀር የአካባቢው ፖሊሶች ፈቃደኛ እንዳልሆኑ ይነገራል::

የትግራዩ አስተዳደር አባይ ወልዱ ላይ የግድያ ሙከራ መደረጉን እና የወያኔ ባለስልጣናት ተብዬዎች በማንኛዉም ወቅት እና ሰአት አደጋ ላይ ሊወድቁ እንደሚችሉ የሚያመላክት ፍንጭ ከብሐራዊ መረጃ አፈትልኳል።


የትግራዩ ነጻ አዉጭ ቡድንን በቁንጮነት እየመሩ መላዉ ኢትዮጵያዊያንን በነጻነት ጥማት ወጥረዉ ሁለት አስርት አመመታትን የዘለቁት ወንጀለኞች በተለይም የብሔራዊ መረጃ ከፍተኛ አመራሮች እርምጃ እየተወሰደባቸዉ ሲሆን በተጨማሪ የትግራዩ አስተዳደር አባይ ወልዱ ላይ የግድያ ሙከራ መደረጉን እና የወያኔ ባለስልጣናት ተብዬዎች በማንኛዉም ወቅት እና ሰአት አደጋ ላይ ሊወድቁ እንደሚችሉ የሚያመላክት ፍንጭ ከብሐራዊ መረጃ አፈትልኳል። የብሐራዊ መረጃ ክትትል ክፍል ኬብል 09አዲስ አበባ 13ቢ l Cable: 09ADDISABABA13 b (S) Ethiopia’s national intelligence program facilitator fastest meting with Ethiopia’s national intelligence chief, Getachew Assefa, for a four hour private meeting on…….. . በሚል ኮድ ያስተላለፈዉ መልእክት ከፍተኛ የመረጃ ሰራተኞችን በቀላሉ እያጡ መሆኑን በመግለጽ በስፋት ተወያይተዉ ያለ በቂ መፍትሄ መበተናቸዉ ተረጋግጧል።
ይህዉ ወንጀለኛ ቡድን በተለይም ለትግራይ ህዝቦች ብቻ ደህንነት የቆመ ይመስል በመላዉ ሐገሪቱ ላይ የተፈጠረዉን አለመረጋጋት ተንተርሶ የትግሬ ተወላጅ የሆኑ የመረጃ ሰራተኞቻችን በቀላሉ እየተጠቁ በመሆኑ በምትካቸዉ የገንዘብ ፈሰስ ተደርጎ በአማራና በኦሮሞዎች ላይ ማተኮር አለብን በሚል ሓሳብ ላይ ቢወያይም ስረአቱ ከደረሰበት ፖለቲካዊ ክስረት የተነሳ በሌላ ብሔሮች ላይ ያለዉ እምነት መመናመኑና ቀጣይ ስራዎችን ሚስጥራዊ አድርጎ እንኳን ለማስፈጸም ያለመቻሉን ገልጾ ደብረጺዮን ለተባለዉ የብሔራዊ መረጃዉ አካል አመልእክቱን አስተላልፏል።
በአጠቃልይ በመላዉ ሐገሪቱ የሚገኙ ወታደራዊ መረጃ ሰራተኞች፣ የሚስጠር መረጃ ሰራተኖች፣ የሲቪል መረጃ ሰራተኞች፣ መንግስታዊ መረጃ ሰራተኞች፣ ተራ መረጃ ሰራተኞች፣ ተደራቢ ወሬ አቀባዬች( undercover police ) ሰራተኞች እርምጃ እየተወሰደባቸዉ መሆኑን ተረጋግጧል ከያንዳንዱ የእርምጃ አወሳሰድ ሁኔታ ጀርባ ያለዉ ህዝብ መሆኑ ደግሞ ጉዳዩን አሳሳቢ ቢያደርገዉም ጉዳዩን ወደ አርበኖች ግንቦት 7 እና ወደ ኦሮሞ ነሳነት ግንባር (በተለይምች ወደ ሙስሊሙ) መሐበረሰብ መዉሰድ እንደሚገባ ወስኗል በመሆኑም መላዉ ኢትዮጵያዊያን የትግራዩ ነጻ አዉጭ ቡድን ግበአተ መሬት እየተፋጠነ መሆኑን በመገንዘብ ለበለጠ ድል እራሱን በማዘጋጀት ሐገሩን ነሳ እንዲያወጣ በእናት ኢትዮጵያ ስም አደራ እንላለን።
ድል ለመላዉ ኢትዮጵያ ህዝብ ! !
ጉድሽ ወያኔ

Thursday, February 18, 2016

ሰበር ዜና ወደ ጎንደር እና አምቦ የሚያደርሱ በርካታ መንገዶች በሰልፈኞች ተዘጋግተዋል::

