እንደተጠበቀው የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች ጸረ ወያኔ ትግሉን ተቀላቅለዋል…..6ኪሎ ዋናው ካምፓስ። የአገራዊ ለውጥ መነሻ በመሆን የሚታወቀው የአአዩ ትልቅ የአገራዊ አንድነት ንቅናቄ ይጠበቅበታል!! ይህንን የስርዓት ተቃውሞ የአዲስ አበባ ህዝብ በነቂስ እንደሚቀላቀለው ሚሉ እምነታችን ነው!!
ከተለያየ የተቃውሞ አመፅ እየተካሄደባቸው ካሉ ስፍራዎች ለአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የተላከች ስንኝ ።
” አንቺ አዲስ አበባ አንቺ አራዳ ሆይ አመፃውን አንቺም ተቀላቀልሽ ወይ? ”
” አንቺ አዲስ አበባ አንቺ አራዳ ሆይ አመፃውን አንቺም ተቀላቀልሽ ወይ? ”
በተያያዘ ዜና ሊተገበር በዝግጅት ላይ የሚገኘውን ማስተር ፕላን ምክንያት በማድረግ በአዳማ ዩንቨርስቲ የተማሪዎች ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው። የወያኔ አጋዚ ጦር ተቃውሞ የሚያሰሙ ተማሪዎችን እየደበደበና እያሰረ ሲሆን ተቃውሞውን ያስፋፉታል በሚል ስጋት ተማሪዎች ወደ ከተማ እንዳይገቡ መንገዱ ተዘግቷል። በዲላ ዩኒቨርስቲም አዲስ የተቃውሞ አመጽ መቀስቀሱ እየተነገረ ነው!! በሌሎች የትምህርት ተቋማትም ተቃውሞው እየተቀጣጠለ ነው!



No comments:
Post a Comment