Tuesday, December 8, 2015

አብርሃም ጌጡ ለዋስትና ያስያዘው ገንዘብ ላይ 5000 ብር ጨምሮ በ10.000 ብር ዋስትና ከእስር ተፈታ


አብርሃም ጌጡ ለዋስትና ያስያዘው ገንዘብ ላይ 5000 ብር ጨምሮ በ10.000 ብር ዋስትና ከእስር ተፈታ
( ለገሠ ወ/ሃና)
ከሰኔ 12 /2007 ዓም ጀምሮ በተለያየ እስር ቤቶች እና ፍርድ ቤቶች በመመላለስ ላይ የነበረው የግፍ አስረኛው አብርሃም ጌጡ በፍርድ ቤት
የሚያስከስሰው ወንጀል ባለመገኘቱ በቀጠሮ ብዛት በልደታ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሲመላለስ ነበር ነገር ግን የዚህን ፍርድ ቤት ሂደት አቋርጠናል በማለት ወደ አዲስ አበባ ፓሊስ ኮሚሽን በመውሰድ ሌላ ክስ መሥርተው እንደታሰረ ይታወቃል ለወራት አራዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመላልሰው
ሊከሱት የሚችሉበት ወንጀል ባለማግኘታቸው የጀመሩትን ክስ ለማቋረጥ ተገደዱ ይህ ያልበቃው የስርአቱ አገልጋይ ፍርድ ቤት ተብየ ሊያስከስሰው
የሚችል ወንጀል ፍለጋ ላለፉት 4 ወራት በማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ የሠው ልጅ ሆኖ በሰው ልጅ ላይ ሊደረግ የማይችል ግፍ ፣ ስቃይ እና መከራ ውስጥ እንዲያሳልፍ ተደርጓል ፡ በ04/03/2008 ዓም በዋለው ችሎት በ11/03/2008 የቀጠረ ቢሆንም በቋራጭ በ06/03/2008 ዓም አራዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት 5ኛ ወንጀል ችሎት በማቅረብ የክስ ቻርጅ እንዲደርሰው ሆኗል ፍርድ ቤቱ ክሱን ለመስማት በ07/03/2008 ዓም ቀጠሮ ሰጠ በዚህ እለት አቶ
አብርሃም ጌጡ የተከሰሰበት ወንጀል በወንጀለኛ መቅጫ ህግ አንቀጽ 486 ተላልፏል የሚል ሲሆን ይህ አንቀጽ ደግሞ የዋስትና መብት በወንጀለኛ መቅጫም ሆነ በህገመንግሥቱ ዋስትና የማያስከለክል በመሆኑ የእስረኛውን ህገመንግስታዊ መብት የይስሙላው ፍርድ ቤት በመጨረሻም ቢሆን በማክበር
በ5000 ብር ዋስ ከእስር ተለቆ በውጭ ሆኖ ጉዳዩን እንዲከላከል ሲል ውሳኔ ሠጥቶ ነበር ነገር ግን ከፍርድ ቤት በላይ ስልጣን አለኝ የሚለው እና
በጉልበቱ የሚተማመነው የማዕከላዊው መንግሥት በህግ ባልተሠጠው ስልጣን የፍርድ ቤቱን ውሳኔ ውድቅ በማድረግ ንፁሁን ዜጋ እስር ቤት ውስጥ ሲያሰቃየው ቆይቷል ይባስ ብሎም በየቀኑ ይፈታል ጠብቁ ሲፈልጉ አቃቤ ህግ ይዞታል ወዘተ በማለት የህግ የበላይነት በግለሰቦች እጅ መሆኑን በትክክል አረጋግጠውልናል
በሌላ በኩል በአለቱ በችሎት ላይ የዋስትና መብት ለተከሳሽ ቢሰጠው ትቃዎማለችሁ ተብለው ሲጠየቁ ተቃውሞ እንደሌላቸው ገልፀዋል ይህንን መልስ ለችሎት ሠጥተው እያለ የማዕከላዊ እስር ቤት ሠዎች አቃቤ ህግ ጉዳዩን ይዞታል እያሉ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ አለመቀበላቸው ስናይ ምን ያክል ከህግ
በላይ መሆናቸውን ያረጋግጣል ፡፡
አራዳ የመጀመሪያ ደረጃ በ5,000 ዋስ ከእስር እንዲፈታ ቢወሰንም የተሠጠውን ዋስትና ይግባኝ በማለት እስከ ዛሬ ህዳር 21 /2008 ዓም አቆይተውታል ህዳር 21/2008 ዓም የሠበር ፍርድ ቤት በ10,000 ብር ዋስትና እንዲፈታ ቢያዝም የቅሊንጦው መንግሥት የተለያየ ሠበብ በመፍጠር እስከ ዛሬ ህዳር 27/2008 ዓም
ድረስ ሲያጉላሉት ቆይተዋል አብርሃም ጌጡን አራዳ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ( ሠባራ ባቡር ) በማቅረብ ይግባኝ ጠይቀው ነበር ህዳር 20/2008 ዓም ሠበር ፍርድ ቤት ቢቀርብም መዝገቡን አላየነው በሚል ሰበብ ለህዳር 21/2008 ዓም ተቀጥሮ ነበር ህዳር 21/2008 ዓም ጉዳዩን የተመለከተው
ሠበር ፍርድ ቤት ለዋስትና ያስያዘው ገንዘብ ያንሳል በሚል ቀደም ሲል ተያይዞ በነበረው 5000 ብር ላይ 5000 ተጨምሮ በድምሩ በ10,000 (አስር ሽህ ብር ) ዋስትና አስይዞ ከእስር እንዲፈታ የወሰነው ውሳኔ በልዩ ልዩ ሰበብ ሳይተገበር ቆይቶል ከበዙ ቀናት በኋላ ተግባራዊ ሆኖ ዛሬ ህዳር 27/2008 ዓም ከእስር ተፈቷል ፡፡
አብርሃም ጌጡ ከታሰረ ጀምሮ በተለያየ መንገድ ከጎናችን ለነበራችሁ ወደፊትም አብራችሁን ስለምትሆኑ እጅግ በጣም እናመሰግናለን

No comments:

Post a Comment