እየተጋጋለ የመጣዉ የኦሮሚያ ክልል ህዝብ አመፅ ወደ መንገዶች መዘጋጋት ተሸጋግሯል በዚህ ተቃዉሞ አሁንም በርካታ አንድን ከተማ ከአንድ ከተማ የሚያገናኙ መንገዶችን በመዝጋት የቀጠሉ ሲሆን በደረሰን መረጃ መሰረት ወደ ጉንደር እና አምቦ የሚያደርሱ መንገዶች ሙሉ በሙሉ ተዘግተዋል::
ሰልፈኞች በፌደራል ፓሊስ ወታደሮች የሚደርስባቸዉን የጥይትና የዱላ ድብደባ ሳይበግራቸዉ አሁንም ይህንኑ የመንገድ መዝጋቱን ተቃዉሞ በተለያዩ ከተምችም እንደሚያደርጉት እየተጠበቀ ነዉ:: ወደ ጎንደር እና አምቦ ከሚያደርሱ መንገዶች በተጨማሪ በወለጋ ሆሮጉድሩ ጃራቴ ወረዳና በምእራብ አርሴ ዋዴና ኤዶ ከተሞች ምስራቅ ሀረርጌ መንገዶች በሰልፈኞች ተዘጋግተዋል::
 

በቅርቡ ለጂቡቲው ፕሬዚዳንት ኦማር ጌሌ የተሰጡት ሴሮፍታ እና ጎፈር የመንግስት እርሻዎች በህዝቡ በተወሰደባቸው እርምጃ በእሳት ጋይተዋል።

በቅርቡ ለጂቡቲው ፕሬዚዳንት ኦማር ጌሌ የተሰጡት ሴሮፍታ እና ጎፈር የመንግስት እርሻዎች በህዝቡ በተወሰደባቸው እርምጃ በእሳት ጋይተዋል። እርምጃውን የወሰዱት ከዋቤ-ኤዶ ከተሞች በነቂስ ወደ ስፍራው የተመሙ ህዝባዊ ታጋዮች ናቸው። ይህ መሬት እትብቱ ከተቀበረበት የኣካባቢው ነዋሪ ህዝብ በሃይል ተነጥቆ የመንግስት ንብረት ከተደረገ በኀላ በቅርቡ ደግሞ ለኦማር ጌሌ የተሰጠ ነው። ህዝቡ በግፍ የተነጠቀውን መሬት በትግሉ ካተቆጣጠረው በኀላ ባአሁኑ ሰአት እየተከፋፈለው ይገኛል ።

