በጎንደሩ የህወሓት አገዛዝ ግዙፍ ወህኒ ቃጠሎ ምክንያት ያመለጡ እስረኞችን በማደን ላይ የነበሩት ፖሊሶችና ሚሊሻዎች ጥቃት ተፈፀመባቸው፡፡
የህወሓት አገዛዝ ፖሊሶችና ታጣቂዎች በአምባ ጊዮርጊስ ጀጀሆ ከፍተኛ አሰሳና የቤት ለቤት ፍተሻ በማድረግ የአካባቢውን ነዋሪ ሲያስጨንቁ የሰነበቱ ሲሆን በመጨረሻም አንድን የጦር መሳሪያ የታጠቀ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ለማዋል ሲሞክሩ ግለሰቡ ድንገት በከፈተባቸው ተኩስ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ ግለሰቡም ገድሎና አቁስሎ ለመሰወር ችሏል፡፡በግለሰቡ ከተገደሉት ታጣቂዎች መካከል አስማማው ሀብቴ የተባለው ሲገኝበት አስከሬኑ በጭልፎ ወንዝ ባለእግዚአብሄር ተቀብሯል፡፡ መኩሪያው የተሰኘው ፖሊስ ደግሞ በጠና ቆስለው የመዳን ተስፋ ከሌላቸው መካከል አንዱ ነው፡፡በህዳር ወር መገባደጃ ላይ በጎንደሩ የህወሓት ወህኒ በተነሳው ከፍተኛ የእሳት ቃጠሎ ምክንያት በርካታ እስረኞች ማምለጣቸውና በጥይት መጨፍጨፋቸው አይዘነጋም፡፡
No comments:
Post a Comment