በትግራይ ክልልና ኣማራ ክልል ዋግ ኽምራ ዞን ድርቁ ባስከተለው ረሃብ የሰውና የእንስሳት ሂወት እየተቀጠፈ ነው።


ድርቁ ለመከላከል ተብሎ እየመጣ ያለው የእርዳታ እህልና እርዳታ ጠባቂ ህዝብ ቁጥር ስለማይመጣጠን፣ የመጣው እርዳታ ከከፍተኛ ባለ ስልጣናት እስከ የቀበሌ ካድሬዎች እየዘረፉትና ኢ_ፍትሓዊ በሆነ መንገድ ስለሚከፋፈል እርዳታው የህዝቡና እንስሳቱ ሂወት ከሞት ሊታደግለት ኣልቻለም።
በሰው ሂወት እየደረሰ ያለው ኣደጋ በህፃናትና ኣረጋውያን የሚብስ ሲሆን ከእንስሶች ደግሞ በፍየሎችና በጎች የበለጠ ኣደጋ ኣስከትለዋል።
በረሃብ እየሞተ ያለው የሰው ስምና ፎቶ በፌስቡ ገፅ መለጥፍ የሚቻል ቢሆንም ለቤተሰቦቻቸው ሞራል ሲባል ኣይበረታታም።
በምስሉ የምታዩት የሞቱ በጎች ምስል በኣፅቢ ወንበርታ ወረዳ ሩባፈለግ የተባለ ቀበሌ ኑዋሪ የሆኑት የኣቶ ሕድሮም ሃይለ ስላሴ በጎች ናቸው። የወረዳዋ እንስሳት በተመሳሳይ ሁኔታ በየቀኑ በረሃብ እየረገፉ ይገኛሉ።
በየወረዳው የሚኖሩ የዓረና ኣባላት ሁለት ጨካኝ ሃይሎች ጎሮሯቸው ኣንቀው መልኣከ ሞት እየጠሩላቸው ይገኛሉ።
እነዚህ ጨካኞች ህወሓትና ድርቅ ሲሆኑ “ታሪክ ራሱን ይደግማል” እንደሚባለው የትግራይ ህዝብ በ77ቱ ድርቅ ግዜ ድርቅና ሻዕብያ ግምባር ፈጥሮው እንደፈተኑት ኣሁንም ህወሓት የሚቃወማቸው ህዝብ ለማንበርከክና ለመበቀል የወቅቱ ድርቅ እንደመልካም ኣጋጣሚ ተጠቅሞ በሂወታቸው እየመጣ ነው። እርዳታ የጠየቀ የዓረና ኣባል “ዓረና ይስጣቹ” የሚል ምላሽ ያገኛል።
እንደ ህወሓት ውሳኔ “ረሃቡ ለመቋቋም ሲሉ ዓረናዎች በእግራችን ይወድቃሉ፣ ይለምናሉ፣ ኣለበለዝያ ሂወታቸው ያጣሉ” በሚል ስሌት መላ የትግራይ ኑዋሪ የዓረና ኣባላት ከእርዳታ ውጭ ኣድራጓቸዋል።
ይኸው… ! የዓረና ኣባላት ለሆዳቸው ሲሉ ወደ ህወሓት ኣልገቡም። ህወሓት በዓረና ኣባላት ላይ ካሰበችው ሴራ በተጨማሪ ያላት ሙሰኛ ባህሪ እርዳታው በየ እርከኑ እየተዘረፈ እርዳታው ለተረጂው ሳይደርስ በመቅረቱ ሰውና እንስሳ በረሃብ እየሞተ ነው።
ህወሓትም እንደ ኢሉሙናቲ “ጠላቶቼ” ብሎ የፈረጃቸው የዓረና ኣባላት፣ ወደ ስልጣን እንዳላስመጣው እየተጠየፈው እየመጣ ያለው የትግራይ ህዝብና የህዝቡ እንስሶች ሲሞቱ ደስ እየተሰኙ ነው ባይባልም ከቁብ ኣልቆጠሩትም።
የተወደዳቹ ኢትዮጵያውያን ሆይ……! መንግስት በጥጋብ ልቡ ሲደነድንና ህዝቡን ቢረሳ እናንተስ እንዴት በወገናቹ ርሃብና ሞት ሆዳቹ ኣይባባም?
የህወሓትና ካድሬዎችና ደጋፊዎች የእርዳታው እህል ወደ ህዝቡ እየደረሰ እንዳልሆነ እኔን ካላመናቹ የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ ኣባልና የትግራይ ምስራቃዊ ዞን ኣስተዳዳሪት ወይዘሮ ያለም ፀጋይ በድምፅ ወያነ ያለፈው ምስክርነት እንዴት ኣታምኑም?
የብኣዴን ዋግህምራ ዞን ካድሬዎችና ኣባላት ወገኖቻቹ በረሃብ እያለቁ ነው። ተሰድደው መጥተው የመቐለ ጎዳናዎችም እያጥለቀለቁዋት ነውና ስለ ህዝባቹ ብላቹ ኣስፈላጊ መላና ድጋፍ ኣድርጉላቸው።
በሌሎች ክልሎች ያለው የረሃብ ሁኔታ መረጃ ባለ ማግኘቴ ላካትተው ኣልቻልኩም።
ስለዚ የህዝባችን ችግር እንጋራ፣ ሂወቱ እንታደግለት፣ እንስሶቹም እናትርፍለት፣ ይሄ ድርቅ ለፖለቲካዊ ትርፍ ተብሎ በዓረና ኣባላት ላይ እየደረሰ ያለው ማግለል የሞት ፍርድ ስለሆነ በህብረት እናቁመው።

Four shot dead, many wounded in Aje, Shashamene towns of West Arsi Zone




Wednesday, February 17, 2016

የህወሓትን‬ አገዛዝ በመቃወም ኤም.አይ-35 ሄሊኮፕተር ይዘው ከሀገር የወጡት እነ ሳሙኤል ግደይ የሞትና የእድሜ ልክ እስራት ተበየነባቸው፡፡


ሳሙኤል ግደይ፣ ፀጋ ዘአብ ግደይ እና ቢልልኝ መኮንን የህወሓትን አገዛዝ በመቃወም ኤም.አይ-35 ተዋጊ ሄሊኮፕተር በማብረር ከምስራቅ አየር ምድብ ድሬዳዋ በውሎ የጠፉት በ2007 ዓ.ም ሲሆን የህወሓት አገዛዝ የጦር ፍርድ ቤት የካቲት 4 2008 ዓ.ም በሌሉበት በሞትና እድሜ ልክ እስራት ቀጥቷቸዋል፡፡
የሄሊኮፕተሯ ዋና አብራሪ ሳሙኤል ግደይ በሞት ሲቀጣ ፀጋ ዘአብ ግደይ እና ቢልልኝ መኮንን የእድሜ ልክ እስራት ተበይኖባቸዋል፡፡
ከእነ ሳሙኤል ግደይ በፊትም በ1993 ዓ.ም ካፒቴን ተሾመ ተንኮሉ ኤል-39 ተዋጊ ጀት እያበረረ ከመቀሌ ተነስቶ ኤርትራ መግባቱ፤ መቶ አለቃ በኃይሉ ገብሬ እና መቶ አለቃ አብዮት ማንጉዳይ ኤም.አይ-35 ተዋጊ ሄሊኮፕተር እያበረሩ ጅቡቲ ማረፋቸው የሚታወስ ነው፡፡ መቶ አለቃ በኃይሉ ገብሬና አብዮት ማንጉዳይ በጅቡቲ መንግስት ለህወሓት ተላልፈው ተሰጥተው የእድሜ ልክ እስራት እና የ15 አመት እስር ተፈርዶባቸው መቶ አለቃ አብዮት የእስር ጊዜውን ጨርሶ በመፈታቱ በአሁኑ ጊዜ አርበኞች ግንቦት 7ን ተቀላቅሎ ኤርትራ በረሃ እንደሚገኝ መዘገባችን አይዘነጋም፡፡
የኤም.አይ-35 ተዋጊ ሄሊኮፕተር አዛዥ እና የበረራ አሰተማሪ የነበረው ሻለቃ አክሊሉ መዘነም ከአመታት በፊት ስርዓቱን በመቃወም ወደ ኤርትራ መጥቶ አርበኞች ግንቦት 7ን በመቀላቀል ትግል ላይ ይገኛል፡፡
 

ሰማያዊና መድረክ ከስዊድን የፓርላማ አባላት ጋር ተወያዩ


የሰማያዊ እና የመድረክ ፓርቲዎች አመራሮች ከስዊድን የፓርላማ አባላት ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ተናግረዋል፡፡
የፓርቲዎቹ አመራሮች የሆኑት ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ፣ ኢ/ር ይልቃል ጌትነት እና ዶ/ር መረራ ጉዲና ከስዊድን ፓርላማ የውጭ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ልዑክ ጋር በኢትዮጵያ ወቅታዊ የፖለቲካ ጉዳዮች ላይ ዛሬ የካቲት 9/2008 ዓ.ም መወያየታቸው ታውቋል፡፡
የፓርቲ አመራሮቹ ከስዊድን ስድስት ፓርቲዎች ከተውጣጡ 11 የልዑካኑ አባላት ጋር በተወያዩበት ወቅት በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች በተለይም በኦሮሚያ በተቀሰቀሰው የህዝብ ተቃውሞ እና በጋምቤላ ክልል ስለነበረው ግጭት ገለጻ አድርገውላቸዋል፡፡ አመራሮቹ ለተቃውሞ አደባባይ በወጣው ህዝብ ላይ የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች እየወሰዱት ያለውን እርምጃ በተመለከተም በውይይታቸው አንስተዋል፡፡
አሁን ላይ በኢትዮጵያ የተቃውሞ ድምጽ የሚያሰሙ የፓርቲ አባላትን እና በነጻነት ስራቸውን በሚያከናውኑ ጋዜጠኞች ላይ እንዲሁም በአጠቃላይ ተቃውሞ በሚያሰማው ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለው አፈና እየጨመረ መሆኑንና በሀገሪቱ ፓርላማም አንድም ተቃዋሚ ድምጽ የማይሰማበት መሆኑን እንደገለጹላቸው ታውቋል፡፡
የስዊድን ፓርላማ አባላትም የተቃዋሚ ፓርቲዎች እያደረጉት ስላለው የፖለቲካ እንቅስቃሴና በጋራ ስለሚሰሩበት ጉዳይ ጥያቄ አንስተው በፓርቲዎች አመራሮች ገለጻ እንደተደረገላቸው ኢ/ር ይልቃል ተናግረዋል፡፡
የስዊድን የፓርላማ አባላት ጠ/ሚ ኃ/ማርያም ደሳለኝን ጨምሮ ከተለያዩ የመንግስት አካላት ጋር እንደተወያዩም ለማወቅ ተችሏል፡፡
Netsanet Beqalu Mannet's photo.

በምዕራብ አርሲ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ወደ ሌሎች አጎራባች አካባቢዎች ተዛምቶ ከፍተኛ ግጭት ተካሄደ


በምዕራብ አርሲ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ወደ ሌሎች አጎራባች ቀበሌዎች መዛመቱንና በአካባቢው ከፍተኛ ግጭት በመካሄድ ላይ መሆኑን እማኞችን ዋቢ በማድረግ አዲስ ስታንዳርድ መጽሄት ማክሰኞ ዘግቧል።
ይኸው ተቃውሞ በሻላ፣ ሲራሮ፣ አጄና፣ ሻሸመኔ ከተማ ተዛምቶ የሚገኝ ሲሆን፣ የፀጥታ ሃይሎችም ከነዋሪዎች ጋር ግብግብ ውስጥ መሆናቸውን መጽሄቱ ነዋሪዎችን ዋቢ በማድረግ አቅርቧል።
የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች በወሰዱት የተኩስ እርምጃዎች በሻሸመኔ ከተማና በአቅራቢያዋ ባሉ አካባቢዎች በትንሹ አምስት ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች አስረድተዋል። 
በሻሸመኔ ከተማ ከሞቱ ሁለት ሰዎች መካከል አንደኛዋ እድሜዋ በ20ዎቹ ውስጥ የሚገኝ ነፍሰጡር መሆኗን የከተማዋ ነዋሪዎች አስታውቀዋል።
በአካባቢው የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ ተከትሎም በሻሸመኔ ከተማ የመንግስትና የግል ተቋማት ተዘግተው የሚገኙ ሲሆን፣ በከተማዋ ወደተለያዩ አካባቢዎች የሚወስዱ መንገደኞችም መዘጋታቸውን ለመረዳት ተችሏል።
የፌዴራልና የክልል የፀጥታ ሃይሎችም በሻሸመኔ ከተማና በዙሪያዋ ባሉ ከተሞች በመስፈር ላይ መሆናቸውን የአይን እማኞች አስረድተዋል።
አካባቢው የተረጋጋ ባለመሆኑ የሟቾች ቁጥር በአግባቡ ማወቅ እንዳልተቻለ የሚናገሩት ነዋሪዎች በርካታ ሰዎችም ለእስር መዳረጋቸውን ገልጸዋል።
የመንግስት ባለስልጣናት በበኩላቸው በአካባቢው የተፈጠረውን ግጭት ምክንያት ለማወቅ ጥረት በማድረግ ላይ መሆናቸውን ማክሰኞ ምሽት አስታውቀዋል።

Tuesday, February 16, 2016

በፀገዴ ህወሓት ድባቅ የተመታችበት መድረክ ሁናለች።


ሰሞኑን በወልቃይት ጉዳይ ለመነጋገር የህወሓት ሊቀ መንበርና የትግራይ ኣስተዳዳሪ ኣቶ ኣባይ ወልዱና የብኣዴን ምክትል ሊቀመንበርና የኣማራ ክልል ኣስተዳዳሪ ኣቶ ደጉ ኣንዳርጋቸው በጎንደር ከተማ ከፍተኛ ፍጥጫ የተሞላበት ውይይት እንዳካሄዱ እየተገለፀ ነው።
በወልቃይት ጉዳይ ወደ ከረረ ፍትግያ የገቡት ሁለቱ መሪዎች በመጨረሻ ሰዓት ድል ወደ ኣቶ ደጉ ኣዘንብላለች።
ኣቶ ኣባይ ወልዱ ለ24 ዓመታት በትግራይ ክልል መስተዳድር ስር የነበሩት የፀገዴ ቀበሌዎች ወደ ኣማራ ክልል እንዲጠቃለል ሳይወዱ በግድ መፍቀዳቸው እየተገለፀ ይገኛል።
በዚህ መሰረት ማይደልየ፣ እምባገላ፣ ግጨው የሚባሉና ሌሎች ቀበሌዎች ለደጉ ለማስረከብ እንደተስማሙ እየተገለፀ ነው።
ፀገዴ ህወሓት በብኣዴን ድባቅ የተመታችበት መድረክ ሁናለች።
ኣየ ህወሓት………… ????
ነፃነታችን በእጃችን ነው።

በምዕራብ አርሲ የፌደራል ፖሊሶች ሬሳ አደባባይ ላይ ተጎተተ | 8 ወታደሮች ተገድለዋል ተብሏል


ባለፈው አርብ በም ዕራብ አርሲ በአንድ የሰርግ ስነ ስርዓት ላይ የፌደራል ፖሊሶች ንጹሃን ዜጎችን ከገደሉ በኋላ በተነሳ የሕዝብ ተቃውሞ ዛሬም ቀጥሎ ውሎ በዛሬው ዕለት 8 የፌደራል ፖሊሶች መገደላቸው ተሰማ:: ይህ የሟች ወታደሮች ቁጥር ሊጨምር ይችላል እየተባለም ነው::
ፖሊሶቹ ለተቃውሞ በወጡ የአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ጥይት ተኩሰው ከገደሉና ካቆሰሉ በኋላ ሕዝቡ በዚህ በመቆጣት በፌደራል ፖሊሶቹ ላይ የአጸፋ እርምጃ መውሰዱ ተሰምቷል:: በዚህም መሠረት በአደባባይ የወደቁት የፌደራል ፖሊሶች ሬሳ ሲጎተት እንደዋለና በየቦታው እንደወደቁም ተዘግቧል::
በም ዕራብ አርሲ አጄ ከተማ እንዲሁም በሻሸመኔ እና ሲራሮ ከተሞች ውጥረቱ እንዳለ ነው:: ሕዝብና የፌደራል ፖሊሶች ተፋጠዋል::
 

Saturday, February 13, 2016

በወልቃይት ሕዝብ የማንነት ጥያቄ ላይ ውሣኔ እንዲሰጠን ለፌደራል መንግሥት ባስገባነው ጥያቄ ምክንያት ዛቻና ወከባ እየደረሰብን ነው ያሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ስሞታ እያሰሙ ነው።




በወልቃይት ሕዝብ የማንነት ጥያቄ ላይ ውሣኔ እንዲሰጠን ለፌደራል መንግሥት ባስገባነው ጥያቄ ምክንያት ዛቻና ወከባ እየደረሰብን ነው ያሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ስሞታ እያሰሙ ነው።
በምዕራባዊ ትግራይ ዞባ በቃስታ ሁመራ ወረዳ ውስጥ በምትገኘውና ከሱዳን ጋር በምትዋሰነው ማይ ካድራ ቀበሌ ውስጥ ያሉ ነዋሪዎች ፖሊስ ሰዉን እየጠራ እያስፈራራ ወረቀት ያስፈርማል ብለዋል።
ቀበሌአችንን መገናኛ ብዙኃን አያውቁትም፤ ሃሣባችንን ተናግረን የፈለጉትን ቢያደርጉንም አንፈራም ሲሉ ማንነታቸውን ሳይደብቁ ከቪኦኤ ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉት ሁለት የቀበሌዪቱ ነዋሪዎች ቀደም ሲል ተወካዮቻቸውን ወደ ፌደራል መንግሥት ልከው እኛ ከዘር ማንዘራችን አማሮች ነን፤ ክልላችንም አማራ ክልል ነው ሲሉ ፊርማ አሰባስበው አቤቱታ ያስገቡትን ሰዎች ፖሊስ ጣቢያ እየጠሩ ያስፈራራሉ፤ ይዝታሉ ብለዋል።
“ሰዎች አሳስተውን ነው እያልን እንድፈርም እያደረጉን ነው፤ ነጭ ወረቀት ላይም እንፈርማለን” ብለዋል።
ስለሁኔታው የአካባቢው ባለሥልጣናት የሚሉትን ለመጠየቅ ወደ ሁመራ ወልቃይት ዞንና ወደ ወረዳው ያደረግናቸው በርካታ ጥረቶች ለጊዜው አልተሣኩም፤ በጥረታችን እንቀጥላለን።
በሌላ በኩል ደግሞ ሰሞኑን የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አባይ ወልዱ የመሩት ስብሰባ እዚያው ምዕራብ ትግራይ ውስጥ ሲካሄድ ቆይቷል።
ስብሰባው የተወያየው በዚሁ የወልቃይት የማንነት ጥያቄ ላይ መሆኑም ተሰምቷል።
ከአራት የአካባቢው ወረዳዎች የተጠራ ወደ ስድስት መቶ የሚሆን ተሣታፊ ተገኝቶበታል።
የተሣታፊዎች የአቋም መግለጫ ነው የተባለ ሰነድም ወጥቷል።
የትግራይ ክልል የፀጥታና የአስተዳደር ኃላፊው አቶ ሃዱሽ ዘነበ “ይህንን ትርምስ የሚመሩት ኃይሎች ኢሕአዴግን በምርጫም በጦር ሜዳም ሊያሸንፉት ያልቻሉ ኃይሎች ናቸው፡፡ የሌለ የማንነት ጥያቄ እያነሱ እርስ በራሱ እንዲጫረስ፣ ከልማት ጎዳና ለማስወጣት እየሠሩ ይገኛሉ፤ ከሻዕቢያና ከሌሎች ኃይሎችም እነማን እንዳሉ መረዳት ይኖርብናል፡፡ መንግሥት ከዛሬ ጀምሮ ትዕግሥቱ ተሟጥጧል” ብለዋል።

ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ምክትላቸው የነበሩት አቶ ሞላ አስገዶም ወደ ኢትዮጵያ የመግባታቸው ጉዳይ


ዶክተር ብርሃኑ ነጋ በዛሬው ቆይታቸው፥ ምክትላቸው የነበሩት አቶ ሞላ አስገዶም ከድተው ወደ ኢትትዮጵያ በመግባታቸው በእንቅስቃሴው ላይ ያደረሰው ጉዳት እንደሌለ ይናገራሉ።
ድርጅታቸው ከኤርትራ መንግሥት ተጠግቷል በሚል ከኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያስፈልገውን ድጋፍ ተነፍጓል ለሚሉ ወገኖችም መልስ አላቸው።
ዶክተር ብርሃኑ ነጋን ያወያያቸው የፕሮግራሙ አዘጋጅና አቅራቢ ሰሎሞን ክፍሌ ነው። ከድምጽ ፋይሉ ያዳምጡ።
 asee

Friday, February 12, 2016

አባዱላ ገመዳ:አባተ ስጦታው፣እና መድህን ኪሮስ በ’ፓርላማ’ ስብሰባ ላይ ድብድብ ቀረሽ ሃይለ ቃል ሲለዋወጡ እንደነበር ተነገረ


አባተ ስጦታው፣ መድህን ኪሮስ እና አባዱላ ገመዳ ያንድ ፓርቲ ስብስብ በሆነው በ’ፓርላማ’ ስብሰባ ላይ ለጭብጨባ የተቀጠሩትን ‘ተሰብሳቢዎቹን’ ከምንም ባለመቁጠር ድብድብ ቀረሽ ሃይለ ቃል የታከለበት አታካሮ ገጥመው ነበር ይለናል ጋዜጣው


Parliament has heard the assessment report on the implementation of the good governance plan. But that report brought no good news to the House and the three people shown above. Abate Sitotaw, deputy mayor of Addis Abeba City Administration (left), Medhin Kiros, vice president for the Federal Supreme Court (centre) and Abadula Gemeda, speaker of the House (right, behind Medhin). Immediately after the report was presented these high level officials were seen and heard grumbling at each other, losing control in front of their audience. During the third extraordinary session of Parliament’s first year, that body received a report from Tadesse Hordofa, member of parliament and head of the supervising committee that had carried out the assessment in selected federal and city districts. The team’s twenty six paged report, rolled out a disaster list, collected from public feedback. The report contained substantial evidence that good governance is still in shambles. Though successful in having his nominees appointed to high positions in the federal courts, Medhin’s institution is reported among the worst performers in the good governance campaign.  Addis Abeba City Administration is no different in that its poor performance related to realising the highly acclaimed good governance, is reflected in its work flow and service delivery. This is not be strange for the Deputy Mayor.  The City Administration held a three-day meeting with public representatives dubbed yehizib kinfe, to hear the same problems mentioned in the report in depth. Participants vented their day-to-day grievances, only to have them dismissed by the City Council’s Speaker, Tabor G.Medihn (PhD). “This is a meeting called to discuss the bigger picture, and not focus on the little details”, the Speaker said as he minimized the complaints. But chances do not seem to work in Abate’s favour. The Speaker gave him the sign that he will have to face the MPs with concrete answers for the public grievances reflected in the report.

ህዝብ የመረጣቸው ኮሚቴዎቹን በመነጣጠል በባዶ ወረቀት በግድ በፖሊስ ፈርሙ እየተባሉ መሆኑ VOA ዘገበ፡፡


በማይካድራ የሚገኙ ሰዎችን/ ጋዜጠኛ ሰለሞን አባተ በስልክ እንዳናገራቸው ሳጅን ሀጎስ እና ሀይሌ የተባሉ ፖሊስ በባዶ ወረቀት የማትፈርም ከሆነ ወደ ጭቃ አስገባሀለሁ ትሞታለህ እያሉ ዛቻና ወካባ እያደረሱብን ይገኛል ሲሉ ገለጹ፡፡
የወልቃይት ህዝብ ቀደም ሲል ጀምሮ አባት ቅድመ አያት የአማራ ማንነት እንጂ እነሱ ባሉት ክልል አንጠራም ያሉት ኮሚቴው የጠየቃችሁትን ጥያቄ አቁመናል በማለት የማትፈርሙ ከሆነ ዋጋህን ታገኛለህ እየተባሉ መሆኑ ተናግረዋል፡፡
/ጋዜጠኛ ሰለሞን አባተ ይሄን ቃለ መጠይቅ በራዲዮ ባስተላልፈው ችግር ይፈጥርበዎት ይሆን? ብሎ ለጠየቃቸው)) “ለምን አይቆራርጡኝም! ለምን አልሞትም! ለምን እንደፈለጉ አያደርጉኝም! የወልቃይት ህዝብ የማንነት ጥያቄ እውነትን ይዘን ነው፡፡ እንደፈለጉ ያድርጉኝ በማለት ሲናገሩ ስማቸውን ለጠየቃቸው በግልጽ ነገረውታል የወልቃይት ህዝብ የማንነት ጥያቄ የጸረ ሰላም የግንቦት 7 ጥያቄ ነው እያሉ ለማሸማቀቅ ቢሞክሩም እስከመጨረሻ ድረስ ጥያቄ ከመጠየቅ አንዳችም ነገር አያግደንም ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ለጆግኖች የወልቃይት ህዝብ ለሚደርስባቸው ችግር ድምጽ እንሁን፡፡
ብዙ የአምባገነኑ የትግራይ አስተዳደር ሴራ ይጠብቅሃልና
በማጭበርበር ቅጥ ያጣው የትግራይ አስተዳደር ሰዎችን በትናንሽ ጥቅማጥቅሞችን በማታለል ወልቃይት ትግራይ ነው የሚል ፔትሽን እያሰባሰበ ይገኛል፡፡ ስለሆነም ማንኛውም የወልቃይት ተወላጅ በማንኛውም መስሪያ ቤት ሲገባ /የሚፈርምበት አጋጣሚ ካለ የሚፈርምበት(ፎርም) ወረቀት ምንነቱን ጠንቅቆ ማንበብ አለበት፡፡
( እኛ የወልቃይት ህዝብ ይህን የተፈጠረውን የትምከተኝነትና የጠባብነት አስተሳሰብ የማንነት ጥያቄ የህዝብ ጥያቄ ስላልሆነ የህዝብ ውክልና የሌላቸው ጥገኛ ሃይሎች የሚያነሳሱት በመሆኑ መንግሥት ከነዚህ ላይ እርምጃ እንዲወሰድ በጥብቅ እናሳስባለን ፡፡ እኛ የግል ማንነታችን እናውቃለንም በህገ መንግሥታችንም ተመልሶልን ያደረ ነው፡፡ ይላሉ)
ድል ለወልቃይት ህዝብ!!!”
ውድቀት ለአምባገነኑ የትግራይ አስተዳደር!!!

የሱዳን መንግስት የኢትዮጵያ ድንበር በርካታ ኪሎሜትሮች በመግፋት ኣዲስ የኢሚግሬሽን ህንፃ በልጉዲ ከተማ ገንብተዋል።


በ2002 ዓ/ም ሃገራቀፍ ምርጫ ወቅት ኣቶ ስዬ ኣብራሃ በኢትዮ_ሱዳን ድንበር ከ35_65 ኪ/ሜ የሚሸፍን የኢትዮጵያ ቆዳ መሬት ለሱዳን ለመስጠት ተደራድረው እንደጨረሱ ኣጋልጠው ነበር።
በዚህ መሰረት እንደ መተማ ዮውሃንስ፣ ቋራ፣ ልጉዲና ሌሎች ለም መሬቶች ለሱዳን ሊሰጡ በሁለቱ መንግስታት ዝግጅት መጠናቀቁ እየተገለፀ ነው።
በወቅቱ የኢትዮጵያ መሬት ለሱዳን ለማስረከብ ሁለቱ መንግስታት ከ17 ግዜ በላይ በድብቅ እየተደራደሩ የነበሩ ሲሆን የዚህ ድንበር ውጤትም ሱዳን በሑመራ በኩል ከነበረው ባህረሰላም የሚባለው የኢትዮጵያ ድንበር በርካታ ኪሎሜትሮች ወደ ኢትዮጵያ በመግፋት ልጉዲ በተባለው የድንበር ከተማ ኣድርገው በመትከል የሱዳን የኢሚግሬሽን ፅሕፈት ቤት ( Passports Office )ኣዲስ ህንፃ ገንብተዋል።
የሱዳን መንግስት በኢትዮጵያ መንግስት ለቀረበለት ገፀ በረከት ለመረከብ ከታች በምስሉ የምትመለከቱት ኣዲስ ህንፃ በልጉዲ ከተማ ገንብተዋል።
*መንግስት እነ ሃፀይ ዮውሃንስ ደማቸው ያፈሰሱበት፣ እነ ሃፀይ ቴድሮስ የተወለዱበት የኢትዮጵያ ሉኣላዊ መሬት ቆርሶ ለባእድ ኣገር መለገሱ ያቁም…!
*መንግስት ስለ በሁለቱ መንግስታት እየተካሄደ ያለው ድርድር ለህዝብ በይፋ ይግለፅ…!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር።

«ለአፍሪካዊያን ዲሞክራሲ ቅንጦት ነው፣ ኃይሌ ገብረሥላሴ።


«ለአፍሪካዊያን ዲሞክራሲ ቅንጦት ነው፣ የሚገባቸው ዲሞክራሲ ሳይሆን መልካም አስተዳደር ነው።»
ኣለ አሉ… ፖለቲሺያን ኃይሌ ገብረሥላሴ። “ፖለቲሺያን” ስል እያፌዝኩት ወይም እያሽሟጠጥኩ አይደለም። ሁላችንም እንደምናውቀው ኃይሌ ኢትዮጵያንና እኛን ሕዝቦቿን በድል ካኮራበት ሙያው ወደ ፖለቲካው ተገብቷል። መብቱ ነው!
ግና ገና ከጅምሩ በፖለቲካው መክሸፍ ሲያበዛ እየታዘብን ነው። በኢትዮጵያ ፖለቲካ ዙሪያ የሚሰጣቸው አስተያየቶች በእዝላልነት ይሁን ወይም ፖለቲካውን ባለመረዳት አላውቅም ብዙውን ጊዜ ግራ የሚያጋቡ ናቸው። … ዲሞክራሲ በሌለበት አኳኋን መልካም አስተዳደርን እንዴት ማስፈን እንደሚቻል አይገባኝም! ኃይሌ ለፖለቲካዊ ነገሮች በጣም የፈጠነ ይመስለኛል፤ ሰከን ረጋ ብሎ ብዙ ጥናቶችን ቢያደርግ ብዙ ጥሩ ነገሮችን አውቆ ማሳወቅ በቻለ ነበር። ለጥናት የሚሆን በቂ ባጀት ባይኖረውም ቅሉsmile emoticon
ሌላውና ሁሌም ሳስበው የሚገርመኝ ነገር ደግሞ የልጆቹ አፈ ፈረንጅነት ነው። እስቲ አስቡት ኃይሌ ተወዳድሮ አሸንፎ የአገሪቱ መሪ ሲሆንና EBC ዶክመንተሪ ሲሰራለትና የልጆቹ ቃለ ምልልስ እየተተረጎመ ሲነገረን wink emoticon … ምናለ እንደው አማርኛው እንኳ ቢቀር ኣፋን ኦሮሚኛ ቢያስተምራቸው?? … እስከማውቀው ድረስ ልጆቹ ኦሮሚኛም አይችሉም።
ግን! ሁሌም እንደምናከብርህ፣ ሁሌም እንደምንኮራብህ፣ ሁሌም እንደምንወድህና የምንጊዜም ጀግናችን እንደሆንክ ትላንትም መስክረናለን ዛሬም እንመሰክራለን ነገው ደግመን እንመሰክራለን።
ይቺን የፖለቲካ ነገር ግን እንደጫማህ ወዲያ ወደ ቆጡ ብትሰቅላትና ዝም ብለህ ቤተስኪያን እየሳምህ ብትኖር ደስ ይለኛል።